Telegram Web Link
ይህ ከስር የምትመለከቱት #የፈረስ ሳንባ ነው 7 ኪ .ግ ይመዝናል ለዚህም ነው ሳይደክም ረጅም ርቀት መሮጥ የሚችለው #ሱብሃን_አላህ

#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
የ22 አመቱ ግብፃዊ ሙሸራ በኒካሁ ቀን በደስታ እየጨፈረ በእጮኛው እጅ ላይ ድንገት ልቡ ቀጥ ብሎ ወደ አሄራ ሄዷል

ብዙዎች የደስታቸውን ቀን ሃላልና ሀራሙ እስኪጠፋቸው አላህን ያምፃሉ አላህ የጠበቀው ሲቀር 😭😭

ከእንዲህ አይነት አሟሟት አላህ ይጠብቀን 🤲
ስሙ ሲወሳ በርካታ መሻኢኾች "ሙስሊም ስለመሆኑ እንጠራጠራለን" ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ "ግልፅ በሆነ ጥመት ውስጥ ነውና አላህ ይምራው" በሚለው ዱዓቸው ንግግራቸውን ይቋጫሉ።
"የእስልምናን እውነተኛ እሴቶች ለማሳየት የሚተጋ ኮከብ ነው" ይሉታል አይሁዶች ስለርሱ ሲናገሩ።

የሚደጋግማት ቃል አለችው "ሁሌም ከወንድሞቼ አይሁዶች ጎን ከመቆም አልቦዘንኩም" ይላል በገዛ አንደበቱ ስለእነርሱ ሲያወጋ። በእርግጥም ከበርካታ መሻኢኾች እስር በስተጀርባ እጁ እንዳለበት ይነገራል።

የሃይማኖቶች አንድነት የአብርሃም እምነቶች ቤተ አምልኮን በሀገረ ዱባይ መርቆ የከፈተ!! ክርስቲያኖች፣ አይሁዳዎችና ሙስሊሞች እምነታቸው አንድ ነው ሁሉም የሚከተሉት ኢብራሂምን ነውና እምነታቸው ሠማያዊ ነው የሚለውን አስተሳሰብ በግንባር ቀደምነት የሚመራ! በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተገኝቶ የቅዳሴ ደውሉን እያንቀጨቀጨ የሚደውል አወዛጋቢ!!

ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐብዱልከሪም ዒሳ ይሰኛል። በሀገረ ሳዑዲ በ1385 ዓመተ ሂጅራ ወደዚህ ዓለም መጣ። በዚያው በትውልድ ሀገሩ የሳውዲ ፍትህ ሚኒስትር፣ በንጉሣዊው ቤተ መንግሥትም በሚኒስትር ማዕረግ አማካሪ ነበር። እንደ አውሮጳዊያን የዘመን ቀመር ከ2016 ጀምሮ ዶ/ር ዐብደላህ ቢን ዐብዱል ሙህሲን አት-ቱርኪን በመተካት የሙስሊም ዓለም ሊግ የራቢጣ ዋና ፀሀፊ ተደርጎ ተሾመ።

ጁላይ 18/2020 ከአል ዐረቢያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ
"እንደ ሌሎች ኃይማኖቶች ከአይሁዶችም ጋር በመልካም እንኗኗር። ኃይማኖታችንን ከማሰደብና ከመጮህ በቀር እነርሱን በመጥላታችን ያተረፍነው ነገር የለም" በማለት በግልፅ ድምፁን አሰማ።

ይህን ተከትሎ "በፀረ ሴማዊነት ላይ የቆመ ሸይኽ" በማለት የእስራኤል ሚዲያዎች አንቆለጳጰሱት። በሙስሊሞችና በአይሁዶች መካከል ውይይት እንዲደረግ ግልፅ ጥሪ ማቅረቡ ያስደሰታቸው የእስራኤል መገናኛ ብዙኃኖች "የለዘብተኛ እስልምና ውበቱን ጽንፈኝነት ማስጠላቱን ያመላከተ ፈር ቀዳጅ ድምፅ" ሲሉ አወደሱት። በእርግጥም ከማወደስም አልፈው የአሜሪካ ልዑካኖች በተገኙበት የምስጋና ምስክር ወረቀት በክብር አበርክተውለታል።

ጥር 23/2020 75 ኛው ዝክረ የአይሁድ ዕልቂት ምዕተ ዓመት ሲከበር ከልዑካን ቡድኑ ጋር ወደ ሥፍራው ባቀናበት ወቅት እዚያው ካንፑ መሐል ኢማም ሆኖ ተሰየመ። እስራኤል ፈነጠዘች። ምስሉን አያይዛ የምስጋና ቃላቶቿን አዥጎደጎደች። "በሺህ ቃል የማይገለፅ ምስል" በማለት ተናገረች። "የራቢጣ አል ኢስላሚያ ዋና ፀሀፊ ሙሐመድ ኢሳ ከልዑካቸው ጋር በሆሎኮስት የተገደሉትን ወገኖቻችንን በማሰብ ፀሎት አደረጉ። ከአንድ ሚሊዮን በላይ አይሁዶች ወንድሞቻችን በዚያ ካምፕ መገደላቸው ልብ ይሏል" በማለት ከተቡ።

"ትክክለኛው እስልምና ይህ ነው!
የሳውዲው የሀይማኖት አባት ሙሐመድ ኢሳ ከነልኡካን ቡድናቸው በአውሽዊትዝ ካምፕ ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑ አይሁዳውያን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ፀልለዋል... ቪዲዮውን ተመልክታችሁ ተመከሩ። በሃይማኖቶች መካከል ያለው ወንድማማችነት የመልካም ነገር ሁሉ መንስኤ ነውና" በማለት ተቀባበሉት።

አይሁዳዊያንን የተወዳጁ አካሄዶች የሚተፉት መርዝ ከባድ መሆኑን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ!!

Https://www.tg-me.com/smithhk
እህቷን ለማዳን እየሞከረች ሳለ ነበር እስትንፋሷ የተቋረጠው

ያኔ ድሮ ጥምሩ ኢስላም ጠሉ ጦር ተባብሮ ተደጋግፎ ሀገራቸውን ሲያፈራርሳት የኔ ህፃን እንደምትመለከቷት እህቷን እንደታቀፈሽ ነፍሷ ወደ ጌታዋ በረረች

ንገሪኝ እስኪ አልኳት መልሷን ለመስማት ጆሮዬን እየቀሰርኩ
ልጅ ሆነሽ እናትነትን ከየት ተማርሽ?
ከሞት ጋር እየታገልሽ እህትሽን ለማትረፍ ፅናቱን ከየት አመጣሽ?!
እሷ በህይወት ትኖር ዘንድ ንጹህ አየር እየሰጠሽ ትንፋሽሽ ተበክሎ ሲቆራረጥ ህመምሽን ለመቋቋም ብርታቱን ከየት አገኘሽ? የታለ አባትሽ የታሉ ወንድሞችሽስ?!

ጠንካሮችን ሁሉ በጥንካሬዋ የበለጠች ንፅህናዋ ብዙዎችን የረታ ርኅራኄዋ ቀልብን ያንበረከከ ምስሏን ማየት ዘወትር ህመምን የምታጭር የኔ ሴት።

የአላህ እዝነትበእርሷ ላይ ይስፈን ነፍስሽን አላህ ያሳርፋት ሰጊረቲ

ያለፈውን ታስታውሱ ዘንድ

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
"ስታድጉ ምን መሆን እንደምትፈልጉ ፅፋችሁ ኑ" በማለት ነበር ለተማሪዎቿ የቤት ስራ የሰጠቻቸው።
በነጋታው ጠዋት በተንጋደደ ፅሑፍ የወደፊት አላማቸው የተፃፈበትን ወረቀት ለአስተማሪያቸው አስረከቡ። ከተማሪዎቹ መካከል አንዱ የፃፈው ግን ትኩረቷን ሳበ። ከልሙጡ ወረቀት መሐል ለመሐል "ሰሐባ" የሚል ቃል በፓርከር አስፍሮ ሰጣት።
"ሰሐባ መሆን የምትፈልገው ለምንድነው?" በማለት ጠየቀችው።

"ምክንያቱም" አለ ንግግሩን ሲጀምር "ምክንያቱም እናቴ በየቀኑ የሰሐቦችን ታሪክ ትነግረኛለች። አላህን ይወዳሉ አላህም ይወዳቸዋል ትለኛለች። እኔም አላህ እንዲወደኝ እፈልጋለሁ" አላት።

የምነግራችሁ ልጆቻቸውን በተርቢያ ስለሚያሳድጉ ድንቅ እናቶች ነው

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ህይወት በሁሉም አቅጣጫ የጠመመብሽ እድለቢስነት አብሮሽ የተፈጠረ ይመስል ፈተናዎች የተደራረቡብሽ ችግርሽን የሚረዳሽ ቀርቶ "እህ" ብሎ የሚሰማሽ ያጣሽ ኑሮሽ ኢምንት የማይጨምር ትላንትም ዛሬም ቀኑ አንድ የሆነብሽ እንስት ሆይ!

ነገሮችን በራስሽ ለማስተካከል ደፋ ቀና እያልሽ ስትደክሚ አላህን ስለምን ዘነጋሽው?
ፈጥሮ የረሳሽ የሚመስልሽስ ለምን ይሆን?
በነገሮች አለመሳካት ትእግስትሽን የሚፈታተንሽ ቢመርጥሽ እንጂ ለምን ይመስልሻል?

እጅሽን አንሺ። ለሊት ተነስተሽ ግንባርሽን ከመስገጃሽ ላይ ድፊ እውነተኛና ትክክለኛ የልብ መቅረብን ቅረቢ። ተናነሺና ከፍታን ጠይቂ እሱ ዘንድ የተዘረጋ እጅ በባዶ አይመለስም እመኚኝ

ስላንተም እንቀጥላለን!

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ከመሐል ረጅሙ!
ሲታይ ውበቱ ዓይንን የሚይዝ!
አቀማመጡ የሚስብ የደስ ደስ ቁመናን የተላበሰ!
ውበቱ የገዘፈ ኩሩ!
የሚያምር ቁመናን ያጠለቀ!
ግን ግን ያበረከተው ምንም አስተዋፅዖ የለም።
አንድ ቃል እንኳ አልተነፈሰም።
ወረቀት ላይ ተሰይሞ አልፃፈም።

አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ናቸው
በመልክ በቁመናቸው እንዳትታለል

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ሳቋ ከልብ ነው በወጣሁ በገባሁ ቁጥር በመንገዴ ዳር አገኛታለሁ። እጅን በአፍ የሚያስጭን ውበትን ተላብሳለች። ስታምር እያስባለች ዓይንን ታዋልላለች። ሲበዛ አፈቀርኳት። በመልእክተኛው ሱና መሰረት ግን እጇን ስሜ ለጋብቻ ልጠይቃት አልታደልኩም ይላል ትረካውን ሲጀምር።

እንዳፈቀርኳት እንኳ ሳልነግራት ሑቤን በልቤ ቋጠሮ ደበቅኩላት። ህመም የቀላቀለ ናፍቆቷ ሲለበልበኝ ሱጁድ ወርጄ ከአላህ ጋር መነጋገር ጀመርኩኝ። ለሊት እየተነሳሁ ጌታዬን እለምነው ገባሁ። ከቀን ወደቀን ቀልቤ ውስጥ የከተመው ፍቅሯ እያበበ መጨመሩ ኸይርን እንዳስብ አደረገኝ።

ግና... አለን ትንፋሹን ሰብስቦ ንግግሩን ቀጠለ። የአላህ ውሳኔ ቀደመኝ። ፍቅሯ እየለበለበ በቅጡ እንኳ ማዘን መተከዝ ተሳነኝ። የልቤ ቁስል ደምቶ ሳይመረቅዝ ለሰርጓ ተጠራሁ። ከነቤተሰብህ ዝለቅ የሚል ጥሪ ቤታችን ደረሰ። አገባች። ከየት መጣ ሳይባል ወደቤቱ ወሰዳት። እያየኋት አጣኋት። ያቺን መሳይ ጉብል የራሴ አደርጋለሁ እያልኩ ከአፌ ጠልፎ ወሰዳት። በሰርጓ ቀን ቀላል ስጦታ ላኩላት።
"ብታገቢም በአላህ ላይ ያለኝ እምነትና ቸርነቱ አልደፈረሰም" የሚል ደብዳቤ አያይዤ ሰደድኩላት።

ለእሷ ያለኝ ፍቅር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በልቤ ውስጥ ላትረሳ ታተመች። በትዕግስት በዱዓ የተዋጀውን የአላህን ውሳኔ ከመልካም ጥርጣሬ ጋር ከመጠበቅ ያለፈ አቅም አነሰኝ።

ከ3 ወራት በኋላ የባሏ እስትንፋስ ቀጥ ብሎ ጌታውን ተገናኘ። አጀሉ ደርሶ እሕል ውሐው ሲቋረጥ እርጉዝ ነበረች። የሐዘኗ ጊዜ ተጠናቆ ዒዳዋ እንዳበቃ ወንድ ልጅን ተገላገለች። ራሴን አዘጋጅቼ ጠበቅኳት። ሽማግሌ ልኬ ለጋብቻ ጠየቅኳት። በእሺታ ተስማምተው ኒካሐችን ፀደቀ። ዘወጅናከ ሲሉኝ ተስገብግቤ ቀቢልቱ አልኩኝ።

የአላህ ቸርነት ለእኔ ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?!
አላህ ለኔ የዋለልኝ መልካም ውለታ እርሷን የኔ እንድትሆን ማድረጉ አልነበረምን?! ለምን አትለኝም?! ምክንያቱም ከትዳራችን በኋላ ልጅ መውለድ እንደማልችል በምርመራ ተረጋገጠልኝ። ልጇ ልጄ ሆነ። እሷም ከእኔ ሳትነጠል ለመኖር ወሰነች። ቤታችን በፍቅር በደስታ ተሞላ። አዛኝ ለሆነው አላህ ምስጋና ይግባውና አሁን ሁለታችንም ቁርአንን ሐፍዘን ጨርሰናል ይላል ታሪኩን ሲቋጭ።

አስታውስ!
በአንድ ነገር ላይ ድርሻህ ከአላህ ዘንድ ከተወሰነ ሚዛኑ ተገልብጦ ታገኘው ዘንድ ይመቻችልሀልና ዱዓህን በስክነት እያደረግክ ውሳኔውን በእርጋታ ጠብቅ!!

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ከሱብሒ ሰላት በፊት ቀደም ብዬ ካይሮ ኤርፖርት ደረስኩ ይሉናል የታሪካችን ተራኪ ሸይኽ ሙሐመድ ሳዊ። ሰዓቱ ለሊት ስለነበር የመስጂድ ኢማም ወደሆነው ወዳጄ ዘንድ ደወልኩ።
"ገና አሁን መግባቴ ነውና መስጂድ መጥቼ እስከ ንጋት አብሬህ እቆይ ዘንድ የመስጂዱን በር ክፍት ተውልኝ" አልኩት።

ሻንጣዬን ሸክፌ በዝግታ እየተራመድኩ መስጂዱ በራፍ ላይ ደረስኩ። መብራቶቹ በርተዋል። አንድ ሰው ሚህራቡ አቅራቢያ ሱጁድ ተደፍቶ አላህን ያናግራል።
"ጌታ ሆይ ከዚህ በላይ መታገስ አቃተኝ አልቻልኩም ደከመኝ ከአንተ በቀር ማንም የለኝ ወዴት ልሂድ ወደማንስ ልጠጋ አረ ተው ጌትዬ!..." እያለ እነዚህን ቃላት ይደግማል።

ሰውነትን የሚያንቀጠቅጥ አስደንጋጭ ዱዓ!!
ዕንባን የቀላቀለ አስቸኳይ መልስን የሚሻ ልመና!!
ከነፍሴ ጋር አወጋሁ በአላህ እምላለሁ ይህ ለቅሶ ኃጢአት ከሠራ ሰው የሚመነጭ አይደለም ችግር ያቆረፈደው መከራና ሐዘን የከበበው ሰው ልመና ነው እያልኩ ባለሁበት ቆምኩ። እስኪጨርስ ጠብቄ ወደ ሰውየው ተጠጋሁ። ሲያየኝ ዝም አለ።
"ወንድሜ!" አልኩት "ምን ነካህ? ምን አገኘህ?!" በማለት ጠየቅኩት።
ከረዥም ዝምታና ውትወታ በኋላ፡-
"በአላህ እምላለሁ ምን እንደምል አላውቅም ነገር ግን ባለቤቴ ነገ ጠዋት ኦፕራሲዮን ታደርጋለች። ለቀዶ ጥገናው የሚያስፈልገኝ 15,400 ፓውንድ ነው። ስባሪ ሳንቲም ስለሌለኝ ጌታዬ እንዲያበድረኝ እየጠየቅኩት ነው" አለኝ።
"የምረዳህ ገንዘብ ባይኖረኝም አላህ የተደገፈበትን እንዲሁ የማይተው መሐሪ ጌታ ነውና አብሽር" ብዬው ዊትሬን ሰግጄ ተኛሁ።

ጎህ ቀዶ ሙአዚኑ ለፈጅር ሰላት ቀሰቀሰኝ። ሱብሒን ባንተ መስገድ እንፈልጋለንና ተቀደም አለኝ። ሰግደን እንዳበቃን ከሦስተኛው ሰፍ ረጅም ካፖርት የለበሰ ሰው እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ ተጠጋ። ሞቅ ባለ ሰላምታ ፈገግታን እየቸረኝ እንዴት ነህ? አለኝ።
ፕሮግራምህንና ትምህርቶችህን እከታተላለሁ ከመስጂዱ ፊት ለፊት የሚገኝን አፓርታማ የገዛሁት ከጥቂት ጊዜ በፊት ነው። አንተን ለማየትና ሰላም ለማለት በመታደሌ አልሐምዱሊላህ" አለኝ።
"እንኳን ደህና መጣህ አላህ ይባርክህ" አልኩት ሰላምታውን እየመለስኩ።

ተመቻችቶ እየተቀመጠ ንግግሩን ቀጠለ:-
"ጌታዬ ወሰን በሌለው ፀጋው አክብሮኛል፤ የፕላስቲክ ፋብሪካ ባለቤት ነኝ። ሁለተኛውን ቅርንጫፍም በቅርቡ ከፍቻለሁ። ምስጋና ለአላህ ይገባውና ዘካውን ሳሰላ 15400 ፓውንድ ... "

ንግግሩን ሳይጨርስ በለቅሶዬ አቋረጥኩት። መላ አካሌ በድንጋጤ ተንቀጠቀጠ። ከሱ በቀር ሌላ አምላክ በሌለው ጌታ እምላለሁ ይህ ሰው የጠራው የገንዘብ መጠንና ያ ከሱብሂ በፊት ያገኘሁት ወንድም ቸግሮት የፈለገው የብር መጠን አንድ ነበር። ያን ሰው በአይኔ ፈለግኩት

"ምን ነካህ ሸይኽ?" አለኝ በሁኔታዬ ግራ እየተጋባ
"ትንሽ ታገሥ" አልኩት።
ሰውየውን አየሁት። ወደ እኛ እንዲመጣ በምልክት ጠራሁት። ከፊታችን ተቀመጠ። አይኖቹ በለቅሶ ብዛት አሞጭሙጨዋል። እስኪ ሐጃህን በድጋሜ ንገረኝ አልኩት።
"ሚስቴ ዛሬ ጠዋት ኦፕራሲዮን እንደምታደርግ፣ ገንዘብ እንደሌለኝ ነግሬሀለው" አለኝ
"ቀዶ ጥገናው ስንት ብር ያስፈልገዋል" አልኩት።
"15400 ፓውንድ"
ነጋዴው በተክቢራ መስጂዱን እየናጠ ምርር ብሎ አለቀሰ! ወደ ደረቱ አስጠግቶ እያቀፈው እንዲህ አለ፡-
"በአላህ እምላለሁ ባለቤቴ ይህንን የአላህ ሀቅ ለሚገባው ባለሐቅ ወስደህ ስጥ እያለች ጠዋት ማታ ትወተውተኛለች። ሐቢብቲ መቶ መቶ እየቆነጠርኩ መስጠት አልሻም። የቂያማ ቀን አላህ ከጭንቅ ይገላግለኝ ዘንድ ሙሉ ገንዘቡን ለተቸገረ አንድ ሰው ሰጥቼ ከጭንቀቱ ገላግዬ ለደስታው ሰበብ መሆን እፈልጋለሁ እላታለሁ"

ገንዘቡን በሙሉ አመጣና ለሰውየው ሰጠ።
እየሆነ ያለውን አላመነም። ገንዘቡን ሲቀበል እኔንም ነጋዴውንም ትቶ ገንዘቡን በእቅፉ እንደያዘ ሱጁድ ወረደና እንዲህ አለ:-
"ጌታዬ ሆይ! እወድሃለሁ እንደምትወደኝም አውቃለሁ"
ዩሒቡሁም ወዩሂቡነህ ይሉሀል ይህ ነው።

ችክ ብሎ በሲድቅ አላህን የለመነና የተቸገረን ሰው ከጭንቅ ለመፈረጅ በኢኽላስ የታተረ ሁለትዮሽ ዱዓ ሲገጥም የሚሆነው እንዲህ ነው። እንደዚያም ተፈፀመ።

ታሪኩ አልቋል የዓለማቱ ጌታ ስጦታዎች ግን አያበቁም.......

ሸይኽ ሙሐመድ ሳዊ ገጠመኛቸውን ከተናገሩበት የድምፅ ቅጂ የተተረጎመ።

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
እነዚህ ጫጩቶች ካጥለቀለቃቸው ጎርፍ በዚህ ነጠላ ጫማ ላይ ተንሳፈው ተደጋግፈው ቆመዋል።

ህይወት ላንተ ዋጋ በማትሰጠው ነገር ሌሎችን ታስደስታለች። ላንተ ዋጋ ቢስ ርካሽ የሆነው ነገር ሌሎች ዘንድ የህይወት ዋጋ ሊኖረው ይችላልና ትንሽ ናት ብለህ አትናቅ።

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ከዕለታት በአንዱ ውሸት ከእውነት ጋር ገላጣ ሜዳ ላይ ተገናኙ። "የዛሬው ቀን በጣም ያምራል" አለ ውሸት ዙርያውን እያየ።
እውነት ይህንን ንግግር ስትሰማ በጥርጣሬ አካባቢውን ቃኘች። አይኖቿን ወደ ሠማይ አቅንታ ግራ ቀኙን ተመለከተች። በእርግጥም ቀኑን ውብ ሆኖ አገኘችው። አየሩም ለስላሳ ነበር። ዛሬን ከውሸት ጋር ለመዋል ወሰነች።

በመንገዳቸው ላይ በፅጌረዳ የተከበበ ሐይቅ መሳይ ውሃን ተመለከቱ። "ምንኛ ያማረ ኩልል ብሎ የሚፈስ ጣፋጭ ውሀ ነው!" አለ ውሸት እግሮቹን ለመንከር እየተጠጋ።

እውነት ለሁለተኛ ጊዜ ውሸትን በጥርጣሬ እየተመለከተች ውሃውን በመዳፏ ዳበሰች። ጥርት ያለ ቆንጆ ሆኖ አገኘችው። ልብሳቸውን አወላልቀው ወደ ሐይቁ ዘለቁ። ውሀውን በእጃቸው እየጨለፉ ሰውነታቸውን ታጠቡ። እየዋኙ ከወዲህ ወዲያ ተንጎራደዱ።

የእውነትን ወደ መሐል መጠጋት ያየው ውሸት ተስፈንጥሮ ከውሃው ወጣ። በፍጥነት የእውነትን ልብስ አጥልቆ ወደፊት ሮጠ።

እውነት ድንገት ስትባንን ውሸት አጠገቧ አልነበረም። ራቁቷን ወደዳርቻው ስትጠጋ ልብሶቿ የሉም። አሻግራ አየች። ውሸት የእርሷን ልብስ ለብሶ ሲሮጥ ተመለከተች። ልትይዘው ራቁቷን ወደርሱ እየሮጠች በመንገዷ ላይ ከሰዎች ጋር ተገናኘች። በቁጣ በንዴት እየተጠቋቆሙ አፈጠጡባት። ፊታቸውን አዙረው ጀርባቸውን ሲሰጧት በፍርሀት እንደተሸማቀቀች ወደ ሀይቀ ጉርጓዱ ተመልሳ ተደበቀች። ለሁለተኛ ጊዜም ከዚያ ስፍራ መውጣት አፈረች።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ውሸት የእውነትን ካባ ለብሶ ይዞራል። አለምም ይቀባበሉታል። በዚያው ልክ እርቃኗን የቀረችውን እውነት ግን ፈፅሞ ማየት አይፈልጉም።

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
የአጭሩ ታሪክ መጨረሻ

በመላኢካዎች ተቀፍድዶ የጀሐነም በራፍ ላይ ቆመ። ዓይኖቹን አሻግሮ ሲመለከት ጓደኞቹ የሉም። ወደ ኋላው ዞሮ ወላፈኑ እየለበለበው የታሉ ጓደኞቼ በማለት መላኢካዎቹን ጠየቀ። ካንተ ሞት በኋላ ቶበቱ ዓቢድ ሆነው ጌታቸውን ተገናኙ ብለው ይመልሱለታል።

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
"ከሰውነቴ የቱን ልሸፍን" በማለት ነበር አባቷን የጠየቀችው። እሱም ዓይኖቿን እያየ "ከጀሀነም እሳት መቋቋም የምትችዪውን የአካል ክፍልሽን ከፍተሽ ተጓዢ" በማለት መለሰላት።

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
"ዓለምን ያለሰይፍ የከፈታችሁ!
የኢስላምን ጦር ያሳረፋችሁ ብርቱዎች!
ስብስባችሁ ሁሉም ሥፍራ የደረሰ!
ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ጎናችሁ ያላረፈ!

በዘመናችሁ የኢስላም ጠላቶችን ረፍት ነሳችሁ!
ሚሽነሪዎችን አደከማችሁ!
ዱር ገደሉን አልፋችሁ እልም ካለው ገጠር መሐል ከተማችሁ!
ምቾታችሁን ትታችሁ ወንድሞቻችሁን ለማዳን ራሳችሁን ሰዋችሁ!

እናንተ የዳዕዋ ሰዎች ሆይ!
ማንም ጋር ያላየነው ሺህ ፍቅርና መውደድ በእርግጥም እናንተ ዘንድ ነበር። አኽላቅና ዙህድን የተማርነውም ከናንተው ነው። በር አንኳኩታችሁ ዘይራችሁ ተሰድባችሁ ተባራችሁ በትዕግስት እንደፀናችሁ ስንቱን ከመስጂድ ጋር አስተዋወቃችሁ"

በታላቁ ሙጃሂድ ዐብደላህ ኢብኑ አዛም ንግግር ፅሑፌን ልቋጭ
"ምርጥ ስነ ምግባርን የተላበሱ ሙጃሂዶች" ይሏቸዋል ስለነርሱ ሲያወጉ።
"ሰካራሞችን ከቡና ቤት ወደ መስጂድ እጃቸውን ይዘው እየተራመዱ ረጅሙን መንገድ አብረዋቸው ይጓዛሉ። መስጂድ አድርሰዋቸው እነርሱ ይመለሳሉ።
በእርግጥም ስህተት የሌለበት ጭፍራ የለም። በውስጡ ያለውን መልካም ነገር እናጣጥላለን ማለት ግን አይደለም"

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
የጓደኛው ቤት ደጃፍ እንደቆመ ሲፈራ ሲቸር እያመነታ በሩን በቀስታ አንኳኳ። ተከፈተለት አይኑን ከመሬቱ እንደተከለ ለጓደኛው እንዲህ አለ፡-
"ብዙ ጊዜ የሆነኝ ዕዳ ሰላም ነሳኝ ጧት ማታ አበዳሪዬ ሲጠይቀኝ የምከፍለው ገንዘብ አጣሁ። የማደርገው ግራ ቢገባኝ ችግሬን ላካፍልህ ወዳንተ መጣሁ"

ወደ ውስጥ ተመለሰና አራት መቶ ዲርሀም ቆጥሮ ሰጠው። በደስታ ሲፍለቀለቅ ተሰናብቶት እያለቀሰ ወደቤት ዘለቀ።

ይህን ሁሉ ተደብቃ ስትከታተል የነበረችው ሚስት የባሏን ለቅሶ ስታይ "ለምን ታለቅሳለህ? ብሩን መስጠት ከብዶህ ከሆነ ይቅርታ የለኝም ብለህ ምክኒያት ፈጥረህ አትመልሰውም ነበር?" አለችው
"ያስለቀሰኝስ ያለበትን ሁኔታ ሳልከታተል በመቅረቴ ተቸግሮ እስኪጠይቀኝ ድረስ ቸልተኛ መሆኔ ነው" አላት።

ኡኹዋ

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
የጌታዬን ውዴታ ተችሬ በፊርደውሱ እንፈላሰስ ዘንድ በመላኢካኦች ታጅቤ ወደ ውስጥ ስዘልቅ ወደ ፊርአውን ሚስት ወደ አሲያ ዘንድ አቀናለሁ
"እንዴት ነበር" ብዬ እጠይቃታለሁ "ግዙፉን ድንጋይ በሆድሽ ተሸክመሽ የፀሐዩ ሐሩር እያነደደ በወላፈኑ ሲገርፍሽ ረሐብና ጥሙ ሲጠናብሽ እንዴት ነበር የቻልሽው ግርፋትና ስቃዩን?! እንዴት ነበርስ ስሜቱ"

ወደ ሙስዓብ አመራለሁ
ዱንያን እርግፍ አድርገህ ስትሰደድ እንዴት ነበር ያ ፅናትህ?! በኡሁድ ዘመቻ ከሸሂድ ተርታ ተሰልፈህ ከአንዲት ቁራጭ ፎጣ በቀር መከፈኛ ታጣልህ። ጭንቅላትህ ሲሸፈን እግርህ እየተገለጠ እግርህን ሲያለብሱህ ጭንቅላትህ እየታየ ሲቸገሩ ነቢ ውስጣቸው በሐዘን ደምቶ ጀናዛህን ሊሰናበቱ ሲመጡ ከአይናቸው እምባ እየረገፈ የተከፈንክባትን ሸካራ ቁራጭ ልብስ እያዩ "መካ ውስጥ ለስላሳና በጌጥ የተሸቆጠቆጠ ልብስ ለብሰህ አይቼሃለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ፀጉርህ በአቧራ ተሸፍኖ መከፈኛ አጣህ!" ብለው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ ብታይ እንዴት ትሆን ነበር ቢገለፅ የውስጥ ስሜትህ?!

በጀነት ወደተበሰሩት አስሩ ሰሐቦች ዘንድ በዝግታ እራመዳለሁ የኔ ውዶች እንዴት ናችሁ እያልኩ ግንባራቸውን ደጋግሜ እስማለሁ ለመሆኑ ጀነት እንደምትገቡ እያወቃችሁ እንቅልፍ እንዴት ወሰዳችሁ?! ስል እጠይቃቸዋለሁ።

ያለህን ሁሉ ተቀምተህ የምትለብሰው የምትቀምሰው አጥተህ ከሞቀው ከደላው ቤትህ ስትባረር ገላህ እንዳይታይ ጆንያ ለሁለት ከፍለህ አንዱን አሸርጠህ ሌላኛውን አገልድመህ ነቢን ለመገናኘት የፀሀዩን ግለት የበረሃውን ሙቀት ተቋቁመህ መካ ደርሰህ የናፈቅካቸውን ረሱልን ለመመልከት አይኖችህን ሽቅብ ስታንከራትት ያን ጊዜ ድንገት ከፊትህ ስታያቸው እንዴት ነበር ስሜቱ? እስኪ ንገረኝ ዙል ቢጃደይኑ?!

ወደ ሠይዲ ቢላል አቀናለሁ አንተ ጥቁር ባርያ ስለስቃይህስ አላወራ ግን ግን አሳዳሪህ በጋለ ድንጋይ ላይ አስተኝቶ ሲያሰቃይህ ጣዖት ወደማምለክ ከመመለስ ይልቅ "አሐድ... አሐድ... በማለት ፅናትህን ስትገልፅ ብርታትህ እንዴት ነበር?! አንተ የአላህ መልእክተኛ ባልደረባ እባክህ አዛንህን ልሰማ?! እያልኩ እማፀነዋለሁ።

ወደ አሊይ ዘንድ አቀናለሁ ገና ለጋ ወጣት ሳለህ የአላህ መልእክተኛ ፍራሽ ላይ ለመተኛት ምን አስቻለህ ስል እጠይቀዋለሁ?!

አቡበከር ሆይ አንተ ሲዲቁ ሰው
ሐቢቢ መሞታቸውን ስትናገር ፅናቱን ከየት አምጥተኸው ይሆን? ከቶ በምን ብርታት በሰሐቦች መሐል የአላህ
መልዕክተኛ ሞተዋል ብለህ ለመናገር ከሚንበሩ ተሰየምክ? በልብህ ስስነት፣ በርህራሄህና በለስላሳነትህ የምትታወቀው አንተ የእንባህን ዘለላ ከዓይኖችህ አብሰህ እንዴት በጥንካሬ መቆም አስቻለህ?!

ከሰዪዲ ከሐቢቢ ጋር ተቀምጬ አወራለሁ። ግንባራቸውን ደጋግሜ እየሳምኳቸው አወጋለሁ። በቅርቢቱ ዓለም በዱንያዋ ህይወት እርስዎን ማየት ሳልምና ሳስብ ኖርያለሁ። በፍቅርዎ ሰመመን ስምዎን ስደጋግም፣ ዓይኖቼ በዕንባ ተሞልተው ናፍቆትዎ አዋለለኝ። እርስዎን በማየቴ ያከበረኝ አላህ የተመሰገነ ይሁን እላቸዋለሁ።

ፊቱን ለመመልከት ከታጨሁ መጋረጃው ተገልጦ ጌታዬን ለማየት ከታደልኩ ከድንጋጤዬ ብዛት ላወራው እንኳ የምችል አይመስለኝም ግን ግን በእንባዬ ዘለላ ታጅቤ እንደምወደው እነግረዋለሁ አዎ ደግሜ ደጋግሜ እወድሀለው እለዋለሁ

ጌታዬ ሆይ!! ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር በጀነትህ ታቀማጥለን ዘንድ እጠይቅሀለው!!!

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
"ሡልጣን ሆይ! ሰላትህን በጀመዓ አትሰግድምና ምስክርነትህ ተቀባይነት የለውም..."
╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍

አሁን የምንገኝው በሙስሊሞች ዋና ከተማ ቡርሳ ነው። በታላቁ መሪ በሱልጣን ባየዚድ ቢን ሙራድ ዘመነ መንግስት!

ቡልጋሪያን፣ ቡርሳንና አልባኒያን ድል አድርጎ የከፈተው የክፍለ ዘመኑ ኃያል መሪ ቃዲ ሸምሰ ድ-ዲን ዘንድ በአንድ ጉዳይ ላይ የምስክርነት ቃሉን ሊሰጥ ከፊታቸው ተጥዷል። እንደማንኛውም ምስክር እጆቹን አጣምሮ ከችሎቱ ፊት ቆሟል።

ዳኛው ዓይኑን አማትሮ ሡልጣኑን እየተመለከተ ከእግር እስከ ራሱ በትኩረት ቃኘ
"ሡልጣን ሆይ!" አለ ዓይን ዓይኑን እያየ። ታዳሚው በዝምታ ተውጦ የዳኛውን ንግግር ለመስማት ጆሮውን ቀሰረ "ሡልጣን ሆይ! ሰላትህን በጀመዓ አትሰግድምና ምስክርነትህ ተቀባይነት የለውም። ሰላቱን በጀመዓ የማይሰግድ በምስክርነት ቃሉ ሊዋሽ ይችላልና አይታመንም ተብሎ ስለሚገመት ያንተን ምስክር አንቀበልህም ሂድ" አሉት።

በፍርድ ቤቱ የተገኙ የዳኛውን ንግግር የሰሙ ታዳሚያን በድንጋጤ አይናቸውን ለጠጡ። ሡልጣን ባይዚድን በሰዎች ፊት ዝቅ ያደረገውን ዳኛ መጨረሻ ለማየት፣ ለዳኛው እየፈሩ ባሉበት ቦታ ተቀመጡ።

ችሎቱ ፀጥ ረጭ አለ። ሡልጣን ባየዚድ አንዲትም ቃል ከአፉ ሳያወጣ አንገቱን ከመሬቱ እንደደፋ በእርጋታ እየተራመደ ፍርድ ቤቱን ለቆ ወጣ። በዚያው ቀን ከቤተ መንግስቱ አጠገብ መስጂድ እንዲሰራ አዘዘ። ተገንብቶ እንዳለቀ ሰላቱን ሳያዛንፍ አምስቱንም አውቃት በጀመዓ የሚሰግድ የአላህ ባርያ ሆነ።

ይህ ፍትህ የንግስና መሰረት፣ የኢስላም ዳኞችና ዑለማኦች ከአላህ በቀር ማንንም በማይፈሩበት ወቅት የተገኘ አስገራሚ ታሪክ ነው

╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍
ምንጮቼ:-
إنباء الغمر بأنباء العمر
الشقائق النعمانية في علماء الدولة العثمانية
حديقة السلاطين
روائع من التاريخ العثماني، سيرة السلاطين الأوائل

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ከአላህ ጋር ነግዶ ማን ከሰረ

በሰባዎቹ መጀመሪያ በሀገረ ግብፅ ግዛት ተፈህና አል-አሽረፍ በምትሰኝ ትንሽዬ መንደር ውስጥ ምንም የሌለው ደሀ የግብርና መሃንዲስ ጣራዋ በተቀደደ፣ ግርግዳዋ በተፈረፈረ ደሳሳ የጭቃ ቤት ውስጥ ከወላጆቹ ጋር ጎጆውን ቀልሶ ይኖር ይዟል። ግርግዳው በጋዜጣ የተሸፈነ ቤት!! በወላጆቹ ልፋት ተምሮ ለወግ ማዕረግ በቅቶ ቢመረቅም ስራ ማግኘት ግን አልተቻለውም። ሰላህ አጢያ ይሰኛል። ያረጀ እንጂ አዲስ ልብስ ለብሶ አያውቅም። ትክክለኛው የጫማ ቁጥር 42 ቢሆንም ከቆሻሻ ገንዳ ያገኛትን 44 ቁጥር ጫማ እንዳታልቅበት በቀስታ እየረገጠ ይጓዝባታል።

በግብርና ፋኩሊቲ ተመርቀው በከፋ ድህነት የሚሰቃዩ፣ ስራ ለመጀመር የሚፈልጉ ዘጠኝ የመንደራቸውን ሰዎች ሰብስቦ አነስተኛ ፕሮጀክት ለመጀመር ወሰነ። አማከራቸው ተስማሙ። አስረኛ አጋር እየፈለጉ እያንዳንዳቸው 200 የግብፅ ፓውንድ አዘጋጅተው ጠበቁ።

ተሰብስበው ሻይ እየጠጡ ወደነበሩት አጋሮቹ ዘንድ አቀናና "አስረኛውን አጋር አግኝቻለሁ" አላቸው።
"ማን እነደሆነ ንገረን" ሲሉ ጠየቁ
"አላህ ነው" በማለት መለሰላቸው። "ገንዘባችንን ከአደጋ ለመጠበቅ፣ ኃብታችንን ለማፋፋት እርሱ አንደኛው አጋራችን ይሆናል" በማለት ንግግሩን አከለ። ሁሉም ተስማሙ።

በጋራ የተቋቋመው የህብረት ኩባኒያ ውሉ ፀድቆ "አስረኛው ባለድርሻ አላህ የትርፉን አንድ አስረኛ ይወስዳል" የሚለው ቃል ከውሉ ወረቀት ላይ ሰፍሮ ሁላቸውም ፊርማቸውን አኖሩ። እውነተኛ የህብረት ስራ፣ ግልፅ ስምምነት ተደረገ።

የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ዙር ውጤት ጥሩ ትርፍና የተለየ ምርት ማስተናገዱን ሲመለከቱ ለተገኘው ትርፍ ለአላህ ምስጋና ይሆን ዘንድ የምርት ዑደት ውጤቱን "የታላቁ አጋር ድርሻ" በሚል መጠኑን ለመጨመር የአላህን ድርሻ ወደ 20% ለማሳደግ ወሰኑ። በየአመቱ ከፍ እያለ የአላህ ድርሻ 50% ደረሰ። አርሰው ቡቃያውን ወቅተው ምርቱን ይሸጣሉ። ነግደው ካተረፉት የአላህን ድርሻ ሳያጓድሉ ሀቁን ጠብቀው ትክክለኛ ቦታ ላይ ያውላሉ።

መስጂዶች፣ የሴቶች ሒፍዝ ማዕከል የአይታሞች ማደርያ የአቅመ ደካሞች መመገብያ ተቋማትን በአላህ ድርሻ ገነቡ። ትርፉ እያደገ ሲመጣ ለመሳኪኖች የዕርዳታ ድርጅትን አቋቋሙ..

በግብፅ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ትንሽዬ መንደር ውስጥ ደረጃቸውን የጠበቁ አራት ኮሌጆችን ገነቡ። እያንዳዳቸው ለ600 ተማሪዎች የሚሆን ማደርያ 1000 ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ ኮሌጆች!
ማንኛውም የኮሌጁ ተማሪ ወደ ቀዬው ለመሄድ ሲፈልግ ነፃ ትኬት ማግኘት እንዲችል በይተል ማል የሚል ቢሮን አቋቋሙ።

በመንደሩ ደሃ እስኪጠፋ ተቋሙ ፋፋ። ኸይራቱ ወደ ጎረቤት መንደሮች ጭምር ዘለቀ። ስራ አጥ ወጣቶች ከድህነታቸው ተላቀው እንዲሰሩ ተመቻቸላቸው። ለጎረቤት ሀገራት አትክልቶችን ኤክስፖርት ማድረግ ጀመሩ። ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት ለከተማዋ ነዋሪ ከትልቅ እስከ ትንሹ የአትክልት ከረጢት በስጦታ ይበረከትላቸው ገባ።

በረመዳን የመጀመሪያዎቹ ቀናት ኢፍጣር ተዘጋጅቶ ወንዶች በአደባባይ ሴቶች በየቤታቸው በፍቅር በአብሮነት ተሰብስበው ያፈጥራሉ። ወላጅ አልባ ሴቶች ለትዳር ሲደርሱ ወጪያቸው ተሸፍኖ ይዳራሉ።

ይህ ሁሉ በአላህ ድርሻ የሚሰራ መልካም ተግባር መሆኑ ያስገረማቸው መስራቾቹ የፕሮጀክቱ ባለቤትነት ወደ አላህ እንዲዞር ወሰኑ። እነርሱም የአላህ ሰራተኛ የረቢ አገልጋይ ሆኑ። ባለቤትነቱን ወደአላህ ሲያዞሩ "ትርፉ ሳይቋረጥ ድሆች ይጠቀሙ ዘንድ ጌታችን ሆይ አደራ!" የሚለውን ቃል ከውሉ ወረቀት ላይ አሰፈሩ።

አትራፊ ንግድ!!
መልካም ግብይይት!!
"አላህ ከምእምናን ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸውን ጀነት ለእነሱ ብቻ ያላቸው በመኾን ገዛቸው" ይሉሀል ይህ ነው።

ኢንጂነር ሰላህ አጢያ በ70 አመታቸው በጉበት በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው እንደ አውሮጳውያን የዘመን ቀመር ጥር 11 ቀን 2016 ሩሐቸው ከጀሰዳቸው ተላቀቀች። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ጀናዛቸውን ሸኘ። እየተላቀሱ ጀሰዳቸውን ከለህዱ አሳረፉ። ልጅ አልነበራቸውም።

አላህ ከምህረቱ አጎናፅፎ ጀነተል ፊርደውሱን ይወፍቃቸው።

╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍
ምንጮቼ:-
- الشيخ خالد الجندي ينعي صلاح عطية نسخة محفوظة 25 فبراير 2020
- تفهنا الأشراف قرية بلا عاطل أو فقير نسخة محفوظة 17 مايو 2017
- صلاح عطية رجل أعمال تاجر مع الله نسخة محفوظة 12 مايو 2017 على موقع واي باك مشين


#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
አልጄሪያዊቷ ጋዜጠኛ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካን እየጎበኘሁ ነበር በማለት ገጠመኟን ማውጋት ጀመረች።

"ዕቃ ለመግዛት ወደ አንድ ሱፐር ማርኬት አቀናሁ። ሒሳብ ለመክፈል ወረፋዬን እየጠበቅኩ ሳለ ሂጃቧን ጠንቅቃ የለበሰች አንዲት ሴት ወደ ሱፐር ማርኬቱ ገባች። የድካም ምልክቶች ይታይባታል። የሳር ማጨጃ ማሽን በእጇ ይዛለች። ክፍያ ለመቀበል ወደተቀመጠችው ሰራተኛ ዘንድ አቀናች።

"ይህንን ማሽን በ500 ዶላር ከሌሎች ዕቃዎች ጋር ገዝቼ ነበር... በማለት ንግግሯን ጀመረች
ደንበኛ በማስተናገድ የተጠመደችው ሰራተኛ ከአፏ ቀበል አድርጋ "መመለስ ፈልገሽ ነው ታዲያ?" በማለት ጠየቀቻት።
ሙተሐጂባዋ ቀጠለች "ዋጋውን መክፈል ፈልጌ ነው....."
ካሽ ሪጅስተር ማሽኑ ላይ የተጣደችው የሒሳብ ሰራተኛ
"አልገባኝም ትናንት ገዛሁት አላልሽኝም?
ሌላ ሱቅ ርካሽ አጊኝተሽ ከሆነ የዋጋው ማረጋገጫ እስካለሽ ድረስ ልዩነቱን አስልተን የምንመልስበት ፖሊሲ አለን" አለች።

"ይሄም ያም አይደለም" በማለት ለማስረዳት መናገር ጀመረች "ትላንት በክሬዲት ካርዴ ይህንን ማሽን ከሌሎች ዕቃዎች ጋር ገዛሁ። መኖርያ ቤቴ ከሱፐር ማርኬቱ ሁለት ሰአታት ያህል ይርቃል። ቤት ገብቼ ሂሳቡን ማየት ስጀምር የዚህን ማሽን ዋጋ ከክፍያ ሪሲቱ ላይ አጣሁት። በዚህ ምክንያት በስራሽ ክፍተት እንዳይፈጠር ደረሰኙ ላይ ባገኘሁት ቁጥር ደግሜ ደጋግሜ ደወልኩኝ። የስራ ሰዓቱ አልፎ ነበርና ሊነሳልኝ ግን አልቻለም። ዛሬ ስራ አስፈቅጄ ማሽኑን ይዤ መጣሁ። መዝግበሽ ከሂሳብ እንድትከችውና ክፍያውን እንደ አዲስ እንድፈፅም አንቺ በእኔ ምክንያት ስራሽን እንዳታጪ እኔም ባልከፈልኩት ነገር እንዳላገለግል"

ይህን የሰማችው ሰራተኛ ከመቀመጫዋ ተነሳች። ሙተሐጂባዋን እያየች አይኖቿ እንባ እንዳቀረሩ አቅፋ ትስማት ጀመር።
"የእኔ ጥፋት ሆኖ ሳለ ገንዘቡን ለመክፈል እንዴት ተመልሰሽ ለመምጣት ወሰንሽ?" በማለት ጠየቀቻት። በአግራሞት ተጭራ "ይህን ከባድ ሳጥን ተሸክመሽ ከስራ ገበታሽ አስፈቅደሽ ደርሶ መልስ አራት ሰአታት የሚያስኬድ መንገድ አቋርጠሽ እኮ እንዴት?!" ሰራተኛዋ ተገረመች።

ሙስሊሟ ሴት ምላሽ ሰጠች፡-
"ምክንያቱም ይህ አማና ነው" አለቻት።
በእስልምና የታማኝነትን ትርጉም አስረዳቻት የአማናን ክብደት አስተማረቻት።

ቢሮ ውስጥ ወዳለው ስራ አስኪያጇ ወሰደቻት። ተያይዘው ገቡ። ከቢሮው መስታወት ጀርባ ብንመለከታቸውም የሚያወሩት ግን አልተሰማንም።
የሱፐር ማርኬቱ ሰራተኛ ሙስሊሟ ሴት ያደረገችውን ​​ለማናጀሯ ስትነግራት ስሜታዊ ትመስላለች።
ከደቂቃዎች በኋላ... ሥራ አስኪያጁ ሰራተኞቹን በመደብሩ ውስጥ ሰብስቦ ስለ ሙስሊሟ ሴት ማውራት ጀመረ።

እሷ ሃይማኖቷ ያዘዛትን ግዴታዋን እንጂ ሌላ ምንም እንዳላደረገች በዓይን አፋርነት ስሜት አንገቷን ሰበር አድርጋ መግለፅ ጀመረች። ስለ እስልምናና አስተምህሮቱ ይጠይቋት ጀመር። እሷም በሚገርም የራስ መተማመን ቅንነትን በተላበሰ ትህትና መለሰች።

ሥራ አስኪያጁ ማሽኑ እንደ ስጦታ ድርጅቱ ሊሰጣት ማሰቡን ነገራት። ነገር ግን ሽልማቷን ከአላህ ዘንድ እንጂ ማሽኑን ከፍላ መግዛት እንደምትችል ተናገረች። ይህ መልካም ስራዋ እንዲያበላሽላት እንደማትፈልግም ይቅርታ ጠይቃ አልቀበልም አለች።

እነሱ እየተገረሙ እርሷም በዝግታ እየተራመደች የማሽኑን ዋጋ ከፍላ ከሱፐር ማርኬቱ ወጣች። ውስጤ በሐሴት ተናጠ። አንዳች ኩራት ተሰማኝ። ከሄደች በኋላ ስለ እሷ በሠራተኞቹ ብቻ ሳይሆን ዕቃ ሊገዙ በተሰበሰቡት ደንበኞች መካከልም ቀጠለ። ስለ ኢስላም መወራት ጀመረ። ይህ ኢስላም ነው ትክክለኛው የአላህ ዲን ተባለ።

ድሮ ድሮ ሙስሊሞች ከአማና ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው አማናው የተቀመጠበትን የፌስታል ቋጠሮ እንኳ ሳይፈታ ዘመናትን ተሻግሮ ባለቤቶቹ ሲመጡ ዕቃቸውን እንዳስቀመጡት ያገኙት ነበር አሁን አሁን ግን የአማናችን ነገር ......

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
2025/07/03 14:42:07
Back to Top
HTML Embed Code: