Telegram Web Link
Sheger Press️️
Photo
በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ።

ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን በማሳረግ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ጸሎቱ እንደ ተሰማ ነገረው፡፡ በሉቃስ 1÷14 እንደተጻፈው ቅዱስ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ተድላና ደስታ ይለዋል፡፡ በዚህ የወንጌል ክፍል ካህኑ ቅዱስ ዘካርያስና ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ ይሰጣቸው ዘንድም እግዚአብሔርን ዘወትር ይማጸኑት ነበር፡፡ ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና፡፡ ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፡፡

ዮሐንስ ማለት የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ለካህኑ ዘካርያስ ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ እንደምትወልድ፣ ስሙንም ዮሐንስ እንደሚለው፤ በመወለዱም ብዙዎች እንደሚደሰቱ፤ ልጁም በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ እንደሚኾን፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ እንደማይጠጣ፤ እንደዚሁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላበት ነገረው፡፡ ዘካርያስም “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ?” አለው፡፡ መልአኩም “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህን የምሥራች እንድናገርህም ተልኬ ነበር፡፡ እነሆም በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም” አለው፡፡ ከውጪ ቆመው ጸሎት ሲያደርጉ የነበሩት ሕዝብም ዘካርያስን ከቤተ መቅደስ እስኪወጣ ይጠብቁት ነበር፤ በመዘግየቱም ይደነቁ ነበር፡፡

ከቤተ መቅደስ በወጣም ጊዜ ሊያናግራቸው ባለመቻሉ ይጠቅሳቸው ነበር፡፡ በሁኔታውም በቤተ መቅደስ ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፡፡ እርሱም ድዳ ሆኖ ኖረ፡፡ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሔደ፤ ከሁለት ቀን በኋላም አረጋዊቷ ቅድስት ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም በመካንነቷ ከሰዎች የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዷላታልና “እግዚአብሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድቤን ያርቅ ዘንድ እንዲህ አደረገልኝ” ስትል ለአምስት ወራት ተሸሸገች፡፡ ጌታችን ሊወለድ ስድስት ወራት ሲቀረው፣ ሰኔ 30 ቀን ንዑድ፣ ክቡር የሆነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ፡፡ ዘመዶቹ ስሙን በአባቱ መጠርያ ዘካርያስ ሊሉት ቢወዱም እናቱ ግን “ዮሐንስ ይባል” አለች፡፡ የመልአኩን የብሥራት ቃል ባለመቀበሉ አንደበቱ ተይዞ የነበረው ካህኑ ዘካርያም ስሙ “ዮሐንስ” ይባል ብሎ ሲጽፍ አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱም ተፈታ፡፡

“አንተ ሕፃን ሆይ! የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፤ እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል፤” በማለት የቅዱስ ዮሐንስን ነቢይነትና አጥማቂነት፣ እንደዚሁም የክርስቶስን የማዳን ትምህርት አብሣሪነት የሚመለከት ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ አባቱ አስቀድሞ ተናገረለት፡፡ ጥር 11 ቀን ጌታችንን ያጠመቀበት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በሔሮድስ ወህኒ ቤት ተጥሎ ከቆየ በኋላ መስከረም 1 ቀን ከጌታችን ቃል ኪዳን ተቀብሎ፤ መስከረም 2 ቀን በሰይፍ አንገቱ ተቆርጦ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ የተቆረጠች ራሱም ለ14 ዓመታት ዞራ ወንጌልን ሰብካለች፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የገዳማዊ ሕይወት ታላቅ ምሣሌ ነው፡፡ ገዳማውያንን ስንደገፍ፣ በዓታቸውንም ስናጸና በረከቱ ያድርብናል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
👍138
ከቀረጥ ነፃ‼️

በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር እንዲገቡ ተወሰነ‼️

👉 ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት ከተፈቀደላቸው ውጪ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት ሙሉ ለሙሉ ታግዷል።
በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ማናቸውም አይነት ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር እንዲገቡ ተወስኗል አለ የገንዘብ ሚኒስቴር፡፡
ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት መሆኑ ቢታወቅም ለዘመናት የዚህ የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ ሳትሆን ቆይታለች፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ መንግስት ሲያደርግ የቆየው እልህ አስጨራሽ ጥረት ተሳክቶ በቅርቡ በካሉብ አካባቢ የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ኢንዱስትሪ ተመርቆ የተፈጥሮ ጋዝ የማምረት ስራ በይፋ ተጀምሯል።

ይህን ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ቤንዚን እና ናፍታ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን የተፈጥሮ ጋዝ በሚጠቀሙት ተሽከርካሪዎች መተካት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

የተፈጥሮ ጋዝ የሚያመነጨው በካይ አየር እጅግ በጣም ዝቅተኛ የሆነ፣ ለተለያየ የሀይል ምንጭ አገልግሎት ሊውል የሚችል፣ በሀይል አጠቃቀም ረገድ ውጤታማነት እንዳለው የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ የተፈጥሮ ጋዝ በኢትዮጵያ የሚመረት በመሆኑ ለነዳጅ ግዥ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ያስቀራል።

በመሆኑ መንግስት የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀምን ለማበረታታት ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ማናቸውም አይነት የደረቅ፣ የፈሳሽ ጭነት እና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር እንዲገቡ መፈቀዱን አስታውቋል፡፡
#fbc
12👏7👍4
ከሚስቱ ጋር በደንብ አላረስከኝም በሚል ጸብ ትታበት የሄደችውን የስድስት ወር ልጁን የገደለው አባት በእስራት ተቀጣ

በባሌ ዞን ሲናና ወረዳ ሰለቃ ቀበሌ ነዋሪ   የሆነው አብድልከሪም ቃዲ በልጅነቱ ከቤተሰብ ተለይቶ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ ቆይተዋል።አብድልከሪም አልያ ከተባለች የ21 ዓመት ወጣት ጋር ፍቅር በመጀመር ከዛም  ትዳር በመመስረት ቤት ተከራይተው ይኖሩ ነበር።

ሁለቱ ጥንዶች በትዳራቸው ሰላማዊ የሆነ ሂደት ቢኖረውም የሃያ አንድ ዓመቷ ባለቤቱን እርግዝና ተከትሎ ግን በቤት ውስጥ ለወሊድ ዝግጅት የሚደረገው ወጭ ላይ ግጭት ተፈጥረው ነበር። ይሁን እንጂ የካቲት ወር 2017ዓ.ም  አልያ አንዲት ሴት ልጅ ተገላገለች። የህጻኗ መወለድ ጋር ተያይዞ የነበረው አለመግባባት በጥቂቱ ቢቀንስም ቤት ውስጥ የሚያስፈልገው የቤት ወጭ የነበረው ግጭት እንደ አዲስ መጀመሩ ተነግሯል።

አልያ አራስ ቤት ሆና ሊጠይቋት የሚመጡ ቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቿ በደንብ እንዳልታረሰች በመውቀስ ነገሮች እንዲባባሱ ምክንያት እንደነበሩ ከምርመራ መዝገቡ መረዳት እንደተቻለ  የባሌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ሳጅን ጎሳ ስንታየሁ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።አልያ  በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች በሌሎች ግፊት በስድስተኛ ወሯ ነሀሴ መግቢያ ላይ የወለደቻትን የስድስት ወር ህጻን ሱሚያ አብድል ከሪም የተባለችውን ቤት ውስጥ ጥላ ትሰወራለች።

አብድል ከሪም እቤት ውስጥ ተጥላ ያለችው የስድስት ወር ህጻን ሱሚያን ለአምስት ቀናት እንደምንም ተቸግሮ በመያዝ ባለቤቱንና  የልጁን እናት አድራሻ ሲያፈላልግ ከአካባቢው መሰወሯን ወሬ ይሰማል።በዚህ ንዴትም  የስድስት ወር ሕፃኗ ሱምያን በጨርቅ አንቆ ህይወቷን በማጥፋት የገለባ ሣር ውስጥ እንደቀበራት በተገኘው ማስረጃ ተረጋግጧል።

ተከሳሽ አብድል ከሪም በገለባ ውስጥ የስድስት ወር ህጻኗን ሲቀብር የተመለከቱ የአካባቢ ሰዎች ወዲያው ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ  አብድል ከሪም በቁጥጥር ስር ውሎ ገለባ ውስጥ የቀበራትን የስድስት ወር ሕፃን ልጅ አስክሬን መውጣቱ ተገልጿል ። በዚህም የድርጊቱን አፈፃፀም መርቶ ያሳየ ሲሆን ፖሊስም  በሆስፒታል የአስክሬን ምርመራ አድርጎ በክብር ካስቀበረ በኋላ የምርመራ መዝገቡን በበቂ ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ልኳል። 

አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ሕግ 539 በከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቷል። ክሱን የተመለከተው የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አብድል ከሪም ቃዱ ሰውን ለመግደል አስቦና ተዘጋጅቶ  የራሱ አብራክ ህጻን ልጅን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉ ሙሉ በሙሉ በማስረጃዎች በመረጋገጡ እጅግ  ጨካኝ፣ነውረኛና አደገኛ መሆኑን ስለሚገልፅ  በአስራ ስምንት አመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲሉ የኮሙኒኬሽን ባለሞያው ዋና ሳጅን ጎሳ ስንታየው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።
23👍10😱2😢2🔥1
#MoE

ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸው ትክክለኛ መረጃ ካላቀረቡ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሀላፊዎቻቸው ከስራ ይባረራሉ ተባለ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቀጣይ 6 ወራት ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ሌሎችም ጉዳዮች መረጃ በትክክል ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ አለባቸው ብለዋል።

ይህንን ያላደረገ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በስራው አይቀጥልም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" ይህንን ስራ እኔ በቀጥታ እከታተለዋለሁ " ማለታቸውን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ከወራት በፊት ሚኒስትሩ " ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ከነፎቶ እንዲሁም ስለሚሠሩት ሥራ ትክክለኛ መረጃ ስጡን ብለን ከጠየቅን ሦስት ዓመት አልፎናል፡፡ ሆኖም እስካሁን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ችግር ሆኖብናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ እውነተኛ መረጃ መስጠት አልተለመደም " ማለታቸው ይታወሳል።

ዩኒቨርስቲዎች ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ የውሸት ሪፖርት ያቀርቡ እንደነበር ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቁጥር በውሸት በመጨመር በጀት እንዲጨመርላቸው ያደርጉም እንደበር ተናግረው ነበር።

@sheger_press
@sheger_press
19👍5
9🥰4🤯2
Sheger Press️️
Photo
ቅዱስ ራጉኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏

የኪሩቤል አለቃቸው የጌትነቱ ዙፋን ጠባቂ

የስሙ ትርጓሜ የኃያላን ኃያል እግዚአብሔር ማለት ነው። ከኃያላን ሁሉ በላይ ኃያል የሆነው እግዚአብሔር ኃያልነቱ ከ - እስከ የሌለው መሆኑን ለመግለጽ የተቀመጠ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ኃያል የኃያላን ኃያል መሆኑን የሚገልጽ ትርጉም አለው። ይህ ኃያል መልአክ ቅዱስ ራጉኤል ነው፡፡ አንድም ራጉኤል ማለት የብርሃናት አለቃ ማለት ነው። የብርሃናት አለቃ ሲባል ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን በማመላለስ ለሰው ልጆች፣ ለአዝርዕት፣ ለእንስሳት፣ ለአራዊት ሁሉ ብርሃንን የሚመግብ ነው ማለት ነው። አንድም ራጉኤል ማለት የሚበቀል ማለት ነው። በቀል የሚገባው ለጠላት ነው የሰው ልጅ ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፡፡ አንድም ራጉኤል ማለት ጽኑ እግዚአብሔር ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ጽኑነት ለማጉላት ሲል ጽኑ አለው። እግዚአብሔር የማይወላውል የማይዋዥቅ የማይከዳ ጽኑ አምላክ መሆኑን የሚያሳይ ትርጉም ያለው ስያሜ ነው።

በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክም ነው። ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነ በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ሥራው የሰመረ እስከዛሬ የሞት ወጥመድ ያልያዘው ነብዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጠላት ዲያብሎስን የሚበቀለው ቅዱስ ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ይለናል፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6÷4 እንደተጻፈው ቅዱስ ራጉኤል እግዚአብሔርን አምነው ሕጉን ጠብቀው በፍርሐት አምልኮቱን ለሚፈጽሙ ሁሉ ጠላት ዲያብሎስን ያርቅላቸዋል ፈጥኖ በመድረስም ይታደጋቸዋል። ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በ64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ ሥጋዋ ተነጥቆ በዕፀ ሕይወት ሥር ሲያርፍ አብሮ ለሔደውና ስጋዋን ሲያጥን ለነበረው ለፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ኅብስትን የመገበ መልአክ ነው።

ሎጥን፣ ሚስቱንና ልጆቹን ከእሳተ ገሞራ ያዳነ፣ የበለአምን እርግማን ወደ በረከት የለወጠ እርሱ ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው። አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ለመተካት ዓለምን የመለወጥ ሥልጣን የተሰጠው ቅዱስ መልአክ ነው። ከእግዚአብሔር የጌትነት አዳራሽ ይገባና ይወጣ ዘንድ ስልጣን ያለው ከኪሩቤልና ከሱራፌል ጋር በፈጣሪ የጌትነት ዙፋን ፊት የሚቆም ነው። በቅዱስ ራጉኤል ሥዕል ላይ የምናየው ይህ ባለ አራት ራስ ንስር ከአርባእቱ ኪሩቤል አንዱ ገጸ ንስር ነው። የሥላሴን የጌትነት ዙፋን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳት ናቸው። የሚሸከሙት ሲባል ጫማ የሰውን ልጅ እንደሚሸከመው እንጂ ችለውትስ አይደለም። እነርሱም የሰው፣ የእንስሳ፣ የንስርና የአንበሳ ገጽ ያላቸው ናቸው።

ቅዱስ ያሬድም በድጓው "አርባእቱ እንስሳ አልቄንጥሩ እንደሚባለው ንስር ፊት ለፊት አይታዩም አንዱም በመራቸው ይሔዳሉ እነርሱም እያንዳንዳቸው አራት ገጽ ሲኖራቸው ሳያርፉና ሳይደክሙ የሚያመሰግኑ ናቸው" በማለት ጽፏል። ነብዩ ሕዝቅኤልም በምዕራፍ 1÷6-13 "ለእያንዳንዱ እንስሳትም የተለያዩ አራት ገጾች ነበሩት። ከዚህ የምንገነዘበው ነገር ቢኖር አራት ገጽ ካላቸው ኪሩቤል መካከል አንዱ ንስር መሆኑን ነው። ቅዱስ ራጉኤል ደግሞ የኪሩቤል አለቃቸው የጌትነቱ ዙፋን ጠባቂ በመሆኑ በዚህ ምክንያት እነርሱ ዙፋኑን ተሸካሚ እርሱ ደግሞ አጠገባቸው መቆሙ መንበሩን ጠባቂ በመሆኑ በዚህ አይነት የአገልግሎት ድርሻ አብረው ሊሳሉ ችለዋል።

ገዳማውያንን ከመንፈሳዊው ጠላት ጋር ሲዋጉ ኃይል፣ ጽንዕ ብርታት የሚሰጣቸው ቅዱስ ራጉኤል ነው፡፡ እኛም ገዳማቸውን በመደገፍ በዓታቸውን በማጽናት የበረታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
26🥰3
በትዳር ግንኙነት ውስጥ "የማይታይ ርቀት" ከተፈጠረ ምን ማድረግ ይቻላል?

የስነ ልቦና ባለሙያዎች ምን ይላሉ?

በትዳር ውስጥ የጋራ መከባበር ከሌለ፣ የማይታይ ርቀት ይፈጠራል። በባህሪይ ውስጥ ህይወት መኖር አለበት፣ ይህም ፍቅርንና ንፅህናን ይጠይቃል። ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ "በድንገት አጋርዎን ማቀፍ፣ ማመስገን ወይም አብሮ መደሰት—እነዚህ ትናንሽ ልማዶች፣ በቅንነት ከተደረጉ፣ ግንኙነቱን ሕያው እና ጠንካራ ያደርጉታል።" በትዳር ግንኙነት ውስጥ የተፈጠረውን "የማይታይ ርቀት" ለማጥፋት ምን ማድረግ እንደሚቻል እነሆ;

አጋሮ ጤና በሚያጣበት ጊዜ መንከባከብ እና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ፍላጎት ማሳየት ግድ ይላል።

አጋርዎ ሲታመም መንከባከብ፣ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ወቅት ሁኔታቸውን መከታተል፣ እና በአጋርዎ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ላይ ፍላጎት ማሳየት ትዳርዎን ጠንካራ እና የተሟላ ያደርገዋል። በየቀኑ ስለ አጋርዎ ደህንነት ይጠይቁ። ለምሳሌ፣ "ቀንህ እንዴት ነበር?" —እንደነዚህ ያሉት ትናንሽ ነገሮች እርስዎን የበለጠ ያቀራርባሉ።

አጋርዎን በጥሞና ያዳምጡ

በየቀኑ ከአጋርዎ ጋር መነጋገር እንደ አስፈላጊነቱ፣ በጥሞና ማዳመጥም እኩል አስፈላጊ ነው። ሁለቱ ሰዎች እርስ በርስ በትክክል ሲደማመጡ እና አልፎ አልፎ አሳቢ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ፣ ግንኙነቱ እየጠለቀ ይሄዳል።

ምስጋናን መግለጽ

በዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ውስጥ አጋርዎ በትናንሽ ሥራዎች ቢረዳዎት፣ ማመስገን ይችላሉ። ይህ ፍቅርንም ሆነ መከባበርን ይጨምራል። አንዲት ትንሽ 'አመሰግናለሁ' ለአጋርዎ ትልቅ ትርጉም አላት።

ትናንሽ የፍቅር ምልክቶች

አካላዊ ፍቅር በትዳር ግንኙነት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው። እጅ ለእጅ መያያዝ፣ ማቀፍ፣ አልፎ ተርፎም ቀላል ንክኪዎች ግንኙነቱን ያጠናክራሉ እና ፍቅርን ለመግለጽ ቀላሉ መንገዶች ናቸው።

አብሮ መስራት

ባልና ሚስቱ እርስ በርስ በትክክል የሚዋደዱ እና የሚከባበሩ ከሆነ፣ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ኃላፊነቶች ይጋራሉ። ይህም አንድ ሰው ከመጠን በላይ እንዳይደክም ይከላከላል።

ለአጋርዎ ትናንሽ ደስታዎችን ይስጡ

ሁልጊዜ ትልቅ ድንገተኛ ስጦታ መስጠት አያስፈልግም። አንዳንድ ጊዜ፣ በሚያምር የእጅ ጽሑፍ የተጻፈ ደብዳቤ በቂ ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ በቸኮሌቶች የሚደረግ ትንሽ ድንገተኛ ስጦታ የአጋርዎን ቀን የተሻለ ሊያደርገው ይችላል።

አብሮ ጊዜ ማሳለፍ

አብሮ ጊዜ ማሳለፍ፣ ለምሳሌ በእግር መሄድ፣ አብሮ መጽሐፍ ማንበብ፣ ወይም አብሮ ማብሰል፣ ከስልኮች ወይም ከስክሪኖች ገጾች ርቆ እርስ በርስ ጊዜ መስጠት ግንኙነቶችን ያጠናክራል።
38
እጀባ‼️

በአማራ ክልልና አዲስ አበባ መካከል በትራንስፖርትና የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ እገታዎችንና ግድያዎችን ለመከላከል መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች ጸጥታ ኃይሎች እጀባ መጀመራቸው ተሰምቷል። እጀባውን ለማግኘት፣ ከአማራ ክልል የሚነሱ ተሽከርካሪዎች ቀን 6 ሰዓት ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጎሐጽዮን ከተማ እንዲሁም ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተሽከርካሪዎች ረፋዱ 4 ሰዓት ላይ ፍቼ ከተማ መሰባሰብ እንደሚጠበቅባቸውና ጸጥታ ኃይሎቹ በየከተማው እየተቀባበሉ እጀባውን እንደሚያካሂዱ ምንጮች ገልጸዋል።

እጀባው ከተጀመረ ወዲህ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ታጣቂዎች በተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጽሙት እገታ መቆሙን ምንጮች ነግረውናል።(ዋዜማ)

@sheger_press
@sheger_press
26🤔9
1
Sheger Press️️
Photo
#ቴምርፕሮፐርቲስ

⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።

📍 ሊሴ ገ/ማርያም

ባለ 1 መኝታ
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)

ባለ 2 መኝታ
👉 78 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,970,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (897,000)
👉 99ካሬ ሙሉ ክፍያ = 11,385,000
                ቅድመ ክፍያ = 10% (1,138,500)

ባለ 3 መኝታ
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
                   ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)

📍 አያት (ፈረስ ቤት)

ባለ 2 መኝታ
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)

ባለ 3 መኝታ
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 121 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 11,495,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,149,500)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)


📍 ተክለሐይማኖት (ሱማሌ ተራ)

ባለ 3መኝታ
👉 110ካሬ ሙሉ ክፍያ = 12,100,000
                  ቅድመ ክፍያ = 10% (1,210,000)

⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።

📍 ፒያሳ (አድዋ ሙዚየም)

👉 ዘመናዊ የንግድ ሱቆች
👉G+5 የንግድ ሞል

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251927179049
+251985686889
Telegram: @Consultantabdu/@murad2717

WhatsApp:https://wa.me/251927179049/

Or
https://wa.me/qr/KHATRTL7M7OJE1
4
በሰሜን ወሎ ተካሔዶ በነበረው ውጊያ፤ በፋኖ ኀይሎች ተይዘው የነበሩትን የመንግሥት የፀጥታ አባላት መረከቡን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ!

በሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያ ዙሪያ ተካሔዶ በነበረው ውጊያ በፋኖ ኀይሎች ተይዘው የነበሩትን የመንግሥት የፀጥታ አባላት መረከቡን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።

በመስከረም ወር አጋማሽ በዞኑ የተካሔደው “ድንገተኛ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳትን ያስከተለ” እንደነበር ዓለም አቀፉ ድጋፍ ሰጪ ተቋም ገልጿል። ባለፉት 6 ቀናት ሁለት ቡድኖችን በወልዲያና በላሊበላ ከተማዎች በማስፈር የሰብአዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጉዳዩ ን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል።

በአንድ ሳምንት ውስጥ ለወልዲያ ሆስፒታል እንዲሁም በሙጃ እና ኩልመስክ አካባቢ ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሕክምና መሳሪያዎችን ማበርከቱን አስታውቋል።ከመሳሪያዎቹ ውስጥ የቀዶ ጥገና ሕክምና ለመስጠት የሚያገለግሉ እንደሚገኝበት ተመላክቷል። በዚህም በውጊያው ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ 250 ለሚሆኑት የቀዶ ጥገና ሕክምና መስጠት እንደቻለ ተገልጿል።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ካደረገው የሕክምና ድጋፍ በተጨማሪ በፋኖ ኃይሎች ተይዘው የሚገኙ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችን መጎብኘቱን ትላንት ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። ኮሚቴው አክሎም ወታደሮቹን ከፋኖ ኃይሎች ተረክቦ ወልዲያ ከሚገኙ አባላቶቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን አመልክቷል።

በላሊበላ ከተማ የሚገኘውን የድጋፍ ሰጪ ቡድን የሚመሩት ማርቲን ታልማን “በቅርብ ቀናት ውስጥ በሰሜን ወሎ በርካታ ሰዎች በውጊያው ተገድለዋል እንዲሁም ቆስለዋል” ሲሉ ተናግረዋል። ሆኖም የጤና ተቋማት “በተገደበ አቅም” የቆሰሉ ወታደሮችንና ሲቪሎችን እያከሙ መሆናቸውንም ቡድን መሪው አስታውቀዋል።

@sheger_press
28🙏8🤯2
የእግዚአብሔር እጅ የመሆን ዕድል🙏🏼

ልብ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 144÷15 “የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ አንተ እጅህን ትከፍታለህ ሕይወት ላለው ሁሉ መልካምን፣ የሚጠቅመውን፣ ታጠግባለህ” ይላል፡፡ ለተራበ የሚሰጥ፣ ለተጠማም የሚያጠጣ እግዚአብሔር የሚሰራበት የታደለ ሰው ነው፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ነው ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያንም በበረሃው ግለት ውስጥ በረሀብና በውሃ ጥም ይሰቃያሉ፡፡ ዓለምን ንቀው ወጥተዋልና ታግሰው ቢኖሩም ገዳሙን ደግፈን በረከት እንፈስ፡፡

ቅዱስ ዳዊት እንዳለው ተስፋቸው እግዚአብሔር አያሳፍራቸውም፤ ምግባቸውን ይሰጣቸዋል፤ እጁንም ይከፍታል፤ ያጠግባቸውማል፡፡ ለመስጠት ፈቃደኛ በሆኑ ልጆቹ በኩል በረከትን ያወርዳል፡፡ ካለን ላይ በአቅማችን ሰጥተን በረከት የምናገኝበት የእግዚአብሔር እጅ የምንሆንበት እድል እነሆ፡፡

ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ ከ 5፡00 ጀምሮ በተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ለመሳተፍ፣ በአንድ መቶ ብር ብቻ እንግዛ፣ በዕለቱም የገዳማውያኑን የእደ ጥበብ ምርት ምርቶች በመግዛት ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤትና በረከት እንሳተፍ፡፡


አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444
25👍2
"ሰራዊቱ ለትልቅ ግዳጅ ይዘጋጅ..." ጀነራል አበባው ታደሰ

‹‹ሁለት ነገር መጠንቀቅ አለብን፤ የዲጂታል ጦርነት፣ በአእምሯችን የሚመጣውን ጦርነት፣ በስድብ የሚመጣውን ጦርነት በቅጡ እናውቀዋለን፡፡ በመንደር የሚመጣውንም ጦርነት በቅጡ እናውቀዋለን፤ ማን እንደሚልከውም እናውቃለን፡፡ ለዚያ በቂ ዝግጅት አድርገናል፡፡ ስለዚህም ደማችሁንም አጥንታችሁንም ከስክሳችሁ ለዚያ ታላቅ ግዳጅ ተዘጋጁ››
ይህን ንግግር ያሰሙት ጀነራል አበባው ታደሰ ከቀናት በፊት በባቱ ከተማ ተገኝተው ነው፡፡
Andafta
👎4315😱8👍7👏4😢2🥴2
#Breaking News

የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤ/ክ 4 ሰዎችን ከቤተ ክርስቲያኗ አባልነት አግደች።

ግለ ሰቦቹ በቤተ ክርስቲያኗ የአጥቢያ ማህተም በገዛ ፍቃዳቸው በማሳተም እና በመጠቀም፡ ቤተ ክርስቲያንን በማወክ፡ የቤተ ክርስቲያኗን የላይኛው መዋቅር ትዕዛዞች አለመቀበል እና ማህበራዊ ሚድያን በመጠቀም የቤተ ክርስቲያኗን እና የመሪዎችን ስም በማጠልሸት ስራ ላይ የቆዩ ናቸው ተብሏል።

እነዚሁ ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያኗ ዋና ጽ/ቤት እና
ቀጣና መሪዎች ጋር ከ10 ግዜ በላይ የተመቻቸ የእርቅ መድረኮችን አፍርሰዋል።
18👍7🤔3
ተስማሙ‼️

ከብስራት ራድዮ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የነበረው የስፖርት ጋዜጠኛው መንሱር አብዱልቀኒ ከጣብያው ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ሸገር ፕረስ ከጋዜጠኛው ይፋዊ ገፅ ተመልክቷል።

ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ በመልክቱም ከጣብያው ማኔጅመንት ጋር በጉዳዩ ዙርያ በመልካም መንፈስ ብዙ ከተወያየን በኋላ ብስራት ስፖርት ወደ አየር ሞገድ እንዲመለስ ከስስምምነት ላይ ደርሰናል ሲል አስታውቋል።

ከነገ እሁድ ማለትም ጥቅምት ሁለት ጀምሮ ፕሮግራሙ በተለመደው ሰዓት እንደሚተላለፍ ስገልፅላቹ በታላቅ ደስታ ጋር ነው ያለ ሲሆን ላለፉት ቀናት ፕሮግራሙን በመናፈቅ በተለያዩ ሚድያዎች በኩል መልክቶቻቹ ላደረሳቹኝ ሁሉ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው ሲል ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ተናገረ።

@sheger_press
@sheger_press
42👎4
በትግራይ ክልል ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 1፤ 2018 ምሽት፤ ለሁለት ጊዜያት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ። ከምሽቱ 1፡01 ላይ የደረሰው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 5.3 መለካቱን የገለጸው መስሪያ ቤቱ፤ ከ17 ደቂቃ በኋላ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.3 መድረሱን አስታውቋል።

ከእነዚህ ክስተቶች አራት ሰዓት አስቀድሞ፤ በሬክተር ስኬል 4.2 የተላከ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመቐለ ከተማ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለ ቦታ ላይ መድረሱን መስሪያ ቤቱ መዝግቧል። ዛሬ ምሽት ከደረሱት ርዕደ መሬቶች የመጀመሪያው የተመዘገበው ከመቐለ ከተማ 58 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለ ቦታ ላይ መሆኑንም ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሁለተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ከውቅሮ ከተማ 32 ኪሎ ሜትር በሚርቅ ቦታ ላይ እንደሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ርዕደ መሬቶችን የሚመዘግበው “ቮልካኖ ዲስከቨሪ” በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል። ርዕደ መሬቱ ያስከተለው ንዝረት በሻጉባይ፣ በውቅሮ፣ ዶሎ፣ በዕዳጋ ሐሙስ እና በአዲግራት ከተሞች እንደተሰማ ድረ ገጹ ጠቁሟል።

የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት፤ ክስተቱ ከተፈጠረበት 92 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የአረርቲ ከተማ ጭምር እንደደረሰ “ቮልካኖ ዲስከቨሪ” ገልጿል። በትግራይ ክልል ርዕደ መሬት ሲያጋጥም ካለፈው የካቲት ወር በኋላ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው።

ባለፈው ዓመት የካቲት ወር መጨረሻ ገደማ ከአዲግራት ከተማ 46 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል። እኩለ ለሊት አቅራቢያ የተከሰተው ይኸው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ ነበር። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@sheger_press
@sheger_press
27👍2🤯2😢1
2025/10/23 06:53:27
Back to Top
HTML Embed Code: