Sheger Press️️
Photo
የቅዱስ ያሬድ ረድኤት እና ምልጃ አይለየን🙏
አንዲት ትል ዛፉ ላይ ለመውጣት ስድስት ጊዜ ስትወጣና ስትወርድ ከቆየች በኃላ በሰባተኛው ዛፉ ላይ ወጥታ የዛፉን ፍሬ ስትበላ ተመልክቶ በወሰደው ትምህርት ትሏ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ ያሰበችውን ስታሳካ ራሱን በመውቀስ ወደ መምህሩ ተመልሶና ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን እንደቀጠለ በሚነገረው አስደናቂ ታሪኩ በርካቶች ያውቁታል፡፡
ሚያዝያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ አባቱ አብዩድ ወይም ይሥሐቅ እናቱ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ይባላሉ። በተወለደ በ7 ዓመቱ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ገበዝ የነበረው አጎቱ ጌዴዎን እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለሰባት ዓመት ተምሮ ፈቀቅ ባለማለቱ አንድ ቀን አጎቱ ተቆጥቶ ገርፈው፡፡ መታገስ ተስኖት ማይኪራህ ወደምትባል የቀዳማዊ ምኒልክ መቃብር ቦታ ሄዶ ተደበቀ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በዛፍ ስር አርፎ እያለ የያችን ትል ትግል ተመለከተ፡፡
ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን አዘውትሮ በመሔድም ጥበብና እውቀትን የሚገልጽ እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በጣም በአጭር ጊዜም 150 መዝሙረ ዳዊት፣ መኃልየ ነቢያት፣ መኃልየ ሰሎሞን ሌሎችንና ትርጓሜ መጻሕፍት ብሉያትና ሐዲሳትን አወቀ፡፡ ዜማ ባልነበረበት በዚያ ዘመን በስልት እያነበቡ ያመሰግኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ኅዳር 5 ቀን 527 ዓ.ም በኤዶም ገነት በሥላሴ አምሳል ሦስት አእዋፍን ወደ እርሱ ላከ፤ እነሱም በግዕዝ፣ ዕዝልና በአራራይ ዜማ ማዜምን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቅዱስ ያሬድ ዜማ ገልጹለት፡፡ ድምጹን ከፍ አድርጎም “ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን….” ብሎ በልሳነ ግዕዝ አዜመ፡፡ ሃሌ ሉያ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድም ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፤ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው” ማለት ነው፡፡
በ534 ዓ.ም ኅዳር 6 ቀን ወደ ሰማይ ተነጠቀ፤ በሰማይ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን ልዩ በሆነ ጣዕመ ዝማሬ ሲያመሰግኑ ሰማ፡፡ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ አክሱም ጽዮን ውስጥ ወደ ምሥራቅ በኩል በመዞር ከሰማይ የሰማውን ዝማሬ ዘመረ፤ አርያም ብሎም ሰየመው፡፡ በዚሁም በ538 ዓ.ም ቅዱስ ያሬድ ማኅሌት ጀመረ፡፡ አሁን ድረስ የሚያገለግሉ ድጓ፣ ጾመድጓ፣ ዝማሬ፣ መዋሥዕትና ምዕራፍ የሚባሉ አምስት የዜማ መጻሕፍትም ደርሷል፡፡ ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት ቦታ “ሙራደ ቃል” ይባላል፡፡ ይህችንም ዜማ “አርያም” አላት፡፡ ይህም ማለት ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘች ማለት ነው፡፡
ይህን ዜማ ከፍ አድርጎ ሲያዜም ሰው፣ እንስሳትና አዕዋፍ ሁሉ እርሱ ወዳለበት ቦታ ተሰብስበው ልዩውን ሰማያዊን ዜማ ይሰማሉ፡፡ ቅዱስ ያሬድ የግእዝ ብሎም የኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ መሥራችም ነው፡፡ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸዉን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በድርሰት ሥራዎቹ እንደ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ብሉያትን ከሐዲሳት፣ ከሊቃዉንት እያጣቀሰ መንፈሳዊ ዜማዎችን ደርሷል፡፡ በመጨረሻ በተወለደ በ75 ዓመቱ በገዳማዊ ሕይወት በኖረበት በሰሜን ተራሮች ደብረ ሐዊ ገዳም ግንቦት 11 ቀን ተሠውሯል፡፡
ገዳማውያን እንኳን ዓለማዊ ደስታ ሊመኙ መንፈሳዊ ክብራቸውም በሰው ፊት እንዲገለጽ አይሹም፡፡ ለኛ ለደካሞቹ ግን ሁሌም ይጸልዩናል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

❤21🙏7
በድሬዳዋ ደወሌ ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
ከደወሌ መነሻውን አድርጎ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡር ትላንት ሌሊት 8:00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ ላይ በደረሰበት አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ከሽኒሌ ወረዳ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሽኒሌ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ ሲሆን፤ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
@sheger_press

😢18❤12😱2
“በሕይወት ዘመኔ እንደ ባሌ ያለ ምድር፣ ሁሉም ነገር በአንድ ስፍራ ያለው ኢትዮጵያም ውስጥ፣ አፍሪካም ውስጥ፣ የትም ዓለም አይቼ አላውቅም።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
@sheger_press
@sheger_press
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
@sheger_press
@sheger_press
👎50👍17❤14👏2🤔2
በዕለተ አርብ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ምንም እንኳን ጌታችን የእሾህ አክሊል ደፍቶ እርቃኑን ተሰቅሎ ደሙ እየፈሰሰ ቢያየውም ንጹህ መሆኑን በመረዳት ጌታው መሆኑን ከማወቅ አላገዳውምና “አቤቱ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ ዐስበኝ” አለው።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ።” ሉቃስ 23÷39-43
ከአዳም ቀድሞ ገነት የመግባትን እድል ያገኘው ራሱን አሳልፎ የሰጠውን ጌታውን በመከራው ሰዓት አይቶት ጌትነቱን በመረዳቱ ነው፡፡
ገዳማውያን ራሳቸውን ለክርስቶስ ፍቅር አሳልፈው ሰጥተው ስናያቸው መንፈሳዊ ክብራቸው ይታየናል? መራብ መጠማታቸው ለነፍሳቸው በማደራቸው መሆኑን እንረዳለን? በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምሥራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያንም በበረሃው ግለት ውስጥ ዓለምን ንቀው በረሃብና በውሃ ጥም ከትመዋል፡፡
ፊያታዊ ዘየማን ጌታው በመከራ መስቀል ላይ ቢሆንም ክብሩን እንዳየ፣ ገዳማውያኑ በስጋዊ ችግር ውስጥ ቢሆኑም መንፈሳዊ ክብራቸውን በመመልከት ችግራቸውን ለመቅረፍ እንረባረብ፤ ከጸሎታቸው ረድኤት እናትርፍ፡፡
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ከ 5፡00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ በመሳተፍ፣ በአንድ መቶ ብር ብቻ በገዛነው ትኬት ከጎናቸው እንቁም፡፡ የእደ ጥበብ ምርቶቻቸውንም በመግዛት ከሊቀ መልአኩ በረከት እንካፈል፡፡
አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

❤24
ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች "መገንጠልም፣ መጠቅለልም" አይሠራም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
"ከሰሜን እስከ ደቡብ" ባለው የአገሪቱ ክፍሎች "ልገንጠል" በሚል የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳሉ የገለጹት ዐቢይ፤ "አንዱም አገሩን አያውቅም" ሲሉ ተችተዋል።
ይህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ንግግር የተሰማው በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ባደረጉት የሦስት ቀናት ጉብኝት ወቅት በተካሄደ "ውይይት" ላይ ነው።
ሰኞ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም. በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የተላለፈው ይህ "ውይይት"፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ባሌ ዞን የተጓዙ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የቀድሞ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ነው።
ሁለት ሰዓት ገደማ የሚጠጋው ይህ ውይይት በአብዛኛው ያተኮረው በባሌ ዞን የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን ማልማት እና መጠቀምን በተመለከተ ነው። መጨረሻ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም እንደ ሌሎቹ ተሳታፊዎች ሁሉ በአካባቢው ያለው ሀብት በሚገባው ልክ ባለመልማቱ የተሰማቸውን ቁጭት ገልጸዋል።
ዐቢይ በንግግራቸው "ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም የለም፣ ሰላም መቅደም አለበት" የሚል ቅሬታ በተለያየ መንገድ እንደሚነሳ ጠቅሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት መንግሥት አቋም፤ "ሰላም እንዲመጣ እንለምናለን፣ ሰላም እንዲመጣ እንሠራለን። ሰላም እስከሚመጣ ግን አንቀመጥም፤
እናለማለን" የሚል እንደሆነ ገልጸዋል።

❤29👎9🤔3
🔥⚽️Evening of Epic Battles
Champions League returns with a fiery clash at Santiago Bernabéu, where Real is ready to decisively take down a Juventus that has lost their form. Meanwhile, in Munich, Bayern will once again turn Allianz Arena into a fortress against Club Brugge.
Feel the excitement and win with Melbet!
⬇️
Promo - PRESSSH
Link - https://bit.ly/423Tlea

❤5
በዎላይታ ሶዶ የቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት ሰርቆ የተገኘ ግለሰብ የ5 ዓመት እስራት ተፈረደበት!
በዎላይታ ሶዶ ከተማ፣ ድል በጌሬራ ቀበሌ ውስጥ፣ በቤተክርስቲያን ንብረት ላይ ስርቆት የፈጸመ ግለሰብ ላይ የ5 ዓመት እስራት ቅጣት ተወሰነ።
የቀበሌው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብረሐም ባሳ እንደገለጹት፣ ግለሰቡ አቶ ስጦታው ጎችሎ ሲባል ነዋሪነቱ ሀባ ጌሬራ ቀበሌ መሆኑ ታውቋል።
የስርቆት ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ?
* ቀን: 8/2/2018 ዓ.ም
* ቦታ: ድል በጌሬራ ቀበሌ ቀጠና 3፣ ከአንድ ቤተክርስቲያን
* የተሰረቁ ንብረቶች: የሙዚቃ መሳሪያ እና አምፕሊፋየር ሲሆን
ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ያዋለው የፖሊስ መምሪያው ጉዳዩን ለፍትህ አካል ማቅረቡን ተከትሎ፣ የሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥፋተኛነት ውሳኔ አስተላልፏል።
የሶዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
የ5 (አምስት) ዓመት ጽኑ እስራት
የቀበሌው ታክቲክ ምርመራ ሃላፊ ዋ/ሳጂን ተመስገን ተገኝ፣ ፖሊስ ከፍትህ ተቋማት ጋር በመተባበር ወንጀለኞች በፍጥነት ፍርድ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ምንጭ: የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ

❤23👍2😢1
Sheger Press️️
Photo
የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏
ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማጽኖ በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከአጋንንት ሠራዊተ ተንኰል የሚያድን ነው፡፡ ሚካኤል የሥሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ “ማንነው እንደ እግዚአብሔር?” ማለት ነው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሳጥናኤልን አለቃ አድርጎ ቢሾመውም የተሰጠውን ክብር ትቶ አምላክነትን በመሻቱና በትዕቢቱ ሥልጣኑ ተገፎ ወደ ምድር ሲጣል ኅዳር 12 ቀን ቅዱስ ሚካኤልን በቦታው ተሾሟል፡፡ በክርስትና በአይሁድ፣ እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡ እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው፡፡ ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይገባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል፤ ይማልዳልም፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙ ነው፡፡
እስራኤላውያን በግብፅ ባርነት ለ215 ዓመታት በስቃይ ሲኖሩ ዕንባቸው መንበረ ጸባዖት ደርሶ በሊቀ ነቢያት ሙሴ መሪነት ባሕረ ኤርትራን ተሻግረውና ዐርባ ዘመናት ተጉዘው ምድረ ርስት ሲገቡ ቀኑን በደመና ሌሊቱን በብርሃን እየመራ ያደረሳቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ በዘጸ.23÷20-22 “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል” በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ከሙሴ ጋር እንደነበረ ከእያሱ ጋር ደግሞ እንዲሁ መሆኑም ይህንን ያሳያል፡፡ በኢያሱ 5÷13 እንዲህ ይላል፡፡ “እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡
እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ይህም የመልአኩን ክብር ያሳየናል፡፡ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው” በማለትም በትህትና ጠየቀ፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃም ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ” ይላል፡፡ ኢያሱ ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሳቸው በዚህ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ በተገለጸለት የእስራኤል መሪ በቅዱስ ሚካኤል እገዛ ነው፡፡
ኢያሱ ጌታዬ ማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ ሳይሆን መላእክት የጸጋ ጌቶች ስለሚባሉ ነው፡፡ ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛስ ጌታዬ፤ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ በማለት የአክብሮት የጸጋ ስግደት በመስገድ ብንለምነው፣ ብንታዘዘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አልወጣንም፡፡ መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔርም ነግሮናል፡፡ ይህን የተረዱ ገዳማውያን የመላእክትን ተራዳኢነት ተስፋ አድርገው ታምነው ይኖራሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተካፋይ እንሆናለን፡፡
ገዳማውያን ይህን ተራዳኢነቱን አምነው ዘወትር ይማጸኑታል፣ ይሰማቸውማል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የጸሎታቸውና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡

❤21👍17🙏4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገርጂ የተፈጠረው‼️
ትናንት ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም ገርጂ ወደ ዩኒቲ ዩኒቨርቲ መታጠፊያ መብራት ላይ አንዲት ሴት ዲዛየር መኪና እያሽከረከረች መጥታ ትቆማለች። ሁለት ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎች ሴትዮዋን ከመኪናዋ ጎትተው ከአስፓልት ከጣሉዋት በኋላ መኪናዋን ቀምተው ለማምለጥ ይሞክራሉ። በዚህ ጊዜ ትራፈክ ፖሊሱ ያይና ሳይረን እያስጮኸ ይከተላቸዋል። የተደናገሩት ሌቦች ለማምለጥ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲነዱ ከአንዲት ቪትዝ መኪና ጋር ይጋጫሉ። በዚህ ጊዜ ትራፊክ ፖሊሱ ይደርስና ግብግብ ይገጥማል።በአካባቢው ሰው ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተጎዳችው ባለ መኪናም ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች። ሰዎቹ በትክክል የህግ አስከባሪ አልነበሩም።
ሴትዮዋ ለአደጋ የተጋለጠችው የመኪናዋን በር ሳትዘጋ በማሽከርከሩዋ ስለሆነ ስታሽከረክሩ በራችሁ መቆለፉን አረጋግጡ።
Amsale Birhanu

👏35❤27🤯1
ምርጫው ይራዘማል ?
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስባተኛውን ሀገራዊ የምርጫ ሰሌዳ በሚመለከት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማወያየት ለጋዜጠኞች ዝግ የሆነ ስብሰባ ትናንት አድርጎ ነበር፣ ይሁንና ፓርቲዎቹ በጊዜ ሰሌዳው ላይ ከመወያየታችን በፊት የሀገሪቱ ሰላምና ፀጥታ ነፃ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ አይደለም የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው አገር ዓቀፍ ምርጫ የሚካሄድበትን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ለውይይት ባቀረበበት ወቅት ተቃውሞ እንደገጠመውም ተሰምቷል።
ለጋዜጠኞች ዝግ የነበረው የቦርዱ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ወይይት ዋና አጀንዳ የምርጫው ማካሄጃ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ቢሆንም፣ የውይይቱ ተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ግን በአገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ ከሰላምና ጸጥታ እንዲሁም ከፖለቲካ ምኅዳር ጋር የተያያዙ አስቻይ ሁኔታዎች በመኖር አለመኖራቸው ላይ ቦርዱ እና ፓርቲዎች ከስምምነት ላይ ባልደረሱበት ሁኔታ በምርጫ ማካሄጃ የጊዜ ሰሌዳ ላይ መነጋገር አንችልም በሚል ተቃውሞ አሰምተዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተወካዮች ግን ኢትዮጵያ ከሰላምና ጸጥታ አንጻር አሁን ባለችበት ነባራዊ ሁኔታ ነጻ እና ፍትሃዊ አገር ዓቀፍ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችላት ቁመና ላይ አይደለችም በማለት የምርጫ ቦርድ አመራሮችን እንደሞገቱ ከምንጮች ተረድተናል።
አብዛኞቹ ፓርቲዎች በተለይ በአማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ያሉት የጸጥታ ሁኔታዎች ነጻ እና አሳታፊ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ አይደሉም የሚል አቋም ይዘው ከስብሰባው ተበትነዋል ተብሏል ።
ዋዜማ

❤24😱2👎1
" የሰላምና የዕርቅ ዕድል ቅድሚያ እንዲሰጠው ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይገባዋል " - ቅዱስነታቸው
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶስ ዓቢይ ጉባኤ መጀመሩን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዚህም መልዕክታቸው የርስ በርስ ግጭቶች ቆመው ግጭቶች በውይይት እና በድርድር እንዲፈቱ ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
ቅዱስነታቸው ምን አሉ ?
" በሀገራችን ያለው ያለመረጋጋት በሕዝባችን አጠቃላይ ሥነ ልቡና በሀገሪቱ አንድነትና ዕድገት የሚያስከትለውን ጫና በቀላሉ የሚታይ አይሆንም፤ የሕዝቡ ሥነ ልቡና ከተጐዳ የነገው ዕድል ጤናማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡
ችግሩ እየታየ ያለው በዋናነት በሀገራችን ፖለቲከኞች በመሆኑ ነገሩ የተወሳሰበና የተራዘመ እንዲሆን አድርጎታል፤ በመሆኑም ይህ የርስ በርስ ግጭት ቆሞ ችግሮች በውይይትና በድርድር በመፍታት የወንድማማች እልቂት የሚያስቆም የሰላምና የዕርቅ ዕድል ቅድሚያ እንዲሰጠው ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይገባዋል፡፡
የነገው ትውልድ ልማታዊ ተስፋ እውን ሊሆን የሚችለው ሰላምና አንድነት ሲኖር ነውና መንግሥት፣ ተፎካካሪ ፖለቲከኞችና ነፍጥ ያነሡ ወገኖች ሁሉ ለሰላም መስፈንና ለልማት ዕድገት መረጋገጥ ሲባል ወደ መግባባት እንዲመጡ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ " ብለዋል።
(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)(tikvah)

❤18👍3👏3
Sheger Press️️
Video
የእግዚአብሔር እጅ የመሆን ዕድል🙏🏼
ልብ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 144÷15 “የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ አንተ እጅህን ትከፍታለህ ሕይወት ላለው ሁሉ መልካምን፣ የሚጠቅመውን፣ ታጠግባለህ” ይላል፡፡ ለተራበ የሚሰጥ፣ ለተጠማም የሚያጠጣ እግዚአብሔር የሚሰራበት የታደለ ሰው ነው፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምሥራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ነው ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያንም በበረሃው ግለት ውስጥ በረሀብና በውሃ ጥም ይሰቃያሉ፡፡ ዓለምን ንቀው ወጥተዋልና ታግሰው ቢኖሩም ገዳሙን ደግፈን በረከት እንፈስ፡፡
ቅዱስ ዳዊት እንዳለው ተስፋቸው እግዚአብሔር አያሳፍራቸውም፤ ምግባቸውን ይሰጣቸዋል፤ እጁንም ይከፍታል፤ ያጠግባቸውማል፡፡ ለመስጠት ፈቃደኛ በሆኑ ልጆቹ በኩል በረከትን ያወርዳል፡፡ ካለን ላይ የዐቅማችንን ሰጥተን በረከት የምናገኝበት የእግዚአብሔር እጅ የምንሆንበት ዕድል እነሆ፡፡
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ከ 5፡00 ጀምሮ በተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባዔ ለመሳተፍ፣ በአንድ መቶ ብር ብቻ እንግዛ፣ በዕለቱም የገዳማውያኑን የእደ ጥበብ ምርቶች በመግዛት ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤትና በረከት እንሳተፍ፡፡

❤22👍1