Telegram Web Link
የ12 አመት የእንጀራ ልጁን ደጋግሞ የደፈረው ግለሰብ በ25 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ በከሚሴ ከተማ በመድፈር ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ በ25 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን ገለፀ።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ እንድሪስ አሊ እንደገለፁት በቀን 07/01/2018 በዋለው ችሎት ተከሳሽ መኪን የሱፍ ሙህዬ የተባለ ግለሰብ የከሚሴ ከተማ የ04 ቀበሌ ነዋሪ የሆነው እስከ ሚታወቅበት ቀን 28/01/2018 አ.ም ከቀኑ 9:00 ድረስ የግል ተበዳይ የእንጀራ ልጁ የሆነችውን ራህመት አሊ ጫኔ እድሜዋ 12 አመት የሆችውን በተደጋጋሚ በመድፈር ክብረ ንፅህናዋን በመውሰድና የአራት ወር ነብሰጡር እንድትሆን ማድረጉን ገልፀዋል።

በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦ በከተማው ፓሊስ ምርመራ ተጣርቶ መዝገቡ የደረሰው የከሚሴ ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት እድሜዋ ከ12 የሆናት ህፃን አስገድዶ መድፈር ወንጀል 1996 በወጣው በወንጀል መቅጫ ህግ መሰረት ለደዋ ጨፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ በቀን 07/01/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ላይ ተከሳሹ ወንጀለኛ ሁኖ በመገኘቱ ተከሳሽን ያርማል ሌሎቹን ያስተምራል በማለት የ 25 አመት ፅኑ እስራት እንዲፈረድበት መደረጉን የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ ሀላፊ ገልፀዋል።

@sheger_press
@sheger_press
🤬1815😢3
ቅጣት‼️

በጋምቤላ ክልል ዲማ ከተማ ከባህል ውጪ በሆነ አለባበስ ምሽት ላይ ዳንስ ቤት የተገኙ ሴቶች የገንዘብ ቅጣት መቀጣታቸውን ተሰማ።

ከማህበረሰቡ ባህል ያፈነገጠ አለባበስ ለብሰው ዳንስ ቤት የተገኙ 13 ሴቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በገንዘብ እንዲቀጡ መደረጉን የዲማ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል ::

የዲማ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ኚካሃ አኳይ ለወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን እንደገለፁት ሴቶቹ ሰሞኑን በዲማ ከተማ ጨለማን ተገን በማድረግ ከባህል ውጪ አለባበስ ለብሰው ከምሽቱ 4:ዐዐ ላይ ዳንስ ቤት በመገኘታቸው ጽ/ቤቱ ከፖሊስ ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ውሎው እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር በአጠቃላይ 65 ሺህ ብር እንዲቀጡ መደረጉን ተናግሯል ::

በመጨረሻም ጽህፈት ቤቱ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የጀመረው የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

@sheger_press
@sheger_press
23👍9🤔4👏3
ለክልል አቃቢ ህጎች ከተላከው አዲሱ የደመወዝ ስኬል ውስጥ የአፋር፣የሲዳማ፣የቤንሻንጉል ጉሙዝ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዓቃቤ ሕግ የደመወዝ ስኬልን ከላይ አያይዘነዋል።

@sheger_press
@sheger_press
6👍5
💥🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿Everton visits Etihad

City has lost to the Toffees just once in the last 18 meetings, but now the teams are neck and neck in the table.

Bet on Premier League and catch every moment with Melbet!

⬇️
Promo - PRESSSH
Link - https://bit.ly/423Tlea
4
በወላይታ ዞን፣ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በአደጋ ምክንያት የደረሰ ጉዳት!

በወላይታ ዞን፣ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ፣ በሌ አዋሳ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ቁልቁለት መንገድ ላይ አደጋ መድረሱ ተዘግቧል።

ነዳጅ የጫነ አንድ ተሽከርካሪ ከነተሳቢው ሲጓዝ፣ ብሬክ (ፍሬን) ከቁጥጥር ውጭ በመውጣቱ ምክንያት መንገድ ስቶ ወጥቷል።

ተሽከርካሪው በከፊል መኖሪያ ቤት ደርምሶ የወደቀ ሲሆን፣ በሰዎች ሕይወት ላይ ከባድ ጉዳት ሳይደርስ መቅረቱ ታውቋል።

ሆኖም በደረሰው አደጋ በሹፌሩ እና በአንዲት ትንሽ ህፃን ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል።

ለአሽከርካሪዎች የተላለፈ መልዕክት፦

ወደዚህ አካባቢ የምትጓዙ አሽከርካሪዎች!

መንገዱ ከባድ ቁልቁለት የሚጠብቅ በመሆኑ፣ ሲያሽከረክሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

@sheger_press
@sheger_press
13😢8🤔1🙏1
7
Sheger Press️️
Photo
የቅድስት ድንግል ማርያም ስደት እየታሰበ ከቅዳሜ ምሽት አራት ሰዓት ጀምሮ ካህናት አባቶች በማሕሌተ ጽጌው እመቤታችን ትመሰገናለች፡፡

የዓለሙን ሁሉ ፈጣሪ ይዛ በበረሃው የደረሰባት መከራ የገጠማት ውሃ ጥምና ረሃብ ይዘከራል፡፡

ልጇን ይዛ የተሰደደችው ንግስተ ሰማያት ወምድር የደረሰባትን መከራ አብነት ሆኗቸው ነፍሳቸውን ለማዳን ስጋቸውን ለክርስቶስ ፍቅር በማስገዛት በረሃብና በውሃ ጥም የሚቸገሩትን ገዳማውያን ለማሰብ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ከቶ ከየት ይመጣል?

በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ያሉ ከአንድ መቶ በላይ ገዳማውያን ስጋዊና መንፈሳዊ ውጊያ በበረታበት አካባቢ በብዙ መከራ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡

ይህን መከራቸውን ለማስታገስ፣ ውሃ ጥማቸውን ለመቁረጥ፣ ረሃባቸውንም ለማስታገስ የእመቤታችን መከራ በሚታሰብበት ዘመነ ጽጌ ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ከ 5፡00 ጀምሮ  በሜሊኒየም አዳራሽ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል፡፡ በአንድ መቶ ብር ብቻ ቲኬቱን በመግዛት የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፡፡
አዘጋጅ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444
31
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሲአርኤስ እና ከተመድ ኤጀንሲዎች ጋር ተወያየ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ (CRS) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ለተፈናቃይ ማህበረሰቦች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን እንዲያፋጥኑ እና ለዘላቂ መፍትሄዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርቧል።

አስተዳደሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው በሰላም እንዲመለሱ እና የትግራይን የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጧል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ፣ ሲአርኤስ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተጋላጭ ማኅበረሰቦች እና ወደ ሱዳን ለሄዱ ስደተኞች የሚሰጠውን የአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

በተያያዘ ውይይት፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ የተፈናቀሉ ሰዎችን በሰላም ወደ ቀዬአቸው መመለስና የትግራይ ክልል ሉዓላዊነት መጠበቅ ለአስተዳደሩ ቀዳሚ ተግባራት ሆነው እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል።

እንዲሁም የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተቻላቸውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
12👎3
👍21
Sheger Press️️
Photo
‹‹ወታደሩ ኃይል ትግስቱ ተሟጧል›› አምባሳደሩ

የትግራይ ታጣቂዎች ሰሞንኛ አመጽ ተከትሎ በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ ትኩሳት እጅግ ጨምሯል፡፡ መንግስት አስተያየት ለመስጠት በተቆጠበበት በዚህ የሰራዊት አመጽ፤ ብዙ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ የሰጡ አስተያት የሚጠቀስ ነው፡፡

በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደዴፎ፣ በህውሓት ታጣቂዎችና በድርጅቱ አመራር መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ አመጽ መቀስቀሱ ድርጅቱን ሊበትነው ተቃርቧል ብለዋል፡፡ አምባሳደሩ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ የትግራይ ህዝብም ሆነ የድርጅቱ ታጣቂ ኃይል በህወሓት አመራር ላይ "ትዕግሥትና ተስፋው ተሟጧል" ብለዋል። እንደ አቶ ሱሌይማን ገለጻ፣ ለዓመታት የድርጅቱ የጀርባ አጥንት የነበረው የታጠቀው ኃይል አሁን ላይ ለአመራሩ ጀርባውን በመስጠቱ የድርጅቱ "የመጨረሻ ምሽግ እየተደረመሰ" ይገኛል።

"ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ናቸው እያሉ ሲያጭበረብሩ ኖረዋል፤ አሁን ግን ከታጣቂዎቻቸው ጋር እንኳ አንድ መሆን አቅቷቸው እርቃናቸውን ቀርተዋል" ያሉት አቶ ሱሌይማን፣ የተቀሰቀሰው አመጽ ተጨማሪ የህይወት መስዋዕትነት ከማስከተሉ በፊት የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ለፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ መሆን አለባቸው ሲሉ በመግለጫቸው አሳስበዋል።

ትግራይ እንደ ኤርታሌ በሚፋጅ የፖለቲካ ትኩሳት እየተናጠች ትገኛለች፡፡ ከዚህ ትኩሳት ጀርባ በርካታ የውጪ ኃይሎ እጅ መኖር ደግሞ ትኩሳቱን እጅግ ያባባሰ እና የከፋ አድርጎታል፡፡ በተለይም ካለፈው ሰኞ አንስቶ የቲዲኤፍ ጦር ወታደሮች ማመጻቸውን ተከትሎ የክልሉ ፖለቲካ ወዴት እያመራ ነው የሚለው ጥያቄ በጉልህ እንዲነሳ አድርጎታል፡፡ ከዚህ የጦር አመጽ ጀርባ ሶስት አካላት ስማቸው ሲነሳ ነበር፡፡ የፈዴራሉ መንግስት፣ እነ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ሻብያ ናቸው፡፡ ህውሓት ከዚህ አመጽ ጀርባ የፌዴራል መንግስቱ እና ከሃዲ ሲል የጠራቸውን እነጌታቸው ረዳን ተጠያቂ ሲያደርግ፤ ባንፃሩ በሌላ ወገን ያሉት ደግሞ ሻብያን ተጠያቂ ሲያደርጉ ለመመልከት ተችሏል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
27
ፖርቱጋል የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ በፓርላማ ውድቅ አደረገች‼️

የፖርቱጋል ፓርላማ ሙስሲም ሴቶች እንዳይሸፈኑ በሕግ ከለከለች።
አንዲት ሴት ተሳስታ ተሸፋፍና ከተገኘች 4,670 የአሜሪካ ዶላር ትቀጣለች።

ከዚህ በተጫማሪ አንድ ሙስሊም ወንድ ሚስቱ ተሸፋፍና ከተገኘች በሶስት አመት እስራት እንደሚቀጣ በህጉ ላይ ተደንግጓል።

በአውሮፓ ሀገራት ፈረንሣይ፣ ዴንማርክ፣ ቤልጄም፣አውስትራሊያ እና ሌሎች ሀገራት ሙስሊም ሴቶች እንዳይሸፋፈኑ የሚከለክል ተመሳሳይ ህግ ያላቸው ሲሆን ፖርቹጋል ሙስሊም ሴቶች እንዳይሸፋፈኑ በመከልከል 20ኛዋ የአውሮፓ ሀገር ሆናለች።

@sheger_press
@sheger_press
👍3925👎16
ደመወዝ አልተከፈለንም‼️

በአማራ ክልል የፀጥታ ችግር ባለባቸው ምስራቅ ጎጃም ዞን 14 ያህል ወረዳዎች እንዲሁም በሰሜን ወሎ የተወሰኑ ወረዳዎች መምህራን የመስከረም ወር ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ገልፀውልናል።

መምህራኑ የደመወዝ ጥያቄ ሲያቀርቡ ደመወዝ እንዲከፈላችሁ ወደ ስራ ግቡ እንደተባሉና ወደ ስራ ለመግባት ደግሞ ለደህንነታቸው ስጋት እንደገባቸው ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ ይታወቃል።

@sheger_press
@sheger_press
17🤔4😢3
2025/10/23 16:31:46
Back to Top
HTML Embed Code: