Telegram Web Link
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#ምርጦች

ኢብን መስኡድ እንዲህ ይላሉ አላህ ከቀናት አራት , ከወራት አራት ከሴቶች አራት, የጀነት ቀዳሚዎችን አራት, ጀነት የምትናፍቃቸውን አራት ሰዎች መርጧል
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🗓ከቀናት
1— የጁምዐ እለት
2— የዐረፋ እለት
3— የውመ ነህር( የእርድ ቀን)
4— የውመል ፊጥር( የረመዳን ዒድ)
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

📆ከወራት
1—ረጀብ
2—ዙልቂዕዳ
3—ዙልሂጃ
4—ሙሀረም
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🌷ከሴቶች
1—መርየም ቢንት ዒምራን
2— ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ
3— አሲያ ቢንት ሙዛሂም
4— ፋጢመቱ ዛህራእ ቢንት ሙሀመድ
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

⚡️የጀነት ቀዳሚዎች
1— ሀቢቢ ሙሀመድ (ሰዐወ) የአረቦች ቀዳሚ
2—ሰልማን የፋርስ ቀዳሚ
3—ሱሀይብ የሮም ቀዳሚ
4— ቢላል የሀበሻ ቀዳሚ
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

ጀነት የናፈቀቸቻቸው
1—ዐሊ ኢብን አቢጧሊብ
2—ሰልማነል ፋሪሲ
3—ዐማር ኢብን ያሲር
4—ሚቅዳድ ኢብን አስወድ



🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#Share #ሼር
#join

Https://www.tg-me.com/smithhk
የዙልሒጃ ወር ነገ ሰኞ  አንድ ብሎ ይጀምራል!

የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሰኔ 21 ዕለተ ረቡዕ እንደሚከበር ታውቋል!

ዛሬ እሁድ ሰኔ 11/Jun18/2023 በሂጅሪያ አቆጣጠር ደግሞ  ዙልቀይዳ 29  በሳዑዲ አረቢያ አዲስ ጨረቃ በመታየቷ የዙልሂጃ ወር  በነገው እለት ሰኞ  ሰኔ 12/june 19  አንድ ብሎ እንደሚጀመር  ታውቋል::

የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልም እሮብ ሰኔ 21/2015/June 28/2023 እለተ ረቡዕ እንደሚውል ታውቋል፡፡

ከነገ ሰኞ ሰኔ 12/June 19  ጀምሮ እስከ ሰኔ 21/june 28 ድረስ ያሉትን 10 ቀናት በኢባዳ ልናሳልፋቸው ይገባል፡፡

የዙልሂጃን ዘጠኙንም ቀናት ለመፆም ፍላጎት ያለው ከነገ ሰኞ ሰኔ  12 /2015  ጀምሮ መፆም ይችላል፡፡

ታላቅ ምንዳ የሚያስገኘውን የዙልሒጃ 9 (የአረፋን ቀንን) ለመፆም የሚፈልግም ሰኔ  20/june27/2023  እለት ማክሰኞ መፆም ይችላል::

ኡዱሂያ ለማረድ ኒያው ያላችሁ ካሁን ሰዓት ጀምሮ ጥፍራችሁን እና ፀጉራችሁን ከመቆረጥ ታቀቡ!

ከነገ ሰኞ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ አስር ቀናቶች በኢባዳ እናሳልፋቸው!
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

አሥሩ የዙል-ሒጃ ቀናት
*******
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ
****
አላህ ሲያስብልን፣ ሲወደን እና ሊጠቅመን ሲፈልግ ምንዳዉና ችሮታው የሚነባበርባቸዉን ቀናትና ጊዜያት ጠቆመን፡፡
አስተዋይ ልቦና የሠጠው ሰው በትኩረት ይጠቀምባቸዋል፡፡ እንደዋዛ አያሳልፋቸዉም፡፡

አሥሩ ምርጥ ቀናት ነገ ሰኞ ይጀምራሉ፡፡ ስለ ምርጥነታቸው በቁርኣን ተመስክሮላቸዋል፣ አላህ ምሎባቸዋል፣ የአላህን ቤት ጎብኝዎችም ወደተከበረዉና የተቀደስው ሥፍራ መካ እና ዙርያው በመጉረፍ የሐጅን ሥርዓት ያከናዉኑባቸዋል፡፡

በቀናቱ ዉስጥ  መሥራት እንችላለን?
1- ከልብ ተፀፅቶ ወደ አላህ መመለስ፤
2- አላህን ማውሳት ማብዛት፣
3- መፆም፣
4- ኢስቲግፋር ማብዛት፣
5- መመጽወት
6- ዱዓእ ማድረግ፣
7- ሶላትን በወቅቱ መስገድ፣
8- ከኃጢኣት መራቅ፣
9- ስለ ቀናቱ ምርጥነትና እንዲጠቀሙባቸው ሌሎችን ማስታወስ፣
10- በነቢዩ ላይ ሶላዋት ማውረድ፣
11- መልካም ሥራዎችና ንግግሮች ለምሳሌ - ወደ አላህ መንገድ መጣራት፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ለጎረቤት መልካም መዋል፣ ወላጆችን ማስደሰት፣ አስቸጋሪን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ፣ የታመሙትን መጎብኘት፣ ለሙታን ዱዓ ማድረግ፣ ወንድም እህቶችን በሌሉበት በዱዓ ማስታወስ፣ የባለዕዳን ዕዳ መሰረዝ፣ የተቸገረን መርዳት፣ የታሠረን መጠየቅ፣ ሰዎችን አለማስቸገር፣ ቤተሰብን መንከባከብ፣ ለሠራተኞች ማዘን ...ሌሎችም ።

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

ሁሉም ዜሮ!
🔹🔹🔹🔹🔹

🔹ሀብታም ቢሆን ዱንያው አምሮ
🔹ዶክተር ቢሆን ተመራምሮ
🔹ቆንጆ ሴት ጋር ቢኖር አብሮ
🔹ልጆች ቢወልድ ትዳር ሰምሮ
🔹ንጉስ ቢሆን ምድርን ዞሮ
🔹ያለ ኢስላም ሁሉም ዜሮ

ሁሉም ባዶ!!
🔹🔹🔹🔹🔹

🔹ምን ቢለፋ ኸይርን ወዶ
🔹ቀኑን ቢፆም ለይሉን ሰግዶ
🔹ሁሉን ቀድሞ ቢጓዝ ማልዶ
🔹ሀጅ ቢያደርግ መካ ሄዶ
🔹ያለ ተውሂድ ሁሉም ባዶ

ሁሉም መና!!!
🔹🔹🔹🔹🔹

🔹ሌት ተቀን ለፍቶ ምን ቢፀና
🔹ቢኖረውም ቅን ልቦና
🔹ኒያው አድጎ ምን ቢቃና
🔹ቢደጋግም በምርቃና
🔹ቢያሳምረው እንደገና
🔹ያለ ሱና ሁሉም መና

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

الله اكبر الله اكبر الله اكبر لا اله الا الله الله اكبر الله اكبر ولله الحمد ...
በእነዚህ ውድ በሆኑ ቀናት እነዚህን ውብ የሆኑ ተክቢር ተህሊል እና ተህሚድ ማለት እናብዛ እነዚህን ውድ ቀኖች ድጋሚ ላንታደላቸው እንችላለን እና እንበርታ
❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️
በነዚህ ውብ እና ውድ በሆኑ ቀኖች በዚህች ባማረችዋ ቀን በካህፍ በሰለዋት በዱአ በአዝካር በሰደቃ የተዋበ እና በተክቢራ የፈካ ጁምዓ ይሁንልን!!!

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

لَبَّيْكَ اللَّهُمَّ لَبَّيْكَ،
ለበይክ አላሁምመ ለበይከ
አቤቱ አላህ ሆይ፣ አቤቱ

لَبَّيْكَ لاَ شَرِيكَ لَكَ لَبَّيْكَ،
ለበይክ ላሸሪከለከ ለበይክ
አቤቱ አጋር የለህም

إِنَّ الْحَمْدَ،
ኢነል ሐምደ
አቤቱ ምስጋና ላንተ ነው

وَالنِّعْمَةَ،
ወኒእመተ
ጸጋ ሁሉ ካንተ ነው

لَكَ وَالْمُلْكَ،
ለከወልሙልክ
የሁሉም ነገር የበላይነት ስልጣንም ያንተ ነው

لاَ شَرِيكَ لَكَ
ላሸሪከለክ
አጋር የለህም

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
Forwarded from سعيد علي حبيب
• باب في فضل يوم عرفة.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

قالت أم المؤمنين أم سلمة رضي الله عنها :

نِعمَ اليومُ يومُ عَرَفَةَ ، يَنزِلُ فيهِ رَبُّ العِزَّةِ إلى السماءِ الدُّنيا.

الرد على الجهمية للدارمي.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن أم المؤمنين أم سلمة رضي الله عنها قالت :

نِعمَ اليومُ يومٌ يَنزِلُ اللهُ فيهِ إلى السماءِ الدُّنيا.

قالوا : يا أُمَّ المُؤمِنين ، وأيُّ يومٍ هو؟. قالت :

يومُ عَرَفَةَ.

النزول للدارقطني.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن أم المؤمنين عائشة رضي الله عنها قالت :
إن رسول الله ﷺ قال :

"مَا مِنْ يَوْمٍ أكْثَرَ مِنْ أنْ يُعْتِقَ اللهُ فِيهِ عَبْدًا مِنَ النَّارِ مِنْ يَوْمِ عَرَفَةَ ، وَإنَّهُ لَيَدْنُو ثُمَّ يُبَاهِي بِهِمُ المَلَائِكَةَ فَيَقُولُ : مَا أرَادَ هَؤُلَاءِ؟".

صحيح مسلم.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن عبدالله بن عمرو رضي الله عنهما ،
أن النبي ﷺ كان يقول :

"إنَّ اللهَ عَزَّ وَجَلَّ يُبَاهِي مَلَائِكَتَهُ عَشِيَّةَ عَرَفَةَ بِأهْلِ عَرَفَةَ فَيَقُولُ : انْظُرُوا إلَى عِبَادِي أتَوْنِي شُعْثًا غُبْرًا".

مسند أحمد.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن عبدالله بن عمرو رضي الله عنهما ،
أن النبي ﷺ قال :

"خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي : لَا إلَهَ إلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ ، لَهُ المُلْكُ وَلَهُ الحَمْدُ ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ".

جامع الترمذي.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن طارق بن شهاب رضي الله عنه قال :
قال رجُلٌ من اليهودِ لِعُمَرَ : يا أميرَ المُؤمِنِين ، لَو أنَّ علينا نَزَلَت هذهِ الآيةُ : ﴿الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الإِسْلامَ دِينًا﴾ لَاتَّخَذنا ذلك اليومَ عيدًا ، فقال عُمر :

إنِّي لَأعلَمُ أيَّ يَومٍ نَزَلَت هذهِ الآيةُ ، نَزَلَت يومَ عَرَفَةَ في يومِ جُمُعَةٍ.

صحيح البخاري.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

قالت أم المؤمنين عائشة رضي الله عنها :

ما مِنَ السَّنَةِ يومٌ أحَبُّ إلَيَّ أن أصومَهُ مِن يومِ عَرَفَةَ.

مصنف ابن أبي شيبة.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن أبي قتادة الأنصاري رضي الله عنه قال :
قال رسول الله ﷺ :

"صَوْمُ يَوْمِ عَرَفَةَ يُكَفِّرُ سَنَتَيْنِ : مَاضِيَةً وَمُسْتَقْبَلَةً".

مسند أحمد.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن أبي قتادة الأنصاري رضي الله عنه ،
أن رسول الله ﷺ قال :

"صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أحْتَسِبُ عَلَى اللهِ أنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ".

صحيح مسلم.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

قال إبراهيم النخعي :

كانوا يُكَبِّرون يومَ عَرَفَةَ وأحَدُهُم مُستَقبِلٌ القِبلَةَ في دُبُرِ الصلاةِ :
اللهُ أكبرُ اللهُ أكبرُ ، لا إلَهَ إلَّا اللهُ ، واللهُ أكبرُ اللهُ أكبرُ ، ولِلهِ الحَمدُ.

مصنف ابن أبي شيبة.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن ابن عباس رضي الله عنهما أنهُ كان يُكَبِّرُ من صلاةِ الفجرِ يومَ عَرَفَةَ إلى آخِرِ أيامِ التَّشريقِ ، يقول :

اللهُ أكبرُ كبيرًا ، اللهُ أكبرُ كبيرًا ، اللهُ أكبرُ وأجَلُّ ، اللهُ أكبرُ ولِلهِ الحَمدُ.

مصنف ابن أبي شيبة.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن عمر بن الورد قال : قال لي عطاء :

إنِ استَطَعتَ أن تخلُوَ بِنفسِك عَشِيَّةَ عَرَفَةَ فافعَل.

زوائد الزهد لعبدالله بن أحمد.

ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ ـــ ـــ ـ

عن ابن عمر رضي الله عنهما أنه كان عَشِيَّةَ عَرَفَةَ يدعُو ويرفعُ صَوتَهُ :

لَا إلَهَ إلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ ، لَهُ المُلْكُ وَلَهُ الحَمْدُ ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ.
اللَّهُمَّ اهْدِنَا بِالهُدَى ، وَزَيِّنَّا بِالتَّقْوَى ، وَاغْفِرْ لَنَا فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى.

ثُم يخفِضُ صَوتَهُ ثُم يقول :

اللَّهُمَّ إنِّي أسْألُكَ مِنْ فَضْلِكَ وَعَطَائِكَ رِزْقًا طَيِّبًا مُبَارَكًا ، اللَّهُمَّ إنَّكَ أمَرْتَ بِالدُّعَاءِ وَقَضَيْتَ عَلَى نَفْسِكَ بِالاسْتِجَابَةِ وَأنْتَ لَا تُخْلِفُ وَعْدَكَ وَلَا تَكْذِبُ عَهْدَكَ ، اللَّهُمَّ مَا أحْبَبْتَ مِنْ خَيْرٍ فَحَبِّبْهُ إلَيْنَا وَيَسِّرْهُ لَنَا ، وَمَا كَرِهْتَ مِنْ شَيْءٍ فَكَرِّهْهُ إلَيْنَا وَجَنِّبْنَاهُ ، وَلَا تَنْزِعْ عَنَّا الإسْلَامَ بَعْدَ إذْ أعْطَيْتَنَا.

الدعاء للطبراني.

منقول
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

ሙሐረም 1445 ዓ.ሂ.

🔹የሰላም የፍቅር የደስታ
🔹የአንድነት የከፍታ ጊዜ ይሁንልን

≈≈≈≈≈≈ ቁርዓን ≈≈≈≈≈≈

በዛ በጭለማ ብርሃን በጠፋበት
ድንጋይ እንደ አምላክ በሚመለክበት
ማንበብ ከማይችለው በረሱል አደበት
ወደምድር መጣ ለሰውም ለጅኑም ብርሀንን ይዞለት!!

የጀሊሉ ልሳን የራህማኑ ቃና
የፍቅሩን መግለጫ አቀናልንና
ለባሮቹ ብርሀን መውጫ ከጅህልና
በዛ ውድ ነብይ ምክኒያት አረገና
ጅብሪልን ላከልን ኢቅራእ አለውና!!

ስልቱ ያልታወቀ ቃላቱ ማራኪ
ምንም የሌለበት ሰዋዊ ንክኪ
ሳይንስ ስነ ፅሁፍ ታሪኩ በሙሉ
ምንጩ ቁርአን ነው ስልጣኔ ሁሉ!!
∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼

ነፍሱ ለተጠማች የእርካታ መንፈስ
በ“ሠው”ነት ልህቀት አብቦ መታደስ
ዓላማ መል ሕይወት አሳክቶ ለመንገስ
በእንስሳዊ መሻት ተረትቶ ከመርከስ
ሊታደግ ተላከ የሠው ልጆችን ነፍስ!!

የቀልቤ ማረፊያ ስክነት መዋቢያዬ
ሚስጥርን ያቀፈ ውዱ መመሪያዬ
ብርሀን የለገሰኝ ፀልሞ ስደናበር
መንገዴን ያቀናው ወደጀነቱ በር
የህይወቴ ፋና የምርጦች አይነታ
ቁርዓን ድንቁ ተዓምር የረህማን ስጦታ!!
∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼

ትዝታ የማይሆን እንደ ጠዋት ጤዛ
ሁሌም ሁሉም ሚያየው ከቅቤ የወዛ
ረሃብን ሚያስረሳ ጥማትን የሚቆርጥ
ዕውቀት ብቻ ሳይሆን ህይወትን የሚሰጥ
ህይወትን ለሻተ አለ መሶብ ሙሉ ህይወት
መሶብ ሙሉ መአድ ከልካይ የሌለበት!!

የቀልብ ፈውስ ነው የህይወት አሳማሪ
ከወንጀል ሽሽጎ በበጎ አብሳሪ
ድንቅ ነው ድንቅዬ ታምረኛ ጉዱ
ስጦታ የዘይኔ የዛ ሙሀመዱ❤️
አንተ ሸፊዑና አንተ ወኑሪና
እንድናለን ሁሌም ባንተ ልቅና!!!

⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅⚅

❤️አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ነቢይና ወሀቢቡና ወሸፊዑና ሙሀመድ ﷺ ❤️

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ግዑዝ ነገሮች መናገር ቢችሉ እንዲህ የሚሉ ይመስላሉ

ጨረቃ፡- ራሳቸውን ከእኔ ጋር እያወዳደሩ ቁንጅናቸውን ይመስላሉ እኔ ግን በፍፁም እነሱን አልመስልም

ደመና፡- አለቅሳለሁ እነሱ ዓይኔ በዘረገፈው ዕንባ ይሳሳቃሉ

ድንጋይ፡- የበዳይን ልብ ከእኔ ጋር አታመሳስሉ እኔ ማንንም አልበደልኩምና ድንጋይ እያላችሁ አትሳደቡ

ዕድል፡- እኔን መውቀስ አቁሙ መጥፎ ዕድል እያላችሁ አትወርፉ ስንፍናችሁን እኔ ላይ አታላኩ

አፈር፡- የሁሉንም የልብ ወዳጆች በአቅፌ አኑሬያለሁ

ልብ፡- ይገባዋል ብዬ በሬን ከፈትኩለት

ሚሴጅ፡- ለማይገባቸው ብዙ ሰዎች ተልኬያለሁ

ጭንቅላት፡- እናንተ የአካል ክፍሎቼ ሆይ አላህን እያመፃችሁ በምትሰሩት ወንጀል ልፈነዳ ነው

#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
መካ በድል ተከፍታ በተክቢራው በተህሊሉ ደምቃ የቁርጥ ቀን ልጆቿ ከሁሉም አቅጣጫ ወደ ውስጥ ዘለቁ። እትብታቸው ከተቀበረበት ሀገር ባይተዋር ተደርገው የከረሙት ሰሐቦች ከሩቅ ሲያይዋት ዓይናቸው በእንባ ተሞልቶ ለጌታቸው ሽኩር ግንባራቸውን ከመሬቱ ደፉ። የአላህ መልዕክተኛ በባልደረቦቻቸው ተከበው ከከዕባ በር ላይ እንደቆሙ "ቢላል የት ነው? ጥሩልኝ" በማለት አዘዙ። ያለፈውን ትዝታ እየቀሰቀሱ ለሰሐቦቻቸው አወጉ "ቁረይሽ ሆይ! ቢላልን በካዕባ በር ላይ ያሰቃያችሁበትን ቀን አስታውሰዋለሁ" አሉ።

ቢላል ደረሶ ወደ ነቢ ተጠጋ
"ወደ ውስጥ ግባ" አሉት። "ከአንተ በቀር ከዕባ ውስጥ ከእኔ ጋር ማንም አይሰግድም" እያሉ ተያይዘው ወደ ውስጥ ዘለቁ። ስለእስልምናው ሲል ለደረሰበት ስቃይ የተቸረው ምላሽ፣ የተሰጠው ክብር ነበር።
ሰግደው እንዳበቁ መልእክተኛው ቢላልን አዘዙ
"በከዕባ ጀርባ ላይ ተሰቀል" አሉት።

ተንጠላጥሎ መውጣት ከብዶት ሲንፈራገጥ አቡበከርና ዑመር እንዲሸከሙት አዘዙለት። ቀኝ እግሩን በዑመር የግራ እግሩንም በአቡበክር ትከሻ ላይ አስደግፎ ከከዕባው አናት ላይ ወጣ "ቢላል ሆይ! ከእርሱ ሌላ አምላክ በሌለው ጌታ በአላህ እምላለሁ ይህ ቤት አላህ ዘንድ ታላቅ ነው። በጌታዬ ይሁንብኝ ዛሬ ከከዕባ የበለጠ አንተ አላህ ዘንድ ትልቃለህ" አሉት።

የአረብ ሹማምንቶችና የተከበሩ ሰሐቦች በተገኙበት ከ10,000 ሺህ በላይ የኢስላም ሠራዊት ፊት ቆሞ የተውሂድን ጥሪ አሰማ። አላሁ አክበር እያለ መካን አንቀጠቀጠ። በአዛኑ የአማኞችን ልብ ናጠ። መገን የቢላልስ ነገር።

አላህ ሆይ ውዴታህና እዝነትህ በአላህ መልዕተኛ እሳቸውንም በተወዳጁ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይስፈን

ምንጭ/ البدايه والنهاية لابن كثير

╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍
ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑልወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍
#share #ሼር
#join

Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#በዐሹራ ቀን የተከሰቱ ድንቅ 25 አበይት ክስተቶች እነሆ

1. #ነብዩላህ_አደም (ዐለይሒ ሠላም) የተፈጠሩበት ቀን።

2. #ነብዩላህ_አደም ( ዐለይሒ ሠላም ) ጀነት የገቡበት ዕለት።

3.#ነብዩላህ አደም (ዐለይሒ ሠላም ) ተውበት ያደረጉበት ዕለት::

4. #ዐርሽ

5. #ኩርሥይ

5. #ሠማይ

7. #መሬት

8. #ፀሀይ

9. #ጨረቃ

10. #ከዋክብት እና

11.ከላይ የዘረዘርናቸው እና #ጀነትም በዛው ታዕመረኛ ዕለት ተሠሩ።

12. #ነብዩላህ_ኢብራሒም ( ዐለይሒ ሠላም ) የተወለዱበት ዕለት።

13. #ነብዩላህ_ኢብራሒም ( ዐለይሒ ሠላም ) ከተቀጣጠለው እሣት በአላህዬ የተጠበቁበት ዕለት።

14. #ነብዩላህ_ሙሣ ( ዐለይሒ ሠላም ) እና ዑመቶቹ ከፊርዐውን ተንኮል በአላህዬ ተጠብቀው እንዲሁም ፊርዐውን ከነወታደሮቹ የጠፉበት ዕለት::

15. #ዒሣ (ዐለይሒ ሠላም ) የተወለዱበት ቀን።

16. #ዒሣ ( ዐለይሒ ሠላም ) ወደ ሠማይ ያረጉበት ቀን።

17. #ኑህ ( ዐለይሒ.ሠላም ) መርከብ የተሰራበት ዕለት።

18. #ሡለይማን (ዐለይሒ ሠላም ) ዱንያ ላይ ለማንም ያልተሠጠ ንግሥና የተሠጣቸው ዕለት።

19. #ዩኑሥ ( ዐለይሒ ሠላም ) ከአሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ በባህር ውሥጥ ተውባቸውን አላህዬ የተቀበላቸውና ከዛም ከሶስት ጨለማ የወጡበት ዕለት።

20. #ያቁብ ( ዐለይሒ ሠላም ) የዐይን ብርሀናቸው የተመለሠበት ዕለት።

21. #ዩሡፍ (ዐለይሂ ሠላም) ከጉድጋድ የወጡበት ዕለት።

22. #ዐዩብ ( ዐለይሒ ሠላም ) ከህመማቸው የተፈወሡበት ዕለት።

23. #ሚያጅበው ለመጀመሪያ ጊዜ #ዝናብ የዘነበው አሹራ ቀን ነበር።

24.# የአሹራ ቀን መፆም #በቀደምት_ህዝቦች(ዑመቶች) መካከል የተለመደ ነበር፤ እንደውም በዛን ዘመን ለሚኖሩ ሰዎች የአሹራ ቀን መፆም #እንደፈርድ ነበር ሚቆጠረው ረመዳን ግን እንደ ፈርድ አይቆጠርም ነበር ግን ከጊዚያት በኃላ ተነሣ።

25. ዒማም_ሁሠይን ልጆቻቸው እንዲሁም ባልደረቦቻቸው #ካርባላ_ሜዳ ላይ ለተከታታይ 3 ቀናት የተራቡበትና በጭቃኔ መሰዋእት የከፈሉበት ዕለት::

@ሙካሺፋቱልቁሉብ

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#Share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

     🌹የአሹራ ቀን ፆም🌹

የአንድ ዓመት ወንጀል🔥
በአንድ ቀን ይማራል
እንዴት ያለ እዝነት ነው⁉️
♾️♾️♾️♾️♾️♾️♾️♾️


ሰማያትና ምድር በውስጣቸው እስካለው ነገር ያለ አጋዥና አማካሪ የፈጠርከው፤
  ከፈጠርክ በኋላም ድካም ያልተሰማህ የሆንከው፤
ጥበበኛና አሸናፊ የሆንከው ጌታዬ ከጎደሎ ነገር ሁሉ ጥራት ይገባህ‼️

ባሮችህ ብትቀጣ በፍትህ፤
ብታዝንላቸው በእዝነትህ፤
ጥበብህ ጉድለት የሌለው፤
ውሳኔህ መላሽ የሌለው፤
እዝነትህ ከቁጣህ የቀደመ፤
አዛኙ ጌታዬ ከፍጥረትህ ብዛት የሰፋ የሆነ ምስጋና ይድረስህ‼️

የአላህ ባሮች ሆይ👇
  አንድ ሰው አንድ ወንጀል ሲሰራ በአንድ ይያዝበታል።
አንድ ሰው አንድ መልካም ስራ ሲሰራ ከ10_700 ከዝያም በላይ እጥፍ ድርብ ተደርጎ ይመነዳል‼️
ከአላህ እዝነት አትገረሙም

ምን ይህ ብቻ?…
የተለያዩ አጋጣሚዎች በመስጠት በጣም ቲንሽ ስራ ሰርተን ትልቅ ምንዳ እንድንመነዳ ያመቻችልልናል።
ከእነዚህም ብርቅዬ አጋጣሚዎች አንዱ ከፊት ለፊታችን የሚገኘው የ«ዓሹራ» ፆም ነው።

የ«ዓሹራ ፆም» የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደ ተናገሩት የአንድ አመት ወንጀልን ያስምራል።

”صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ“
“የዓሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ወንጀል እንዲያስምርልኝ አላህ ዘንድ ታሳቢ አደርጋለሁ”

አላህ ማስተዋልን የሰጠው የሆነ ሰው የአመት ወንጀል በአንድ ቀን የሚያስምር ፆም አግኝቶ አይደለም የአንድ ቀን ወንጀል እንዲማርልህ አንድ አመት ፁም ቢባል ከመፆም ወደ ኋላ አይልም።

ታድያ እኛስ ይህንን አጋጣሚ ለመጠቀም ምን ያህል ተዘጋጅተናል

የአላህ መልዕክተኛ አይሁዳዎችን እንቃረን ዘንዳ ከዓሹራ ከበስተ ፊት አንድ ቀን (9ኛው ቀን) ጨምረን እንድንፆም አዘውናል።

  በዚህም መሰረት በአላህ ፍቃድ የዘንድሮው የዓሹራ ቀን የሚሆነው የፊታችን
   👉ጁሙዓ👈 ነው።
እኛም አይሁዳዎችን ለመቃረን
👉ሐሙስ እና ጁሙዓ👈
በመፆም የዚህ ትልቅ ስጦታ ተቋዳሽ እንሁን።

👉እንፁም‼️
👉ቤተሰቦቻችን እንዲፆሙ እንዘዝ‼️
👉ሁሉም ሙስሊሞች እንዲፆሙ መልዕክቱን እናስተላልፍላቸው‼️

   الدالّ على الخير كفاعلِه
ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው‼️


   ✍🏿منقول 
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

ከሱብሒ ሰላት በፊት ቀደም ብዬ ካይሮ ኤርፖርት ደረስኩ ይሉናል የታሪካችን ተራኪ ሸይኽ ሙሐመድ ሳዊ። ሰዓቱ ለሊት ስለነበር የመስጂድ ኢማም ወደሆነው ወዳጄ ዘንድ ደወልኩ።
"ገና አሁን መግባቴ ነውና መስጂድ መጥቼ እስከ ንጋት አብሬህ እቆይ ዘንድ የመስጂዱን በር ክፍት ተውልኝ" አልኩት።

Mahi Mahisho

ሻንጣዬን ሸክፌ በዝግታ እየተራመድኩ መስጂዱ በራፍ ላይ ደረስኩ። መብራቶቹ በርተዋል። አንድ ሰው ሚህራቡ አቅራቢያ ሱጁድ ተደፍቶ አላህን ያናግራል።
"ጌታ ሆይ ከዚህ በላይ መታገስ አቃተኝ አልቻልኩም ደከመኝ ከአንተ በቀር ማንም የለኝ ወዴት ልሂድ ወደማንስ ልጠጋ አረ ተው ጌትዬ!..." እያለ እነዚህን ቃላት ይደግማል።

ሰውነትን የሚያንቀጠቅጥ አስደንጋጭ ዱዓ!!
ዕንባን የቀላቀለ አስቸኳይ መልስን የሚሻ ልመና!!
ከነፍሴ ጋር አወጋሁ በአላህ እምላለሁ ይህ ለቅሶ ኃጢአት ከሠራ ሰው የሚመነጭ አይደለም ችግር ያቆረፈደው መከራና ሐዘን የከበበው ሰው ልመና ነው እያልኩ ባለሁበት ቆምኩ። እስኪጨርስ ጠብቄ ወደ ሰውየው ተጠጋሁ። ሲያየኝ ዝም አለ።
"ወንድሜ!" አልኩት "ምን ነካህ? ምን አገኘህ?!" በማለት ጠየቅኩት።
ከረዥም ዝምታና ውትወታ በኋላ፡-
"በአላህ እምላለሁ ምን እንደምል አላውቅም ነገር ግን ባለቤቴ ነገ ጠዋት ኦፕራሲዮን ታደርጋለች። ለቀዶ ጥገናው የሚያስፈልገኝ 15,400 ፓውንድ ነው። ስባሪ ሳንቲም ስለሌለኝ ጌታዬ እንዲያበድረኝ እየጠየቅኩት ነው" አለኝ።
"የምረዳህ ገንዘብ ባይኖረኝም አላህ የተደገፈበትን እንዲሁ የማይተው መሐሪ ጌታ ነውና አብሽር" ብዬው ዊትሬን ሰግጄ ተኛሁ።

ጎህ ቀዶ ሙአዚኑ ለፈጅር ሰላት ቀሰቀሰኝ። ሱብሒን ባንተ መስገድ እንፈልጋለንና ተቀደም አለኝ። ሰግደን እንዳበቃን ከሦስተኛው ሰፍ ረጅም ካፖርት የለበሰ ሰው እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ ተጠጋ። ሞቅ ባለ ሰላምታ ፈገግታን እየቸረኝ እንዴት ነህ? አለኝ።
ፕሮግራምህንና ትምህርቶችህን እከታተላለሁ ከመስጂዱ ፊት ለፊት የሚገኝን አፓርታማ የገዛሁት ከጥቂት ጊዜ በፊት ነው። አንተን ለማየትና ሰላም ለማለት በመታደሌ አልሐምዱሊላህ" አለኝ።
"እንኳን ደህና መጣህ አላህ ይባርክህ" አልኩት ሰላምታውን እየመለስኩ።

ተመቻችቶ እየተቀመጠ ንግግሩን ቀጠለ:-
"ጌታዬ ወሰን በሌለው ፀጋው አክብሮኛል፤ የፕላስቲክ ፋብሪካ ባለቤት ነኝ። ሁለተኛውን ቅርንጫፍም በቅርቡ ከፍቻለሁ። ምስጋና ለአላህ ይገባውና ዘካውን ሳሰላ 15400 ፓውንድ ... "

ንግግሩን ሳይጨርስ በለቅሶዬ አቋረጥኩት። መላ አካሌ በድንጋጤ ተንቀጠቀጠ። ከሱ በቀር ሌላ አምላክ በሌለው ጌታ እምላለሁ ይህ ሰው የጠራው የገንዘብ መጠንና ያ ከሱብሂ በፊት ያገኘሁት ወንድም ቸግሮት የፈለገው የብር መጠን አንድ ነበር። ያን ሰው በአይኔ ፈለግኩት

"ምን ነካህ ሸይኽ?" አለኝ በሁኔታዬ ግራ እየተጋባ
"ትንሽ ታገሥ" አልኩት።
ሰውየውን አየሁት። ወደ እኛ እንዲመጣ በምልክት ጠራሁት። ከፊታችን ተቀመጠ። አይኖቹ በለቅሶ ብዛት አሞጭሙጨዋል። እስኪ ሐጃህን በድጋሜ ንገረኝ አልኩት።
"ሚስቴ ዛሬ ጠዋት ኦፕራሲዮን እንደምታደርግ፣ ገንዘብ እንደሌለኝ ነግሬሀለው" አለኝ
"ቀዶ ጥገናው ስንት ብር ያስፈልገዋል" አልኩት።
"15400 ፓውንድ"
ነጋዴው በተክቢራ መስጂዱን እየናጠ ምርር ብሎ አለቀሰ! ወደ ደረቱ አስጠግቶ እያቀፈው እንዲህ አለ፡-
"በአላህ እምላለሁ ባለቤቴ ይህንን የአላህ ሀቅ ለሚገባው ባለሐቅ ወስደህ ስጥ እያለች ጠዋት ማታ ትወተውተኛለች። ሐቢብቲ መቶ መቶ እየቆነጠርኩ መስጠት አልሻም። የቂያማ ቀን አላህ ከጭንቅ ይገላግለኝ ዘንድ ሙሉ ገንዘቡን ለተቸገረ አንድ ሰው ሰጥቼ ከጭንቀቱ ገላግዬ ለደስታው ሰበብ መሆን እፈልጋለሁ እላታለሁ"

ገንዘቡን በሙሉ አመጣና ለሰውየው ሰጠ።
እየሆነ ያለውን አላመነም። ገንዘቡን ሲቀበል እኔንም ነጋዴውንም ትቶ ገንዘቡን በእቅፉ እንደያዘ ሱጁድ ወረደና እንዲህ አለ:-
"ጌታዬ ሆይ! እወድሃለሁ እንደምትወደኝም አውቃለሁ"
ዩሒቡሁም ወዩሂቡነህ ይሉሀል ይህ ነው።

ችክ ብሎ በሲድቅ አላህን የለመነና የተቸገረን ሰው ከጭንቅ ለመፈረጅ በኢኽላስ የታተረ ሁለትዮሽ ዱዓ ሲገጥም የሚሆነው እንዲህ ነው። እንደዚያም ተፈፀመ።

ታሪኩ አልቋል የዓለማቱ ጌታ ስጦታዎች ግን አያበቁም.......

ሸይኽ ሙሐመድ ሳዊ ገጠመኛቸውን ከተናገሩበት የድምፅ ቅጂ የተተረጎመ።

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
2025/07/04 04:16:44
Back to Top
HTML Embed Code: