Telegram Web Link
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

አውፍ በሉኝ

መቼም ሰው ነኝና ድንገት ተሳስቼ
በማወቅም ሆነ ያለ እውቀት ዘንግቼ
ስሜቴ ገፋፍቶኝ ድንበር ተላልፌ
አዛ ያረኳችሁ በምላሴ በአፌ
ስማችሁን አንስቼ በሌላችሁበት
የወነጀልኳችሁ በሀሰት በሀሜት
አውፍ በሉኝና ልቤ ትረጋጋ
ከራህመቱ እንዳርቅ ከረመዳን ፀጋ
ትንሽቱም ትሁን ትልቁ ስህተቴ
ሚዛን እንዳትደፋ ነገ በአኼራ ቤቴ
በፆም እንዲታበስ እንዲረግፍ ወንጀሌ
ትንሽ ትልቅ ሳልል እገሊት እገሌ
ያስቀየምኩት ሁሉ አውቄም ሳላውቅ
የተሸከምኩት ወንጀል ያለብኝ የእሱ የእሷ ሀቅ
ለአላህ ስትሉ አውፍ በሉኝ
እኔ አውፍ ብያለሁ K ነኝ

በዱአ አትርሱኝ ኢንሻአላህ🤲🤲

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

🌙አህለን ያረመዷን🌙

አህለን ያረመዷን የፍጥረት ስጦታ
ከልቁን አስታራቂ ከሀያሉ ጌታ
ሁሌም ተናፋቂ ሁሌም ተጠባቂ
አንተ ታላቁ ወር ከወንጀል አራቂ
ልቦችን በቁርአን ፍቅር አሸብራቂ
ከመስጂድ የራቀን የጠፋን ሰብሳቢ
አህለን ያረመዷን የፈረሰን ገንቢ
አህለንቢከ ብለን ተነስተን ከቦታ
ከዱንያ ፍቅር ወተን ከትዝታ
ያለፈ አመት ስህተት ላይደገም ለአፍታ
ከጌታችን እዝነት ከጅለን መሀርታ
ታጥቀን ተነስተናል ያለንን ሰውተን
አንተ ታላቁ ወር አህለን ያረመዷን
አንተ ታላቁ ወር አህለን ያረመዷን

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#ማረኝ

ራቂው ያልከኝን በድፍረት ሰርቼ
ቅረቢው ያልከኝን ሳልሰራ ዘንግቼ
ነፍሴን በድያለው ማረኝ ያረበና
ምህረት ለጠየቀ ተቀባይ ነህና
ከላይ ለሚያየኝ ሰው ፃድቅ እየመሰልኩ
ከእነሱ ዞር ስል አንተኑ እያመፅኩ
ኖሬያለው በከንቱ ሁልጊዜ ሳጠፋ
አላህ ይምረኛል እያልኩኝ በተስፋ

ግን ለምን ይሆን?
ሁልጊዜ እያስታወስኩ ገፉሩ ረሂምን
ለምን እረሳሁኝ ሸዲዱል ኢቃብን
በወንጀል ታስሬ ተዘፍቄ እያለው
አዝራኢል ቢመጣ ምንድነው ምሆነው
ትንሽ ቆይተክና ገናኮ አልቶበትኩም
ብዬ ብለምነው መቼም አይሰማኝም
አጀል ከቀረበ የለም ወደ ኋላ
ሳይደርስ ነው እንጂ መመለስ ወደ አላህ
ነፍሴን በድያለው ለጊዜያዊ ነገር
አኼራን ዘንግቼ ዘላቂውን ሀገር
ኢላሂ ችለኸኛል በሰፊው እዝነትክ
ብዙ አልፈኸኛል በታጋሽነትክ

እንደኔማ ቢሆን
እንደኔማ ቢሆን እንደ ሀጢአቴ ግዝፈት
ትንፋሼ ተቋርጦ በበቃሁኝ ለሞት
እንደኔማ ቢሆን እንደ ስራዬ ዝቅጠት
ይዘጋብኝ ነበር መግቢያው የተውበት
አውቃለው ጌታዬ ነፍሴን በድያለው
የሀጢአትን ሸማ ተከናንቤያለው
በወንጀል ተዘፍቄ ከደጃፍህ ብርቅም
ከአንተ እዝነት ፍፁም ተስፋ አልቆርጥም
እንዲህ እንደዘቀጥኩ ሞት ቢመጣብኝ
ምን ይሆን ጌታዬ ያዘጋጀክልኝ
ምን ይሆን ያረቢ የቀብር ቆይታዬ
ምን ይሆን ያአላህ የአኼራ ኑሮዬ
ጀነት ወይስ ጀሀነም የኔ እጣ ፈንታ
የዘላለም ቤቴ ሀዘን ወይስ ደስታ
ያረህማን ያረሂም ተውበቴን ተቀበለኝ
ከጀሀነም አርቀህ ጀነትን ወፍቀኝ

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ፕሮፋይል አድርጉት ትልቅ በላእ ከፊታችን አለ

profile እናድርገው


በሰላት አንደራደርም !!
በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤቶች
ሙስሊም ተማሪዎችን ከሰላት ለመነጠል የሚደረገውን ዘመቻ እንቃወም
ወላሂ ነገ ቤታችን ድረስ ነው የሚመጣልን የቦሩ ሜዳው ታሪክ ላለመደገሙ ዋስትና የለንም

በሰላማዊ መንገድ በሶሻል ሚድያ ዘመቻ እንጠይቅ

በሴኩላሪዝም ሽፋን ሙስሊሞችን ከትምህርት ስርዓት ማግለል ይቁም


በአላህ ስም እጠይቃችኋለው በስልካችሁ ላይ ላሉ ሙስሊሞች አዳርሱ እስልምናችን አደጋ ላይ ነው

አነሰ ከተባለ ለ20 ሰው ሼር

#ሼር_አድርጉት
Https://www.tg-me.com/smithhk
በየደረሳችሁበት ስገዱ
~
በየጊዜው እየተነሱ አንዴ ሶላት አንዴ ሒጃብ የሚከለክሉ ጠባቦች ወቅታዊ ቀስቃሽ ምክንያቶች ቢኖሯቸውም ቀዳሚው ሰበብ ግን ስር በሰደደ ጥላቻ የተነሳ በኢስላማዊ ነፀብራቆች የሚደነብሩ መሆናቸው ነው። ሶላቱ ለኛ የሰላም ምንጭ ቢሆንም ለነሱ ግን ክፉኛ ይረብሻል። ሒጃቡ ለኛ ከክፉ መጠበቂያ ዋስትና ነው። ለነሱ ደግሞ አፈሙዙን ያዞረ ጠመንጃ ያክል ያስፈራቸዋል።
እና እንዴት እንግባባ? መሰራት ካለባቸው ስራዎች በተጓዳኝ የማላመድ ስራ መስራት አለብን። ሶላቱንም ሒጃቡንም አእምሯቸው እንዲለምደው ማድረግ። ይሄ ነገር ቀላል ባይሆንም ፈፅም የማይቻል ግን አይደለም። መስጂድ በማንሄድባቸው ሁኔታዎች ጊዜ እራሳችንን ለአደጋ በማያጋልጥ ሁኔታ ባለንበት እንስገድ። "ምድር ሁሉ መስገጃ ተደርጋልኛለች" ብለዋል ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰላም። ስለዚህ በህክምና ቦታዎች፣ ጉዳይ ለማስፈፀም በሄድንባቸው ግቢዎች፣ በጎዳናዎች፣ ... ያለ ምንም መሸማቀቅ ጥግ ይዘን እንስገድ። ወቅቱ እየገፋ እያየን የግድ መስጂድ እስከምናገኝ ወይም ቤት እስከምንደርስ መቆየት የለብንም። ይሄ ብዙ ፋይዳዎች አሉት። ሶላትን በወቅቱ መስገድ ያለው ዋጋ ይታወቃል። ለረሱት ማስታወሻ፣ ለተዳከሙት ማነቃቂያ ይሆናል። የሚረበሹ ጭንቅላቶችም ለጊዜው ቢረበሹም ቀስ እያሉ እንዲለምዱት፣ 'ኖርማል' አድርገው እንዲቀበሉት መንገድ ይጠርጋል። ጉዳዩ ፈፅሞ የምንደራደርበት እንዳልሆነም በቂ መልእክት ያስተላልፋል።
ከኢብኑ ሙነወር
#ሼር #share
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
﴿وَلَذِكْرُ اللهِ أَكْبَرُ﴾

- «سُبْحَانَ اللهِ»
- «الحَمْدُ للهِ»
- «لَا إلَهَ إلَّا اللهُ»
- «اللهُ أكْبَرُ»
- «سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ»
- «سُبْحَانَ اللهِ العَظِيمِ»
- «لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ»
- «أسْتَغْفِرُ اللهَ وَأتُوبُ إلَيْهِ»
- «لَا إلَهَ إلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ»🍁
መልዕክት ለተማሪዎች‼️
===================
✍️ ሁላችሁም ከወትሮው የተለዬ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አይኑራችሁ። ማለትም እስከዛሬ በምሳ ሰዓት ውጭ ላይ ወጥታችሁ ትሰግዱ የነበራችሁ እንደተለመደው ወጥታችሁ ስገዱ። አትወጡም ብለው ከከለከሉ ውስጥ ላይ ስገዱ። በሁሉም ሁኔታ አትሰግዱም ብለው ከከለከሉ ግን፤ እናንተ ገና ሰውነታችሁ ያልጠና ጾመኛ ታዳጊዎች መሳሪያ በታጠቀ ጨቃኝ ኃይል መጎዳት የለባችሁምና አትሰግዱም ብሎ የሚከለክላችሁን መምህርም ይሁን ርዕሰ መምህር፣ ጥበቃም ይሁን ፖሊስ ቢያንስ ስሙን እንኳ አጣርታችሁ ያዙ። የተቀመጠውን ህግ ከሠሩበት በርሱ እንፋረደዋለን፤ ካልሠሩበት ግን መብታችንን ሊነጥቅ በመጣበት መልኩ እንረከበዋለን። ዚያራ ፈላጊም ከሆነ ቀኝ እጅ ሲሰጥ ግራ እጅ በማያይበት መልኩ የፈለገውን ዚያራ ይሰጠዋል። ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ በስልካችሁ የፎቶና የቪድዮ ማስረጃ ያዙ። ስድብም ይሁን ድብደባ አሊያም ሌላ ነገር የሚፈጽም ካለ ለጊዜው ስሜታዊ ሁናችሁ አላማቸውን አታሳኩላቸው። በቀጣዩ ቀን ግን ጉዟችሁ ወደ ትምህርት ቤት ለመማር ሳይሆን በቅድሚያ በኃይማኖታችሁ ላይ ቀይ መስመር አልፎ ትዕዛዝ ወዳስተላለፈው የበላይ አካል ይሆናል። የእምነት ነጻነታችሁ ሳይረጋገጥ ትምህርት አይኖርም። ተወልዳችሁ ባደጋችሁባት ሃገር በነጻነት ሶላታችሁን የመስገድና የመማር ሙሉ መብት አላችሁ። ይህን መብታችሁን የሚጋፋ አካል ካለ እስከ ጥግ ታግሎ መገርሰስ እንጂ እርሱን አዝሎ የሚኖር የለም። ለዚህም ሰላማዊ ትግላችሁ አይደለም ሙስሊሙ የሃገሩን ሰላም የሚሻ የሌላው እምነት ተከታይ ሁሉ ከጎናችሁ ይቆማል። ብቻ ግን እናንተ እዛ ድንጋ ውርወራ ወይም ሌላ ነገር ውስጥ መግባት አለባችሁ ብዬ አላምንም።

መንግስት ግን የእውነት የሃገራችን ሁኔታ የሚያስጨንቀው ከሆነ ይህን ቀላል ጉዳይ ዙሩን እያከረረ ቦታውን በመሳሪያ ትግል ለመረከብ ለሚሹ ሰዎች ከሚያመቻች ይልቅ ተፈቅዶላችሁ በሰላም የመማር ማስተማር ሂደቱ ቢከናወን መልካም ነው። አሁንም በድጋሜ በልመናም ጭምር የምንጠይቀው፤ መንግስት ጸብ ያለሽ በዳቦ አይሁን። ሌላ ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳ ከመለኮስ ይልቅ የተለኮሰውን ማብረድ ላይ ኃይሉን ይጠቀም። አሁንም በድጋሜ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ ግን፤ ነገ በሰላማዊና ንጹሐን ተማሪዎች ላይ አንዳች አይነት ትንኮሳ ቢፈጸም መንግስት ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ከወዲሁ ይታወቅ።

ይሄው ነው‼️
||
Via Murad Tadesse
#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
​مهلاً يا رمضان ! ما أسرعَ خُطاك​ ،،
*بالامس 1 واليوم 9
​تأتي على شوقٍ وتَمضي على عجل​ ،،
​فسبحان من وصفك ب أيام معدودات​ ،،
​يارب تقبل منّا مامضى . وأعنّا على ما بقي 🌙

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
"ረመዳን እኮ የተባለው ወንጀሎችን በመልካም ስራዎች አቃጥሎ አመድ ስለሚያደርጋቸው ነው"
ኢማሙል ቁርጡቢ

ማነው በዚህ በተከበረ ወር መልካም ስራዎችን አብዝቶ በመስራት ዓመቱን ሙሉ ያከማቸውን ወንጀል አቃጥሎ አመድ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ!?
⭐️⭐️⭐️
ለዚህ የላቀ ወር ላይ በሰላምና በጤና በመድረስ የታደልክ ፆመኛ ሆይ! ሳያመልጥህ በፊት ተጣደፍ፣ ከመሞትህ በፊት ነፍስህን ከጥልቅ እንቅልፏ ቀስቅሳትና የሁለቱንም ዓለም ስኬት እንድታጣጥም አድርጋት፣ ነገ ጀነትን እንድታሸንፍ ዛሬ አበርታት።
⭐️⭐️⭐️
ማሊክ ኢብን አነስ የረመዳን ወር በገባ ጊዜ የሐዲስና የዕውቀት ማዕዶች ላይ መገኘታቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ፊታቸውን ወደ ቁርኣን ብቻ ያዞሩ ነበር።
⭐️⭐️⭐️
አቡ ቀታዳህ በረመዳን ውስጥ በየሦስት ሌሊቶች፣ እንዲሁም በመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት ውስጥ ደግሞ በያንዳንዷ ሌሊት ሙሉ ቁርኣንን አንብበው ይጨርሱ ነበር።
⭐️⭐️⭐️
አል-አስወድ የረመዳን ወር ሲገባ፣ በየሁለት ሌሊት ቁርአንን አንብበው በመጨረስ ሙሉ ወሩን ያጠናቅቁ ነበር።

━━━━━━━━━━
ተደራሽ ይሆን ዘንድ ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያስተላልፉ ከማይቋረጠው አጅር ተካፋይ ይሁኑ

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ፆም  ማለት  በሰዎች  ላይ  የተጣለ  ቅጣት  ወይም  ሸክም አይደለም፡፡ ከፆም በስተጀርባ ያለዉ አላማ ባህሪን ማስተካከል መንፈሳዊ ስርአትን ማስተማር  የሰዉን ልጅ  ስሜቱና  ስይጣን እንዳይቆጣጠሩት  የአላህንም  ትዕዛዝ  እንዳይጥስ  ተቅዋን ለመጨመር ነዉ፡፡
ረመዳንም አመታዊ ስልጠና የምናደርግበት ራሳችንን የምናድስበት ሀይል የምናገኝበት አላህ(ሱወ) ያዘዘንን ለመፈፀም የሚገራልን    ወር   ነዉ፤  ፆም ለስላሳ ቀናት ራሶን የሚቆጣጠሩበት ከመጥፎ ስራ የሚርቁበት ዐይንን የሚሰብሩበት ከሃሜትና ወሬ ከማመላለስ የሚታቀቡበት   ጤናማ    ካልሆነ    ግንኝነቶች    የሚርቁበት   አዋዋሎን የሚያሳምሩበት  ስንፍናን  እና ሌሎች ስህተትን  ለመቆጣጠር   የሚያስችለን ወቅት ነዉ፡፡ በተቃራኒዉ ለሰላሳ ቀናቶች የሚጾሙበት ሰላትን በጀመዐ የሚሰግዱበት ቁርአን የሚቀሩበት ተራዊህ የሚሰግዱበት ሰደቃ የሚሰጡበት ዱአና ዚክር የሚያበዙበት ወር ፤ ይህንን   ተከታታይ   ስልጠና   ለአንድ  ወር   በአግባቡ   የወሰደ   ሰዉ ነብሱና አካሉ ለመልካም ስራ ይገራል በስነምግባሩ የታነጸ ይሆናል፣ ተቅዋም ይጨምርለታል ይህም ከረመዳን በኋላ መልካም ባህሪዉንና ዒባዳዉን ይዞ  ለመቀጠል   ያስችለዋል፡፡
ፆም ወደ   መልካምነትና   አላህን   መፍራት   ይመራል፡፡ ፆም  የደም   ቧንቧዎችን ያጥባል  የሰይጣን  እንቅስቃሴ  ይቀንሳል፡፡ የሚፆም ሰዉ  ትልቅ   ምንዳ   አለዉ   ኢባዳም   ይገራለታል፡፡ 

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም(ረሂመሁሏህ)
በበኩላቸው የዕይታን አጠቃላይ ውጤት እንደሚከተለው ይገልጹታል፡-

«መጥፎ ዕይታህን(ዓይኖችህን መወርወርን) ተቆጣጠረው፤ ሐሳብ ይሆናልና፡፡ መጥፎ ሐሳብህን ታገለው፤ አስተሳሰብ ይሆናልና፡፡ መጥፎ አስተሳሰብህን ታገለው፤ ድርጊት ይሆናልና፡፡ መጥፎ ድርጊትህን ታገለው፤ ልማድህ ይሆናልና፤ መጥፎ ልማድህን ታገለው፤ ለኪሳራ ይዳርግሃልና፡፡» (ኤልፈዋኢድ)

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
በሰላት አንደራደርም!
ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 3 ሰላት እንሰግዳለን ባሉ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን
መዋከብ መንግስት በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል::
በሰላት እንደማንደራደር ሁሉም ማህበረሰብ በደንብ የተገነዘበው
ይመስለኛል::
ችግር በተፈጠረባቸው ት/ቤት የተገኛችሁ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች
በስልካችሁ የቪድዮና የፎቶ ማስረጃ መያዛችሁን እንዳትረሱ እንጠይቃለን::
ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!
#أذكار_الصباح

«اللَّهُمَّ إنِّي أسْألُكَ عِلْمًا نَافِعًا ، وَرِزْقًا طَيِّبًا ، وَعَمَلًا مُتَقَبَّلًا»

-----------------------‐

«سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ ، عَدَدَ خَلْقِهِ ، وَرِضَا نَفْسِهِ ، وَزِنَةَ عَرشِهِ ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ»

- ٣ مرَّات.

-----------------------‐

«اللَّهُمَّ بِكَ أصْبَحْنَا ، وَبِكَ أمْسَيْنَا ، وَبِكَ نَحْيَا ، وَبِكَ نَمُوتُ ، وَإلَيْكَ النُّشُورُ»

-----------------------‐

«اللَّهُمَّ مَا أصْبَحَ بِي مِنْ نِعْمَةٍ أوْ بِأحَدٍ مِنْ خَلْقِكَ فَمِنْكَ وَحْدَكَ لَا شَرِيكَ لَكَ ، فَلَكَ الحَمْدُ وَلَكَ الشُّكْرُ»

-----------------------‐

«اللَّهُمَّ إنِّي أصْبَحْتُ أُشْهِدُكَ ، وَأُشْهِدُ حَمَلَةَ عَرْشِكَ ، وَمَلَائِكَتَكَ ، وَجَمِيعَ خَلْقِكَ ، أنَّكَ أنْتَ اللهُ لَا إلَهَ إلَّا أنْتَ وَحْدَكَ لَا شَرِيكَ لَكَ ، وَأنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُكَ وَرَسُولُكَ»

- ٤ مرَّات.

-----------------------‐

«أصْبَحْنَا وَأصْبَحَ المُلْكُ للهِ رَبِّ العَالَمِينَ ،
اللَّهُمَّ إنِّي أسْألُكَ خَيْرَ هَذَا اليَوْمِ ، فَتْحَهُ ، وَنَصْرَهُ ، وَنُورَهُ ، وَبَرَكَتَهُ ، وَهُدَاهُ ، وَأعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِيهِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهُ»

-----------------------‐

«أصْبَحْنَا عَلَى فِطْرَةِ الإسْلَامِ ، وَعَلَى كَلِمَةِ الإخْلَاصِ ، وَعَلَى دِينِ نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ، وَعَلَى مِلَّةِ أبِينَا إبْرَاهِيمَ ، حَنِيفًا مُسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ المُشْرِكِينَ»

-----------------------‐

«أصْبَحْنَا وَأصْبَحَ المُلْكُ للهِ والحَمْدُ للهِ ، لَا إلَهَ إلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ ، لَهُ المُلْكُ وَلَهُ الحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ،
رَبِّ أسْألُكَ خَيْرَ مَا فِي هَذَا اليَوْمِ وَخَيْرَ مَا بَعْدَهُ ، وَأعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِي هَذَا اليَوْمِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهُ ،
رَبِّ أعُوذُ بِكَ مِنَ الكَسَلِ وَسُوءِ الكِبَرِ ، رَبِّ أعُوذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ فِي النَّارِ وعَذَابٍ فِي القَبْرِ»

#ረመዷን_11

በዛሬው ተመሳሳይ ቀን ማለትም በሂጅራ አቆጣጠር በ13ተኛው አመት በረመዷን 11ደኛው ቀን ላይ ነበር ..... ሙስሊሞች በዒራቅ በተካሄደው የ"ቡዎይብ" ዘመቻ ላይ ድል የተጎናፀፉት።

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ጥያቄ፡- ጥርስን ማፅዳት በሸሪዐው በጥብቅ የታዘዘ መሆኑ ይታወቃል። ነገርግን ይህ ሸሪዐዊ ትዕዛዝ የጾመኛን የአፍ ጠረን ከሚያሞግሰው ሐዲስ ጋር አይጋጭም?

መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም። አልሐምዱሊላሂ ረቢል-ዐለሚን። ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዓላ ረሱሊላህ ወበዕድ፡-

ቡኻሪይ እና ሙስሊም ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ የሚል ንግግር ዘግበዋል፡-

والذي نفس محمد بيده لخلوف فم الصائم أطيبُ عند الله من ريح المسك

“የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ የጾመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽታ የበለጠ ተወዳጅ ነው።”

በሌላ በኩልም አቡዳዉድ እና ቱርሙዚይም ከዓሚር ኢብኑ ረቢዐህ እንዲህ የሚል ዘግበዋል፡-

رأيتُ رسول الله ـ صلى الله عليه وسلم ـ يتسوّك ما لا أُحصي وهو صائم

“የአላህን መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በቁጥር ልጠቅሰው የማይቻለኝን ያህል ጊዜ ጾመኛ ሆነው ጥርሳቸውን ሲፍቁ አይቻቸዋለሁ።”

ኢማም ሻፊዒይ ከመጀመሪያው ሐዲስ በመነሳት ጥርስን በመፋቂያ -ወይም በቡሩሽ- መፋቅ የተጠላ መሆኑን አመልክተዋል። መጠላቱንም ከዙህር ሶላት ወቅት በኋላ ባለው ጊዜ ገድበውታል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያሞገሱት የተበላሸውን የጾመኛን የአፍ ጠረን እንዳይወገድ ለማድረግ ነው ይጠላል ያሉት። የአፍ ጠረን መለወጥ ምግብና መጠጥ ካለመቅመስ የሚመጣ ነው። በተለይም ይህ የሚከሰተው ፀሀይ ወደ ምዕራብ ከምትዘነበልበት -የዙህር ሶላት ወቅት- ጀምሮ ነው።

ኢማም ሻፊዒይ በሁለተኛው ሐዲስ አልሰሩበትም። ምክንያታቸው ሐዲሱ ከመጀመሪያው ሐዲስ ዝቅ ያለ ደረጃ ያለው መሆኑ ነው። የሻፊዒይን ሃሳብ የበይሀቂይ ዘገባ ያጠናክረዋል። የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

إذا صمْتم فاستاكُوا بالغَداة ولا تَستاكُوا بالعَشِيّ

“ጥርሳችሁን ከፋቃችሁ በጧት አድርጉት። ከሰዐት በኋላ አትፋቁ።”

ነገርግን ከሻፊዒይ ውጪ ያሉት ሦስቱ ኢማሞች -ማሊክ፣ አቡ ሐኒፋና አሕመድ- “በማንኛውም ሁኔታ ጾመኛ ጥርሱን መፋቁ አይጠላበትም። ጸሀይ ወደ ምዕራብ ከመዘንበሏ በፊትም ሆነ በኋላ ጥርስን መፋቅ አይከለከልም።” ብለዋል።

ማስረጃቸው ዓሚር ኢብኑ ረቢዐህ ያስተላለፉት ከላይ የጠቀስነው ሐዲስ ነው። የጾመኛን የአፍ ጠረን የሚያወድሰው የመጀመሪያውን ሐዲስ በጾም ለማበረታታት የተነገረ ንግግር እንደሆነ ነው የተረዱት። ጾም የአፍን ጠረን ማበላሸቱ ሰዎችን ከመጾም እንዳያግዳቸው የተነገረ ሐዲስ ነው እንጂ ጠረኑ እንዲቆይና እንዳይጠፋ እንድናደርገው የሚያዝ ወይም የሚያበረታታ መልእክት የለውም።

ከዚያም እነዚህ ኢማሞች እንዲህ አሉ፡- መጥፎው የአፍ ጠረን ተደጋግሞ በሚሰራው ለዉዱእ በመጉመጥመጥ ይጠፋል። ነገርግን አትጉመጥመጡ የሚል ክልከላ አልተዘገበም። ከላይ የተጠቀሰው የበይሀቂይ ሐዲስ ደግሞ ደካማ ነው። ይህንንም እራሳቸው በይሀቂይ ተናግረዋል።

ጾመኛ ከዙህር ወቅት በኋላ ጥርሱን መፋቅ የለበትም ያሉት -ከአራቱ ኢማሞች መሀል- ሻፊዒይ ብቻ ከመሆናቸው ጋር የመዝሀባቸው ትልልቆቹ ልሂቃን ደግሞ የርሳቸውን አቋም አልወደዱም።

ነወዊይ -ትልቁ የሻፊዒይ መዝሀብ ልሂቅ- አል-መጅሙዕ የተሰኘው መፅሐፋቸው -ቅፅ 1፣ ገፅ 39- ላይ እንዲህ ይላሉ፡- “ለጾመኛ በማንኛውም ወቅት ጥርስን መፋቅ አለመጠላቱ የተሻለው አቋም ነው።”

የሻፊዒይን ንግግር ተከትለው ኢማም ኢብኑ ደቂቅ እንዲህ ብለዋል፡- “የጾመኛን የአፍ ጠረን የሚያወድሰውን ሐዲስ ጥቅል መልእክት የሚገድብ -ጸሀይ ወደ ምዕራብ ከተዘነበለ በኋላ ብቻ ጥርስን መፋቅ መከልከሉን የሚያመለክት- ልዩ መረጃ ያስፈልጋል። ስለዚህ በረመዳን በማንኛውም ቀውት ጥርስን መፋቅ አይጠላም።”

በጾም ውስጥ ሲዋክን/መፋቂያን መጠቀምን አስመልክቶ የተነገሩ ሃሳቦች እንዳሉ ሆነው ግን የአብዝሃኞቹ ዑለሞች ሃሳብ የተሻለ እንደሆነ እናምናለን። ጥርስን በማንኛውም መንገድ በማንኛውም ወቅት ማፅዳት አይጠላም። ነገርግን ጥርሱን ለማፅዳት የሚጠቀምባቸው ኬሚካሎችም ሆኑ ደም ወደ ሆዱ እንዳይገባ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ለመጠንቀቅ የሚያስቸግሩ ነገሮችን የሚጠቀም ከሆነ ደግሞ በሌሊት ማድረጉ የተሻለ ነው።

አላህ የበለጠ ያውቃል!


#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
2025/07/07 06:54:57
Back to Top
HTML Embed Code: