Telegram Web Link
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሲአርኤስ እና ከተመድ ኤጀንሲዎች ጋር ተወያየ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ (CRS) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ለተፈናቃይ ማህበረሰቦች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን እንዲያፋጥኑ እና ለዘላቂ መፍትሄዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርቧል።

አስተዳደሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው በሰላም እንዲመለሱ እና የትግራይን የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጧል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ፣ ሲአርኤስ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተጋላጭ ማኅበረሰቦች እና ወደ ሱዳን ለሄዱ ስደተኞች የሚሰጠውን የአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

በተያያዘ ውይይት፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ የተፈናቀሉ ሰዎችን በሰላም ወደ ቀዬአቸው መመለስና የትግራይ ክልል ሉዓላዊነት መጠበቅ ለአስተዳደሩ ቀዳሚ ተግባራት ሆነው እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል።

እንዲሁም የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተቻላቸውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
12👎3
👍21
Sheger Press️️
Photo
‹‹ወታደሩ ኃይል ትግስቱ ተሟጧል›› አምባሳደሩ

የትግራይ ታጣቂዎች ሰሞንኛ አመጽ ተከትሎ በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ ትኩሳት እጅግ ጨምሯል፡፡ መንግስት አስተያየት ለመስጠት በተቆጠበበት በዚህ የሰራዊት አመጽ፤ ብዙ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ የሰጡ አስተያት የሚጠቀስ ነው፡፡

በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደዴፎ፣ በህውሓት ታጣቂዎችና በድርጅቱ አመራር መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ አመጽ መቀስቀሱ ድርጅቱን ሊበትነው ተቃርቧል ብለዋል፡፡ አምባሳደሩ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ የትግራይ ህዝብም ሆነ የድርጅቱ ታጣቂ ኃይል በህወሓት አመራር ላይ "ትዕግሥትና ተስፋው ተሟጧል" ብለዋል። እንደ አቶ ሱሌይማን ገለጻ፣ ለዓመታት የድርጅቱ የጀርባ አጥንት የነበረው የታጠቀው ኃይል አሁን ላይ ለአመራሩ ጀርባውን በመስጠቱ የድርጅቱ "የመጨረሻ ምሽግ እየተደረመሰ" ይገኛል።

"ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ናቸው እያሉ ሲያጭበረብሩ ኖረዋል፤ አሁን ግን ከታጣቂዎቻቸው ጋር እንኳ አንድ መሆን አቅቷቸው እርቃናቸውን ቀርተዋል" ያሉት አቶ ሱሌይማን፣ የተቀሰቀሰው አመጽ ተጨማሪ የህይወት መስዋዕትነት ከማስከተሉ በፊት የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ለፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ መሆን አለባቸው ሲሉ በመግለጫቸው አሳስበዋል።

ትግራይ እንደ ኤርታሌ በሚፋጅ የፖለቲካ ትኩሳት እየተናጠች ትገኛለች፡፡ ከዚህ ትኩሳት ጀርባ በርካታ የውጪ ኃይሎ እጅ መኖር ደግሞ ትኩሳቱን እጅግ ያባባሰ እና የከፋ አድርጎታል፡፡ በተለይም ካለፈው ሰኞ አንስቶ የቲዲኤፍ ጦር ወታደሮች ማመጻቸውን ተከትሎ የክልሉ ፖለቲካ ወዴት እያመራ ነው የሚለው ጥያቄ በጉልህ እንዲነሳ አድርጎታል፡፡ ከዚህ የጦር አመጽ ጀርባ ሶስት አካላት ስማቸው ሲነሳ ነበር፡፡ የፈዴራሉ መንግስት፣ እነ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ሻብያ ናቸው፡፡ ህውሓት ከዚህ አመጽ ጀርባ የፌዴራል መንግስቱ እና ከሃዲ ሲል የጠራቸውን እነጌታቸው ረዳን ተጠያቂ ሲያደርግ፤ ባንፃሩ በሌላ ወገን ያሉት ደግሞ ሻብያን ተጠያቂ ሲያደርጉ ለመመልከት ተችሏል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
26
ፖርቱጋል የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ በፓርላማ ውድቅ አደረገች‼️

የፖርቱጋል ፓርላማ ሙስሲም ሴቶች እንዳይሸፈኑ በሕግ ከለከለች።
አንዲት ሴት ተሳስታ ተሸፋፍና ከተገኘች 4,670 የአሜሪካ ዶላር ትቀጣለች።

ከዚህ በተጫማሪ አንድ ሙስሊም ወንድ ሚስቱ ተሸፋፍና ከተገኘች በሶስት አመት እስራት እንደሚቀጣ በህጉ ላይ ተደንግጓል።

በአውሮፓ ሀገራት ፈረንሣይ፣ ዴንማርክ፣ ቤልጄም፣አውስትራሊያ እና ሌሎች ሀገራት ሙስሊም ሴቶች እንዳይሸፋፈኑ የሚከለክል ተመሳሳይ ህግ ያላቸው ሲሆን ፖርቹጋል ሙስሊም ሴቶች እንዳይሸፋፈኑ በመከልከል 20ኛዋ የአውሮፓ ሀገር ሆናለች።

@sheger_press
@sheger_press
👍3524👎16
ደመወዝ አልተከፈለንም‼️

በአማራ ክልል የፀጥታ ችግር ባለባቸው ምስራቅ ጎጃም ዞን 14 ያህል ወረዳዎች እንዲሁም በሰሜን ወሎ የተወሰኑ ወረዳዎች መምህራን የመስከረም ወር ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ገልፀውልናል።

መምህራኑ የደመወዝ ጥያቄ ሲያቀርቡ ደመወዝ እንዲከፈላችሁ ወደ ስራ ግቡ እንደተባሉና ወደ ስራ ለመግባት ደግሞ ለደህንነታቸው ስጋት እንደገባቸው ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ ይታወቃል።

@sheger_press
@sheger_press
16🤔4😢2
Sheger Press️️
Photo
በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር።
ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት።
ትውልዷ ከእስክንድርያ፣ ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። በአስራ ሁለት ዓመቷ የሰው ሁሉ ጠላት ሰይጣን ሸንግሎ አሳታት፡፡ በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ፡፡ ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና። ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በመርከብ ተሳፈረች።
ባለ መርከቦችም የጉዞ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው፡፡ የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወዳለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም።

ይህን ጊዜ የረከሰ ስራዋን አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ እግዚአብሔር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስዕል አየች። በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጂያቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት።  ወደ ቤተ ክርስቲያን በገባችም ጊዜ የበዓሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኃላ እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ፣ እያለቀሰች ስለነፍሰዋ ተማጸነች፡፡ የለመኗትን የማትነሳ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእልም ወደ ዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ እረፍትንና ድኀነትን ታገኛለሽ የሚል ቃል ወጣ።

ወጥታ ስትሄድም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ዲናር ሰጣትና ሕብስት ገዛችበት፡፡ የዮርዳኖስንም ወንዝ ተሻግራ በበረሀው ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በጸሎትና በስግደት አርባ ሰባት ዓመት ኖረች፡፡ ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር። እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች የገዛችውን ሕብስትም ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለትና ሶስት ቀናት እየጾመች ጥቂት ሕብስት ትቀምስ ነበር፡፡ ባለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች። ከአርባ ሰባት ዓመት በኋላ ቅዱስ አባ ዞሲማ እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ወደዚያች በረሀ መጣ። ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚጽናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው። በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሀት መሰለችው በጸለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት።

ግብጻዊቷ ማርያም ነገር ግን ከእርሱ ሸሸች ከኃላዋ በመሮጥም ተከተላት። እርሷም በስሙ ጠርታ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ አለችው። በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ እርሱ ካህን ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት በላዩዋም ጸለየላት። በብዙ ልመናም ገድሏን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። በቀጣዩ ዓመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው አምጥቶም ጸልዮ አቀበላት። በሁለተኛው ዓመት ወደ ዮርዳኖስ በረሀ ሲመጣ ግብጻዊቷ ቅድስት ማርያም ሙታ አገኛት፣ አንበሳ ጉድጓዷን ቆፍሮለትም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት። ገዳማውያን የዓለምን ከንቱነት ተረድተው ትተዋት ሔደዋል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
27
ፓኪስታን ደበደበች

ሰዓታት የታወጀዉ የፓኪስታንና የታሊባን ጦርነት ከሽፎ፤ ፓኪስታን ምድር አንቀጥቅጥ የአየር ድብደባ ፈፅማለች፡፡

ከቀናት በፊት ሁለቱ ሀገራት የቶክስ አቁም በማወጅ ጦርነቱ ገተዉት የነበረ ቢሆንም፤ ድንገት ፓኪስታን በፈፀመችዉ ጥቃት ስምምነቱ ፈርሷል፡፡ በአፍጋኒስታን ሰማይ ላይ እያጓሩ መብረቅ ያዘነቡት የፓኪስታን የጦር ጄቶች በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች ለሞትና ለጉዳት ተዳርጓል፡፡

ለ2 ቀናቶች ይዘልቃል የተባለዉ የቶክስ አቁምን ድንገት በፍንዳታ የሰበረዉ የፓኪስታን አየር ሀይል አርብ እለት በፈፀመዉ ጥቃት 10 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በደርዘን የሚቆጠሩት ደግሞ ለጉዳት መዳረጋቸዉን የአፍጋኒስታን መንግስት ገልፀዋል፡፡

“ፓኪስታን የተኩስ አቁም ስምምነቱን አፍርሳ በፓኪቲካ ሶስት ቦታዎች ላይ በቦንብ ደበደበች” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የታሊባን ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
17👍2👏1
ጦሩ ወደ አሰብ እርምጃ ጀመረ‼️

ወደ አሰብ ከፍተኛ የሆነ ሃይል ተንቀሳቅሷል። ሻብያን ለመገርሰስ በትጥቅ የሚንቀሳቀሰው የቀይ ባህር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ጦሩን ወደ አሰብ አቅጣጫ ማንቀሳቀሱን አሳውቋል። የኢርትራ መንግስት በዚሁ አቅጣጫ አለ ብሎ ካሰበው የኢትዮጵያ ስጋት ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ የሃይል ክምችት እንዳደረገ ቀደም ብለው ሲወጡ የነበሩ ዘገባወች አመላክተዋል።

ይኸው ታጣቂ በዚሁ አቅጣጫ ከኢርትራ መንግስት ጋር ለአመታት ሲፋለም የቆየ ሲሆን በቀደመው የኢሕአዴግ መንግስት ወቅትም ጠንከር ያሉ ወታደራዊ ድጋፎችን ያገኝ ነበር። የቀይ ባህር ዳርቻን ተተርሶ የሚኖረው የአፋር ህዝብ በኢሳያስ አገዛዝ ከፍተኛ ጭቆና እየደረሰበት ነው በሚል ነፍጥ አንግቦ የተነሳው ቡድኑ፤ በአሁኑ ሰአትም ጦሩን ዳንኪላ ወደተባለ የኢርትራ አፋር ግዛት ፍሊሚያ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በኤክስ ገጹ ባሰራቸው ተንቀሳቃሽ ምስል አመልክቷል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ታጣቂ ቡድኑ በሚገባ የተደራጀ ትጥቅ ያለው መሆኑን ያሳያል ።

@sheger_press
@sheger_press
👍3220👎10🤯9
የመቁረጫ ነጥብ‼️

የ2018 ዓ.ም የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል‼️

የኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው መስፈርቱን የሚያሟሉ በሙሉ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በመሄድ መሰልጠን እንደሚችሉ አሳወቀ፡፡

በዚህም መስፈርቶችን የሚያሟሉ በመረጡት ሙያ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በመሄድ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን አሳውቋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ መግቢያ ነጥብ ለደረጃ 5 ወንዶች 179 እና ከዚያ በላይ፤ ለሴቶች 168 እና ከዚያ በላይ፤ ለደረጃ 3 እና 4  ወንዶች 135 እና ከዚያ በላይ፤ ለሴቶች 122 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ለደረጃ 1 እና 2   ወንዶች 134 እና ከዚያ በታች፤ ሴቶች 121 እና ከዚያ በላይ መሆን እንደምጠበቅበት አሳውቋል፡፡
7👍2
2👍1
Sheger Press️️
Photo
በሰማይ ቤተ መንግሥት ሠርቼልሃለሁ

በትንሣኤ ሙታን ከማያምኑት ከሰዱቃውያን ወገን ስለነበር ጌታችን ከሙታን በተነሳ ጊዜ እጆቹን ካልዳሰስኩ በጦር የተወጋ ጎኑን ካላየሁ ብሎ ዳሶ ካረጋገጠ በኋላ ያመነ ደቀመዝሙር ነው፡፡ በኋላ ግን እስከ ሞት ድረስ የታመነ ሆኗል ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ፡፡ የስሙ ትርጓሜ ጸሐይ ማለት ነው፡፡

በሀገረ ስብከቱ በህንድ ታከሻሊላ በተባለ ከተማ በኢየሩሳሌም ስለ ነበረው የንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት ዝና እየሰማ ማሰራት የሚፈልግ ጎንዶፓረስ የተባለ ንጉሥ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ነጋዴዎች በየሀገሩ ሲጓዙ የታወቀ ግንበኛ እንዲያመጡለት አዘዛቸው፡፡ አንዱ ነጋዴ ወደ ፋርስ ሲጓዝ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን አገኘው፡፡ ቶማስ ከኢየሩሳሌም እንደመጣ ሲሰማ የግንበኝነት ሙያ ይችል እንደሆነ ጠየቀው፤ እርሱም ወደ ህንድ ሄዶ ማስተማር ይፈልግ ስለነበር አጋጣሚውን በመጠቀም “በኢየሩሳሌም ሳለሁ ህንፃ በመገንባት እኖር ነበር፡፡” አለው፡፡

ነጋዴውም በጣም ተደስቶ ቶማስን ወደ ህንድ ወሰደው፡፡ ንጉሡም ከከተማው አጠገብ ወደሚገኘው ጫካ ወሰደውና ቤተ መንግሥቱ በዚያ ቦታ ላይ እንዲሠራ ነገረው፡፡ ቅዱስ ቶማስ የቤተ መንግሥቱን አሠራር ሲነግረው ንጉሡ ተሠርቶ እስከሚያየው ቸኮለ፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ንጉሡ ለህንጻው መሥሪያ ብዙ ገንዘብ ለቅዱስ ቶማስ ይልክለት ጀመር፡፡ እርሱ ግን ወደ ድሆች መንደር እየሔደ ለተራቡት ምግብ፣ ለታረዙት ልብስ፣ መጠለያ ለሌላቸው ቤት እየገዛ፣ ሕሙማንን እየፈወሰ ወንጌል እየስተማረ ይኖር ጀመረ፡፡ ንጉሥ ጎንዶፓረስ ለሕንፃው መሥሪያ የመደበው ጊዜ እንዳለቀ፣ ቤተ መንግሥቱን ሊጎበኝ መጣ፡፡ ወደ ቦታው ደርሶ ቢመለከት እንኳን ሕንፃው ሊሠራ ጫካው አልተነካም፡፡ ንጉሡም በዚያ የሚያልፍ መንገደኛ ጠርቶ ቶማስ የታለ? ሲል ጠየቀው፡፡ “ቶማስ በድሆች መንደር የተቸገሩትን እየረዳና እያስተማረ ይገኛል፡፡” ሲል መለሰለት፡፡

“እርሱስ ጥሩ ግን የሰራልኝ ቤተ መንግሥት የታለ?” ሲል ጠየቀው፡፡ መንገደኛውም “በድንጋይ የተሠራ ቤተ መንግሥት ላያዩ ይችላሉ፤ ጌታዬ፤ ነገር ግን ሕዝብዎ በጣም እንደተደሰተ መመልከት ይችላሉ፡፡” አለው፡፡ ንጉሡ ያ ሁሉ ገንዘብ እንደባከነበት መጠራጠር ጀመረ፤ ወታደሮቹን ልኮም ቶማስን አስመጣውና “ቤተ መንግሥቴን ለምን አልሠራህልኝም ጫካው እንኳን መቼ ተነሣ?” አለው፡፡ ቶማስም “በእርግጥ በምድር ላይ ቤተ መንግሥት ላያዩ ይችላሉ፡፡ እኔ ግን በሰማይ ቤተ መንግሥት ሠርቼሎታለሁ፡፡” አለው፡፡

ንጉሡ እጅግ ተቆጣ፤ እጅ እግሩን አስረው እንዲያሰቃዩትም አዘዘ፡፡ በዚያች ሌሊት በክርስቶስ ያመነው የንጉሡ ወንድም ልዑል ጋድ በድንገት ታሞ ሞተ፡፡ ነፍሱም በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማያት ወጣች፡፡ ከመላእክቱ አንዱ ብዙ ቤተ መንግሥታትን እያሳያት “እንድትኖሪበት ደስ ያለሽን ምረጪ፡፡” አላት፡፡

ከቤተ መንግሥታቱ ሁሉ የሚያምረውን ስትመርጥም “ይህ ቤተ መንግሥት ቶማስ ለንጉሥ ጎንዶፓረስ የሠራለት ሰማያዊ ቤተ መንግሥት ነው፡፡” አላት፡፡ ጋድ ሊቀብሩት በተሰበሰቡት ሰዎች መካከል ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ተነሣ፡፡ ያየውን ሁሉ ለንጉሡና ለተሰበሰቡት ሰዎች ነገራቸው፡፡ ንጉሡ በቶማስ ላይ በሠራው ሁሉ አዘነ፣ ያሰበው ቤተ መንግሥት መሠራቱን ሲሰማ ሐዋርያውን ከእስር ቤት አስመጣው፡፡ ከነቤተሰቡም በክርስቶስ አምላክነት አምኖ ተጠመቀ፡፡

ለቶማስም ያለውን ገንዘብ ሁሉ “ሌላም ቤተ መንግሥት ሥራልኝ” እያለ ይሰጠው ጀመር፡፡ የሀገሩ ሰዎችም እንደርሱ ያደርጉ ጀመር፡፡ ጥቅምት 9 ዓለመታዊ በዓሉ ነው፡፡ ገዳማውያኑም ስለ ሰላመያዊ ቤታችን እያሰቡ ስለኛ ይጸልያሉ፤ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
17
የማር ጥቅሞች

1. ንጹህ ማር በቫይታሚን እና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ሲሆን እነዚህ ቫይታሚኖች እና ንጥረ ነገሮችም ሰውነታችንን ከባክቴሪያዎች ይከላከላሉ፡፡

• ማር የሰውነታችንን የበሽታ መከላከል አቅም ይጨምራል፡፡
• ጉንፋን ሲይዘን እና የሚያስለን ከሆነ አንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ ማር በትኩስ ውሃ ውስጥ መበጨመር አንዲሁም የተወሰነ ሎሚ እና ቀረፋ በማድረግ መጠቀም ይቻላል፡፡

2. ማርን በትኩስ ውሀ ውስጥ ከሎሚ ጋር በመጨመር ጠዋት ምግብ ከመውሰዳችን በፊት ከወሰድን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ ቆሻሻን እና ቅባትን ያስወግዳል፤ የሰውነት ክብደትንም እንድንቀንስ ይረዳል፡፡

3. ማርን ከቀረፋ ጋር በመደባለቅ የምንወስድ ከሆነ የሰውነታችንን የኮሌስትሮል መጠን በ10 በመቶ መቀነስ እንችላለን

• አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ቀረፋ ጋር በትኩስ ውሃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡

4. በሀይል ሰጪነቱ ከፍተኛ ጥቅም ያለው ማር ከቡና ባልተናነሰ ሰውነታችን ያነቃቃል፡፡

5. ማር ለቆዳችን ልስላሴ እና ጥራት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

• በተጎዳው ቆዳ ላይ በመቀባት አንድ ሌሊት ማሳደር እና ጠዋት ጠዋት በንጹህ ውሃ መታጠብ ፡፡ ይህንን በተደጋጋሚ የምናደርግ ከሆነ ለስላሳ እና ንጹህ ቆዳ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡

6. የምግብ አለመፈጨትን ይቀንሳል ፡፡

አንድ ወይም ሁለት የሾርባ ማንኪያ ማር ከበድ ያሉ ምግቦችን ከመመገባችን በፊት ብንወስድ አሊያም ምግብ ተመግበን የመክበድ ስሜት ከተሰማን በኋላ መውሰድ የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡፡via.zena.since
20👍5🤬1
Sheger Press️️
Video
ቃላተ ወንጌሉን የመኖር አንዱ መንገድ 

“በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣ በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣ በራብ ደርቀው ያልቃሉ።” ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ፣ በሰቆቃወ ኤርምያስ 4÷9፡፡ በገዳማዊው ሕይወት በበረሃው ሀሩር ስለ ጽድቅ የሚራቡ እናቶችና አባቶች የዕለት ጉርሳቸውን ሲያጡ ማየት ደግሞ ልብ ይሰብራል፡፡

ረሀብ ገዝግዞ የሚገድል በጣርና በጋር ሕይወትን የሚነጥቅ ኃያል ጠላት ነው፤ ሰይፍ ግን አንድ ጊዜ ይገላግላልና ታላቁ ነቢይ ይህን ብሏል፡፡ በረሀብ ላይ ውሃ ጥም ሲጨመር ደግሞ ሰውነት መቋቋም ይሳነዋል፡፡ ከስድስቱ ቃላተ ወንጌልም ሁለቱ “ብራብ አብልታችሁኛል፣ ብጠማ አጠጥታችሁኛል፣” የሚሉ ናቸው፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምሥራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያን በረሃብና በውሃ ጥም ውስጥ ታላቅ መንፈሳዊና ተጋድሎ እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህን ለሀገር ሰላምና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽናት የሚጸልዩ ገዳማውያን መደገፍ ቃላተ ወንጌሉን የመኖር አንዱ መንገድ ነው፡፡

ጋን በጠጠር እንዲደገፍ እንዲሁ ደግሞ በመጪው ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም በሚሊኒም አዳራሽ ከ 5፡00 ጀምሮ በተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ የተዘጋጀውን ትኬት በአንድ መቶ ብር ብቻ በመግዛት ወዳጅ ዘመዶቻችንም በመጋበዝ የድርሻችንን እናበርክት የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፡፡ በዕለቱ የሚቀርቡ የእደ ጥበብ ሥራዎቻችንም እየገዛን አብሮነታችንን እናሳያቸው፡፡ 


አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444
እንቅልፍ የለኝም - ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት ሊሞላኝ ነው፤ ለሊት እንቅልፍ የለኝም ፥ ለ 2 ሠዓታት ብተኛ ነው ቀሪውን አለቅስበታለሁ። ለምንደነው ብዙ ለማንቆይበት የምንጋደለው!? ለምንስ ነው የምንጫረሰው!? በጣም ያሳስበኛል ያስለቅሰኛል!"
ሰውነት ይቀድማል!

‹‹ሰው ሁኑ! ቅድሚያ ሰውነት ይቀድማል!
ከሐይማኖት ሰውነት ይቀድማል! ከዘርም ሰውነት ይቅደም!
አላህ ሰውን ከሁሉ በላይ አልቆታል::

ሰው ሊገፋ፣ ሊሰደድ፣ ሊገደል፣ ሊናቅ፣ ሊወገዝ በፍፁም አይገባም:: ልዩ ፍጥረቴን ክብሩን ጠብቁት በማለት አዟል››
የክብር ዶክተር፣ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ።

@sheger_press
@sheger_press
8👍1
2025/10/19 15:09:59
Back to Top
HTML Embed Code: