Telegram Web Link
ወላጆችህ ባንተ ደስ እንዲሠኙ ለማድረግ የሚያግዙ 10 ነጥቦች


ልጅ ሆነን ሣለ ወላጆቻችን የሚሰሩት ነገር አይመቸንም። እንዲያውም አብዛኞቻችን ድርጊታቸውንና ሁኔታቸውን እንተችና እናጣጥል ነበር። አድገን የነርሱ ቦታ ላይ ስንድርስ ግን ያኔ እነርሱ ሲሠሩ የነበረው ነገር ትክክል መሆኑ ይገለፅልናል። በጊዜው በነርሱ በኩል ይደርስብን የነበረው ጫና ያላግባብ መስሎ ቢታየንም ዛሬ ላይ ሆነን ስናይ ግን ያደርጉት የነበረው ነገር ትክክልና ለኛው ብለው ስለመሆኑ ይገባናል። በኛ ላይ የወላጆቻችን ውለታ እጅግ ብዙ ስለመሆኑ በጥቂቱም ቢሆን የሚገባን ልጅ ያገኘን እንደሆነ ነው።

“ቢር አልዋሊደይን” (ለወላጅ መልካም መዋልን) እስልምና ትልቅ ዋጋ ሠጥቶታል። ለወላጅ መልካም መዋል የቀደምት የአላህ ነቢያትም መንገድ ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዳለው ነቢዩ ዒሣ ዐለይህ ሠላም ገና በእናታቸው አንቀልባ ውስጥ ሆነው ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር።

وَبَرًّا بِوَالِدَتِي وَلَمْ يَجْعَلْنِي جَبَّارًا شَقِيًّا

 

“ለእናቴም ታዛዥ (አድርጎኛል)። ትዕቢተኛ እምቢተኛም አላደረገኝም።” (መርየም 19፤ 32)

ቀጥሎ ወላጆቻችን በኛ ደስ እንዲሠኙ ለማድረግ ሊያግዙን የሚችሉ 10 ውብ ነጥቦችን እንዘርዝር

ትዝታ – ልጅ ሆነን ሣለ እንዴት ያጨናንቁንና ይጫኑን እንደነበረ እናስታውሣቸው። በማዝናናት መልኩም እንተርክላቸው። አሁን ላይ ሆነን ሁኔታውን ስናጤን ግን ያኔ እነርሱ በርግጥም በድርጊታቸው ትክክል የነበሩ መሆኑንም እንንገራቸው።

ውስጣዊ ስሜት – ወላጆቻችን የሆነ ነገር አሊያም ስጦታ የሠጡን እንደሆነ ደስታችንና ውስጣዊ ስሜታችንን አውጥተን እናሣያቸው። አጋጣሚውንም በመጠቀም ይህ የሠጡን ስጦታ በጣም ጠቃሚና እጅግ ያስፈልገን እንደነበረም እንግለፅላቸው።

ስጦታ – ለነርሱ ያለንን ውዴታና ከበሬታ የምንገልፅበት ስጦታ ገዝተን እንስጣቸው። ስጦታው የግድ ውድ ነገር መሆን የለበትም። ባይሆን በተቻለን አቅም ሁሉ ደጋግመን እንስጣቸው። የሠጠናቸውን ስጦታ ለሌላ ሰው አሣልፈው ቢሰጡ እንኳ አንቀየማቸው። ያደረግነው ሁሉ ለነርሱ ያለንን ውዴታ ለመግለፅና ውዴታቸውን ለማግኘት ነውና።

ወግ – ከነርሱ ጋር ጊዜ ወስደን እናውራቸው። ወላጆቻቸው (አያቶቻችን)፤ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው በህይወት ካሉ ባሉበት ሄደን እንዘይራቸው። በጉብኝታችን ወቅት ያየነውንና የሠማነውንም ነገር እነርሱን ደስ በሚያሠኝ መልኩ መልሠን እንንገራቸው።

ማማከር – ማግባት ስንፈልግ፣ ቤት አለያም መኪና ለመግዛት ስናቅድ፣ እሩቅ መንገድ ለመሄድ ስንወጥንና ሌሎችም ከባባድ ውሳኔዎች ማድረግ ስንፈልግ እናማክራቸው። ቀለል ያሉ ነገሮችን ለምሳሌ ለጓደኛችን ልብስ መግዛት፣ ምግብ ማድረስ፣ አሊያም ስጦታ ነገር መስጠት ስንፈልግም ሀሣባችንን እናማክራቸው። ማማከራችን ለነርሱ ያለንን ግምት ያሳያቸዋልና።

ጨዋታ – በልጅነታችን ወቅት ከነርሱ፣ ከወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ያሣለፍናቸውን አዝናኝ ገጠመኞችና ትዝታዎችን ሌሎችንም በማንሣት እናጫውታቸው። ጨዋታ በመፍጠርና በመቀለድም እናስፈግጋቸው።

ቴክኖሎጂን መጠቀም – በፌስቡክ፣ በትዊተርና በመሣሰሉት ገፆች የነርሱን አባባል በመለጠፍ ለነርሱ ያለንን አክብሮት እናሣይ። እናታችን የሠራችውን ምግብ፤ አባታችን የለፋበትን የእርሻ ማሳ አሊያም ሌላ ነገር ፎቶ በማንሣት ለጓደኞቻችን፣ ለወዳጆቻችንና እነርሱንም ለሚያውቅ ሁሉ እናሠራጭ። ይህንንም ድርጊታችንን መልሠን እንንገራቸው። ከሌሎች ሰዎች በሚደርሣቸው መልእክት በመነሣት ልጃቸው በሠራው ሥራ ውስጣቸው ደስ ይሠኛልና።

መጎብኘትና ማስተናገድ – እነርሱን ለመጎብኘት፣ ወደ ቤት ጠርተን ለመጋበዝና አብሮ ተመቀማምጦ ለመብላትና ለማውራት ጊዜ ይኑረን። መንገድ የሚሄዱ ከሆነም በቤታቸው ተገኝተን እንሸኛቸው። አቅሙ ካለንም ወጭያቸውንም እንቻል።

ርህራሄና እዝነት – በተለይ ዕድሜያቸው የገፋ እንደሆነ እዝነትና ርህራሄ እናሣያቸው። ባልተገባ መልኩ አስቆጥተናቸው ከሆነም ቶሎ ብለን ይቅርታቸውንና ውዴታቸውን እንፈልግ።

ጓደኞች – መልካም ጓደኞቻችንና ወዳጆቻችንን እቤታቸው ድረስ በመውሰድ እናስተዋውቃቸው። በዚህ ድርጊታችን ደስ ይሠኛሉና።

ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) አባታቸው ገና ሳይወለዱ፤ እናታቸው ደግሞ ገና የስድስት አመት አካባቢ ልጅ ሆነው ሣሉ ነው የሞቱባቸው። በመሆኑም የቲም /ወላጅ አልባ/ ሆነው ነው ያደጉት። ምናልባት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እርሣቸው እስኪያድጉ ድረስ ወላጆቻቸው በህይወት ቆይተው ቢሆን ኖሮ እኛ ፈፅሞ በማንወጣው መልኩ ለወላጆች መልካም መዋልን ባሣዩን ነበር። ለወላጅ መልካም መዋል ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በቃል እንጂ በተግባር አልደረሠንም። በተግባር ቢደርሰን ኖሮ የወላጅ ሀቅ ከመክበዱ የተነሣ ትግበራው ኢማናችን ይፈታተን ነበር። ያም ሆነ ይህ ወላጆቻችን በህይወት ያሉ እንደሆነ በተቻለን መጠን እነሱን በሚያስደስት መልኩ መልካም ነገር ልናደርግላቸው ይገባል። በህይወት የሌሉ እንደሆነም ለነርሱ ዱዓእ በማድረግ፣ ምህረትን በመለመን፣ ዘመዶቻቸውን በመቀጠል፣ ጓደኞቻቸው በመጠየቅና ሌሎች መልካም ሥራዎችን በነርሱ ሥም በመስራት ማስደሠት ይቻላል።

ለወላጅ መልካም መዋል ሁሌም መደረግ ያለበት ነገር ነው። ምንዳውም እጅግ ትልቅ ተፅእኖውም ከባድ ነው። ለወላጅ መልካም መዋል እጅግ አስፈላጊ ነገር በመሆኑ አላህ (ሱ.ወ) ቁርዓኑ ውስጥ ከአምልኮው ቀጥሎ አውስቶታል። አዞበታልም። እንዲህ በማለት

وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا

 

“ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ። በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ። በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው። አትገላምጣቸውም። ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው።” (አል-ኢስራእ 17፤፡ 23)

ኢማም ሀሠን ልበስሪ “አንድ ሰው የሱና ፆም በመፆም ላይ እያለ ወላጆቹ ፆሙን እንዲፈታ ጠይቀውት የታዘዛቸው እንደሆነ ሁለት ምንዳ ማለትም ለወላጅ የመታዘዝንና የፆም ምንዳን ያገኛል።” ይላሉ።

بروا آباءكم يبركم أبناؤكم

“ለወላጆቻችሁ መልካም ዋሉ ልጆቻችሁ መልካም ይውሉላችኋል። /ለእናት አባት ጥሩ ሁኑ ልጆቻችሁ ጥሩ ይሆኑላችኋል።/

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🕋قال رسول الله - صلى الله عليه وسلم - (من قرأ "قل هو الله أحد" عشر مرات بنى الله له بيتاً في الجنة) صحيح رواه الإمام أحمد.



🕋የአላህ መልእክተኛ (ሰ. ዐ. ወ) እንዲህ ብለዋል፡-(“ሱረቱል ኢኽላስን ” 10 ጊዜ የሚያነብ ፣ አላህ በጀነት ውስጥ ቤት ይሠራለታል)
🕋ኢማም አህመድ ዘግበውታል




#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
አኽላቅ

እነዚህ ሰባት ድንቅ ባህሪያት ቀጥለን ከምናየው የአቡ ሁረይራ ሀዲስ ውስጥ ይገኛሉ። አቡ ሁረይራ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ ይለናል፡-

سبعة يظلهم الله في ظله يوم لا ظل إلا ظله: إمام عادل، وشاب نشأ في عبادة الله، ورجل قلبه معلق بالمساجد، ورجلان تحابا في الله اجتمعا عليه وتفرقا عليه، ورجل دعته امرأة ذات منصب وجمال فقال إني أخاف الله، ورجل تصدق بصدقة فأخفاها حتى لا تعلم شماله ما تنفق يمينه، ورجل ذكر الله خاليًا ففاضت عيناه

“በዚያ ከአርሹ ጥላ በስተቀር ምንም ጥላ በሌለበት ቀን (የፍርዱ ቀን)፤ አላህ ሰባት ሰዎችን በአርሽ ጥላ ስር ያኖራቸዋል። እነሱም፡- ፍትሃዊ መሪን፣ አላህን በመገዛት ወጣትነቱን ያሳለፈ፣ ልቡ ከመስጅድ ጋር የተቆራኘን ሰው፣ ለአላህ ብቻ ብለው በአላህ መንገድ ላይ የተዋደዱንና በርሱም መንገድ ላይ የተለያዩ (ሲለያይም ለአላህ ብለው)፣ አንዲት ቆንጆ ሴት ራሷን ለዝሙት አዘጋጅታለት ‘አላህን እፈራለሁ’ በማለት እምቢ ያለ፣ በድብቅ ምጽዋት የሚሠጥ ሰው፣ ብቻውን ሆኖ አላህን ሲያስታውስ አላህን ፈርቶ አይኖቹ በእንባ የሚሞላና ጉንጮቹ የሚርሱ ሰው” (አል-ቡኻሪ 620)

በእርግጥ በዚያ ቀን ጥላ ያሻናል። የማንም ሳይሆን የአላህ ጥበቃ ያስፈልገናል፤ ከዚያን ያህል ርቀት በቃጠሎዋ የምናውቃት ፀሐይ በአንድ ስንዝር ልዩነት ስትቀርበን ሁላችን በላባችን ስንጠመቅ ሞልቶም እስከ አንገታችን ሲደርስ ያኔ በእርግጥ ጥላ ያስፈልገናል። ምንስ ጥላ ይኖራል ከአላህ ሁሉን ከሚችለው ጌታ ጥላ በስተቀር። በዚያን ወቅት ከነዚህ ሰባት ሰዎች መካከል ከሆንን የአላህን ጥበቃና ጥላ እናገኛለን። ኢንሻአላህ! እስቲ ስለ ሰባቱ ሰዎች ባህሪ ጥቂት እንበል።

ፍትሃዊ መሪ፡- ይህ የትልቅ ስልጣን ባለቤትን ብቻ አይመለከትም። ማንኛውም የትንሽም ሆነ ትልቅ ስልጣን ባለቤት ኃላፊነት የሚሰማው መሪ መሆን አለበት። አላህ ሁሉንም የሰው ልጅ ፍትሃዊ ይሆኑ ዘንድ ያዛል። ፍትሃዊነት የስልጣን ባለቤትነት ሲረጋገጥ ከባድ ይሆናል። ይሄኔ ነው የፍትሃዊነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባው። በጣም ከባዱ ደግሞ ከሚጠሉህ ሰዎች ጋር የአንተን መውደቅ ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር በፍትሃዊነት መኖር ነው። ምንም እንኳ ስልጣንና ኃይል በእጅህ ቢሆን እንኳን! ይህ በእርግጥ ታላቅ ትዕግስተኝነትንና ታማኝነትን ይሻል። ጉዳዩ ግለሰባዊ ሳይሆን ማህበረሰባዊ ነው። ለዚህም ይመስላል ከሰባቱ ሰዎች የመጀመሪያ በመሆን የተጠቀሰው።

አላህን በማምለክ ላይ ወጣትነቱን ያሳለፈ፡- አላህን መገዛት በሁሉም ሰብዐዊ ፍጡር ላይ ግዴታ ነው። ጉዳዩ ግን ወጣትነት ስሜታዊነት የሚንፀባረቅበት እድሜ በመሆኑ ነው። ዓለም ያረገዘችውን ሁሉ የምትወልድበት ወቅት በወጣትነት አይን የተመለከትናት ወቅት ነው። ተቃራኒ ፆታ፣ ገንዘብና ስሜት በወጣት ላይ ያበረታሉ። እነዚህን መጋፈጥ ደግሞ በእርግጥ ትልቅ ችሎታን፣ ትዕግስተኝነትንና ቆራጥነትን ይጠይቃል። ለእነዚህ ሁሉ ስሜቶች ከተሸነፉ በኋላ በእርጅና ወቅት ለኢስላማዊው መንፈስ ራስን መስጠት የሚገርም አይሆንም። የሚገርመው የሚደንቀውም በፍርዱ ቀን የአላህን ጥላ የሚያጋነውም እነዚህን ፈተናዎች በሚገባ ተቋቁሞ አላህ በመገዛት ያሳለፈ ወጣት ነው።

ልቡ ከመስጅድ የተቆራኘ ሰው፡- በዚህ ገለፃ ወቅት ነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ የተጠቀሙት የአረብኛ ቃል (ሙአለቅ) የሚለውን ነው። በቀጥታ ሲተረጎምም የተንጠለጠለ ማለት ነው። ይህን ኢማም ማሊክ የተባሉ የኢስላም አዋቂ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ:- “ይህ ሰው ወደ መስጅድ ይመጣል፤ ከመስጅድ ሲወጣ ግን በፍጥነት የሚመለስበትን ጊዜ እየናፈቀ ነው።” በእርግጥ የሰዎች ልብ ከስራቸው፤ ከቤተሰቦቻቸውና ከንግዳቸው ላይ የተንጠለጠለ ነው። መስጅድ የቅድሚያ ፍላጎታቸው አይደለም። ነገር ግን አላህን በእውነት ለሚወዱ ሰዎች በምድር ካለ ቦታ ሁሉ መስጅድ ለነርሱ ተወዳጅ ስፍራ ነው። የቅድሚያ ፍላጎታቸውም የአላህን ቤት መጠበቅና በውስጡም ዘውታሪ መሆን ነው። ታዲያ ለነዚህስ የአላህን ጥላ አይገባቸውምን? አላህም በእርግጥ በነገሮች ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው።

ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሁለት ሰዎች፡- ፍቅር የማህበረሰባችን ቋሚ ነው። ያለውዴታ የተሟላ ማህበረሰብን መገንባት የማይታሰብ ነው። ኢስላም ከሁሉም ሰዎች ጋር በፍቅርና በርህራሄ እንድንኗኗር ያዛል። ነገር ግን ውዴታው የአላህን ውዴታ በመሻት ለአላህ ብቻ ተብሎ ሲሆን ደግሞ የልቅናን ማማ ይቆናጠጣል። ውዴታውም የተባረከ ይሆናል። ጉዳያቸው ሁሉ አላህን በማስደሰት ላይ ስለሚገነባም ለራሳቸውም ሆነ በዙሪያቸው ላሉት ሁሉ መልካምን ይለግሳል። ይህን አይነቱ ውዴታ እውነትን፣ ታማኝነትን፣ የተላበሰ ውዴታም በመሆኑ የአላህን በረከት ይቸራል፣ ዘለዓለምም የእዝነት መሠረት ይሆናል። እነኚህስ አይገቡምን? የአላህ ጥበብ በእርግጥ ሰፊ ናት!!

ቁርጠኝነት የተላበሰ የመልካም ባህሪ ባለቤት፡- ነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ስለዚህ ሰው ድንቅ ባህሪ ሲያወሱ የተጠቀሙት የአረብኛ ቃል “መንሰብ” የሚለውን ሲሆን ይህ ማለት ሁሉንም ያሟላች ሴት (ቁንጅና፣ ሀብት፣ ጥሩ ዘርና የተከበረ ቤተሰብ) ማለት ነው። ይህን ሁሉ ያላት ሴት ማንም ሰው በሌለበት ይህንን ከባድ የስሜት ጥያቄ ስታቀርብ እምቢ፣ አሻፈረኝ ማለት ድንቅ የአላህን ፍራቻ ያመላክታል። ታላቁ የኢስላም አዋቂ ኢብን ሀጀር አል አስቀላኒ ሐዲሱ በተከበረ፣ መልከ መልካምና ሀብታም ወንድ ጥያቄ ያልተሸነፈችን ሴትንም ያመላክታል ይላሉ። በእርግጥም ይህንን ጥያቄ አሻፈረኝ ማለት ጠንካራ ስብዕናን ይሻል። በአላህ ፍራቻ ልባቸው የተሞላ ግን ይህን አማላይ ጥያቄ አሻፈረኝ ለማለት አያንገራግሩም። ታዲያ የአላህ ጥላ አይገባቸውምን? የአላህ ራህመት ምንኛ ሰፋች!

ለዝና ብሎ የማይለግስ ቸር፡- የዚህ ሰው ባለቤት የራሱ ግራ እጅ በማይመለከትበት ሁኔታ ቀኝ እጁ ይሰጣል ማለት ለመስጠቱ ምላሽን ከሰዎችም ሆነ ከራሱ አይሻም። ይልቁንም የሥራውን ምስጋና ከአላህ ብቻ ይጠብቃል። የሰዎች ምስጋና ፍላጎት ፈፅሞ አይቀይረውም። ፍላጎቱ አላህን ማስደሰት ብቻ ነው። ይህ ከስጦታዎች ሁሉ የላቀው አሰጣጥ ነው ሽልማቱም አርሽ ጥላ ስር መቀመጥ ነው።

አላህን ብቻውን ባስታወሰው ጊዜ ጉንጮቹ በእንባ የሚርሱ ሰው፡- አላህን ብቻ በማሰብ፣ ድንቅ ባህሪያትን እና ስሞቹን በማስታወስ፣ እርሱንም በማመስገንና በማወደስ የምታልፍ ሰዓት ከሰዓቶች ሁሉ እጅግ የተዋበችዋ ሰዓት ነች። አላህን ማስታወስ በማንኛውም ወቅት የሚተገበር የአምልኮ አይነት ሲሆን ስሙም “ዚክር” ይባላል። ማንም በማይመለከትህ ሰዓት፣ ልብህ ከአላህ ጋር ሲገናኝ፣ ውለታዎች ስታስታውስና አይኖችህ በእንባ ጎርፍ ሲሞሉ ጉንጮችህ በዚህ የተቅዋ (አላህን ፍራቻና ጠንቃቃነት) ዶፍ ሲናጡ በእርግጥም ለአላህ ያለህን ውዴታና ተቅዋ ያመላክታል። የአላህን ፊት መሻትህን ያስገነዝባል። አላህን በእውነት የወደዱ ደግሞ በእርግጥ ስኬትን ይጎናፀፋሉ። በዚያች የጭንቅ ቀንም የአርሽ ጥላ ስር ይጠለላሉ።
እነዚህ ሰባት ድንቅ ባህሪያት እውነተኛ እምነትን፣ ቁርጠኛ አቋምን መለኪያ ሚዛን ናቸው። ስሜት፣ መንፈስን፣ አስተሳሰብንና ተግባርን ባማከለ ሁኔታ ለአላህ ያለንን ውዴታ ያሳያሉ። እነዚህ የምርጥ አማኞች ባህሪያት ናቸው። አላህ እነዚህን ባህሪያት በእውነት ከሚጎናፀፉት ሰዎች ያድርገን። ሁላችንንም በጭንቁ ቀን በእርሱ አርሽ ጥላ ስር ያኑረን።

Https://www.tg-me.com/smithhk
#ረሱል_መንገድ_ዳር_አፈር እየጫሩ ቁጭ ብለው አሸዋ ጫር ጫር እያደረጉ በሀሳብ ተጉዘው ተከዙ ምነው ያረሱለላህ ሲሏቸው?
በጣፋጭ አንደበት እንዲህ ሲሉ መለሱ
"ኢሽተቅቱ ኢላ ኢኽዋኒ"
እኔ ወንድሞቼ ናፈቁኝ ከኔ ቡሃላ የሚመጡ አማኞች ናቸው እኔን ሳያዩ ያመኑብኝ .. ወንድሞቼ ናፈቁኝ

#ፊዳከ_አቢ_ወኡሚ_ያረሱላለህ🧡
#ፊዳከ_ሩሂ_ወደሚ_ያሀቢበላህ🧡

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
እዝነትና ፍትህ በረሱል (ሰዐወ) ሲጣመሩ

የዚህን ታላቅ ነብይ ሁለንተናዊ ስኬት ለመረዳት ብሎም ለሰብዓዊና ቁሳዊው ስልጣኔ መነሻ የሚሆን ትውልድን በመፍጠር ሂደት ውስጥ የተከፈለውን መስዋትነት ክብደት ለመረዳት ይረዳ ዘንድ ከውልደታቸው በፊት የነበረውን ጨለማ አለም በተለይም የአረቡ ምድር ሰጥሞበት የነበረውን ባስ ያለ ጨለማ ወደ ኋላ መመልከት በራሱ በቂ ማስረጃ ሊሆን ይችላል። አለም ጥቂቶች በርካታ ሀብትን ሰብስበው ብዙዎች ግን በረሀብ አለንጋ የሚረግፉበት፣ ጥቂቶች በአምባገነንነት ስልጣንን ተቆናጥጠው ብዙዎች በባርነት ቀንበር ውስጥ ከመኖር በታች የሆኑባት አስፈሪና መራራ ቦታ ሆና ነበር።

ይሄኔ ነበር የነብዩ ውልደት ህይወት ላላቸውም ህይወት ለሌላቸውም ፍጡራን የተለየ ትርጓሜ የቸረው። ከውልደታቸው ጀምሮ እስከመላካቸው ያለው ክቡሩ ህይወታቸው በራሱ አንድ ግለሰብ በመለኮታዊ ራዕይ ሳይታገዝ ንፁህ ተፈጥሯዊ ማንነቱን ጠብቆ እንደሰው ልጅ ለትክክለኛ መርህ መገዛት መሻትን የምንመለከትበት ብርቅዬ ተምሳሌት ነው።በመሆኑም በመወለዳቸው አለም ይሄን ታላቅ ብርሀን ተለገሰው ልንል ያስችለናል። ተልዕኳቸው በራሱ ከሰው ልጅ ሁሉ አልፎ ፍጡራንን በጠቅላላ ያካተተ፤ በዕዝነት መሰረት ላይ የቆመ፤ ሆድ ለባሳቸውና ለተቸገሩ፣ በሀዘንና ትካዜ ለተከበቡ፣ መሄጃ ጠፍቷቸው ለተወዛገቡ፣ ህይወት በአንዱ መራራ ኩርባዋ ላይ ለጣለቻቸውና የእርዳታ እጆችን ለተነፈጉ፣ የውስጣቸውን ምሬት አዳማጭ ጆሮዎችን ለተከለከሉ፣ በጉንጮቻቸው ላይ የሚፈሱ ዕንባዎችን አባሽ መዳፎችን ላጡ ታላቅ ብስራት ሆነ።

በዛ በርካታ ቀናትንና ሌሊቶችን ያዘወትሩበት ከነበረበት የሂራ ዋሻ ውስጥ “አንብብ!” የሚለው የመለኮታዊ ጥሪ ጅማሮ ድምፅ ከገቡበት ጥልቅ ሀሳብና የማሰላሰል አለም አባነናቸው።ፈጣሪያችንና ተንከባካቢያችን ጠባቂያችንና ጌታችን የሆነው አላህ(ሱ.ወ) በርግጥም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በፊደላት ስብስብ የተሰሩ ፅሁፎችን ማንበብ እንደማይችሉ ያውቃል ለዚህም ነው የተሰማው “የአንብብ” ጥሪ ሁለንተናዊ ንባብን የሚመለከት መሆኑን የምንረዳው። ለዚህም ነው ጥሪው የነበረውን የግለሰባዊ ፤ የማህበራዊ ፤ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ህይወትን የማስተንተን ሁለንተናዊ የንባብ ጥሪ መሆኑን የምንገነዘበው።

የኚህን ታላቅ መልዕክተኛ ጥልቅ የሆነ የነፃነትና የፍትህ እንዲሁም የነፃነትና ፍትህ ውጤት የሆነውን ደስታና ሰላም የማስፈን ጉዞ የሚያረጋግጡ በውስጣቸው የርሳቸውን ድንቅ የሆነ መንፈሳዊ ልቅናና አእምሯዊ ብስለት የሚናገሩ ክስተቶችን ለአብነት ያህል እናንሳ። የባሪያ ንግድ በአረቢያ ባህረ ሰላጤ የዕለተዕለት ህይወት አንዱ አካል ከሆነ ሰነባብቷል። ሰዎች ሰዎችን እንደዕቃ ይገዛሉ ይሸጣሉ። ነቢዩ በመጀመሪያዎቹ የጥሪ ሂደቶች ሁኔታው ምንም እንኳን የአንበሳ ልብ ቢጠይቅም እርሳቸውን ከመቀበል አልፈው ጥሪው ከስጋቸውና ደማቸው ጋር የተዋሀደን ግለሰቦች ማግኘት ችለዋል። ለዚህ ታላቅ አላማ መሰዋትን እጅግ የሚመኙ አማኞችን ከግራና ቀኝ ይዘዋል። ይህም ሆኖ ግን በሳሉ መልዕክተኛ ለነዚሁ አማኞች የባሪያ ንግድ ውስጥ መሳተፍን በመከልከል አልጀመሩም። የባርነትን ስነልቦናዊ እውነታ መረመሩ ውስጣዊ መሰረቱን ከውጫዊ መገለጫው ለዩ። በዚህም መሰረት የሰው ልጅ የተፈጥሮአዊ መነሻ አንድ መሆኑን ፤ ማጠናቀቂያውና የምድራዊ ህይወቱ መዝጊያም አፈር መሆኑን፤ አንዱ ከሌላ እንደማይበልጥና የሰው ለጆች በሙሉ እኩል መሆናቸውን አስተማሩ፤ ነፃነት ከውስጥ ፈንቅሎ የሚወጣ፤ የሰው ልጅ ሲነቃ በራሱ ጊዜ የሚወስደው እንጂ በሌሎች የሚሰጠው አለመሆኑን አበሰሩ አስተማሩ። በዚህም የሁለተኛውን ዙር የባሪያ ንግድን የመደምሰስ እውነታ አስገኙ። በውጪ ገፅታው ከመሸጥና መገዛት ሂደት ባይወጡም እኩልነት የሚሰማቸው፤ ነፃነት ካለችበት ማንሳት እንደሚችሉ የሚያምኑ ግለሰቦች ግን ተፈጠሩ። በዚሁ ዙር ከተፈጠረው የነፃት ስሜት ጎን ለጎን ባሪያን ነፃ የማውጣት ደረጃና ምንዳ፣ በዚህና በመጪ አለም የሚኖረውን ጥቅም በማሳወቅ የተፈጠረውን የነፃነት ስሜት የሚያስተናግድ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ውጪያዊ ስርዓት አንዲኖር አደረጉ። የሚገርመው ሂደቱ ወደሌላ የሶስተኛ ዙር እራሱን ማሻገሩ ነው። እያየለ የመጣውን የነፃነት ውስጣዊ ፍላጎት ሊመዝን የሚችልና እራሱ በስም ብቻ ባሪያ ተብሎ የሚጠራው አካል አስፈላጊውን ክፍያ ፈፅሞ ምሉዕ ነፃነቱን የሚጎናፀፍበትን ስርዐት እንዲወለደ አደረጉ። በመሆኑም ግለሰቡ በትርፍ ጊዜው ሰርቶ በሚያካብተው ገንዘብ የራሱን እድል መወሰን እንዲችል ሆነ።

በነፃነትና ፍትህ የታጀበው ጉዞዐቸው ከ13 ዓመት የመካ ቆይታ ቦሀላ ወደ መዲና መሰደድ ግድ አለው። በዚሁ የሂጅራ ሂደት ውስጥ ታላቅ ምሳሌንም ጥሎ አለፈ። ነብዩና ባልደረቦቻቸው አለም አቀፋዊ (የኒቨርሳል) የሆነውን የኢስላም መርሆ ከነበሩበት የመካ ባህል፤ ወግና ልምድ ነጥለው የሚመለከቱበት እድል በዚሁ ወደ መዲና በተደረገው ስደት ተፈጠረ። የመዲናው የህይወት ስርዓት ያካተተው የጎሳዎች የዕርስበርስ ግንኙነት፣ የሴቶች ማህበራዊ ሚና፣ የአይሁዶችና ክርስቲያኖች ተፅዕኖ እና በአጠቃላይ መሰረታዊ ከባህልና ኑሮ ጋር የተገናኙ ሂደቶች ከመካው የተለዩ በመሆናቸው ለሙስሊሞች ለፈጣሪና መርህ በተለየ ባህልና የህይወት ስርዐት ውስጥም ሆኖ ታማኝ የመሆንን ተሞክሮ ለግሷቸዋል። ይህም ሙስሊሞች በተመሳሳይ ርዕዮትና መርህ ለተለያዩ ባህሎችና ወጎች ክፍት በመሆን በአለም አቀፋዊ ወንድማማችነት መተሳሰር የሚቻልበትን ድንቅ ምሳሌ እንዲያስቀምጡ አስችሏቸዋል።

የነብዩን ፍትህን ሰፍኖ የመመልከት ጉጉት የሚያስረዳውና በርግጥም ተልዕኳቸው ሁሉንም ያካተተ መሆኑንና ፍትህን ለማስፈን እስከሆነ ድረስ ከማንም ጋር ለመቆም ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳየው ከመላካቸው በፊት በዐብደላ ኢብን ጁድዐን ጓሮ የተደረገች ስብሰባ ናት አላማውም ማንም ይሁን ማን ከየትም ይምጣ ከየት ከተበዳይ ጎን ለመቆም የሚያስችልን ዕቅድ ለማውጣት የተደረገች ነበረች። እርሳቸውም የዚህ ስብሰባ ተካፋይ ነበሩ።ከመላካቸው በኃላ ሲናገሩ “ያቺ ስብሰባ ዛሬ ብትኖርና ጥሪ ቢደረግልኝ በደስታ እገኝ ነበር” ሲሉ ተሰምተዋል። ተሰብሳቢዎቹ አጋሪዎች መሆናቸው የስብሰባው ቦታም የሙስሊም ግለሰብ አለመሆኑ ለፍትህ ከሚደረግ ጥረት ጎን እንዳይቆሙ አላደረጋቸውም። ሙሀመድ የአብደላህ ልጅ የጌታችን ሠላትና ሠላም በርሳቸው ላይ ይሁን በሚዕራጅ (ወደ ሰማይ አለም)ጉዞዓቸው ሲድረተል ሙንተሀን ተሻግረዋል። የሰው ልጅ ሎጂክ፤ ምክንያታዊነትን ሀሳብ ሊደርስ የማይችልበትን ድንበር አልፈዋል። ታዲያ ለዚህ ነብይ ፍቅርን ለመግለፅ ምን አይነት ምክንያታዊነትና ሎጂክ ሊሰራ ይችላል። ምን አይነት ደንብና ቅርፅ ይፈልጋል። የውዴታችን አላማ ግን አይዘነጋም። የመውደዳችን ጥበብ ግን ከፍቅሩ ጋር አብሮን ይጓዛል። እርሱም ከታላቁ ጌታችን አላህ ጋር አስተዋውቀውናል። ይህም የመውደዳችን ጥበብ ይሆናል።

ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይሂ


#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
عن عامر بن ربيعة رضي الله عنه ،
عن النبي ﷺ قال :

((مَا مِنْ مُسْلِمٍ يُصَلِّي عَلَيَّ إلَّا صَلَّتْ عَلَيْهِ المَلَائِكَةُ مَا صَلَّى عَلَيَّ ، فَلْيُقِلَّ العَبْدُ مِنْ ذَلِكَ أوْ لِيُكْثِرْ))

رواه ابن ماجه.🍂

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ»🧡
عن ابن عمر رضي الله عنهما قال :
كان رسول الله ﷺ إذا أفطر قال :

((ذَهَبَ الظَّمَأُ ، وَابْتَلَّتِ العُرُوقُ ، وَثَبَتَ الأجْرُ إنْ شَاءَ اللهُ))

رواه أبو داود.🍂
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሱቢህ መስጂደል አቅሳ ሲሰግዱ የነበሩት ላይ መስጂድ ድረስ በመግባት
ጥቃት የፈፀሙትን ወሰኽ የእስራኤል ወታደሮች ጀግኖቹ ፍልስጤማዊያን
በወታደሮቹ ጥይት እየተተኮሰ እንኳን ባሉበት ባላቸው ውጊያውን ሳይሸሹ
ተጋፍጠዋል # የጀግንነት_ተምሳሌቶች ፍልስጤማዊያን
#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ቀደምት ሙሰሊም ሳይንቲስቶችና ተመራማሪዎች

ኢብኑ ነፊስ (1213-1288 እ.ኤ.አ)

ዐላእ አድ-ዲን አቡ አል ሀሠን ዓሊ ኢብኑ አቢ አል ሀዝም አል ቀርሺ አል ደመሽቂ አልሚስሪ ይባላል፡፡ የተወለደው እ.ኤ.አ በ607 በደማስቆ ከተማ ነው፡፡ ትምህርቱንም የተማረው በኑረዲን አዝ-ዘንኪ በተመሠረተው የህክምና ኮሌጅ ሆስፒታል ነው፡፡ በህክምናው ትምህርት ዙሪያ መምህሩ የነበረው ሙሀዘብ አድ ዲን አብዱል ረሂም ሲሆን ከህክምናው ትምህርት ሌላ ኢብኑ ነፊስ የህግ ትምህርትን፣ የሥነ-ፅሁፍንና ሥነ-መለኮትን ትምህርት ተከታትሏል፡፡

በፊቅሂ እውቀትም በሻፊዒይ መዝሀብ እውቀቱ የበቃ (ኤክስፐርት) ሲሆን የታወቀ ሃኪምም ነበር፡፡

በህክምናና በህግ እውቀት ከፍተኛ ትምህርት ካገኘ በኋላ ወደ ካይሮ በመጓዝ በታዋቂው ናስሪ ሆስፒታል በዋና ሥራ አስኪያጅነት የተሾመ ሲሆን እዚያም ሣለ ለታዋቂው የቀዶ ጥገና ባለሙያ ኢብኑ አል ቁፍ አል መሲሂን ጨምሮ ለበርካታ የህክምና ጠበብቶች ሥልጠና ሠጥቷል። ከዚህም ሌላ በካይሮ በሚገኘው መንሱሪያ ትምህርት ቤት ግልጋሎት ሠጥቷል፡፡ የሞተውም እ.ኤ.አ በ678 ሲሆን የግል ቤቱን፣ ቤተ-መፅሃፍቱንና ክሊኒኩን ለመንሱሪያ ሆስፒታል በስጦታነት አበርክቷል፡፡

የኢብኑ አን-ነፊስ ዋነኛ አስተዋፅኦዎቹ በህክምና ዙሪያ ያተኮሩ ናቸው፡፡ አቀራረቦቹም በቀደሙት ሥራዎች ላይ ዝርዝር አስተያየቶች መፃፍን፣ እነሱን በጥልቀት መመርመርንና የራሱን ወጥ የሆኑ አስተዋፅኦዎች መጨመርን ያካትታሉ፡፡ ጉልህ ተፅእኖ ከነበራቸው ትላልቅ ወጥ ሥራዎቹ መካከል ከሦስት ምእተ አመታት በኋላ በዘመናዊው ሣይንስ እንደገና የተደረሠበት የደም ዝውውርን ማግኘቱ ይጠቀሳል፡፡ ሣንባ ውስጥ የሚገኙትን ነገሮች በትክክል ለመግለፅ የመጀመሪያው ሰው ሲሆን ስለ ብሮንካይ ምንነት፣ በሰው ልጅ የደም ቱቦዎችና በአየርና በደም መካከል ስለሚከሠተው አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር አስፍሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ልብ ላይ የሚገኘውን የኮሮናሪ አርተሪን (ልብ ላይ የሚገኝ የደም ሥር) ጥቅም በመግለፅ የልብ ጡንቻዎችን የሚመግብበትን ሁኔታ ተንትኗል፡፡

አሽ-ሻሚላ ፊ አጥ-ጢብ የሚባለው ባለ ብዙ ጥራዝ መፅሃፉ ሦስት መቶ ክፍሎችን ሊይዝ የሚችል እንሣክሎፒዲያ ተደርጎ የተቀረፀ ሲሆን በመሞቱ ምክኒያት ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡ የእጅ ፅሁፎቹ ግን ዛሬም ድረስ በደማስቆ ይገኛሉ፡፡ በአይን ህክምና ዙሪያ የተፃፈው መፅሃፉ ወጥ የሆነ የራሱ አስተዋፅኦው ሲሆን ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ነገር ግን እጅግ ሊታወቅ የቻለው መፅሃፉ ሙጃዝ አልቃኑን የሚባለው ሲሆን በሱ ዙሪያ በርካታ ማብራሪዎችም ተፅፈዋል፡፡ ከሱ ማብራሪያዎች መካከል አንዱ በሂፖክራተስ መፅሃፍ ላይ የጻፈው ነው፡፡ የኢብኑ ሲናን ቃኑን አስመልክቶ ዛሬም ድረስ ያሉ በርካታ ጥራዞችን ፅፏል፡፡ እንደዚሁም በሁነይን ኢብኑ ኢስሃቅ መፅሃፍ ላይም ማብራሪያ ፅፏል፡፡ ሌላው ታዋቂውና የሱ ወጥ ጥንቅር አስተዋፅኦ የሆነው መፅሃፍ ምግብ በጤና ላይ ስለሚያሣድረው ተፅእኖ የሚዳስሰው ኪታብ አልሙኽታር ፊ አል አግዚያ የሚባለው ነው፡፡

የኢብኑ አን-ነፊስ ሥራዎች በያኔውን ዘመን የነበረውን እውቀት በእጅጉ ከመዋሃዳቸውም በላይ  አበልፅገውታልም፡፡ ከዚህም ባለፈ መልኩ በምሥራቁም ሆነ በምእራቡ ዓለም በነበረው በያኔው የህክምና ሣይንስ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ሆኖም ከመፅሃፎቹ መካከል አንደኛው ብቻ ነው ወደ ላቲን የተተረጎመው፡፡ በመሆኑም ከፊል ሥራዎቹ ለአውሮፓ ሣይታወቁ ለረጅም ዘመናት ኖረዋል፡

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
የበድር ዘመቻ‼️
============
✍️ በሒጅሪያ የዘመን አቆጣጠር የዛሬ 1439 ገደማ በፊት ወደኋላ ስንመለስ፣
ለሙስሊሙ አለም አንድ ፋና ወጊ ቀንን እናስታውሳለን።
313 ገደማ የሚሆኑ ሙስሊሞች፣ ወደ 950 ገደማ የሚጠጉ የቁረይሽ አጋሪያንን በበድር ላይ ጦርነት ገጥመዋል።
ይህ ጦርነት የተካሄደው መልዕክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከመካ ወደ መዲና በተሰደቱ በሁለተኛው አመት፣ እለተ ጁሙዓ በወርሃ ረመዳን 17, ልክ የዛሬ 1439 አመት በፊት ነበር።
በጎርጎረሳውያኑ አቆጣጠር March 13, 624 G.C መሆኑ ነው።
*
✔️የቁረይሽ ሙሽሪኮች ሙስሊሞችን አላስቀምጥ ብለው ከመካ አባረሯቸው።
ሙስሊሞቹ መካ ላይ ግፍ ሲበዛባቸው በየቦታው ተሰደቱ።
ወደ መዲናም ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር አቀኑ።
መዲና ላይ ሙስሊሞቹ ተመችቷቸው መቀመጣቸውን ያወቁ ጊዜ፣ ቁረይሾች አሁንም ከመዲና ማጥፋት አለብን ብለው ጦር ሰብቀው ተነሱ።
ለጦርነቱ በጣም ተዘጋጅተው ብዙ የጦር መሳሪያ ይዘዋል።
ሙስሊሞቹ ግን ምንም አልያዙም ከአላህ እርዳታ ውጭ።
በዚህ እለት እነ አቡበከር፣ ዑመር፣ ዓልይ፣ ሐምዛ፣ ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር፣ ዙበይር ኢብኑል አዋም፣ አማር ኢብኑ ያሲር፣ አቡዘር አልጚፋሪይና ሌሎችም ታላላቅ ሶሐቦች ተገኝተዋል።

👉ጦርነቱ ተጀመረ።
አላህ አማኞችን ረዳ።
ወደ አምስት ሺህ መላኢካዎችን አላህ ለሙስሊሞቹ ረዳት ሰጣቸው።
ከሙስሊሞቹ አስራ አራት ሶሐቦች ተገደሉ።
ከቁረይሽ ሙሽሪኮች ግን ወደ ሰባ የሚሆኑ አጋሪያን ተገደሉ።
||
በመጨረሻም ዲሉ ለሙስሊሞች ሆነ።
የመጀመሪያው መዕረካም ነበር። ከዚያን ጊዜ በፊት ሙስሊሞች የሚኖሩት እየተሰቃዩና እየተገፉ ነበር። አምልኮ የሚፈጽሙት ተደብቀውም ነበር።
የዚያን ቀን ጀምሮ ግን ይበልጥ አንገታቸውን ቀና አደረጉ። ልባቸው ይበልጥ በተስፋ ተሞላ። ወኔያቸው ጨመረ።
የአጋሪያኑን ትቢያነት አወቁ። ቀኑ ለሙስሊሞች ፈር ቀዳጅ ነበር።
ቀኑ የዲል ቀን ነው፣ ሁልግዜም ይዘከራል።
እለቱ ሐቅና ባጢል የለየበት የፉርቃን ቀን በመባልም ይታወቃል።
በሐዲሥ ላይ እንደመጣው አላህ የበድር ጦርነት ላይ የተሳተፉትን ጀነት እንደሚያስገባቸው ተነግሯል።

✍️ክስተቱን አላህ ቁርኣን ላይ እንዲህ ሲል አስፍሮታል፥
"በበድርም፣ እናንተ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ፤ አላህንም ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት።
ለምእመናን ጌታችሁ በሦስት ሺህ መላእክት የተወረዱ ሲሆን ቢረዳችሁ አይበቃችሁንም? በምትል ጊዜ (አስታዉስ)።
አዎን፣ ብትታገሡና ብትጠነቀቁ ከዚህም ፍጥነታቸዉ (ጠላቶቻችሁ) ቢመጡባችሁ፣ ጌታችሁ ምልክት ባላቸዉ፣ አምስት ሺህ መላእክትን ይረዳችኋል።
አላህም (እረዳታዉን) ለናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በርሱ እንዲረኩ እንጂ አላደረገዉም፤ ድልም መንሳት አሸናፊ ጥበበኛ በሆነዉ አላህ ዘንድ እንጅ ከሌላ አይደለም !!
(ድልን ያጐናጸፋችሁ) ከነዚያ ከካዱት ከፊልን ሊቆርጥ (ሊያጠፋ)፣ ወይም ሊያዋርዳቸዉን ያፈሩ ሆነዉ እንዲመለሱ ነዉ !!"
[አሉ ዒምራን፥ 123-127]
||

"ከጌታችሁ ርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ፣ እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲሆኑ እረዳችኋላሁ ሲል ለናንተ የተቀበላችሁን (አስታውሱ)።
አላህም (ይኽንን ርዳታ) ለብስራትና ልቦቻችሁ በርሱ ሊረኩበት እንጂ ለሌላ አላደረገውም፤ ድልም መንሳት ከአላህ ዘንድ እንጂ ከሌላ አይደለም፤ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና። "
[አል አንፋል፥ 9-10]
||
በጥቅሉ ከበድር ዘመቻ ብዙ የምንማረው አለን።
1) የበላይ ለመሆንና ዲልን ለመጎናጸፍ በቁጥር መብዛት አያስፈልግም።
በቁጥር በነበር ሙስሊሞች ከሙሽሪኮች በሶስት እጅ ያነሱ ነበሩ።
ዋናው ትክክለኛ እምነትና በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነ ቁርጥ ተመኪነት ነው።
*
2) አላህ ካልረዳህ በቁጥር ብትበዛም ትሸነፋለህ።
ለምሳሌ አጋሪያኑ ሶስት እጥፍ በቁጥር ይበልጡ ነበር።
*
3) ድል ለመጎናጸፍ የግድ ተወርዋሪ ሚሳኤልና የጦር ካምፕ ሊኖርህ አይገባም።
የቁረይሽ አጋሪያን በዘመኑ አለ የተባለን የጦር መሳሪያን ታጥቀው ተዘጋጅተው ነበር፣ ግን ተሸነፉ።
||
በአጠቃላይ፣ እኛ በገንዘብም ይሁን በጦር መሳሪያ ከከሐዲያን አንጻር ትንሽ ያለን ብንሆንም፣
እውነተኛ አማኝ ከሆንን እናሸንፋለን።
አለበለዚያ ግን ሁልጊዜም እንዋረዳለን፣ የፈለገ ያክል በቁጥር ብንበዛም፣ ተወንጫፊ ሚሳኤል ቢኖረንም ዋጋ የለውም።
||
አሁንም ቢሆን በዘመነኛ ነገሮች ከመለከፍ ተቆጥበን፣
የዚያን ዘመን ትውልድ አርአያችን እናድርግ።
የነርሱን ፈለግ እንከተል።

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ህይወትን ተመለከትኳት
ድንቅ ምክር በሼኽ ኻሊድ ራሺድ
አማርኛ ትርጉም

#ሼር #share
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
#ረመዷን_18

በዛሬው ተመሳሳይ ቀን ማለትም በሂጅራ አቆጣጠር በ21ደኛው አመት በረመዷን በ18ተኛው ቀን ላይ ነበር ... ታላቁ የጦር መሪ "ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ" (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ይችን ዓለም የተሰናበቱት።
#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ኢዕቲካፍ
ኢዕቲካፍ፡- ድንጋጌው፣ መስፈርቶቹ፣ የሚያበላሹት እና ጊዜው
ኢዕቲካፍ፡- ድንጋጌው፣ መስፈርቶቹ፣ የሚያበላሹት እና ጊዜው


ጥያቄ፡- ብዙ ጊዜ ኢዕቲካፍ የማድረግ ልምድ ቢኖረኝም በተጨባጭ ስለኢዕቲካፍ የማላውቃቸው ነገሮች ሞልተዋል። በኢዕቲካፍ ወቅት የሚፈቀድልኝ ነገሮች ምንድን ናቸው? በኢዕቲካፍ ወቅት ሐራም የሚሆኑብ ነገሮችስ ምንድን ናቸው? ለስራ እየወጣሁ ተመልሼ መግባት እችላለሁ?…

መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ

ኢዕቲካፍ ወደ አላህ የሚያቃርብ መልካም ተግባር ነው። ሱናም ነው። በተለይም በረመዷን ውስጥ እጅግ ከሚወደዱ ተግባራት መሀል አንዱ ነው። በተለይም ደግሞ በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት እጅግ የጠበቀ ሱና ነው። ምክንያቱም ለይለቱል-ቀድር (የውሳኔዋ ለሊት) ያለችው በእነዚህ አስርት ቀናቶች ውስጥ ነውና።

ኢዕቲካፍ እንደማንኛውም አምልኮ መስፈርቶች (ሹሩጥ)፣ ስነስርዐቶች (አዳብ)፣ የሚያፈርሱት ነገሮች እና በውስጡ የሚፈቀዱ ነገሮች አሉት።

በፊሊስጢን ውስጥ በሚገኘው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ኡስታዝ፣ ዶክተር ሳሊም አሕመድ ሰላማ እንዲህ ብለዋል፡-

ኢዕቲካፍ ማለት፡-
በቋንቋ ትርጉሙ አንድን ነገር አጥብቆ መያዝ ማለት ነው። በሸሪዓ ትርጓሜው ደግሞ መስጂድን አለመልቀቅ፣ ወደ አላህ ለመቃረብ በሚል ኒያ እርሱ ውስጥ መቆየት ማለት ነው።

የኢዕቲካፍ ድንጋጌ
ኢዕቲካፍ በሸሪዓው ውስጥ የተደነገገ ስለመሆኑ በዑለሞች መካከል ስምምነት አለ። ኢዕቲካፍ ስለጾም የተጠቀሱ አንቀጾች መሀል በቁርኣን ውስጥ ተጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَلَا تُبَاشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَاكِفُونَ فِي الْمَسَاجِدِ
“እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው፡፡” (አል-በቀራ 2፤ 187)

ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ.) የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ላይ ኢዕቲካፍ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ባረፉበት የመጨረሻው ዓመት ላይ ግን- አቡሁረይራ እንዲህ ይላሉ- “የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) በረመዷን አስርት ቀናት ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ባረፉት አመት ላይ ግን ሃያ ቀናት ኢዕቲካፍ አድርገዋል።”

የኢዕቲካፍ ብይኑ (ሁክም)፡-
ኢዕቲካፍ ወደ አላህ የሚያቃርብ ሱና የአምልኮ ዘርፍ ነው። በተለይም በረመዷን ጥብቅ አምልኮ ነው። በተለይም በመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ውስጥ በጣም የጠበቀ ሱና ነው። ምክንያቱም በእነዚህ አስርት ቀናት ውስጥ ለይለቱል-ቀድር ትገኛለች። ነገርግን ስለት ባደረገ ሰው ላይ ግዴታ ይሆናል። ማለትም ሰውየው ኢዕቲካፍ ለማድረግ ከተሳለ ዋጂብ ይሆናል።

የኢዕቲካፍ ሸርጦች፡-
ሙስሊም መሆን
አዕምሮ ጤነኛ መሆን
የመለየት እድሜ (ተምዪዝ/ስድስት ወይም ሰባት ዓመት መሙላት)
ኒያ ማድረግ
መስጂድ ውስጥ መሆኑ
ከወር አበባ፣ ከድህረ ወሊድ ደም እና ከጀናባ ንፁህ መሆን
በኢዕቲካፍ ወቅት የሚወደዱ ነገሮች (ሙሰታሃባት)፡-
የአምልኮ ተግባራት ማብዛት። ሶላት፣ ቁርኣንን ማንበብ፣ የዒልም ሰዎችን መፅሀፍት ማንበብ፣ በመስጂዱ ውስጥ የሚሰጡ ምክሮችን እና ትምህርቶችን መከታተል።
ዋዛ ነገርን (ማላ የዕኒን) መተው። ከክርክር፣ ከስድድብ፣ ከትችት፣ ከሃሜት እና ነገር ከማሳበቅ መራቅ።
በመስጂዱ ውስጥ አንድ ስፍራን አጥብቆ መያዝ። ቦታ አለመቀያየር።
በኢዕቲካፍ ወቅት የሚፈቀዱ ነገሮች (ሙባሃት)፡-
የግድ ለሆኑ ጉዳዮቹ መውጣት። ለምሳሌ፡- ለመፀዳዳት፣ ህመም ላይ ካለ ለህክምና፣ ኢዕቲካፍ ያደረገበት መስጂድ ጁሙዓ የማይሰገድበት ከሆነ ጁሙዐ ለመስገድ…
መስጂድ ውስጥ መብላት፣ መጠጣት እና መተኛት ይችላል። ነገርግን የመስጂዱን ንፅህና መበከል ሐራም ነው።
የሚፈቀዱ ንግግሮችን መናገር ይቻላል።
ፀጉር ማበጠር፣ ጥፍር መቁረጥ፣ አካሉን ማፅዳት፣ ጥሩ ልብስ መልበስ እና ሽቶ መቀባትም ይቻላል።
በኢዕቲካፍ ጊዜ የሚጠሉ ነገሮች (መክሩህ)፡-
መሸጥና መግዛት
ኃጢያት ያለበትን ነገር መናገር
አምልኮ ነው ብሎ አስቦት ከሆነ ዝም ማለት
ኢዕቲካፍን የሚያፈርሱት ነገሮች (ሙብጢላት)፡-
አውቆ- ያለጉዳይ- ከመስጂድ መውጣት
ወሲብ መፈፀም
በእብደት ወይም በስካር አዕምሮን መሳት
የወር አበባ እና የድህረ ወሊድ ደም መከሰት
አላህ ይጠብቀንና ከኢስላም መውጣት (ሪድ-ዳ)
የኢዕቲካፍ መጀመሪያ እና መጨረሻው፡-
ሰውየው ወደ መስጂድ ገብቶ ኢዕቲካፍ መስጂድ ውስጥ በመቆየት ወደ አላህ ለመቃረብ ከነየተ እስከሚወጣ ድረስ ኢዕቲካፍ ላይ እንዳለ ይቆጠራል። የመጨረሻዎቹን አስርት የረመዷን ቀናት ኢዕቲካፍ ለማድረግ ከነየተ ኢዕቲካፍ ወደሚያደርግበት ስፍራ በአስራ ዘጠነኛው ቀን ፀሃይ ከመጥለቋ በፊት መግባት አለበት። ሲወጣም የወሩ መጨረሻ ላይ ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ- ማለትም በዒድ ለሊት- መውጣት አለበት።

የኢዕቲካፍ ጥቅሙ፡-
ኢዕቲካፍ ማድረግ የነብዩን ሱና ህያው ማድረግ ነው። ተከታታይ የአምልኮ ተግባራት ላይ በማሳተፍም ልብን ህያው ያደርጋል። ሰውየው ከራሱ ጋር የመገለል እና እስትንታኔ የማድረግ እድል ያገኝበታል። ያለፈውን ሂደቱን ገምግሞ እርምት ለመውሰድ እና መጪውን ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ወደ አላህ የመቅረብ ወኔ እንዲያገኝ ያስችለዋል። ኢዕቲካፍ የልብ ብርሃን ነው። ብዙ መልካም ነገሮች ያስገኛል። በአላህ እዝነትም ከፍታና ደረጃንም ይጨምራል። በተለይም በአስርቱ የረመዷን የመጨረሻ ቀናት ሲሆነ ለይለቱል-ቀድርን ያስገኛል። ለይለቱል-ቀድርን ያገኘ ሰው ከአንድ ሺህ በላይ የሆኑ ወራትን አግኝቷል።

አላሁ አዕለም!

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ለይለቱል ቀድር

ጥያቄ፡ ያለሁበት ለሊት ለይለቱል ቀድር መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? ይህን የተከበረ ለሊት እንዴትስ ላሳልፍ? ሶላት በመስገድ ወይስ ቁርአን በመቅራት?

መልስ፡ ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሒም

ለይለቱል ቀድርን (የውሳኔዋን ለሊት) ህያው ማድረግ እንደሚወደድ የሚጠቁሙ ብዙ ሐዲሶች ተዘግበዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

”من قام رمضان إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه “ ”ومن قام ليلة القدر إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه“

“(የአላህን ቃልኪዳን) እያመነና (ምንዳውን) እየተሳሰበ በረመዳን ለሊት የቆመ (የሰገደበት) ሰው ያሳለፈውን ወንጀል በሙሉ ይማራል።” “(የአላህን ቃልኪዳን) እያመነና (ምንዳውን) እየተሳሰበ ለይለቱል ቀድርን የቆመ (የሰገደበት) ሰው ያሳለፈውን ወንጀል በሙሉ ይማራል።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ለይለቱል ቀድር የተባረከ ለሊት ነው። አላህ ወህይ (ራእይ) ለማውረድ መርጦታል። አላህ እንዲህ ይላል፡-

حم * وَالْكِتَابِ الْمُبِينِ * إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ

 

“ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡ እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡” (አድ-ዱኻን 44፣ 1-3)

አላህ በዚህ አንቀፅ ውስጥ በመፅሀፉ (በቁርአን) ይምላል። በተባረከ ለሊት እንዳወረደውም ይናገራል። ይች ለሊትም ለይለቱል ቀድር ናት።

ለይለቱል ቀድር የተለያዩ ምልክቶች አሏት። በርሷ ውስጥ ሙስሊሞች የሚጠመዱባቸው የተለያዩ ሥራዎችም አሉ። በዚያ ቀን የሚሠሩ አምልኮዎችም ሌላ ጊዜ ከሚሠሩት ይበልጥ የላቀ ክብርና ደረጃ ያስገኛሉ።

ከለይለቱል ቀድር ምልክቶች መሀል የተወሰኑትን እንጥቀስ። ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ፈታዋ አል-ኩብራ ላይ እንዲህ ይላሉ፡-

“ለይለቱል ቀድር ከረመዳን የመጨረሻው አስር ቀናት ላይ የሚከሠት አንድ ለሊት እንደሆነ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተነግሯል። ‘ከረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ነው ያለችው።’ ብለዋል፤ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)። በአስሩ የረመዷን ወር የመጨረሻ ቀናት በነጠላ የሚቆጠሩት ቀናት ላይ እንደሆነችም የሚጠቁሙ ሐዲሶችም እንዲሁ ተዘግበዋል። ነጠላነት ግን ካለፉት የረመዳን ቀናት ወይም ከሚቀሩት የረመዳን ቀናት አንፃር ሊታይ ይችላል። ስለዚህ ካለፈው አንፃር ካየነው ሀያ አንደኛው፣ ሀያ ሦስተኛው፣ ሀያ አምስተኛው፣ ሀያ ሠባተኛው እና ሀያ ዘጠነኛው ቀን ይበልጥ ለይለቱል ቀድር ሊሆኑ እንሚችሉ ይጠረጠራሉ። እነዚህ ብዙዎች የሚጠብቁበት አቆጣጠር ነው። ይሁንና የቀሩትን የረመዷን ቀናት በማሰብ ልንቆጥርም እንችላለን። ምክንያቱም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

لتاسعة تبقى لسابعة تبقى لخامسة تبقى لثالثة تبقى

“እርሷ በሚቀሩት ሰባት፣ አምስት፣ ሦስት… ቀናት ውስጥ ትሆናለች።”

በዚህ መሠረት ወሩ ሠላሳ ቀን ከሆነ ከታች ወደ ላይ ሲቆጠር ጥንድ ቀናት የሚሆኑት ለሊቶች ከላይ ወደ ታች ሲቆጠር ለይለቱል ቀድር ሊሆኑ ይችላሉ። ማለትም ሀያ ሁለተኛው ለሊት ዘጠኝ ቀናት የሚቀሩት ለሊት ሊሆን ቻለ። ስለዚህ ሀያ አራተኛው ቀን ደግሞ ሰባት ቀናት የሚቀሩት ለሊት ሆነ… እያልን ልንሄድ ነው። ታላቁ ሶሐባ አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረ.ዐ)- በሶሒሕ እንደተዘገበው- ያለፈውን ሐዲስ በዚህ መልኩ ተረድተውታል።

በዚሁ መሠረት ወሩ በሀያ ዘጠኝ ካበቃ ደግሞ ሒሳቡ ከዚህ በፊት ከተጠቆሙት ቀናት ጋር ተመሳሳይ ቀናት ላይ ለይለቱል ቀድርን ልንጠብቅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ሙስሊም ሁሉ የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ለይለቱል ቀድርን በሙሉ ንቃት መጠበቅ ይገባል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “አስሩ የመጨረሻ ቀናት ላይ በንቃት ጠብቋት!” ብለዋል። በተለይም የመጨረሻዎቹ ሰባት ቀናት ላይ መጠበቁ በጣም ይጠነክራል። በተለየ ሁኔታ ደግሞ ሀያ ሰባተኛው ለሊት እንደሆነች ኡበይ ኢብኑ ከዕብ (ረ.ዐ) ይነግሩናል። ‘እንዴት አወቁ?’ ተብለው ቢጠየቁ ‘ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በነገሩን ምልክት ነዋ። የእርሷ (የለይለቱል ቀድር) ንጋት ላይ ፀሀይ ልብስ እንደሚታጠብበት ሳፋ (ጠሽት) ንፁህና ደካማ ሆና ትወጣለች። ሲሉ መልእክተኛው ነግረውናል።’

ኡበይ ኢብኑ ከዕብ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዘው የነገሩን ይህ ምልክት የታወቀ የለይለቱል ቀድር ምልክት ነው። ለሊቷ መሀለኛ የአየር ሁኔታ ያላትና ብርሀን ያላት መሆኗ ሌሎች ምልክቶች ናቸው። በእርግጥም አላህ ለአንዳንድ ሠዎች በመናም (በህልም) ሊያሳውቃቸውና ብርሀኗን ሊያሳያቸው ይችላል። ይህ ለይለቱል ቀድር ነው ብሎ የሚነግራቸው ሠው ሊልክባቸው ወይም ልቡን ከፍቶለት እውነት ለይለቱል ቀድር መሆኗን የሚለይበት ነገር ልቡ ውስጥ ሊጥልበት ይችላል።” የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር እዚህ ላይ አበቃ።

በእለቱ የሙስሊሞች ሥራ ምን መሆን አለበት?

ለሊቱ የተባረከ ለሊት ነው። ከአንድ ሺህ ወራት በላይ ዋጋ ያለው ለሊትም ነው። አላህ -ልክ ጁምዓ ውስጥ ያለችውን፣ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝባትን ውድ ሰዓት እና ታላቁን ስሙን (ኢስሙል አዕዘምን) እንደደበቀ ሁሉ- ለይለቱል ቀድርንም ደብቋታል። የመደበቃቸው ምስጢርም ሠዎች እነሱን ለማግኘት እንዲጥሩ ለማድረግ ነው። በእርግጥ ለይለቱል ቀድር መች እንደሆነ በውል ባይታወቅም አስሩ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ መሆኑን አሳልፈናል። ስለዚህ እርሷን ለማግኘት አስሩን የመጨረሻ ቀናት ለሊቶች በሙሉ በዚክር፣ በዱዓ፣ ቁርአን በመቅራት፣ ሶላት በመስገድ… ማሳለፍ ያስፈልጋል።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስሩ የመጨረሻ የረመዳን ቀናት ውስጥ -ከምንም ጊዜው በላይ- ለዒባዳ ይጠነክራሉ። ቁርኣን ያነባሉ። ሶላት ያበዛሉ። ዱዓ ላይ ይጠነክራሉ። ቡኻሪ እና ሙስሊም አዒሻን (ረ.ዐ) ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት:-

أن النبي صلى الله عليه وسلم كان إذا دخل العشر الأواخر أحيا الليل وأيقظ أهله وشد المئزر

“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስሩ የረመዳን የመጨረሻ ቀናት በሚገቡ ጊዜ ለሊቱን ህያው ያደርጋሉ። ቤተሰቦቻቸውን ያነቃሉ። ሽርጣቸውን ያጠብቃሉ።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

በአህመድና በሙስሊም ዘገባ:-

كان يجتهد في العشر الأواخر ما لا يجتهد في غيرها

“መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) በሌላ ጊዜ ከሚያደርጉት አምልኮ በላቀ ሁኔታ በእነዚህ አስር ቀናት ውስጥ ያደርጋሉ።” (አህመድና ሙስሊም ዘግበውታል)

ለይለቱል ቀድርን እንድንጠብቅ የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) ብዙ ጊዜ ቅስቀሳዎችን አድርገዋል። ከሰዪዲና አቡሁረይራህ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “(የአላህን ቃልኪዳን) እያመነና (ምንዳውን) እየተሳሰበ ለይለቱል ቀድርን የቆመ (የሰገደበት) ሰው ያሳለፈውን ወንጀል በሙሉ ይማራል።” ስለዚህ ይህ ሐዲስ ለሊቱን በሶላት ማሳለፍ እንሚወደድ እያስተማረ ነው።

ያን ቀን ዱዓ እንድናደርግ የሚቀሰቅሱ ሐዲሶችንም እናገኛለን። ቲርሚዚ አዒሻን (ረ.ዐ) ዋቢ አድርገው ባስተላለፉት ሐዲስ

قلت: يا رسول الله، أرأيت إن علمت أي ليلة ليلة القدر ما أقول فيها؟ قال: قولي: اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني
“የአላህ መልእክተኛን (ሰ.ዐ.ወ) ለይለቱል ቀድርን ካወኩኝ ምን ብዬ ዱዓ ላድርግ? ብዬ ጠየኩኝ። እርሳቸውም ‘አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ። ይቅርታንም ትወዳለህ። ይቅር በለኝ!፤ በይ’ አሉኝ።” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

አላህ የተሻለ ያውቃል!

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
Gize ye Allah stota nw be agebabu myaz yegna gdeta nw yalefut kenat alefu be krut kenay enberta teketari demoz mikefelew ye weru magebadja lay mehonun anzenga
ye tsomu alama ke mgb na wha takbo mwalu sayhon Allahn mfrat nw ke wenjeloch mrak na be ibada mtenaker yasfelgal
Resul s.a.w endih blewal jenet wst reyan yemibal ber ale ye kyama elet tsomegnoch besu ygebalu... Allah kenesu yadrgen

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🔎~ለይለቱል ቀድር~🖇
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱
:አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል ቀደር ላይ እንዲህ ብሏል፦
▽▽▽➷
إِنَّا أَنْزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ)) القدر: ١))
እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡

وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ)) القدر: ٢))
መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?

لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِنْ أَلْفِ شَهْرٍ)) القدر: ٣))
መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡

تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِمْ مِنْ كُلِّ أَمْرٍ)) القدر: ٤))
በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡

سَلَامٌ هِيَ حَتَّى مَطْلَعِ الْفَجْرِ)) القدر: ٥))
እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡
△△△➹
📖:በዚህ አያ ለይለቱል ቀድር ከሺ ወራቶች በላይ በላጭ እንደሆነች ተገልፃል። ታዲያ ማነው ከእኛ መካከል ይችን ሌሊት በኢባዳ በማሳለፍ የዚችን ሌሊት ሙሉ በረካዋን ለማግኘት የሚተጋ? ኢንሻአላህ አላህ ያሳካልናል

📗:በሰኺህ ሙስሊም በተዘገበው ሐዲስ ነብዩ(ﷺ) በመጨረሻዎቹ አስር ሌሊቶች ለይለቱል ቀድርን ሻቱ (ፈልጉ) ብለዋል።

🖊:በመጨረሻዎቹ የረመዷን ምሽቶች አብዝተን ቁርአን መቅራት ፣ አሏህን ማውሳት እና ዱአ ማብዛት ይኖርብናል። ምክኒያቱም የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ሶደቃ ወይም ዘካ የምንሰጥበት ፣ ነፍስያችነን የምንመረምርበት ፣ ዱአ አብዝተን የምናደርግበት ፣ መሃርታን የምንለምንበት ፣ ፆማችንን ሙሉ የምናደርግበት ጊዜ ነውና።

📌:በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ጥረታችነን ወይም ኢባዳችነን እጥፍ እናደርግ ዘንድ አሏህ(ﷻ) የለይለቱል ቀድር ቀን መቼ እንደሆነ ደብቆታል።

➥:ነብዩ(ﷺ) በለይለቱል ቀድር አምኖበትና ከአሏህ ምንዳ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ ለሶላት የቆመ ሰው ያለፉት ወንጀሎቹ ሁሉ ይማሩለታል ብለዋል።

📗:በሰኺህ ሙስሊም በተዘገበው ሐዲስ ነብዩ (ﷺ) ከሌላው ጊዜ በበለጠ በመጨረሻዎቹ አስር ሌሊት በኢባዳ ላይ ይተጉ ነበር።

➯:በዚህ ጊዜ ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግኑኝነት በመገደብ ዱአቸውን ያጧጡፉ ነበር። ነብዩ(ﷺ) ይህን ያደርጉ የነበረው ልባቸው የበለጠ አሏህ ጋር እንዲሆንና ህሊናቸውን ከአለማዊ ጉዳይ ለማላቀቅ ነበር።

📘:በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ የረመዷን የመጨረሻዎቹን አስር ቀናት መጀመሩን ተከትሎ ነብዩ(ﷺ) ጠንክረው ይሰራሉ፤ ሌሊቱን ሙሉ ሶላት ይሰግዳሉ። ቤተሰባቸውንም ለሶላት ይቀሰቅሱ ነበር።
💫💫
ለ አሽረል አዋኺር መረሳት የሌለባቸው 3 ነገሮች
💞💞
-ለመስራት ቀላል
-ቦታ የማይመርጡ
-ጊዜ የማይወስዱ
-ትልቅ አጅር የሚያስገኙ
💞💞

💌በየቀኑ ከኢሻዕ ቡሃላ ቢያንስ 1ብር ሰደቃ ላገኘነው ድሀ መስጠት
💮1ዱ ለሊት ለይለቱል ቀድር ላይ ስለምንሰጥ 84 ዓመት ሙሉ ሰደቃ የሰጠን ያህል ይፃፍልናል

💌ሁለት ረከዐ በየለሊቱ መስገድ
💮ለይለቱል ቀድር ላይ 84 ዓመት ሙሉ ለይል እንደቆምን ይፃፍልናል

💌ሱረቱል ኢኽሏስ 3 ጊዜ መቅራት
💮ሱረቱል ኢኽላስ 3 ጊዜ የቀራ ሰው ቁርአን ሙሉ እንደቀራ ይቆጠራል፡ ለይለቱል ቀድር ላይ ስንቀራ 84 ዓመት ቁርዓን እንዳከተምን ይፃፍልናል

💥ሱብሀነላህ!!

ይሄን ቪዲዮ ቢያንስ ለ30 በመላክ ተጠቃሚ አንዲሆኑ አድርጉ

Share
2025/07/06 20:38:48
Back to Top
HTML Embed Code: