Telegram Web Link
🎁 🎁

📬 የሴቶች ለሴቶች የክረምት ኮርስ መዝጊያ ፕሮግራም!


ላለፉት ሁለት ወራት በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር አማካኝነት በተለያዩ ቅርንጫፎች ሲሰጥ የነበረው የሴቶች ለሴቶች የክረምት ኮርስ አስተማሪ በሆኑ ፕርግራሞች ታጅቦ የፊታችን እሁድ ይጠናቀቃል።

እህቶችም በዚህ ልዩ ፕርግራም ላይ እንድትታደሙ ተጋብዛችኃል።

📅 ቀን ፦ እሁድ ጳግሜ 5 / 2009

ሰዓት ፦ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ

🔎 አድራሻ፦ 18 በሚገኘው ኢስላሚክ ሴንተር።
ተከታታይ የኪታብ ቂራአት ኮርስ ቁ.9

📕 ባቡ አል አስማኢ ወሲፋት ከሸይኽ ፈውዛን አቂደቱ ተውሂድ ኪታብ

🎙ማብራሪያ ፡- በኡስታዝ ጣሀ አህመድ (ሀፊዘሁላህ)

🗓 ት/ርቱ የሚሰጥበት ቀን ፡-
ከእሮብ መስከረም 3/ 2010 እስከ ጁምዓ መስከረም 5/ 2010

ሰዓት ፡- ከጠዋቱ 4፡00 - ዝሁር

🏛 በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 አደባባይ)
💎ታላቅ የሙሀደራ ግብዣ

👉🏼ኢልም የመቅሰም ቴከኒኮችና አዳቦች

🎙በሸይኽ ሙሀመድ ሰኢድ አስልጢይ

📆 እሮብ መስከረም 3 ከመግሪብ ሰላት በኃላ

🕌በኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር
(18 አደባባይ)
🛑 ከድግምትና ከምቀኝነት እንዲሁም
ከቡዳ (ዓይን) መጠንቀቂያ

🖌 በአል ኢማም ኢብኑ ቀዩም አል ጀውዚያህ

🛑አል ኢማሙ አል ሀፊዝ ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያህ አላህ ይዘንላቸውና “ዛደ አል ሚዓድ ፊ ሀድዬ ኸይሪ አል ዒባድ” በሚባው ምርጥ መፅሐፋቸው ስለ ምቀኝነትና ስለቡዳ እንዲሁም ስለድግምት ካወሩ በኃላ እንዲህ አሉ፡- “የምቀኛ ተንኮል ድግምት ከተደረገበት ግለሰብ ላይ ከአስር መንገዶች በአንደኛው ይወገድበታል፡፡🛑

1️⃣ የመጀመሪያው መንገድ፡- ከተንኮሉ በአላህ መጠበቅ

👉🏼በአላህ መጠበቅ፣ ወደ እርሱ መጠጋት ከዚህች ምዕራፍ (አል ናስ) የተፈለገበትም ይኸው ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በእርሱ ለጠበቀበት ሰሚ ነው፡፡ ከሚጠበቅበትም ነገር አዋቂ ነው፡፡

👌🏼ይሰማል ማለት በዚህ አገባብ ምላሽ የመስጠት መስማትን እንጂ አዳራሽ የሆነውን መስማት አይደለም፡፡ የዚህም ንግግር አምሳያ “ሰሚ አላሁ ሊመን ሀሚዳህ” የሚለውና የአላህ ምርጥ ወዳጅ የሆኑት ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና እንዳሉት

إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ إبراهيم: ٣٩

“ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና” (ኢምራን 39)

👉🏼አንዳንድ ጊዜ የሱን ሰሚነት ከእውቀቱ ጋር ያጣምረዋል፤ አንዳንዴ ደግሞ ከማየት ጋር ያጣምረዋል፡፡ ይኸውም የሚጠበቅበት ግለሰብ ሁኔታ በሚያስፈርደው መልኩ ነው፡፡ እርሱ ከጠላት የሚጠበቅበት አካል አላህ እንደሚያየውና ሴራውንና ተንኮሉንም እንደሚያውቀው ያውቃል፡፡

👉🏼አላህ (ሱ.ወ) ለዚህ ለሚጠበቅበት ግለሰብ በእርሱ በመጠበቁ የተቀበለውና የጠላቱን ተንኮል አዋቂ መሆኑን፤ እንደሚያየውም ነገረው፡፡ በእርሱ የሚጠበቀው አካል ተስፋው እንዲያብብና አላህን ወደ መለመን ልቡ እንዲዞር፡፡

👌 የቁርአንን ጥበብ አስተውል በአላህ መጠበቅ (አል ኢስቲዛህ) መኖሩን በምናውቀው ነገር ግን የማናየው ከሆነ {السَّمِيعُ الْعَلِيمُ} በሚል ቃል በምዕራፍ አል አዕራፍ እና አል ሰጅዳህ ሲመጣ ከሰዎች ተንኮል መጠበቅ ሲሆን ግን በአይን የሚታይና የሚጨበጥ በመሆኑ {السَّمِيعُ البَصِيرُ} በሚል ቃል በምዕራፍ አል ጋፊር ላይ ተጠቅሷል፡፡

አላህ (ሱ.ወ) በዚህ ምዕራፍ እንዲህ ይላል፡-

إِنَّ الَّذِينَ يُجَادِلُونَ فِي آيَاتِ اللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَانٍ أَتَاهُمْ ۙ إِن فِي صُدُورِهِمْ إِلَّا كِبْرٌ مَّا هُم بِبَالِغِيهِ ۚ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ غافر: ٥٦

‹‹እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ አንቀጾች የሚከራከሩ በልቦቻቸው ውስጥ እነርሱ ደራሾቹ ያልኾኑት ኩራት ብቻ እንጅ ምንም የለም፡፡ በአላህም ተጠበቅ፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነውና፡፡›› (አል ጋፊር 56)

👉🏼ምክንያቱም የእነዚህ ተግባር በአይን የሚታይ ሲሆን የሰይጣን ጉትጐታና ውስወሳ ግን በልብ ላይ የሚጥለው ከእውቀት (ኢልም) ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ላይ ሰሚና አዋቂ በሆነው እንድንጠበቅ አዘዘ፡፡ በአይን ከሚታይ ነገሮች “ በአል-ሰሚዕ አል በሲር” በሆነው እንድንጠበቅ አዘዘ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከሁሉ በላይ አዋቂ ነው፡፡


🔷 ሺፋዕ 🔷

ቁርዓናዊ ፈውስ- እራስን ከጂን እና ከድግምት ለመጠበቅ

ስለ ሲህር እና መሰል ነገሮች ግንዛቤን ማስጨበጥ፡፡

ምልክቶች፣ መከላከያዎች እና መፍትሄዎችን መጠቆም፡፡

አድራሻችን ፡-

ፌስ ቡክ www.fb.com/nosihr

ቴሌ ግራም https://www.tg-me.com/nosihr

ብሎገር www.nosihr.blogspot.com
🛑 ከድግምትና ከምቀኝነት እንዲሁም
ከቡዳ (ዓይን) መጠንቀቂያ

🖌 በአል ኢማም ኢብኑ ቀዩም አል ጀውዚያህ

🛑አል ኢማሙ አል ሀፊዝ ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያህ አላህ ይዘንላቸውና “ዛደ አል ሚዓድ ፊ ሀድዬ ኸይሪ አል ዒባድ” በሚባው ምርጥ መፅሐፋቸው ስለ ምቀኝነትና ስለቡዳ እንዲሁም ስለድግምት ካወሩ በኃላ እንዲህ አሉ፡- “የምቀኛ ተንኮል ድግምት ከተደረገበት ግለሰብ ላይ ከአስር መንገዶች በአንደኛው ይወገድበታል፡፡🛑

2️⃣ሁለተኛው መንገድ፡- አላህን መፍራት

👉🏼የአላህ (ሱ.ወ) ትዕዛዝንና ክልክልን መጠበቅ፡፡ አላህን (ሱ.ወ) የፈራ አላህ (ሱ.ወ) ይጠብቀዋል ከእርሱ ሌላ ወደ ሆነ አካል አይጥለውም፡፡

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا لَا يَضُرُّكُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئًا آل عمران: ١٢٠

“ብትታገሱና ብትጠነቀቁም ተንኮላቸው ምንም አይጐዳችሁም” (አል ዒምራን 120)

👉🏼ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ለአብደላህ ኢብኑ አባስ እንዲህ አሉ፡-

«احفظ الله يحفظك، احفظ الله تجده تجاهك»

“አላህን ጠብቅ እርሱ ይጠብቅሃልና አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህና …”

👉🏼 አላህን የጠበቀ (ትእዛዙን በመታዘዝና የከለከለውን በመከልከል) አላህ ይጠብቀዋል፡፡ ወደ የትም አቅጣጫ ቢሄድ ፊት ለፊቱ ያገኘዋል፡፡ አላህ ጠባቂው የሆነውና ፊት ለፊቱ የሆነለት ለመሆኑ ማንን ነው የሚፈራው!?


🔷 ሺፋዕ 🔷

ቁርዓናዊ ፈውስ- እራስን ከጂን እና ከድግምት ለመጠበቅ

ስለ ሲህር እና መሰል ነገሮች ግንዛቤን ማስጨበጥ፡፡

ምልክቶች፣ መከላከያዎች እና መፍትሄዎችን መጠቆም፡፡

አድራሻችን ፡-

ፌስ ቡክ www.fb.com/nosihr

ቴሌ ግራም https://www.tg-me.com/nosihr

ብሎገር www.nosihr.blogspot.com
🛑ከድግምትና ከምቀኝነት እንዲሁም
ከቡዳ (ዓይን) መጠንቀቂያ

🖌 በአል ኢማም ኢብኑ ቀዩም አል ጀውዚያህ

ሶስተኛው መንገድ፡-

በአላህ ላይ መመካት

👉በአላህ ላይ የተመካ እርሱ በቂው ነው፡፡ በአላህ ላይ መመካት አንድ ባሪያ ሊሸከመው የማይችለው የሆነ ችግርና በደል እንዲሁም ጠላትነትን ከሚከላከልበት ጠንካራ መንገዶች አንዱ ነው፡፡

🍓አላህ (ሱ.ወ) የበቃውና ጠባቂው ለሆነን ግለሰብ ጠላቱ ሊከጅለውና ሊጐዳው አይችልም፡፡ እንደ ሙቀትና ብርድ ወይም ራህብና ጥማትን የመሰለ የማይቀር የሆነ ፈተና ሊገጥመው ይችላል፡፡ እንጂ ጠላቱ ፈላጐቱን የሚሞላበት ጉዳት ፈፅሞ አይገጥመውም፡፡ በግልፅ ሲታይ የእርሱ ችግር የሚመስለውና ነገር ግን እውነታው ለእርሱ በጐ መዋል በሆነው ችግርና አላህ ከእርሱ እንዲያድነው በሚለምነው ጉዳት መሀከል ልዩነት አለ፡፡

👍ከቀደሞቶቹ አንዱ እንዲህ ይላል፡- አላህ (ሱ.ወ) ለእያንዳንዱ ተግባር አምሳያውን ክፍያ አድርጓል በእርሱ የመመካት ክፍያውን የእርሱን ጥበቃ ለባሪያው አድርጐታል፡፡

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-
وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ ﮭ الطلاق: ٣
‹‹በአላህ ላይ የተመካ እርሱ በቂው ነው፡፡›› (አል ጠላቅ 3)

👉እንደሌሎች ተግባር እንዲህ ክፍያ እንሰጠዋለን አላለም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በእርሱ ላይ ለሚመካ ባሪያው ራሱን በቂውና ጠባቂው አድርጓል፡፡

👉አንድ ባሪያ በአላህ ላይ እውነተኛ መመካት ቢመካ ሰማያትና ምድር በውስጧም ያሉት ቢያሴሩበት አላህ (ሱ.ወ) ከዚህ መውጫ ቀዳዳን ያደርግለታል፤ ይበቃዋልም፤ ይረዳዋልም፡፡

➡️ በእርግጥ የመመካት እውነታን፣ ትሩፋቶችንና ከባባድ ጥቅሞቹን እንዲሁም አንድ ባሪያ ወደዚህ ርዕስ ምን ያህል እንደሚያስፈልገው “አል ፈትሁ አል ቁድሲ” በሚባለው መፅሐፍ ላይ አውስተዋል፡፡

➡️ እንዲሁም በአላህ ላይ መመካትን የደካሞች ደረጃና የተራው ህብረተሰብ ደረጃ ያደረገን ከንቱነትን አውስተናል፡፡ በብዙ አይነት መልኩ ንግግሩንም ውድቅ አድርገናል፡፡

➡️ እንዲሁም በአላህ መመካት ከአዋቂዎች ደረጃዎች ዋንኛው መሆኑንና የአንድ ባሪያ ደረጃ ከፍ ባልክ ወደ አላህ መመካት የበለጠ እየፈለገ የሚመጣና በአላህ ላይ ያለው መመካት በእምነቱ ልክ እንደሚሆን አውስተናል፡፡

➡️በዚህ ቦታ ላይ የተፈለገው የምቀኛ እና የሰው ዓይን እንዲሁም የድግምተኛና የድንበር አላፊን ተንኮል የምንከላከልበትን መንገዶች መጥቀስ ነው፡፡


🔵 ሺፋዕ 🔵

ቁርዓናዊ ፈውስ- እራስን ከጂን እና ከድግምት ለመጠበቅ

ስለ ሲህር እና መሰል ነገሮች ግንዛቤን ማስጨበጥ፡፡
ምልክቶች፣ መከላከያዎች እና መፍትሄዎችን መጠቆም፡፡

አድራሻችን ፡-

ፌስ ቡክ www.fb.com/nosihr
ቴሌ ግራም https://www.tg-me.com/nosihr
ብሎገር www.nosihr.blogspot.com
ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም

#ሙሐደራ

1⃣ዒልም

🎙በኡስታዝ ዐብድረዛቅ ያሲን (ቤተል)

2⃣ሹቡሀ እና ሸህዋ

🎙 በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር

#ጥያቄ እና መልስ ፣ግጥም እና ሌሎችም

🔎 ከነቤተሰብዎ የፊታችን እሁድ መስከረም 21/2010 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ስልጤ ሰፈር በሚገኘው ዓኢሻ መስጂድ ተጋብዘዋል።

እንዳያመልጦ!!!

🕹በኢኽላስ የሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የተዘጋጀ
🛑 ከድግምትና ከምቀኝነት
እንዲሁም
ከቡዳ (ዓይን) መጠንቀቂያ

🖌 በአል ኢማም ኢብኑ ቀዩም አል ጀውዚያህ

አራተኛው መንገድ

በእርሱ ከመጠመድና እርሱን ከማሰብ ልብን ንፁህ ማድረግ

ከአእምሮ ውስጥ እርሱን ለመሰረዝ ማሰብ፣ ውል ባለበት ጊዜ ሁሉ ወደ እርሱ አለመዞር እርሱንም አለመፍራት፣ ስለ እርሱ በማሰብ ልብን አለመሙላት፡፡

ይህ ተንኮሉን ለመመከት ከማረዱ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ መድሃኒቶችና ጠንካራ ከሆኑ መንገዶች መሀከል አንዱ ነው፡፡

የዚህ ምሳሌው ጠላቱ ሊይዘውና ሊያሰቃየው እንደሚፈልገው ነው፤ ወደ እርሱ ካልቀረበ ደግሞ በእርሱና በጠላቱ መሀከል ምንም የሚያያይዛቸው ነገር አይኖርም፡፡ እንዲሁም ከእርሱ ይርቃል፡፡ እርሱን ማሸነፍም አይችልም፡፡ የተያያዙና አንዱ በሌላኛው የተንጠለጠሉ ከሆነ ግን መጥፎው ነገር ይከሰታል፡፡ የነፍሶችም ሁኔታ እንደዚሁ አንድ ነው፡፡

ነፍሱን በእርሱ ላይ ያንጠለጠለና በእርሱ ላይ ያጠነጠነ ከሆነ እንዲሁም የምቀኛ ድንበር አላፊ ነፍስ በእርሱ የተንጠለጠለች ከሆነ በውንም በህልምም በእርሱ የማይደክም ሲሆን ሁለቱ ነፍሶች እንዲገናኙ ይመኛል፤ ይጠነጥናልም፡፡

አንደኛዋ ነፍስ በሌላኛው ነፍስ ላይ ከተንጠለጠለች መረጋጋት ይጠፋል፡፡ አንዱ ሌላኛውን እስኪያጠፋ ድረስ ተንኮል ይፀናል፡፡

ነፍሱ ወደ እርሱ ባሰበች ጊዜ ስለ እርሷ ከማሰብና በእርሷ ላይ ከመንጠልጠል የጠበቃት እንደሆነ በአእምሮ ውልብ እንኳን አይልበትም፡፡

በአእምሮ ውልብ ያለበት ከሆነ ይህን ውልብ ያለበትን ለማጥፋትና በእርሱ መጠመድን ለማጥፋት በጣም ጠቃሚና በላጭ ወደሆነው ይቻኮላል በዚህን ጊዜ ያ ድንበር አለፊው ምቀኛ እርስ በእርስ ይበላላል፡፡

ምቀኝነት እንደ እሳት ነው፡፡ እሳት የምትበላውን ካላገነች እርስ በእርሷ ትበላላች፡፡ ይህ የተከበረች ነፍስና የከፍተኛ ቁርጠኝነት ባለቤት የሆኑ ካልሆኑ በስተቀር ማንም የማያገኘው ትልቅ ጥቅም ያለው ርዕስ ነው፡፡

ያ መበቀልን የሚፈልግ እልኸኛና ለጠላቱ ይቅርታ የማያደርግ እርሱ የተለየ ነው፡፡ አስተዋይ አራዳ በሆነ ነውና በእርሱ መሀከል ያለው ልዩነት ሰፊ ነው፡፡ የዚህን ጥፍጥና ፀጋውን እስኪቀምስ ድረስ ማንም ግለሰብ ደረጃውን ሊያውቅ አይችልም፡፡

ልክ እንደትልቅ የልብ ቅጣት አድርጐ ይመለከተዋል፡፡ ነፍስያው በጠላቱ ተጠምዷል፤ በእርሱ ላይመ ተንጠልጥሏሏ፡፡ ለነፍስያው ከዚህ የበለጠ ህመም ምንም ነገር አይታየውም፡፡

ይህን የሚያረግጥ የተረጋጋች ነፍስ ያቺ የአላህን ጠባቂነት የወደደችና የእርሱ ረዳትነት እርሷ እ ከምትረዳው የተሻለ መሆኑን ያወቀችው ካልሆነች በስተቀር ማንም የለም፡፡

በአላህ ተማመነች፤ ወደ እርሱ ረጋች፤ በእርሱም ተረጋጋች፤ የእርሱ ጥበቃ እውን መሆኑን አወቀች፤ ቀጠሮው እውነት መሆኑንና ከአላህ በላይ ቃሉን የሚሞላ ማንም እንደሌለና እንደ እርሱ እውነትን ተናጋሪ ማንም እንደሌለ አወቀች፡፡

የእርሱ እርዳታ ለእርሷ የበረታና የፀና እንዲሁም እርሷ ለነፍሷ ከምትረዳው የበለጠ ወይም የእርሷ አምሳያ ፍጡር ከሚረዳት የበለጠ ጠቃሚ መሆኑን አወቀች፡፡


🔵 ሺፋዕ 🔵

ቁርዓናዊ ፈውስ- እራስን ከጂን እና ከድግምት ለመጠበቅ

ስለ ሲህር እና መሰል ነገሮች ግንዛቤን ማስጨበጥ፡፡
ምልክቶች፣ መከላከያዎች እና መፍትሄዎችን መጠቆም፡፡

አድራሻችን ፡-

ፌስ ቡክ www.fb.com/nosihr
ቴሌ ግራም https://www.tg-me.com/nosihr
ብሎገር www.nosihr.blogspot.com
📡 ሴቶች ለሴቶች የሙሐደራ ፕሮግራም 📡

🎤 ርዕስ ፡-

🎙 የሰብር አንገብጋቢነት


🎙 የሸፈዓ ምንነት

እና ሌሎችም

🗓 ቀን ፡-

እሁድ መስከረም 28 / 2010

ሰዓት ፡-

ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ

🛣 አድራሻ፦

ዳሩል ሀዲስ የዓረብኛ ቋንቋና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት – ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 አደባባይ)

🔵 የፌስቡክ ገፃችን
www.facebook.com/tenbihat

🔎 ዌብሳይት
http://www.nesiha.com
🔊የአዳዲስ ሙሐደራዎች ግብዣ 📀
#⃣ቁጥር 12

ርዕስ ፦ ምክር ለሩቃ አድራጊዎች!

🎙 በኡስታዝ ሳላሕ አሕመድ

ርዝመት፦ 15:40 ደቂቃ

💾 መጠን፦
ጥራት ያለው (64kbps) 7.25 MB
ዝቅተኛ (32kbps) 3.66 MB

🗒ልናደምጠው የሚገባ ጠቃሚና አዲስ ሙሐደራ !
____
🏳ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ

📲 #ነሲሀ_አዲስ_ሙሐደራ

https://www.tg-me.com/nesihastudio
2025/07/13 05:04:41
Back to Top
HTML Embed Code: