Telegram Web Link
ረመዳን 19

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ድል ማለት አኼራ ነው። አላህ ሆይ በሰዎች ፊት ትልቅ መስሎ ባንተ ፊት ከመዋረድ በአንተ እጠበቃለሁ በሉት! 

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዳን 20

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት እየገቡ ነው። አላህ ሆይ በጤና ያለእንከን ቀጣዮቹን ቀናት ፆመን የምንጠቀም አድርገን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዳን 21

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

የአላህ ተውፊቅ ባልኖረ መልካም የተባለ ባልገጠመን ነበር። አላህ ሆይ የመልካም ነገርን ሁሉ ተውፊቅ ስጠን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
3
ረመዳን 22

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

የነቢን ﷺ ምድር አልረገጥነውም። የረገጡትም ናፍቀዋል ደግመው! ያ ረብ ሀጅና ኡምራን ወፍቀን አንዴ ብቻም ሳይሆን ደጋግመህ ከጥፍጥናው አቅምሰን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዳን 23

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ለይለተል ቀድርን የተገጠመ ሰው በእርግጥ 83 ዓመት በላጭ የሆነች ለሊትን ተገጥሟል። የአንድ ቀን ልፋቱ እንዲያ ይታጠፋል። አንተ የለሊቷ ጌታ ሆይ ይችን የመወሰኛ ለሊት ግጠመን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ረመዳን ተገባደደ ! የረመዳን መገባደድ አቅል ላለው ሰው ትልቅ ትምህርት በውስጡ ይዟል ።
ረመዳን 24

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

የጀነት ሰዎች የጀነት ፀጋ እያጣጣሙ ከዚህ በላይ ደስታ የለም ብለው ሲያስቡ አላህ መለኮታዊ ፊቱን ይገልጥላቸዋል። ፊቱን ማየታቸው ከዚያ በፊት ከተሰጣቸው ሁሉ በላይ ያስደስታቸዋል። አላህ ሆይ በጀነት የተከበረ ፊትህን ያለማቋረጥ ከሚያዩት መሀል አድርገን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዳን 25

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ረመዳኑ እየተገባደደ ነው። አላህ ሆይ የሞከርናትን ትንሽ ከነእንከኗ ተቀበለን። ላጎደልነው ሁሉ ይቅር በለን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዳን 26

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

አላህ ሆይ የአይን ማረፊያ የሆኑ ልጆችን ስጠን! በእኛ መሞት ስራችን እንዳይቋረጥ የሚያደርጉ ደጋግ ልጆችን ወፍቀን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዳን 27

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

አላህ ሆይ ጤነኛ፣ ሰላም፣ አፊያ ሆነን ረመዳንን መላልስብን! ከበረከቱም በውስጡ ካለው መልካምም ሁሉ አጣቅመን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
👍2
ረመዷን - 28

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ሰው ዘንድ በአደራ ልናስቀምጣቸው ከምንችላቸው ነገሮች አንዱ ዱዓ ነው። አንዳንዴ በራስ አቅም መወጣት የማንችላቸውን ነገሮች የሰው ኃይል እንጨምርበታለን። እኛ አሳምረን አንፈጽመውም በለን የተጠራጠርነውን ጉዳይ መልካም ወንድም እህትን አግዙን እንላለን ።
ወዳጆቼ
በራሳችን ዱዓ ያላገኘነውን በረከት በደጋግ ወንድምና እህቶች ዱዓ ልናገኝ እንችላለን ። ለዚህ ነው ዱዓ አድርጉልን ማለት የምናበዛው።
እኔ ዘንድ ዱዓ ያኖራችሁ ሁሉ ቢስሚላህ አላህ የልባችሁን መሻት ይሙላው።

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
👍5
ረመዷን - 29

የቁርአን ኺትሚያ ምሽት።

ረመዷን ሊወጣ ነው። አቀባበሉ ያልሆነለት አሸኛኘቱን ያሳምር።

ዐፉ በሉን ወዳጆች ።

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
👍51
عيد مبارك እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል_ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🌙

ዒድ ሙባረክ ❤️
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

የወንጀሌ ብዛት  ቁጥር ስፍር የለው
መልካም ስራ የለኝ  የምተማመነው

በማይጠቅምበት ቀን  ወዳጅ ከጓደኛ
በእዝነትህ ካልሆነ  የለኝም መዳኛ

ሰዎች ሲገምቱኝ  መልካም እውነተኛ
እኔ ግን ሌላ ነኝ  ምስኪን ወንጀለኛ

ጌታዬ ሆይ ማረኝ  ድክመቴን ዕይና
መዳኛው ተስፋዬ  ምህረትህ ነው


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀
3
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

«ከመቃብር ግባ!!»
---------------------

መከራ ምን ቢከብድ ችግር ቢፈረጥም፡
በዱንያዊ ጥቅም ህሌና አይሸጥም፡
ምን ብታብለጨልጭ ይህች ጠፊዋ አለም፡
ለርሷ ባሪያ መሆን ትክክል አይደለም፡

ወርቅህን በብረት አልማዝክን በጠጠር፡
የምትለውጥ እርኩስ ሆነህ አትፈጠር፡
ነቄ ሁን እባክህ በህይወትህ ሰጠር፡

ለስልጣን ለዝና ሁሌ ከመጓጓት፡
ዋጋ ክፈሉና ሐቅን ከፍ አድርጓት፡
ከወተት በስተፊት አይገኝም አጓት፡

ሁለት ፊት አታሳይ ወዳጄ ልምከርህ፡
የእንሰሳ ሳይሆን የሰው ልብ ይኑርህ፡
የምትኖረው ህይወት ይሁን ንግግርህ፡

ነፍስህን አጥግበህ ስጋህ ግን ተርባ፡
ውስጥህ ሰላም ሰፍኖ ፈክተህ እንደ አበባ፡
ሰው ሰው እየሸተትክ ከመቃብር ግባ!!!

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀
2👍1
🟡 በዩንቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የህክምና አስተማሪ ነው። ከእጁ የማትለይ፣ ሲበዛ የሚወዳት ሰዓት አለችው። መልኳም ሆነ ይዘቷ የሴት ነው። ሊያስተምር እጁን ሲያወራጭ ተማሪዎች ይጠቋቆሙበታል። ከዕለታት በአንዱ ቀን ታዲያ በአደጋ ምክንያት የተለየችው የልጁ ሰዓት መሆኑን ከጓደኛው አንደበት ሰሙ። ለእሷ ካለው የገዘፈ ውዴታ የተነሳ ሰዓቷን ከእጁ ሊያወልቅ አልተቻለውም።

(ሊያወሩላቸው የሚደክሙ፣ ሊገልጿቸው የሚከብዱ ንፁህ ልቦች)

🟡 ረጅም ርቀት በእግሯ ከአባቷ ጋር ተጉዛ የምትወደውን አይስክሬም አባት ገዝቶ ሲሰጣት በግንባሯ ሱጁድ ወረደች። አይስክሬም ሻጩ በአግራሞት እየተመለከታት እስክትነሳ ጠብቆ ጠየቃት። ሱጁድ የወረድሽበት ምክንያት ምንድነው?! አላት። እናቷ ስትደሰት እንዲህ እንደምታረግ ነገረችው::

(የመልካም ተርቢያ ውጤት ይሉሀል ይህ ነው)

🟡 በአረጋውያን መጦርያ ማዕከል የምትገኘውን ሚስታቸውን ለመዘየር ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው እርሷ ዘንድ ይሰየማሉ። ከጎኗ ተቀምጠው የሆድ ሆዳቸውን ያወጋሉ። ከአስር ዓመታት በፊት የማስታወስ ችሎታዋን አጥታ ባሏንም ሆነ ልጆቿን አታስታውስም ነበርና
"እየተመላለሱ ለምን ይለፋሉ?! ማንነትዎን ለማታውቅ ሴት ስለምን ብለው ይቸገራሉ?!" በማለት ጠየቋቸው። አዛውንቱም ፈገግ አሉና "እኔ ግን ባለቤቴ የህይወት አጋሬና ጓደኛዬ እንደሆነች አውቃለሁ" በማለት መለሱ።

(ከዚህ ወዲያ ስለየትኛው ንፁህ ፍቅር ነው የምታወሩት)

🟡 በቤትህና በሥራ ቦታህ መካከል ያለው ርቀት ምን ያህል ነው ተብሎ ተጠየቀ
"በመኪና ከሆነ 500 ተስቢህና ተህሊል። በእግሬ ከሆነ ደግሞ 1200 ተህሚድና ኢስቲግፋር የሚያዘክር ወቅት ያደርሰኛል" ሲል መለሰ።

(አላህን ሳያስታውሱ የማያመሹ ልቦች)

🟡  አንድ አዛውንት ተጠየቁ "ንፁህ የመጠጥ ውሀ በቤትዎ ኖሮ ለምን ወቅፍ የተደረገ የመስጂድን የቧንቧ ውሃ መጎንጨት ፈለጉ?!" ተባሉ።
"ለመስጂዱ የወቀፉት ሰዎች አጅር ያገኙ ዘንድ" ሲሉ መለሱ።

(መልካም ነገርን ለራሳቸው እንደሚወዱት ለሌሎችም የሚወዱ ንፁህ ልቦች)

የምተርክላችሁ ስለ ቅን ልቦች
የማወጋችሁም ስለ እነርሱ ነው
5👍4
{وَعَدَ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ وَرِضْوَانٌ مِنَ اللَّهِ أَكْبَرُ ذَلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ}
👍1
أصبحنا وأصبح الملك لله والحمد لله ، لا إله إلا الله وحده لا شريك له ، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير . ربي أسألك خير ما في هذا اليوم وخير ما بعده . وأعوذ بك من شر ما في هذا اليوم وشر ما بعده ربي أعوذ بك من الكسل وسوء الكبر ، ربي أعوذ بك من عذاب في النار وعذاب في القبر
👍1
{ أَوَلَا یَرَوۡنَ أَنَّهُمۡ یُفۡتَنُونَ فِی كُلِّ عَامࣲ مَّرَّةً أَوۡ مَرَّتَیۡنِ ثُمَّ لَا یَتُوبُونَ وَلَا هُمۡ یَذَّكَّرُونَ }

በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መኾናቸውን አያዩምን ከዚያም አይጸጸቱምን እነሱም አይገሰጹምን
[Surah At-Tawbah: 126]
👍1
2025/10/28 10:29:56
Back to Top
HTML Embed Code: