Telegram Web Link
ይህ መፅሐፍ .......
በሚያናውዝ የስቃይና የግፍ ትውስታ ጀምሮ ልብን በሐዘን አየናጠ በቁጭት ቀልብን አተራምሶ ወደ ጀግንነት መንደር ይዘልቃል። ገድላቸውን አያተተ በሀሴት ውስጥን ያረሰርሳል። የማር ወለላን የተላበሱ የአርአያዎቻችንን የፍትሕ ብርሐን ይተርካል። በምናብ ሰመመን ውስጥ አስጥሞ ያለንበትን የኑረት ሹረት አስወግዶ ከግሳንግስ ትርክምርኪ አርቲፊሻል ገጽታ አውጥቶ ውብ ከሆነው ዘመን ወደ ተምሳሌቶቻችን የሕይወት ገጽ ያዘልቀናል። አንዲያ ያለ ዓለም፣ አንዲያ ያለ መጣፈጥ፣ አንደዚያ ያለ ፍትሕ በተዋበ ልዕልነት ልስልስ ባለ ሙቀት ውስጥ ጥዶ አጀብ የሚያሰኝ ፍትሕን ይዳስሳል።

ታሪክ መስራት ላቃተን ለአኔው ዘመን እርቃነ ገላዎች በከፊሉም ቢሆን ዓውራችንን በመሸፈን ከቦታው ያለን እስክንመስል ዱር ሸንተረሩን አልፈን አብረን አንዘልቃለን። በንዴት በደስታ በፈገግታ አየታጀብን እንነጉዳለን። እየዋለሉ የሚተራመሱ ነፍሶች ላይ ሕይወትን የዘሩ ተምሳሌቶችን በአስገራሚ የኑረት ኃይል ንዝረትን እየቃኘ ድንቃድንቅ ክስተቶችን አያወሳ ይጠናቀቃል። ትንፋሽ አያቆራረጠ በጥልቁ ወደ ኃያልነት ይመጥቃል። በጥልቅ ማንቀላፋት ውስጥ ያሉትን ወደራስጌያችው ጠጋ ብሎ የተጠቀለሉበትን አንሶላ ገፎ ንቁ እያለ ይጣራል። አንደጠዋት ፀሓይ በመስኮት ዘልቆ ያበራል አንሻአላህ።

በ410 ገፅ ተሰናድቶ የተዘጋጀውን ይህን የፅሑፎቼን ስብስብ ኢንሻ አላህ ፒ ዲ ኤፉን ነገ በዚህ የቴሌግራም ቻናል እለቀዋለሁ አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን።

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch
tarikochen terekelachew.pdf
15.7 MB
"ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው"

ፒ ዲኤ ፍ

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch
Forwarded from Eksi online market
ሰለዋት እናብዛ‼️
🌴🌴🌴

ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዓ ተጠባብቀን በረሱል [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ላይ ሰለዋት የምናወርደው
ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ የምንዘናጋው

📚እስኪ አላህና መልዕክተኛውን ምን እንደ ሚሉን እንመልከት
👇👇👇

🌴💥🕋🌴💥🕋

قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾
[الأحزاب: ٥٦]
አላህ እንዲህ ይላል፦
{አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ; እናንተ ያመናችሁ ሆይ በእሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ}


📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇

"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا "
و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407
{ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል}

"من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات"
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩)
{በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል}

" من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات "
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠)
{ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል}

" من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا "
رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠)
وصححه الألباني رحمه الله
{በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል}

🌴🌱🌴🌱🌴🌱
"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"


"ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው"
#share
#Join
@smithhk
እንደ አውሮጳውያን የዘመን ቀመር 2016 በፍቅር የቀለሱት ጎጆ በእርሱ ህመም ደበዘዘ። በሽታ እያንፈራፈረ አልጋ ላይ አኖረው። ህመሙ በጠናበት አንድ ዕለት እንዲህ ተከሰተ። ፍራሹ ላይ ተንጋሎ ዓይኖቹን እንደምንም እየገለጠ ያ ኡሙል-ሙቅረአይን ሲል ተጣራ። ሲወዳት አምሳያ የሌላት ሚስቱ ናትና እንዲህ ነው የሚጠራት። ሰባቱን ልጆቹን ቁርአንን እንድትሐሳፍዛቸው አደራ እያለ እስትንፋሱ ተቋረጠ። ወሲያ መሆኑ ነው። እርሷም አደራውን ተቀብላ ከዱንያ ውጣ ውረድ ጋር ታግላ እናትም አባትም ሆና ልጆቿን እያሳደገች ተራ በተራ ቁርአንን አስሐፈዘች። ከቀናት በፊት የመጨረሻው ሰባተኛው ልጇ ቁርአንን ሐፍዞ በመጨረሱ የምስክር ወረቀት ተበረከተላት።

እንዲህ ያሉ እናቶች ሲኖሩ የኢስላም ክብር ዳግም ያብባል ኢንሻ አላህ።

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ካነበብኳቸው ልብ አስለቃሽ ታሪኮች

1- በስኳር በሽታ ለደከመችው እንስት
"ህመሙ ሰውነትሽ ውስጥ እየተሰራጨ ነውና እጅሽ መቆረጥ አለበት" ተባለች።
ደንገጥ ብላ እየተመለከተች
"ልጄ ወደ ሌላ ሀገር ሊጓዝ ትንሽ ቀናት ስለቀረው አይሮፕላን ውስጥ ሲገባ እጄን አወዛውዤ እንድሰናበተው አንድ ሳምንት መጠበቅ እችላለሁን?" በማለት ጠየቀች።

2- ከምሽቱ 2 ሰአት ፈጣሪ አለመኖሩን የሚያትት ጽሁፍ በማስታወሻ ደብተሬ ላይ አስፍሬ ጎኔን ላሳርፍ አልጋዬ ላይ ተጋደምኩኝ። አላህ የሆነ ነገር እንዳያደርገኝ በመስጋት ማብራቱን ለማጥፋት ፈራሁ።

3- የእናቴን ጀናዛ በሲድር አጥቤ እንዳበቃሁ ከፈኗን ሚስክ እየቀባሁ የአፍንጫዋን ቀዳዳ ለመክደን ጥጥ ፈልጌ ተጣራሁ ጮክ ብዬ "እማ! ያንን ጥጥ ስጪኝ" አልኳት።

4- ባለቤቴ ከሚቀርበው ምግብ ውስጥ የረገፈ ፀጉሬን ሁሌ ስለሚያገኝ ንፅህናሽን የማትጠብቂ ቸልተኛ ሴት ይለኛል ካንሰር እንዳለብኝ ግን አያውቅም።

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
መነሻውን በሞሮኮ ያደረገው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር 6.7 ስኬል አልፎ በአልጄሪያና በሞሪታኒያ ድንበር ከተሞች እየተዛመተ ይገኛል። እስካሁን የሟቾች ቁጥር ከ 1000 ማለፉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል።

ጌታዬ ሆይ! ኃያልነትህን እንዳሳየካቸው እዝነትህን ቸራቸው አሚን

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
በሀገረ ሞሮኮ በሐውዝ ከተማ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሰውነቷ ቆስሎ ከፍርስራሽ መሐል ተጋግጣ ወደ ሆስፒታል አቀናች። ራሷን አውቃ ስትነቃ ጋዘጠኞች ጥያቄ ሊያቀርቡላት ከሆስፒታሉ ቅጥር ከተሙ።

ስለሰለባው ሊጠይቋት ማይካቸውን አስጠጉ። ንፁኋ ሴት ግን ባሏ እስካልፈቀደላት ካሜራ ፊት ቀርባ ክስተቱን ለማውጋት ፈቃደኛ አለመሆኗን ተናገረች።

#ሼር
#share #join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

ኒስፈ ሻእባን
የዛሬዋ ለሊት የ ሸዐባን አጋማሽ ነች።
""''''''''''"""""
በዚህ በሸእባን ወር በጣም የተላቀችና የተከበረች ለሊት ትገኛለች። እሷም የሻእባን አጋማሽ(ኒስፈ ሻእባን) ለሊት ነች። በዚህች ለሊት አላህ ባሮቹን ሙሉ በሆነ እዝነቱና ረህመቱ ይሸፍናቸዋል። ይቅርታን ለጠየቀ ይቅር ይለዋል፡ ለጠየቀም ይሰጠዋል፡ የተቸገረን ከችግሩ ያላቀዋል፡ ለባሮቹ ስራቸውንና ሲሳያቸውን ይጽፍላቸዋል።
የሻእባን አጋማሽ ለሊትን አስመልክቶ ብዙ የሀዲስ ዘገባዎች ሰፍረው ይገኛሉ፡ ከነዚህ ዘገባዎች ውስጥ ሶሂህ፡ ሀሰንና ዶኢፍ የሆነ አለ። በኡለሞች የሀዲስ ሚዛን ሶሂህ እና ሀሰን ከተባሉት የተወሰኑትን ብቻ ልጥቀስ።
የአላህን መልእክተኛ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) የሚከተለውን ብለዋል፡-

1. "አላህ በሻእባን አጋማሽ ለሊት ለባሮቹ ረህመቱን ይገልጣል፡ ሙሽ-ሪክና ሙና-ፊቅ የሆኑት ሲቀሩ ለሁሉም ምህረት ያደረጋል" (ጦበራኒይና ኢብኑ ሂባን)

2. "ጂብሪል(አለይሂ ሰላም) መጣና 'ይህች የሻእባን አጋማሽ ለሊት ናት፡ በአላህ ይሁንብኝ በዚህች ለሊት በከሊብ ጎሳ በጎ ጸጉር ቁጥር ልክ ከእሳት የሚድኑ ሰዎች አሉ፡ አላህ ወደ ሙሽሪኮች፡ ሙናፊቆች፡ ዝምድና ቆራጭ ወደሆኑት፡ ልብሳቸውን ጎታች ወደሆኑት(ልብሳቸውን ማያሳጥሩ ወንዶች)፡ ወላጆቹን ወደሚበድል፡ አስካሪ መጠጥ ወደሚጠምቅ. . . . አይመለከትም" (በይሀቂይ)

3."የሻእባን አጋማሽ ለሊት ሲሆን ተጣሪ ይጣራል 'ማርታ የሚፈልግ ምህረት የማደርግለት፡ የሚጠይቀኝ የምሰጠው' ይላል። በዚህች ለሊት አንድ ባሪያ ጠይቆ የሚከለከለው ነገር የለም በብልቷ ዝሙትን የፈጸመች እና ሙሽሪክ የሆነ ሲቀር" (በይሀቂይ)

አላህ በዚህ ወር፡ በዚች የተከበረች ለሊት ከሚምራቸው ባሮቹ ያድርገን። ረመዷንንም በሰላም ያድርሰን።

ምንጭ፡- 'ማዛ ፊ ሻእባን' ከተሰኘው ከሀረመይኑ(ከሁለቱ ሀረሞች) ሙሀዲስ ሙሀመድ ቢን አለዊይ(ረሂመሁሏህ) ኪታብ

ጸሐፊ፦ ሙዓዝ

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀
#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
Forwarded from Zad Islamic Channel
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️

#ቁርኣን

🌟የ Youtube ቻናላችንን ተቀላቀሉ👇
youtube.com/@ZadIslamicChannel

👉@ZadIslamicChannel✔️
👉@ZadIslamicChannel✔️
Forwarded from Zad Islamic Channel
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

#ቁርኣን

🌟የ Telegram ቻናላችንን ተቀላቀሉ👇

👉@ZadIslamicChannel✔️
👉@ZadIslamicChannel✔️
Forwarded from Zad Islamic Channel
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዚህ ውስጥም እየታለፈ ነው። ይህ በረፈህ የስደተኞች ካምፕ ላይ እየተፈፀመ ካለው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከፊል ትዕይንት ነው።

ጭንቅላቱ አልተገኘም። ግማሹን አርደው ግማሹን ከነሂወታቸው አቃጠሏቸው... ከአንገት በታች ያለው አካሉን ከፍ ያደርገዋል ግራና ቀኝ እያዟዟረ ሸሚዝና ሱሪ የለበሰውን ሰውነቱን ይታቀፈዋል። ይህ ሁሉ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርስ ግፍ ሰቆቃና ግድያ ነው።

ወላሂ ነው ምላቹ ካየሁት እና እዛ ካለው ነገር እሄ ባጣም ትንሹ ነው.... ለመላክ ቀርቶ ድጋሜ ማየት እስከሚያቅተኝ ድረስ ብዙ ክስተቶች አሉ


ምድር ያኔ ምስክርነቷን ስትሰጥ ምን አደረግን ልንል ነው ? ዱዐ አደረግንላቸው...
ድምፅ ሆንላቸው...
ምን?

Credit: (@STRONG_IMAN)

👉@ZadIslamicChannel✔️
👉@ZadIslamicChannel✔️
Forwarded from Zad Islamic Channel
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተሰረቁ የልጅነት ጊዜዎች...

👉@ZadIslamicChannel✔️
👉@ZadIslamicChannel✔️
Forwarded from Zad Islamic Channel
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
★አስርቱ የዙል-ሒጃ ቀናት★

👉@ZadIslamicChannel✔️
👉@ZadIslamicChannel✔️
📢 ምርጥ ፕሮግራም 👍

📋 በአስሩ የዙልሒጃ ቀናት ቁርኣንን ለማኽተም የሚረዳ ፕሮግራም 👇

📆 ዙልሒጃ 01 : ከፋቲህ - አል ዒምራን
📆 ዙልሒጃ 02 : ከኒሳእ - ማኢዳህ
📆 ዙልሒጃ 03 : ከአንዓም - ተውባህ
📆 ዙልሒጃ 04 : ከዩኑስ - ኢስራእ
📆 ዙልሒጃ 05 : ከከህፍ - ኑር
📆 ዙልሒጃ 06 : ከፉርቃን - ፋጢር
📆 ዙልሒጃ 07 : ከያሲን - ሐዲድ
📆 ዙልሒጃ 08 : ከሙጃደላህ - ናስ
📆 ዙልሒጃ 09 : ፆም ፣ ተክቢራ፣ዱዓ ...
📆 ዙልሒጃ 10 : የዒድ ቀን 🎈🎁🎈
Forwarded from Zad Islamic Channel
የዙል-ሒጃን ጨረቃ ለማየት በመጠባበቅ ላይ


Dhul Hijjah 1445/2024 Crescent search this evening!


The dates will determine the days of #Hajj and #EidAlAdha
◾️በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው

#አስሩ_የዙልሒጃ_ቀናት

♦️ዙልሒጃ ብሎ ማለት የዐረበኛ 12ኛ ወር ሲሆን የዚህ ወር 10ቀናት ልዩ ትሩፋት እንዳላቸው ነቢያችን - ﷺ - ተናግረዋል። እንደዚሁ ቁርአን ላይም እነዚህ ቀናት ተጠቅሰዋል። አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ከፈጠራቸው ፍጡር ውስጥ አንዱን ከሌላኛው አበላልጧል። የረመዷን ወር ከወሮች ሁሉ በላጭ ነው። የረመዷን የመጨረሻዎቹ 10ቀን ለሊቶች ከለሊቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ምክንያቱም ለይለተል ቀድር በውስጧ ስላለ ነው።
°
♦️የዙልሒጃ አስሩ ቀናት ደግሞ ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ለዚህም ነው ሸይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያ - ረሒመሁላህ - ከረመዷን የመጨረሻዎቹ 10 ቀናቶች የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናቶች እንደሚበልጡና ከዙልሒጃ10 ለሊቶች ደግሞ የረመዷን 10 የመጨረሻ ለሊቶች እንደሚበልጡ ተናግሯል። 📒(መጅሙዓል ፈታዋ 25/287)
°
♦️አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - በተከበረው ቁርአኑ ላይ እንዲህ ይላል ፦

{ لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ }

[| ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡ ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡ |] 📒(ሐጅ ፥ 28)
°
♦️እነዚህ ቀናት ብሎ ማለት ዐብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንደገለፁት አስሩ የዙልሒጃ ቀናት እንደሆኑና በነሱም ላይ አላህን በጣም ማውሳት እንዳለብን ተናግረዋል።
°
♦️ከዚህም በተረፈ ዐብደላህ ኢብን ዓባስ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ባስተላለፈው ነቢያችን - ﷺ - ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፦ [ ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም።] በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን! ተብለው ሲጠየቁ ፦ [ አዎ. በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን , ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ] 📒(ቡኻሪ ፥ 969)
°
♦️ኢብኑረጀብ - ረሒመሁላህ - እነዚህ አስር ቀናት ከሌሎቹ ሊበልጡ የቻሉበት ምክንያት ሲናገሩ ፦ | በጣም ዋና የሚባሉት የዒባዳ አይነት በአንድ ላይ ስለሚሰባሰቡበት ነው እነሱም ሰላት ፣ ፆም ፣ ሰደቃ እና ሐጅ ናቸው ብለዋል። | 📒(ፈትሑልባሪ ፥ 2/460)
°
◾️ዋና ዋና በዚህ ወር ልንሰራቸው ከሚገቡ ተግባራቶች ውስጥ ፦
🔺1️⃣.ፈርድ ሰላትን ወቅት ጠብቆ መስገድ ይኖርብናል። ሱጁድ በማብዛት ወደ አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - መቃረብ ተገቢ ነው። ነቢዩም - ﷺ - [ ሱጁድ በማብዛት ላይ አደራ ; አንተ እኮ ምንም ሱጁድ አታደርግም በሰጁዱህ ልክ አላህ ዘንድ ማእረግህ ከፍ ቢል እና ወንጅልህም ቢራገፍልህ እንጂ ብለዋል። ] 📒(ሙስሊም ዘግቦታል). ሱና ሰላቶችንም ማብዛት ይጠበቅብናል። በተለይም 12ቱ "ራቲባ" የሚባሉትን እነሱም ፦ ከሱብሂ በፊት 2ረከዓ ፣ ከዙሁር በፊት 4ረከዓ , በኋላ 2ረከዓ ፣ ከመግሪብ በኋላ 2ረከዓ እና ከዒሻእ በኋላ 2 ረከዓ ናቸው።
°
🔺2️⃣.ፆም መፆምም ተገቢ ነው። አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆንባቸው ቀናቶች የሉም ከነዚህ 10 ቀናቶች የበለጠ ሰለተባለ ፆም ደግሞ ከመልካም ስራ ስለሚገባ መፆም ተገቢ ነው። ኢማሙ ነወዊም አስሩ የዙልሂጃን ቀን መፃም የጠበቀ ሱና ነው ብለዋል።
🔺3️⃣.ሰደቃ በመስጠት ላይም መጠናከር ይኖርብናል።
°
🔺4️⃣.ተክቢር እና ተህሊልልን ማብዛትም ተገቢ ነው። ሰሓባዎችም በነዚህ ቀናት ውስጥ ተክቢርና ተህሊልን ያበዙ ነበር። በአሁን ሰአት ግን በጣም ከተረሳ ሱናዎች ውስጥ አንዱ ነው። ኢማም አል-ቡኻሪም እንዲህ ብለዋል ፦ | ኢብኑ ዑመርና አቡሁረይራ ወደገበያ ቦታ በመውጣት በነዚህ ቀናቶች ውስጥ ተክቢር ይሉ ነበር ሰዎችም በነሱ ተክቢራ ማለት ተነሳስተው ተክቢራ ይሉ ነበር። |. አባባሉም ፦ አሏሁ አክበር , አሏሁ አክበር , ላኢላሀኢለላህ, አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ.
ሌሎችም በትክክለኛ ሐዲስ የተዘገቡ ተክቢራዎችን ማለት ይቻላል።
°
🔺5️⃣.ከአስሩ ቀናት በተለየ መልኩ የ9ኛውን ቀንማለትም የዐረፋን ቀን መፆም ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ -  ስለዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል ፦ [ ያለፈውን አመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ] 📒(ሙስሊም ዘግቦታል). በዚህም ቀን ዱአን ማብዛት አስፈላጊ ነው።
°
🔺6️⃣.ሌላኛው 10ኛው ቀን ላይ ሚተገበሩ ተግባሮች ናቸው። እነሱም ፦ ዒድ ሰላት መስገድ ፣ ኡድሂያን ማረድ ... ሐጅ ላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ጀመራት ይወረውራሉ ፣ ፀጉራቸውን ይላጫሉ ፣ ሀድይ የያዙ ሰዎች ሀድያቸውን ያርዳሉ ፣ ወደ መካ ተመልሰው ጠዋፈል ኢፋዷ ያደርጋሉ። በአጠቃላይ 10ኛው ቀን አላህ ዘንድ በጣም ትልቅ ነው።
°
♦️ስለዚህ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን በምናገኝበት ጊዜ ተውበት አድርገን ራሳችንን ለኸይር ስራ ዝግጁ አድርገን ከወንጀላችን ታቅበን ሌሎችንም ከዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ይሄን እድል እንዲጠቀሙ መገፋፋት ያስፈልጋል ። እንደዚህ አይነት እድል በሚመጣ ጊዜ ሳናውቀው ስለሚያልፈን መስነፍ አያስፈልግም መጠንከር እና ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል።
°
♦️በመጨረሻም ኡድሂያን ማረድ የፈለገ ሰው ከሰውነቱ ላይ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን እስኪያርድ ድረስ መቁረጥ የለበትም። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ - ኡሙሰለማ ባስተላለፈችው ሀዲስ እንዲህ ስላሉ ፦ [ የዙልሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና , ከእናንተ አንድኛችሁ ኡድሂያን ማረድ ከፈለገ ፀጉሩን እና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ። ] 📒(ሙስሊም ፥ 1977 ላይ ዘግቦታል). አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገን።
Forwarded from Zad Islamic Channel
በዐስሩ ቀናት ምን እንስራ?
        (ክፍል አንድ)
================

⚀  በእነዚህ ቀናት ውስጥ ምን እናድርግ?

ተውበት: ‐
በማንኛውም ጊዜ‐ ለኔ ቢጤ ኃጢኣተኛ ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የአላህ ባሪያ ምርጡ ተግባር ተውበት ነው። በተለይ እንዲህ ዓይነት ጊዜያትን በተውበት ስሜት ማሳለፍ ወሳኝ ነው። እውነተኛ ተውበት፣ በሙሉ ወኔ ወደ አላህ መመለስ፣ ርቀነው ወደሄድነው የጌታችን እቅፍ መጠጋት የመጀመሪያም የመጨረሻም ስራችን መሆን አለበት።
በዱንያም ሆነ በአኺራ የሰው ልጅ መድህን እና ስኬት ያለው በዚህ ውስጥ ነው። ያፈረስነውን መገንባት፣ ያቆሸሽነውን ማፅዳት፣ ያበላሸነውን ማደስ… ተውበት ነው።
ማን አለ ከእኛ መሀል ያላመፀ? ማናችን አለ ያላጠፋ? ማን አለ ንፁህ? ማን አለ ግፍ ያልሰራ?
ማንም! ማጥፋቱን እንደተካንበት ሁሉ ያሳለፍነውን ደግሞ እንድንክስ ዘንድ የተሰጠን እድል ነው፤ ተውበት።
አላህ እንዲህ ብሏል: ‐
[وَتُوبُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ ٱلْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ]
«ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡»

❷ ጊዜውን ለመጠቀም መጓጓት: ‐


እነዚህን ጊዜያት ለመጠቀም እና በመልካም ስራዎች ለማሸብረቅ መጓጓት አለብን። አላህ በሚፈልገው መልኩ በአግባቡ ጊዜውን ለመጠቀም መወሰን አለብን። አንድን ነገር ከልቡ ወስኖ የነየተን ሰው አላህ ያግዘዋል።
[وَٱلَّذِينَ جَٰهَدُوا۟ فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا وَإِنَّ ٱللَّهَ لَمَعَ ٱلْمُحْسِنِينَ]
«እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡»

@ZadIslamicChannel
Forwarded from Zad Islamic Channel
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከተማው ተቆራርጦ በወደቁ፣ ደም በለበሱ ሬሳዎች ተሞልቷል....
ሁኔታወን መግለፅ የከብዳል ወለሂ... ምን ልበል እንዴት ህመማቸውን ልግለፅ ....የሴቶች ጩህት የእናቶች እልቅሻ ከተማው ላይ ተሰራጭቷል...

👉@ZadIslamicChannel✔️
👉@ZadIslamicChannel✔️
Forwarded from Zad Islamic Channel
ጸጥ ብለህ አትቀመጥ
ያለኸው እጅግ በጣም በላጭ በሆኑት የዱንያ ቀናት ውስጥ ነው።
አላህን አውሳ! ሱብሐነ-ል'ሏህ ፣ አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሃ ኢለ-ል'ሏህ… በል፣


👉@ZadIslamicChannel✔️
👉@ZadIslamicChannel✔️
2025/07/03 06:55:19
Back to Top
HTML Embed Code: