Telegram Web Link
"እርቦናል ጠምቶናል ደመወዝ ይከፈለን " የገዋኔ ከተማ ሠራተኞች‼️

በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ ደመወዝ ያልተከፈላቸው ሰራተኞች ዛሬ መንገድ በመዝጋት ድምፅ አሰምተዋል።
እንጨት ሰብስበው ከአሮጌ ጎማ ጋር ሲያቃጥሉ ታይተዋል።

መንገድ ከመዝጋት ውጭ በተሽከርካሪም በተሳፋሪም ላይ ምንም ችግር አላደረሱም፣ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ አቅርበዋል።

ጥያቂያቸው የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ያልተከለን ደመወዝ ይከፈለን የሚል ነው።
የመንግስት ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው የያዙት መፈክር ይህንኑ ያሳያል።

ሰራተኞቹ ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ አሁን ላይ መንገዱን ከፍተውታል።

ከደመወዝ አለመከፈል በተጨማሪ የውሃ ችግር እና የመልካም አስተዳደር ችግር በመኖሩ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

@sheger_press
@sheger_press
9👍8😢5🙏3🤔1
በታቦተ ህጉ ላይ የተሳለቁ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በደቡብ ምዕራብ ክልል በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስተዳደር መስከረም መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተከሳሽ አብረሃም ክፍል በሚል መጠሪያ በተከፈተ የቲክቶክ አካውንት በኦርቶዶክስ እምነትና በታቦተ ህጉ ላይ በመሳለቅ ቪዲዮ በመስራት ያጋሩ 5 ተከሳሾች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ነበር።

ጉዳዩን የተመለከተው የዋቻ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአምስቱ ተከሳሾች እያንዳንዳቸዉ ላይ በአንድ ዓመት ፅኑ እስራትእንዲቀጡ ወስኖባቸዋል

የካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን

@sheger_press
@sheger_press
42👍10👏7
Sheger Press️️
Video
የቅድስት ድንግል ማርያም ስደት እየታሰበ ከቅዳሜ ምሽት አራት ሰዓት ጀምሮ ካህናት አባቶች በማሕሌተ ጽጌው እመቤታችን ትመሰገናለች፡፡

የዓለሙን ሁሉ ፈጣሪ ይዛ በበረሃው የደረሰባት መከራ የገጠማት ውሃ ጥምና ረሃብ ይዘከራል፡፡

ልጇን ይዛ የተሰደደችው ንግስተ ሰማያት ወምድር የደረሰባትን መከራ አብነት ሆኗቸው ነፍሳቸውን ለማዳን ስጋቸውን ለክርስቶስ ፍቅር በማስገዛት በረሃብና በውሃ ጥም የሚቸገሩትን ገዳማውያን ለማሰብ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ከቶ ከየት ይመጣል?

በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምሥራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያን ሥጋዊና መንፈሳዊ ውጊያ በበረታበት አካባቢ በብዙ መከራ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

ይህን መከራቸውን ለማስታገስ፣ ውሃ ጥማቸውን ለመቁረጥ፣ ረሃባቸውንም ለማስታገስ የእመቤታችን መከራ በሚታሰብበት ዘመነ ጽጌ ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ከ 5፡00 ጀምሮ  በሚሊኒየም አዳራሽ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል፡፡ በአንድ መቶ ብር ብቻ ትኬቱን በመግዛት የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፡፡
አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444
27
በመዲናዋ እስከ ባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ድረስ ያሉ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ እየተካሄደ መሆኑን ቢሮው አስታወቀ!

በአዲስ አበባ ከተማ ከጥቃቅን የንግድ ዘርፎች እስከ ባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ድረስ ያሉ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ከጥቅምት 1 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ቆጠራው የከተማዋን እና የሀገሪቱን ጥቅል ኢኮኖሚ ዕድገት ከዓለም ኢኮኖሚ ጋር በማነፃፀር ደረጃውን ከማወቅ ባሻገር የግል አልሚዎች የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመጠቆም ያግዛል ብለዋል፡፡

አቶ አደም ቆጠራው የአገልግሎት፣ "የኢንዱስትሪና የከተማ ግብርና የኢኮኖሚ ዘርፎች ለአጠቃላይ የሀገር ምጣኔ ሀብት ያላቸዉን አበርክትዎ (GDP) ለማወቅና የዘርፎች የተናጠል ድርሻን ወቅታዊ ለማድረግ የሚረዳ ስታቲስቲካላዊ መረጃ ለማግኘት፤ ብሎም በቀጣይነት ለሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ጥናቶችና ለፖሊሲዎች ግብዓት የሚሆን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ነው" ብለዋል።

በተጨማሪም በከተማዋ የሚገኙ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ብዛት፣ በድርጅቶቹ ያሉ ሠራተኞች ቁጥር የካፒታል መጠን እና የሚመረቱ ምርቶችን ማወቅ ከቆጠራው ይገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ውጤት እንደሆነም ተገልጿል።
9🤔2
በግፍ ያጣናው የባህር በር የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር መመለሱ አይቀርም" ኮሞዶር ተገኝ ለታ፤የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ

“በግፍ ያጣናው የባህር በር የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር መመለሱ አይቀርም” ሲሉ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ኮሞዶር ተገኝ ለታ አስታወቁ።የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ሰላምና መረጋጋት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ምክትል ባሕር ኃይል አዛዡ ገልጸዋል።

ምክትል አዛዡ ይህን የተናገሩት ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣በመከላከያ ዋር ኮሌጅና በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ትብብር“የሁለቱ የውሃ ሥርዓቶችና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ነፃነት፣ የዓባይና የቀይ ባሕር ትስስር እና የአፋር ክልልን ስትራቴጂካዊ ሚና መዳሰስ” በሚል ዐቢይ ርዕስ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
“የወደብ ጉዳይ መንግስታዊ አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል”ያሉት የባህር ኃይል ምክትል አዛዡ፤በቀይ ባሕር ቀጣና እየታዩ ናቸው ያሏቸው ጂኦ ፖለቲካዊ ለውጦች ኢትዮጵያ ከቅርብ ባሉት ነገር ግን በውል ካልጠቀሱት ጊዜ ወዲህ በቀይ ባህር ላይ ያላት ጥያቄ ቀዳማዊ ብሔራዊ አጀንዳ ለማድረጓ ገፊ ምክንያት መሆናቸውን ጠቁመዋል። በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ያለው የሎጂስቲክስ ፍላጎት ለጥያቄው መነሳት አንደኛው ምክንያት መሆኑንም አመላክተዋል።

እንደምክትል አዛዡ ገለጻ፤የባሕር በር ያስፈለገበትን ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ከትናንሽ እስከ ትላልቅ ያሏቸው ነገር ግን በስም ያልጠቀሷቸው ሀገራት በቀጣናው የጦር ሰፈር መገንባታቸው ነው።
“በመሆኑም የጦር ሰፈሮች በቀጣናው መኖራቸው ይዟቸው የሚመጡ ችግሮችን ቀድሞ በመተንበይ፣በመዘጋጀት፣ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል”ብለዋል።
አዲስ ማለዳ
25👎20🤔3🔥1🥰1
ለመዝረፍ ነበር የመጣሁት
አቶ ጌታቸው ረዳ ‼️

ጠ/ሚ አብይ አህመድን ፈገግ ያስባለው የአቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር

ባሌ የመጨረሻ የመጣሁት ከ 13 ዓመት በፊት ነበር ባሌ መልከዓምድር ነው ለእኛ እንጂ ሌላ ነገር የለውም ያኔ መንገድ ለመመረቅ ነበር የመጣሁት በስንት ዘመን የተሰራች ብቸኛ አንድ መንገድ ነበረች በሄሊኮፕተር ነበር የሄድኩት በጣም ሃብታም ምድር መሆኑ ምንም የሚያጠራጥር አልነበረውም ይሄንን ሃብት ለመጠቀም እንኳን መንገድ እንዴት ቀደም ብለው መስራት አልታየቸውም ነበር ብየ እጠይቅ ነበር ያኔ እንኳን ያልኩት ለመዝረፍ ነበር ፡

@sheger_press
@sheger_press
16👎15🤔6🥰1👏1🤯1
🙏51
Sheger Press️️
Photo
የቅዱስ ያሬድ ረድኤት እና ምልጃ አይለየን🙏

አንዲት ትል ዛፉ ላይ ለመውጣት ስድስት ጊዜ ስትወጣና ስትወርድ ከቆየች በኃላ በሰባተኛው ዛፉ ላይ ወጥታ የዛፉን ፍሬ ስትበላ ተመልክቶ በወሰደው ትምህርት ትሏ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ ያሰበችውን ስታሳካ ራሱን በመውቀስ ወደ መምህሩ ተመልሶና ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን እንደቀጠለ በሚነገረው አስደናቂ ታሪኩ በርካቶች ያውቁታል፡፡

ሚያዝያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ አባቱ አብዩድ ወይም ይሥሐቅ እናቱ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ይባላሉ። በተወለደ በ7 ዓመቱ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ገበዝ የነበረው አጎቱ ጌዴዎን እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለሰባት ዓመት ተምሮ ፈቀቅ ባለማለቱ አንድ ቀን አጎቱ ተቆጥቶ ገርፈው፡፡ መታገስ ተስኖት ማይኪራህ ወደምትባል የቀዳማዊ ምኒልክ መቃብር ቦታ ሄዶ ተደበቀ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በዛፍ ስር አርፎ እያለ የያችን ትል ትግል ተመለከተ፡፡

ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን አዘውትሮ በመሔድም ጥበብና እውቀትን የሚገልጽ እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በጣም በአጭር ጊዜም 150 መዝሙረ ዳዊት፣ መኃልየ ነቢያት፣ መኃልየ ሰሎሞን ሌሎችንና ትርጓሜ መጻሕፍት ብሉያትና ሐዲሳትን አወቀ፡፡ ዜማ ባልነበረበት በዚያ ዘመን በስልት እያነበቡ ያመሰግኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ኅዳር 5 ቀን 527 ዓ.ም በኤዶም ገነት በሥላሴ አምሳል ሦስት አእዋፍን ወደ እርሱ ላከ፤ እነሱም በግዕዝ፣ ዕዝልና በአራራይ ዜማ ማዜምን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቅዱስ ያሬድ ዜማ ገልጹለት፡፡ ድምጹን ከፍ አድርጎም “ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን….” ብሎ በልሳነ ግዕዝ አዜመ፡፡ ሃሌ ሉያ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድም ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው” ማለት ነው፡፡

በ534 ዓ.ም ኅዳር 6 ቀን ወደ ሰማይ ተነጠቀ፤ በሰማይ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን ልዩ በሆነ ጣዕመ ዝማሬ ሲያመሰግኑ ሰማ፡፡ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ አክሱም ጽዮን ውስጥ ወደ ምሥራቅ በኩል በመዞር ከሰማይ የሰማውን ዝማሬ ዘመረ፤ አርያም ብሎም ሰየመው፡፡ በዚሁም በ538 ዓ.ም ቅዱስ ያሬድ ማኅሌት ጀመረ፡፡ አሁን ድረስ የሚያገለግሉ ድጓ፣ ጾመድጓ፣ ዝማሬ፣ መዋሥዕትና ምዕራፍ የሚባሉ አምስት የዜማ መጻሕፍትም ደርሷል፡፡ ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት ቦታ “ሙራደ ቃል” ይባላል፡፡ ይህችንም ዜማ “አርያም” አላት፡፡ ይህም ማለት ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘች ማለት ነው፡፡

ይህን ዜማ ከፍ አድርጎ ሲያዜም ሰው፣ እንስሳትና አዕዋፍ ሁሉ እርሱ ወዳለበት ቦታ ተሰብስበው ልዩውን ሰማያዊን ዜማ ይሰማሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ የግእዝ ብሎም የኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ መሥራችም ነው፡፡ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በድርሰት ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ብሉያትን ከሐዲሳት፣ ከሊቃዉንት እያጣቀሰ መንፈሳዊ ዜማዎችን ደርሷል፡፡ በመጨረሻ በተወለደ በ75 ዓመቱ በገዳማዊ ሕይወት በኖረበት በሰሜን ተራሮች ደብረ ሐዊ ገዳም ግንቦት 11 ቀን ተሠውሯል፡፡

ገዳማውያን እንኳን ዓለማዊ ደስታ ሊመኙ መንፈሳዊ ክብራቸውም በሰው ፊት እንዲገለጽ አይሹም፡፡ ለኛ ለደካሞቹ ግን ሁሌም ይጸልዩናል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡  


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
19🙏6
በድሬዳዋ ደወሌ ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

ከደወሌ መነሻውን አድርጎ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡር ትላንት ሌሊት 8:00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ ላይ በደረሰበት አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ከሽኒሌ ወረዳ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሽኒሌ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ ሲሆን፤ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
😢1710😱2
“በሕይወት ዘመኔ እንደ ባሌ ያለ ምድር፣ ሁሉም ነገር በአንድ ስፍራ ያለው ኢትዮጵያም ውስጥ፣ አፍሪካም ውስጥ፣ የትም ዓለም አይቼ አላውቅም።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

@sheger_press
@sheger_press
👎44👍1713👏2🤔2
በዕለተ አርብ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ምንም እንኳን ጌታችን የእሾህ አክሊል ደፍቶ እርቃኑን ተሰቅሎ ደሙ እየፈሰሰ ቢያየውም ንጹህ መሆኑን በመረዳት ጌታው መሆኑን ከማወቅ አላገዳውምና “አቤቱ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ ዐስበኝ” አለው።

ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ።” ሉቃስ 23÷39-43

ከአዳም ቀድሞ ገነት የመግባትን እድል ያገኘው ራሱን አሳልፎ የሰጠውን ጌታውን በመከራው ሰዓት አይቶት ጌትነቱን በመረዳቱ ነው፡፡

ገዳማውያን ራሳቸውን ለክርስቶስ ፍቅር አሳልፈው ሰጥተው ስናያቸው መንፈሳዊ ክብራቸው ይታየናል? መራብ መጠማታቸው ለነፍሳቸው በማደራቸው መሆኑን እንረዳለን? በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምሥራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያንም በበረሃው ግለት ውስጥ ዓለምን ንቀው በረሃብና በውሃ ጥም ከትመዋል፡፡

ፊያታዊ ዘየማን ጌታው በመከራ መስቀል ላይ ቢሆንም ክብሩን እንዳየ፣ ገዳማውያኑ በስጋዊ ችግር ውስጥ ቢሆኑም መንፈሳዊ ክብራቸውን በመመልከት ችግራቸውን ለመቅረፍ እንረባረብ፤ ከጸሎታቸው ረድኤት እናትርፍ፡፡

ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም  ከ 5፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ በመሳተፍ፣ በአንድ መቶ ብር ብቻ በገዛነው ትኬት ከጎናቸው እንቁም፡፡ የእደ ጥበብ ምርቶቻቸውንም በመግዛት ከሊቀ መልአኩ በረከት እንካፈል፡፡


አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444
17
ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች "መገንጠልም፣ መጠቅለልም" አይሠራም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

"ከሰሜን እስከ ደቡብ" ባለው የአገሪቱ ክፍሎች "ልገንጠል" በሚል የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳሉ የገለጹት ዐቢይ፤ "አንዱም አገሩን አያውቅም" ሲሉ ተችተዋል።

ይህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ንግግር የተሰማው በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ባደረጉት የሦስት ቀናት ጉብኝት ወቅት በተካሄደ "ውይይት" ላይ ነው።
ሰኞ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም. በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የተላለፈው ይህ "ውይይት"፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ባሌ ዞን የተጓዙ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የቀድሞ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ነው።

ሁለት ሰዓት ገደማ የሚጠጋው ይህ ውይይት በአብዛኛው ያተኮረው በባሌ ዞን የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን ማልማት እና መጠቀምን በተመለከተ ነው። መጨረሻ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም እንደ ሌሎቹ ተሳታፊዎች ሁሉ በአካባቢው ያለው ሀብት በሚገባው ልክ ባለመልማቱ የተሰማቸውን ቁጭት ገልጸዋል።

ዐቢይ በንግግራቸው "ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም የለም፣ ሰላም መቅደም አለበት" የሚል ቅሬታ በተለያየ መንገድ እንደሚነሳ ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት መንግሥት አቋም፤ "ሰላም እንዲመጣ እንለምናለን፣ ሰላም እንዲመጣ እንሠራለን። ሰላም እስከሚመጣ ግን አንቀመጥም፤
እናለማለን" የሚል እንደሆነ ገልጸዋል።
19👎7🤔1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ቭላድሚር ፑቲን ዳግም ሊገናኙ ነው?

የሩሲያው የዜና ጣብያ ታስ፣ በሚቀጥለው ቅዳሜ ኢትዮጵያ እና ራሽያ በመሪዎች ደረጃ እንደሚገናኙ ዘግቧል። የሁለቱ አገራት መሪዎች የሚገናኙት በሞስኮ ይሁን በአዲስአበባ ዘገባው አልጠቀስም። በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ ሞስኮ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ እና ራሽያ ግንኙነታቸውን ይበልጥ እያሳደጉ ነው!
26
🔥⚽️Evening of Epic Battles

Champions League returns with a fiery clash at Santiago Bernabéu, where Real is ready to decisively take down a Juventus that has lost their form. Meanwhile, in Munich, Bayern will once again turn Allianz Arena into a fortress against Club Brugge.

Feel the excitement and win with Melbet!
⬇️
Promo - PRESSSH
Link - https://bit.ly/423Tlea
3
በዎላይታ ሶዶ የቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት ሰርቆ የተገኘ ግለሰብ የ5 ዓመት እስራት ተፈረደበት!

በዎላይታ ሶዶ ከተማ፣ ድል በጌሬራ ቀበሌ ውስጥ፣ በቤተክርስቲያን ንብረት ላይ ስርቆት የፈጸመ ግለሰብ ላይ የ5 ዓመት እስራት ቅጣት ተወሰነ።

የቀበሌው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብረሐም ባሳ እንደገለጹት፣ ግለሰቡ አቶ ስጦታው ጎችሎ ሲባል ነዋሪነቱ ሀባ ጌሬራ ቀበሌ መሆኑ ታውቋል።

የስርቆት ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ?
* ቀን: 8/2/2018 ዓ.ም
* ቦታ: ድል በጌሬራ ቀበሌ ቀጠና 3፣ ከአንድ ቤተክርስቲያን
* የተሰረቁ ንብረቶች: የሙዚቃ መሳሪያ እና አምፕሊፋየር ሲሆን

ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ያዋለው የፖሊስ መምሪያው ጉዳዩን ለፍትህ አካል ማቅረቡን ተከትሎ፣ የሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥፋተኛነት ውሳኔ አስተላልፏል።

የሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
የ5 (አምስት) ዓመት ጽኑ እስራት

የቀበሌው ታክቲክ ምርመራ ሃላፊ ዋ/ሳጂን ተመስገን ተገኝ፣ ፖሊስ ከፍትህ ተቋማት ጋር በመተባበር ወንጀለኞች በፍጥነት ፍርድ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጭ: የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
11👍2
2025/10/22 03:18:27
Back to Top
HTML Embed Code: