Telegram Web Link
በአፍሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለው የጋራ ፈጠራ 'ታላቅ ዕድል' ነው ሲሉ ደቡብ አፍሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ

"አፍሪካ እጅግ ብዙ ታሪኮች አሏት። ማንነታችን ውስጥ ያሉትን ውስብስብ እና ድንቅ ታሪኮቻችንን የምንናገርበት ጊዜ አሁን ነው" ሲሉ የ"ፍሪ ውመን ፊልምስ" ዋና ሥራ አስፈፃሚ  ጁዲ ንዎከዲ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።


🎬🇷🇺 ንዎከዲ በሩሲያ እና በደቡብ አፍሪካ ፊልም ሰሪዎች መካከል ስላለው  'የእኔ አፍሪካ' የትብብር ፕሮጀክት ሲናገሩ፣ የሩሲያዊቷን ዳይሬክተር ኦልጋ አካቲየቫን  “ሩሲያውያን የሚወዷት፣ ዘመናዊና ወቅታዊ የሆነች አፍሪካን የማስተዋወቅ” ራዕይ አድንቀዋል።

"ከአፍሪካ ጋር ወደፊት " በተሰኘው የአፍሪካ የባህል እና ሲኒማ ቀናት ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ጎን ለጎን በሁለቱ ቀጣናዎች መካከል እየጎለበተ የመጣውን የፈጠራ ትብብር አጉልተው አሳይተዋል።

"ሩሲያ-አፍሪካዊ እና አፍሪካ-ሩሲያዊ በሆኑ ታሪኮች ላይ በጋራ ፈጠራ እና በጋራ ስራ ላይ አብረን እንሰራለን። ይህ እኛ ልንመረምረው የሚገባ ታላቅ ዕድል ነው ብዬ አስባለሁ።"


☝🏽ንዎከዲ በተጨማሪም የትክክለኛ ውክልና አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል፦

"አፍሪካን በተመለከተ ያለውን ነገር ማረም እና በጥንቃቄ ማቅረብ በጣም አስፈላጊ ነው... ዓለም አፍሪካን እንደ ድሃ ወይም ሙሰኛ አድርጎ ማየት ይወዳል። ብዙ ማኅበረሰቦች ግን ተመሳሳይ ተግዳሮቶች አሏቸው።"


💫 ፍላጎት ላላቸው ፊልም ሰሪዎች ያላቸው መልዕክት አስመልክቶም፤

"ጥሩ ታሪኮችን እየፈለጋችሁ ከሆነ መገኘት ያለባችሁ አፍሪካ ውስጥ ነው" ብለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8
🇪🇹 አይኤምኤፍ በዚህ የ2025 ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7.2 በመቶ ያድጋል ሲል ተነበየ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ትንበያ መሠረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት ከሚያድጉ ኢኮኖሚዎች መካከል አንዱ ሆኖ እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያ የእድገት ትሩፋቶችን ለማስጠበቅ እና ማክሮ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን ለማስቀጠል የአገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰብን እና የዕዳ አስተዳደርን ማጠናከር እንደሚገባትም አሳስቧል፡፡

እነዚህ እርምጃዎች፣ የብድር ወጪን ለመቀነስ፣ ግልጽነትን ለማሻሻል እና ለአስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶች በቂ የገንዘብ ድጋፍን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው።

ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ያቀረበቻቸው ምርቶች፣ ከውጭ የሚገኘው ዕርዳታ በመቀነሱና ዓለም አቀፍ የንግድ መስተጓጎል በመፈጠሩ ምክንያት የሚመጡትን አንዳንድ ጫናዎች ለማካካስ እገዛ ማድረጉንም ጨምሮ አመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😁9🔥6👍43
🇪🇹 ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት ተማሪዎች የምታቀርባቸው የነፃ ትምህርት ዕድሎች ቀጣናዊ ትስስርን ያጠናክራሉ ተባለ

በተለይም በሕክምና ዘርፍ ዕድሉን ያገኙ ከጎረቤት አገራት የመጡ ተማሪዎች  እንደገለጹት፤ በመውሰድ ላይ ያሉት ትምህርት እና ሥልጠና የየአገራቸውን የጤና ሥርዓት በማሻሻል ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

በስፔሻሊቲ እና በንዑስ-ስፔሻሊቲ የሕክምና የትምህርት ዕድሎችን ከሚጠቀሙ የጎረቤት አገራት ዶክተሮችን ውስጥ የሚከተልሉት አገራት ዜጎች ይጠቀሳሉ፦

🇸🇸 ደቡብ ሱዳን፣ 
🇸🇴 ሶማሊያ እና
🇷🇼 ሩዋንዳን ይጠቀሳሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ430 በላይ የሚሆኑ የሕክምና ዶክተሮች በኢትዮጵያ በሚገኙ 19 የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ 105 የሚሆኑ የዕድሉ ተጠቃሚዎች መርሃ ግብሩን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍9😁81
#viral | ከሀንግዡ ወደ ሴኡል ሲበር በነበረ የኤር ቻይና አውሮፕላን ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ

🔋 እሳቱ የተነሳው በአንድ ተሳፋሪ ሻንጣ ውስጥ በነበረ ሊቲየም ባትሪ ምክንያት እንደሆነ ተዘግቧል።

የአውሮፕላኑ ሠራተኞች እሳቱን በፍጥነት የተቆጣጠሩ ሲሆን አውሮፕላኑ ወደ ሻንጋይ ፑዶንግ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲዛወር ተደርጓል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4👏3🙏3
🇪🇹 የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አገር በቀል አይደለም - የትምህርት አስተዳደር ባለሙያ

ለዘመናት የቆየው የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ከምዕራባውያን የተቀዳ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ መልክ ይጎድለዋል ሲሉ ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

"ቀጥታ የውጭውን ዓለም የሥርዓተ ትምህርት ከኢትዮጵያውያን ሕይወት ጋር ብዙም ግንኙነት የለውም፤ ልጆችን የማያሸጋግር፣ አካባቢውን የማይለውጥ፣ አካባቢውን ያልተገነዘበ ሥርዓተ ትምህርት ... ኢትዮጵያ አምጥተህ ስታስቀምጠው ግን አይገጣጠምም" ብለዋል።


የትምህርት አስተዳደር ባለሙያው አክለውም፣ የኢትዮጵያ ልጆች የራሳቸው የሆነ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ሥነ ልቦና እና ባሕል ስላላቸው በሌላ አገር ዐውድ ውስጥ የተጻፈ ሥርዓተ ትምህርት አምጥቶ መጫን ልክ አለመሆኑን አስረድተዋል።

"ቋንቋ ትልቁ እና በግልጽ የሚታየው የግንኙነታችን መስመር ነው፡፡ አሁን እንግዲህ ቋንቋ ስትወለድ ጀምሮ ያደክበት፣ የምታስብብበትና የምትናገረው ቋንቋ ተረስቶ በሌላ በባዕድ ቋንቋ መማር እና ማስተማራችን ሁሌም ይገርመኛል" በማለት ለአገር ውሰጥ ቋንቋ የተሰጠው ቦታ ማነሱን አስረድተዋል።


በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍13👏86💔1
🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በባሌ ዞን የሚገኘውን የወልመል ወንዝ የመስኖ ፕሮጀክት መረቁ

ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር ሲገባ 20 ሺህ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የሚያገለግል፣ 9 ሺህ 687 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት አስተማማኝ የመስኖ አቅርቦት ይኖረዋል ሲሉ ዐቢይ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

የመስኖ ፕሮጀክቱ፦

🔶 የግብርና ምርታማነትን የሚያሳደግ፣

🔶 ለድርቅ የማይበገር ከባቢን የሚፈጥር እና

🔶 ለማኅበረሰቡ አዳዲስ የሥራ እድል የሚከፍት ነው ተብሏል።

ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ባሻገር የአካባቢውን የውሃ አስተዳደር ተቋማትን በማጠናከር፣ የአካባቢውን ሕዝብ ባለቤትነት በማሳደግ የወልወልን ወንዝ ዘላቂ አጠቃቀም በማሻሻል የተሻለ የምግብ ሉዓላዊነት ጠቀሜታ ያገለግላል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍11👎93
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ ሩሲያ ሥር በሰደደው የሶቪዬት ዐሻራ ሥር 'ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት በሰፊው እያሳደገች ነው' - በተመድ የሩሲያ መልዕክተኛ

በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ መልዕክተኛ ቫሲሊ ኔቤንዚያ፣ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት፤  "ሩሲያ እና የቀድሞዋ ሶቪዬት ሕብረት ሁልጊዜ ከአፍሪካ ጋር ወዳጅ ነበሩ ... የአፍሪካ አገሮች ነፃነታቸውን እንዲያገኙ በማስቻል ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።"


⛓️ ኦክቶበር 14 የዓለም ፀረ የቅኝ ግዛት ቀን ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ መወሰኑ የሩሲያ የላቀ ሚና ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

"ሩሲያ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት በጉልህ ታሳድጋለች ... ንግድ እያደገ መሆኑን ታዝበናል፤ በርካታ ኤምባሲዎችን እየከፈትን ነው" ሲሉም ኔቤንዚያ አክለዋል፤ እንደማሳያም እየሰፋ ላለው ትብብር   የተቋቋመውን የአፍሪካ አጋርነት
ጠቁመዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍85👏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#viral | የሕንዱ መከላከያ ሚኒስትር ራጅናት ሲንግ 'ቨቹዋል' የብራህሞስ ሚሳኤል ጥቃት ተመለከቱ

👉 በሲሙሌሽኑ (ምስለ እውነታ ልምምድ) ላይ ሚሳኤሉ የተተኮሰው ሩሲያ-ሠራሽ ከሆነው ሱ-30 አውሮፕላን ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍52
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ ሩሲያ የዓለምን የተዛባ ሚዛን ለማስተካከል የምትታገል አገር ናት - ድምጻዊ ወንድዬ አበበ

የኪን ኢትዮጵያ የባሕል እና ኪነ ጥበብ ቡድን አባሉ፣ አገሪቱ መንፈሳዊ ሐብትን ከሚያንኳስሰው የአዲሱ ዓለም ሥርዓት ጋር ብርቱ ትግል በማድረግ ማንነቷን ይዛ መዝለቋን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።


🗣"ዓለም አቅጣጫ ቀይራ በተሳሳተ መንገድ እየሄደች ነው። ሩሲያዊያን ለእምነት ተገቢውን ዋጋ የሚሰጡ ሕዞቦች ናቸው። እኛም በምዕራቡ ዓለም የባሕል ወረራ እየተነጠቅናቸው ያሉ መንፈሳዊ ጸጋዎችን በንቃት መጠበቅን አለብን።" ብሏል።


📌 ወንድዬ ኮንታ ብሪክስ ጥምረት ለዓለም ያለውን ትሩፋትም አንስቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍119
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️❗️❗️ ሩሲያ ሥር በሰደደው የሶቪዬት ዐሻራ ሥር 'ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት በሰፊው እያሳደገች ነው' - በተመድ የሩሲያ መልዕክተኛ በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ መልዕክተኛ ቫሲሊ ኔቤንዚያ፣ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት፤  "ሩሲያ እና የቀድሞዋ ሶቪዬት ሕብረት ሁልጊዜ ከአፍሪካ ጋር ወዳጅ ነበሩ ... የአፍሪካ አገሮች ነፃነታቸውን እንዲያገኙ በማስቻል ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።"…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ ሩሲያ በፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን በተመለከ አፍሪካ ያቀረበችውንና ቅድሚያ በተሰጣቸው ሌሎች ምክንያቶች የቆመውን ጥያቄ ትደግፋለች ሲሉ መልዕክተኛው  ተናገሩ

በተመድ የሩሲያ ቋሚ መልክተኛ ቫሲሊ ኔቤንዚያ እንደተናገሩት፤ የማሻሻያው ሂደት በተጋጩ ብሔራዊ ጥቅሞች እና በአምስት ቁልፍ የድርድር ስብስቦች ትስስር ምክንያት ተደናቅፏል።

⏱️ ኔቤንዚያ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቃለ-ምልልስ እንዳብራሩት፣ በሁሉም ስብስቦች ላይ በአንድ ጊዜ ስምምነት ስለሚያስፈልግ፣ የጥያቄው ምላሽ ሂደት "በጣም የዘገየ" ሆኗል።

"አፍሪካን በተመለከተ፣ እኛ እንደ ሩሲያ እንዲሁም ሌሎቹም ብዙዎች በተመሳሳይ እንደሚሉት፣ በአፍሪካ ላይ የደረሰው ታሪካዊ ኢፍትሐዊነት መስተካከል አለበት። አፍሪካ በተሻሻለው የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በበቂ ሁኔታ መወከል አለባት" ሲሉ አረጋግጠዋል።


👉  ኔቤንዚያ የአዳዲስ ምዕራባውያን አባላትን መጨመር ሞስኮ እንደምትቃወም በግልፅ በመግለጽ፣ ይልቁንም በአነስተኛ ውክልና ካለው የደቡብዊ  ዓለም "በመጀመሪያ ደረጃ አፍሪካ፣ እስያ እና ላቲን አሜሪካ"  ከፍተኛ ድምፅ እንዲኖራቸው ይገባል ብለው ሞግተዋል።

ዲፕሎማቱ የአፍሪካ የጋራ አቋም ለምክር ቤቱ ቋሚ መቀመጫ ያላትን ጥያቄ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል። በማሻሻያው ላይ ሁሉን አቀፍ ስምምነት ላይ ሲደረስ አፍሪካ "በተገቢው ሁኔታ እንደምትወከል" ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

🇵🇸 ንቤንዚያ የአፍሪካ አገራት በጋዛ ቀውስ ላይ የያዙትን አቋም አድንቀዋል።

"ይህ ግጭት ብዙ ሰላማዊ ዜጎችን ያለአግባብ ሕይወት እየቀጠፈ ስለሆነ፣ [የቅርብ ጊዜው] የተኩስ አቁም እንደሚዘልቅ ሁላችንም እየጸለይን ነው። ብዙ ሲቪሎች ሞተዋል" ብለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‘በፍልስጤም ፍትሕ ከሌለ ዓለም ላይ ሰላም የለም’ ሲሉ ለጋዛ ድጋፍ የወጡ የፓሪስ ሰልፈኞች ድምጻቸውን አሰምተዋል

🇫🇷 ተሳታፊዎቹ “የፍልስጤምን ልጆች ማስራብ ይቁም” ብለው ከመጮህ ባለፈ፣ “የጋዛን የዘር ማጥፋት ይብቃ”፣ “ዝምታ ይገድላል” እና “እስራኤልን አውግዙ” የሚሉ ጽሑፎችን የያዙ ምልክቶችን ይዘው ነበር።

☝️ ተንቀሳቃሽ ምስሉ የቀረጻው በስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🥰11👎42👍1😁1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️❗️❗️ ሩሲያ በፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን በተመለከ አፍሪካ ያቀረበችውንና ቅድሚያ በተሰጣቸው ሌሎች ምክንያቶች የቆመውን ጥያቄ ትደግፋለች ሲሉ መልዕክተኛው  ተናገሩ በተመድ የሩሲያ ቋሚ መልክተኛ ቫሲሊ ኔቤንዚያ እንደተናገሩት፤ የማሻሻያው ሂደት በተጋጩ ብሔራዊ ጥቅሞች እና በአምስት ቁልፍ የድርድር ስብስቦች ትስስር ምክንያት ተደናቅፏል። ⏱️ ኔቤንዚያ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቃለ-ምልልስ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ ሩሲያ በሽብርተኝነት ላይ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ትግል አጽንኦት በመስጠት ለአፍሪካ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች

🌍 ሞስኮ የአፍሪካ አገራትን ሽብርተኝነትን እንዲዋጉ ለመርዳት ቁርጠኛ ነች ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ ቋሚ ተወካይ ቫሲሊ ኔቤንዚያ ለስፑትኒክ አፍሪካ አረጋገጡ፡፡

ቀደም ሲል በሩሲያ ምክትል ዋና ፀሐፊ ቭላድሚር ቮሮንኮቭ ይመራ የነበረው የተባበሩት መንግሥታት የሽብርተኝነት መከላከል ጽሕፈት ቤት፣ እንደ ድንበር ቁጥጥር እና የአሸባሪነት መከላከል ስትራቴጂዎች ባሉ ዘርፎች ለአፍሪካ አገራት ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ አብዛኛውን ጊዜ በሩሲያ ሽምግልና እና አስተባባሪነት ነበር።

🇷🇺🤝 ኔበንዚያ አክለውም፣ ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል እንደመሆኗ መጠን፣ በብሔራዊ ኤጀንሲዎቿ በኩል በንቃት ተሳትፋለች እንዲሁም ለተዛማጅ ፕሮግራሞች በፈቃደኝነት አስተዋፅዖ አድርጋለች።

ዲፕሎማቱ እንዳሉት፣ "ሽብርተኝነት አሁን ዓለም አቀፍ ችግር ነው። አፍሪካን ብቻ የሚመለከት አይደለም። እያደገ ያለ ነገር ሲሆን፣ ለዓለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነት ከዋና ዋና ስጋቶች አንዱ ነው። አፍሪካም መጠበቅ አለባት።"


ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል እንደመሆኗ፣ ይህንን ፈተና ለመዋጋት "በአፍሪካ የሚገኙ ወንድሞቿን ለመርዳት የምትችለውን ሁሉ ለማድረግ" ቁርጠኛ ነች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
9👍1
2025/10/19 03:49:41
Back to Top
HTML Embed Code: