በዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል ዋና መጋዘን ላይ ከባድ የእሳት አደጋ ደረሰ!
ጥቅምት 06 ቀን 2018 ዓ.ም.በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን የአካባቢው ምንጮች አስታወቁ።
የጉዳቱ ክብደት:
እሳቱ በተለይ ሆስፒታሉ የሚጠቀምበትን ዋና የመድሃኒት መጋዘን (Main Pharmacy Store) ያወደመ ሲሆን፣ በውስጡ የነበሩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድመዋል።
ይህ በሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ ከባድ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ይጠበቃል።
ቃጠሎው ከተነሳ በኋላ፣ በርካታ አካላት በአፋጣኝ ተረባርበው አደጋውን በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል። ከተሳተፉት መካከል፡-
* የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና የጤና ሳይንስ ተማሪዎች
* የአክሱም ከተማ ፀጥታ አባላትና ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች
* የከተማዋ ወጣቶች
* ፌደራል ፖሊስ አባላት
* ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተውጣጡ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በሁሉም አካላት ትብብር አደጋው ተረጋግቷል።
የእሳት ቃጠሎው መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን በይፋ ያልተገለጸ ሲሆን፣ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።
Via መናኸሪያ ሬዲዮ
@sheger_press

❤13🤔3😢2
ተቃውሞው ቀጥሏል‼️
የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ለአራተኛ ቀን ዛሬ የመኪና መንገድ ዘግተዋል።
ዛሬ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው የዓዲግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ ሶስት ዋና መንገዶች ተዘግተዋል።
ትናንት ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት መንገድ ተዘግቷል።
ከጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ወዲህ ከክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች በኣጉላዕና ፣ በመኾኒ ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስድ መንገድ በእንዳባጉና ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት የሚወስድ በሴሮ ተዘግተው በዚያው ቀን በተለያዩ ሰዓቶች መከፈታቸው ይታወሳል።
የክልሉ ካቢኔ በመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በኩል ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ የሰራዊቱ አባላት ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱን ትላንት አሳውቆ ነበር።
ያም ቢሆን ግን ዛሬም መንገዶች ተዘግተዋል።
tikvah ethiopia

❤11👎2👏2🤔1
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ዛሬ ጠዋት በታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባሰራጨው ዘገባ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ተሻለ ዛሬ ጠዋት 12፡30 ከመኖሪያ ቤታቸው ተነስተው ወደ ጽ/ቤታቸው ሲጓዙ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው አልፏል፡፡
አስተዳደሩ ለግድያው “ጽንፈኛ” ብሎ የጠራውንና በአካባቢው የሚንቀሳቅሰውን ታጣቂ ኃይል ተጠያቂ ነው ሲል በመግለጫው ከስሷል፡፡የግለሰቦች ህይወት በተለያየ ጊዜና ቦታ እየጠፋ እንደሆነም መግለጫው አመልክቷል፡፡

❤21👍7🤔3
Sheger Press️️
Photo
‹‹ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገር ይኮበልላሉ››
የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ሻብያን ነክሰው ይዘዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ፈርጥጠው ከአገር ይወጣሉ ይህም በቅርብ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የአሰቡ ዘመቻ ከተጀመረ ኢሳያስ ከስልጣን ይወገዳሉ የሚል ትንተና እየተሰጠ ባለበት በዚህን ወቅት አምባሳደሩ ያሰሙት ጉዳይ ሻብያን ያስደነገጠ እና ያሸበረ ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከጸረ ሻብያ ቡድኖች ጋር አምባሳደሩ በአሜሪካ እንደመከሩም ታውቋል፡፡
የቀድሞው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ቲቦር ናጂ የአስመራውን መንግስት በተመለከተ አነጋጋሪ አስተያየቶችን መስጠት ቀጥለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ከጸረ ሸብያ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ እያሳደጉ ይገኛል፡፡ አምባሳደሩ በትናንትናው እለትም ከብርጌድ ንሓምዱ የሰማያዊ ማዕበል ንቅናቄ መሪዎች ጋር በአሜሪካ መወያየታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከሰማያዊ ማእበል ንቅናቄ መሪዎች ጋር መወያየታቸውን በገለጹበት የኤክስ ልጥፋቸው ላይ፣ ‹‹ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዚህ ቀደም እንደነበሩ አምባገነኖች ሁሉ ከአገር ይኮበልላሉ›› ብለዋል፡፡ አምባሳደሩ ከዚህ ቀደም በአለም ላይ ያለፉ እንደ መንግስቱ ኃይለማሪያም እናጋዳፊ ያሉ አምባገነን መሪዎችን በመጥቀስ የኢሳያስ አፈወርቂም እጣ ከዚህ የሚለይ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮ ኤርትራ መሀል ውጥረቱ እጅግ መባባሱን ተከትሎ ውጊያ የሚነሳ ከሆነ ጦርነቱ ሁለት ውጤት ሊነኖረው እንደሚችል ተንታኞች በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡ አንደኛው ኢትዮጵያ አሰብን የመቆጣጠሯ ነገር ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከስልጣን የመወገድ ጉዳይ ነው፡፡ ከወራቶች በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ የነበሩት ጀነራል አበበ ተክለሀይማኖት በሰጡት አንድ አስተያት፣ ጦርነቱ የሚነሳ ከሆነ በርግጥም የሻብያ ግብአተ መሬት የሚፈጸምበት ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠው ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ አምባሳደር ቲቦር ናጂ የቀድሞው አምባገነን መሪዎችን በመጥቀስ የኢሳያስ እጣ ፈንታም ከዚህ የሚለይ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡(andafta)

❤46👍12👎10🤔1
ትራምፕ ለፑቲን ፡ “ይህንን ከንቱ ጦርነት ለማስቆም በቡዳፔስት እንገናኛለን።”
የዩናይትድ ስቴትስ እና የሩሲያ ፕሬዚዳንቶች ዶናልድ ትራምፕ እና ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን የሰላም ድርድር ለማራመድ ቡዳፔስት ውስጥ፣ ገና ባልተወሰነ ቀን፣ እንደሚገናኙ ይጠበቃል። መግለጫው የተሰጠው ኋይት ሀውስ “አዎንታዊ እና ውጤታማ” ሲል በገለጸው፣ ከሁለት ሰዓታት በላይ በፈጀው የመሪዎቹ የስልክ ውይይት ማብቂያ ላይ፣ በትራምፕ እራሳቸው በትሩዝ ሶሻል በኩል ነው።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በስልክ ወይይቱ ወቅት “ትልቅ መሻሻል” እንደነበረ የተናገሩ ቢሆንም የተለየ ዝርዝር ነገር አላቀረቡም።
በተጨማሪም በመካከለኛው ምስራቅ የተደረገው የእርቅ ስምምነት ይህንን ሌላኛው “ከንቱ” ግጭት ለማስቆም ቀላል እንደሚያደርግ አስረግጠው ተናግረዋል።
ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ በሁለቱ መሪዎች መካከል ስምንተኛው የሆነው ይህ የስልክ ውይይት፣ ትራምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ከሚኖራቸው የሞላላው ቢሮ ስብሰባ ዋዜማ ላይ የሚደረግ ሲሆን፣ ስብሰባው በፌዴሬሽኑ ግዛት ውስጥ ጠልቀው መምታት የሚችሉ ረጅም ርቀት ያላቸው ቶማሆክ ሚሳኤሎች ለኪየቭ ሊሰጡ ስለመቻላቸው ትኩረት ያደርጋል።
ፑቲን፣ የዲፕሎማሲ አማካሪያቸው ዩሪ ኡሻኮቭ እንዳስታወቁት፣ እነዚህን መሳሪያዎች መላክ በምድር ላይ ያለውን ሁኔታ እንደማይለውጥ አስጠንቅቀዋል፤ በምድር ላይ “ሞስኮ በጠቅላላው የግንኙነት መስመር ላይ ተነሳሽነቱን እንደያዘች” ቢሆንም፣ ይህ ግን የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን እና፣ በዚህም ምክንያት፣ ጦርነቱን ለማቆም የሚደረገውን ድርድር ይጎዳል ብለዋል።

❤15👍4
Sheger Press️️
Photo
ቃላተ ወንጌሉን የመኖር አንዱ መንገድ
“በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣ በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣ በራብ ደርቀው ያልቃሉ።” ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ፣ በሰቆቃወ ኤርምያስ 4÷9፡፡ በገዳማዊው ሕይወት በበረሃው ሀሩር ስለ ጽድቅ የሚራቡ እናቶችና አባቶች የዕለት ጉርሳቸውን ሲያጡ ማየት ደግሞ ልብ ይሰብራል፡፡
ረሀብ ገዝግዞ የሚገድል በጣርና በጋር ሕይወትን የሚነጥቅ ኃያል ጠላት ነው፤ ሰይፍ ግን አንድ ጊዜ ይገላግላልና ታላቁ ነቢይ ይህን ብሏል፡፡ በረሀብ ላይ ውሃ ጥም ሲጨመር ደግሞ ሰውነት መቋቋም ይሳነዋል፡፡ ከስድስቱ ቃላተ ወንጌልም ሁለቱ “ብራብ አብልታችሁኛል፣ ብጠማ አጠጥታችሁኛል፣” የሚሉ ናቸው፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምሥራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያን በረሃብና በውሃ ጥም ውስጥ ታላቅ መንፈሳዊና ተጋድሎ እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህን ለሀገር ሰላምና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽናት የሚጸልዩ ገዳማውያን መደገፍ ቃላተ ወንጌሉን የመኖር አንዱ መንገድ ነው፡፡
ጋን በጠጠር እንዲደገፍ እንዲሁ ደግሞ በመጪው ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም በሚሊኒም አዳራሽ ከ 5፡00 ጀምሮ በተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ የተዘጋጀውን ትኬት በአንድ መቶ ብር ብቻ በመግዛት ወዳጅ ዘመዶቻችንም በመጋበዝ የድርሻችንን እናበርክት የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፡፡ በዕለቱ የሚቀርቡ የእደ ጥበብ ሥራዎቻችንም እየገዛን አብሮነታችንን እናሳያቸው፡፡
አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444

❤21
በጃፓን የክፍያ መሰብሰቢያ ሲስተም ብልሽት ወቅት ነፃ የተጓዙ 24,000 አሽከርካሪዎች ክፍያቸውን በፈቃደኝነት ከፈሉ
በጃፓን የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መሰብሰቢያ (ETC) ሥርዓት ባልተጠበቀ ሁኔታ ለ38 ሰዓታት ያህል አገልግሎት መስጠት ሲያቆም፣ የክፍያ መግቢያ በሮች ለነፃ መተላለፊያ ተከፍተው ነበር። በሌሎች አገራት ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ሊያስከትል ይችል የነበረ ቢሆንም፣ በጃፓን ግን ነገሩ የተለየ ነበር።
ችግሩ ከተስተካከለ በኋላ ከ24,000 በላይ የሚሆኑ አሽከርካሪዎች በቀላሉ ከመክፈል መሸሽ ይችሉ የነበረ ቢሆንም፣ በፈቃደኝነት የየራሳቸውን የክፍያ መጠን በመስመር ላይ አስገብተው ከፍለዋል።
ይህ የዜጎች የሀገር አቀፍ ታማኝነት ተግባር በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ መነጋገሪያ ርዕስ በመሆን፣ የጃፓንን ጥልቅ ሥር የሰደደ ሥነ ምግባርና ማኅበራዊ ኃላፊነት ምልክት ሆኗል። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደተናገሩት፣ ይህ ክስተት ጃፓን ለክብር እና ለታማኝነት የሰጠችውን ከፍተኛ ባህላዊ ትኩረት ያንፀባርቃል፤ እነዚህ እሴቶች ያለምንም ማስገደድ ኅብረተሰቡን በአንድነት የሚይዙ ናቸው።
በተጨማሪም ጠንካራ የዜግነት ሥነ ምግባር እንዴት ወደ የጋራ ተጠያቂነት እንደሚመራ የሚያጎላ ሲሆን፣ ይህም በርካታ አገራት ሊያሳኩት የሚፈልጉት ነገር ነው። ዓለም በአቋራጭ መንገዶችና በሕግ ክፍተቶች በሚመራበት በዚህ ዘመን፣ የጃፓን አሽከርካሪዎች ታማኝነት የሚገለጸው መታየት ላይ ሳይሆን፣ ማንም በማያይበት ጊዜ እንኳን ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ላይ መሆኑን ለሁሉም አስታውሰዋል።
Via: መናኸሪያ ሬዲዮ

❤39👍5🤔1
መረጃ ‼️
በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት ጥረት እያደረኩ ነው ሲሉ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡
የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽ ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ያለውን ግጭት ለማስቆም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
በክልሉ ያለው ግጭት ሀብት፤ ንብረትና የሰው ነፍስ ላይ ውድመት እያደረሰ ነው፤ ግጭቱ እያደረሰ ያለውን ውድመት በማስቆም የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ግጭቱን በድርድር ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡
ግጭቱን በድርድር ለማስቆም እየተሰራ ያለው ስራ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት አመራሩን ከላይ እስከ ታች ድረስ የማደራጀት፤ የጸጥታ ኃይሉ ላይ ሪፎርም የመስራት፤ የሰላም ጥሪ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።(adnafta)

❤20👎19
"የኢንዱስትሪ መንደር" ከተባለችው ኮምቦልቻ የወንዝ ውሃ በፋብሪካ ኬሚካል ወደ መርዝነት ተቀይሯል!
ኮምቦልቻ፣ ኢትዮጵያ— የ"ኢንዱስትሪ መንደር" ተብላ የምትሞካሸው ኮምቦልቻ ከተማ ውስጥ ካሉ ፋብሪካዎች የሚለቀቅ አደገኛ ኬሚካሎችን የያዘ ተረፈ ምርት፣ የወንዙን ውሃ ደም የመሰለ ቀለም እንዲይዝ በማድረግ የአካባቢውን ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል።
የኮምቦልቻና የቃሉ አርሶአደሮች በኢንቨስትመንት ስም መሬታቸውን በዝቅተኛ ዋጋ ከተቀሙ በኋላ፣ የተረፋቸውንም እርሻ ከዚህ ከባድ የኬሚካል ፍሳሽ የሚመጣ መርዝ ተንከባክበው እንዳያለሙት ስጋት ላይ ወድቀዋል።
ይህ ደም የመሰለ ፈሳሽ ወንዝ የተረፈ ምርት የኮምቦልቻ እና የቃሉ አርሶአደሮች የሰብል ምርትንና የመሬቱን ለምነት በመግደል ላይ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎችና አርሶአደሮች ይህ መርዝ የአካባቢ ስነ-ምህዳር ላይ እያሳደረ ያለውን ከባድ ተፅዕኖ ገልጸዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ድምጹን ቢያሰማም፣ "የራሱን ምቾት የሚጠብቅ አመራር እንጂ ለሕዝብ ደህንነት ደንታ የሌለው ነው" በማለት በሕዝብ ደህንነት ጉዳይ ላይ የኃላፊነት ስሜት የጎደለው አመራር መኖሩን ይወተወታሉ። እስካሁን ለቅሬታቸው የሚሰማ ኃላፊ ማጣታቸው ነገሩን ይበልጥ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
ጥሪ ለሚመለከተው አካል!
የኮምቦልቻ እና የአካባቢው ወንዞች በዚህ አሰቃቂ የፋብሪካ ኬሚካል ተረፈ ምርት መበከሉ የአርሶአደሩን ኑሮ ከመናድ ባሻገር፣ ለወደፊት የጤና ቀውስና የአካባቢ ጥፋት ሊዳርግ ይችላል።
ፌዴራልና ክልላዊ የመንግስት አካላት ለሕዝብ ደህንነትና ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ በመስጠት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።
Via አሊ ወሎ

❤19🤔3👍1
የ 4 ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ ፤ የ 2 ሚሊዮን ብር ሎተሪ አሸነፉ
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ዓለምፀሐይ በላቸው በ39ኛ ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛ ዕጣ የ2 ሚሊየን ብር / ሁለት ሚሊየን ብር / ዕድለኛ በመሆን ቼካቸውን ተረከቡ ፡፡
ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ባለትዳርና የ4ልጆች እናት ሲሆኑ በደረሳቸውም ገንዘብ ወደንግድ ለመሰማራት እንዳሰቡ ተናግረዋል፡፡

👍23❤3🥰2👏2
አረቄ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ሊዘጉ ነው‼️
ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም. (E.C.) : ቢንጎ እና አረቄ ቤቶች በአዲስ አበባ አይኖሩም ተባለ! አስተዳደሩ ቆራጥ ውሳኔ አስተላለፈ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የቢንጎ ማጫወቻ እና የአረቄ መሸጫ ቤቶችን በተመለከተ አስቸኳይ እና ቆራጥ ውሳኔ አሳለፈ።
ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አንድም የቢንጎ ማጫወቻም ሆነ የአረቄ መሸጫ ቤት መኖር የለበትም!
የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት፦
"እነዚህ ቤቶች (የቢንጎ ማጫወቻ እና በየመንደሩ ያሉ አረቄ ቤቶች) የከተማው ወንጀል መፈልፈያ ቦታዎች ናቸው።"
መመሪያውም ቤቶቹ የወንጀል ምክንያት በመሆናቸው ምክንያት ከከተማው እንዲጠፉ ታስቦ ነው።
ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ መመሪያ ተሰጥቶ እንደነበር ቢታወቅም፣ ቤቶቹ አሁንም በስራ ላይ መሆናቸው ታውቋል። አስተዳደሩ ግን አሁን ባጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባን ከእነዚህ ቤቶች ነፃ ያደርጋታል ብሏል።
ትዕዛዙን ላለማስፈፀም የሚከፈል ዋጋ፦
ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ትዕዛዙን ተፈጻሚ የማያደርጉ ኃላፊዎች ላይም ማስጠንቀቂያ "ይህንን ማስፈፀም ያልቻሉ ኃላፊዎችም በቦታቸው አይቀጥሉም!"
Via ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

❤41👏9👎4🤯1