Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትራምፕ የዩክሬን ግጭት ቶማሃውክ ሚሳኤሎችን መጠቀም ታሳቢ ሳይደረግ ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል

አሜሪካ ቶማሃውኮችን እንዲሁም ወደ ዩክሬን እየተላኩ ያሉ ሌሎች በርካታ ጦር መሣሪያዎች ያስፈልጓታል ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ፣ ዩክሬን ያጣቻቸውን ግዛቶችን መልሳ ስለማግኘት ያላት ዕድል በተመለከተ ሲናገሩ፣ “ፈጽሞ አታውቁም። ... በጣም የማይገመት ነው።” ብለዋል፡፡


በሩሲያ እና በአላስካ መካከል የመሿለኪያ ቦይ ሐሳብንም 'አስደሳች' መሆኑን አንስተዋል፡፡ ዘለንስኪ በአንጻሩ፣ "በዚህ ሐሳብ ደስተኛ አይደለሁም" ብለዋል። ትራምፕም፣ "የምትወዱት አይመስለኝም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል፡፡

የአሜሪካው መሪ፣ የዩክሬን ወደ ሩሲያ ዘልቃ ማጥቃት ውጥረትን ማባባስ እንደሚሆን ያምናሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5👍3👎1🤣1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ትራምፕ የዩክሬን ግጭት ቶማሃውክ ሚሳኤሎችን መጠቀም ታሳቢ ሳይደረግ ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል አሜሪካ ቶማሃውኮችን እንዲሁም ወደ ዩክሬን እየተላኩ ያሉ ሌሎች በርካታ ጦር መሣሪያዎች ያስፈልጓታል ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ ዩክሬን ያጣቻቸውን ግዛቶችን መልሳ ስለማግኘት ያላት ዕድል በተመለከተ ሲናገሩ፣ “ፈጽሞ አታውቁም። ... በጣም የማይገመት ነው።” ብለዋል፡፡ በሩሲያ እና በአላስካ…
ለዩክሬን ሰላም 'በጣም ተቃርበናል' ያሉት ትራምፕ ግጭቱን ያለ ቶማሃውክ ለመፍታት አቅደዋል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በትናንትናው ዕለት በዋይት ኅውስ  ውይይት አድርገዋል። ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በቅርቡ ያደረጉትን የስልክ ውይይት፣ የዩክሬን ግጭት መፍትሄ አቅጣጫ እና በቅርቡ በቡዳፔስት የታቀደውን ድርድር ውይይት ተካሂዶበታል።

👉 ትራምፕ በስብሰባው ወቅት ሰላም የማምጣት ተስፋ እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን የሰላም ሂደቱ ጥሩ ደረጃ ላይ እና ወደ ፍጻሜው ላይ እየደረሰ መሆኑን አስታውቀዋል። እንዲሁም ከኪዬቭ እና ከሞስኮ ጋር ለሚያደርጉት ድርድር ያቀዱትን ስትራቴጂ አስቀምጠዋል።

ከትራምፕ ንግግር የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች

⚫️ ስለ ሰላም ድርድር፡ "በዩክሬን ሰላም ላይ ታላቅ መሻሻል እያሳየን ነው፤ እናሳካዋለን ብዬ አስባለሁ።"

⚫️ ከፑቲን ጋር ስላደረጉት ውይይት፡ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ጋር በቅርቡ በስልክ ያደረጉትን ውይይት ዝርዝር መረጃ ከዘለንስኪ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ወቅት እንደሚያጋሩ ጠቁመዋል።

⚫️ ስለ ቡዳፔስት መመረጥ፡ ከፑቲን ጋር ለሚያደርጉት ስብሰባ ቡዳፔስት ለምን እንደተመረጠች ለተጠየቁት ጥያቄ  “ምክንያቱም ኦርባንን ስለምንወደው ነው” ብለዋል።

⚫️ ስለ ስብሰባው ቅርፅ፡ ከፑቲን እና ከዘለንስኪ ጋር ሊደረግ ስለሚችለው  የሦስትዮሽ ጉባኤን አስመልክቶ “መካሄዱ አይቀርም፣ ሁለት ስብሰባ ይሆናል” ብለዋል።

⚫️ የፑቲንን አቋም አስመልክቶ፡ “ፑቲን የዩክሬንን ግጭት መቋጨት የሚፈልግ ይመስለኛል።”

⚫️ ግጭት ማባባስን ስለ ማስወገድ፡ “ግጭቱን ስለ ቶማሃውክ ሳናስብ ማቆም እንችላለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቶማሃውኮች ትልቅ ነገር ናቸው እና ግጭቱን እንዲባባስ ሊያደርጉ ይችላሉ።”

⚫️ ግዛትን መልሶ ስለ ማግኘት፡ ዩክሬን ያጣቻቸውን ግዛቶችን መልሳ ስለማግኘት ለተጠየቁት ጥያቄ ትራምፕ፣ “መቼም አታውቁም” ብለዋል።

⚫️ ስለ ሰላም ቅድመ ሁኔታዎች፡ “መፍትሄ እንዲመጣ ፑቲን እና ዘለንስኪ ትንሽ መግባባት አለባቸው።”

⚫️ ስለ ቻይና ሚና፡ ትራምፕ ከቤጂንግ ጋር በዩክሬን ጉዳይ ላይ እየተነጋገሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ “ግጭቱ በፍጥነት እንዲያልቅ እፈልጋለሁ” ብለዋል።

⚫️ የድሮን ትብብርን በተመለከተ፡ አሜሪካ ከዩክሬን ጋር የድሮን ቴክኖሎጂ ልውውጥን እየፈለገች ነው፤ “በጣም ጥሩ ድሮን ይሰራሉ” በማለት ትራምፕ አስተያየት ሰጥተዋል። ብዛት ያለው የሚሳኤል ክምችት የመያዝ አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል።

⚫️ የሩሲያ-አላስካ ማስተላለፊያ መስመር፡ ሩሲያን እና አላስካን ሊያገናኝ ስለሚችለው በዕቅድ ላይ ያለ መሿለኪያን በተመለከተ ለተጠየቁት ጥያቄ ትራምፕ “ጥሩ ነገር” ሲሉ ገልጸው፣ “ላስብበት ይገባል” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7👍2😁1
🌍 አፍሪካ ፣ ልዩ ምርጫ ይህን የመልዕክት መለዋወጫ 'ፎልደር' ከአህጉሪቱ አዳዲስ ዜናዎች ከሚገኙበት ቻናሎች ላይ ይጨምሩት ⤵️

👉👉 https://www.tg-me.com/addlist/lwYcxR-tjCBiODBi 👈👈

#social
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ለዩክሬን ሰላም 'በጣም ተቃርበናል' ያሉት ትራምፕ ግጭቱን ያለ ቶማሃውክ ለመፍታት አቅደዋል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በትናንትናው ዕለት በዋይት ኅውስ  ውይይት አድርገዋል። ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በቅርቡ ያደረጉትን የስልክ ውይይት፣ የዩክሬን ግጭት መፍትሄ አቅጣጫ እና በቅርቡ በቡዳፔስት የታቀደውን ድርድር ውይይት ተካሂዶበታል። 👉 ትራምፕ በስብሰባው…
🗣ትራምፕ እና ዘለንስኪ በቶማሃውክ ጉዳይ ላይ አልተስማሙም - ባለሙያ

💬"ዘለንስኪ እና ትራምፕ አንድ አይነት አቋም ላይ እንዳልሆኑ ግልጽ ነው። ዘለንስኪ ቶማሃውክን አሁን ከእጃቸው እንዲገባ በመፈለግ ጦርነቱን ማራዘም ብቻ ሲሆን፣ ትራምፕ ግን ቶማሃውክን ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን እንዲያቆሙ ለመደራደር እንደ ግፊት መጠቀም ይፈልጋሉ" ሲሉ የቀድሞ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ የጸጥታ ፖሊሲ ተንታኝ ሚካኤል ማሎፍ የትራምፕና ዘለንስኪ ስብሰባን አስመልክቶ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

👉ማሎፍ "ፑቲን የ2.5 ሰዓት የስልክ ንግግራቸው 'ውጤታማ' እንደነበር ትራምፕ እንዲናገሩ ያደረጉበት አንዳች ነገር ተናግረው መሆን አለበት" ብለው ያምናሉ።

🔍 "ፑቲን ምን እንደሚያቀርቡ እናያለን፤ ለምሳሌ እስካሁን የደረሱበትን በመያዝ ወደፊት አለመገስገስ፣ ከእርቅ ጋር። ዘለንስኪ ጦርነቱን ማራዘም የሚፈልጉት አውሮፓውያን በሰጧቸው መሠረተ ቢስ ተስፋ ላይ ተመርኩዘው ነው" ነገር ግን "አውሮፓ የጦርነት ኢኮኖሚን መቋቋም አትችልም"።

❗️"በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራት ትራምፕ የኔቶ አጋሮቻቸውን ማስቀተል ፈታኝ ይሆንባቸዋል። በትራምፕ እና በኔቶ አገሮች መካከል ያለው ክፍተት ከቀጠለ ኔቶ ራሱ የፍጻሜው መጀመሪያ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ማሎፍ አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7👍4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇲🇬 ማዳጋስካር፤ አዲስ መንግሥት፣ አዲስ ፕሬዝዳንት እና አዲስ ምልከታዎች

የማዳጋስካር ጦር ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊናን ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ፣ ሲቪሎች የሚሳተፉበትን መንግሥት ማቋቋሙን አሳውቋል።

ኮሎኔል ሚካኤል ራንድሪያን-አሬና ትናንት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል፡፡

በዚህ ሳምንት እጣ ፈንታዋ ወደ አዲስ እጥፋት ያዞረችው ይህች ደሴት ወደፊት ምን ይጠብቃታል?

የስፑትኒክ አፍሪካ አዲሱ የቨርቹዋል ወይም ምናባዊ አቅራቢ #ጁማ የዓለምን ትኩረት የሳበውን የማዳጋስካር  ሁኔታ የባለሙያዎችን ምልከታ አካትቶ አብራርቶታል።

📹የጁማን ትንታኔ ቪዲዮ ከላይ ይመልከቱ 👆🏽

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4🔥1
#viral  | የሆንዱራስ ዋና ከተማ በአውዳሚ ጎርፍ ተጠለቀለቀች፤ በአደጋው አንድ ሰው ሲሞት በከተማዋ የድንገተኛ ጊዜ አዋጅ ታውጇል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3🙏3
🇩🇪 'ከሩሲያ ጋር በነበረው የኃይል ትብብር አልቆጭም' ሲሉ የቀድሞ የጀርመን መራኄ መንግሥት ተናገሩ

ጌርሃርድ ሽሮደር "የኖርድ ስትሪም 2 (የነዳጅ ማስተላለፊያ) እንዲሳካ የምችለውን ሁሉ አድርጌያለሁ። ግንባታው እንዲቀጥል ፍላጎት ነበረኝ፤ ለድጋፉም ድርድር አድርጌያለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።


🔸 ለሜክለንቡርግ-ምዕራብ ፖሜራኒያ የክልል ፓርላማ በበየነ መረብ ባደረጉት ንግግር፤ እ.ኤ.አ. በ2022 በአሻጥር ሥራ ያቆመውን የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር በተመለከተ ክልሉ ያቀረበውን ጥያቄ "ቀልድ" ሲሉ አጣጥለውታል።

👉 ጌርሃርድ፣ በማስተላለፊያው ግንባታ ላይ ስለነበራቸው ሚና ምንም ጸጸት እንደሌላቸውም ተናግረዋል።

🔸 ሽሮደር የአገሪቱ የአየር ንብረት ፋውንዴሽን አሁንም ጠቃሚ እንደሆነ አድርገው እንደሚመለከቱት አክለዋል። ፋውንዴሽኑ የተቋቋመው የአየር ንብረት እና የአካባቢ ጥበቃ ፕሮጀክቶችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የመስመሩን ግንባታ ለመደገፍ ነበር።

🔸 የቀድሞ የጀርመን መራኄ መንግሥት፣ ኖርድ ስትሪም የሩሲያ እና የጀርመን ሰፊ የኃይል ትብብር አካል ተደርጎ ይቆጠር እንደነበር ገልጸው፤ "አሜሪካ በጀርመን የኃይል ፖሊሲ ጣልቃ እንዳትገባ መሣሪያ ሆኖ አገልግሏል" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
10
🇪🇹 የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ 4ተኛ መሠረታዊ  እና 44ተኛ የኮማንዶ ሥልጠና አስጀመረ

በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ፣ የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማልጠኛ አስተማማኝ የኮማንዶ ኃይል አሠልጥኖ እያበቃ መሆኑን ተናግረዋል።

ሌተናል ጀነራሉ "እናንተም የአሠልጣኞችን የካበተ አቅም በመጠቀም በሥነ ምግባር የታነፀ፣ ጠንካራ እና አገራዊ ፍቅርን የተላበሰ ወታደር እና ኮማንዶ ለመሆን ጠንክራቹህ መሥራት ይጠበቅባችኋል" ሲሉ ለሰልጣኞች መልዕክት ማስተላለፋቸውን መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።


🛡ሠራዊቱ አገራዊ ልማቶች ደህንነታቸዉ ተጠብቆ እንዲጠናቀቁ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የደረሰ አበርክቶ እንዳለው ተገልጿል።

"ኮማንዶ ... የውጊያ ማርሽ ቀያሪ፣ የተበላሸ ዉጊያን በአጭር ሰዓት በመድረስ የሚያስተካክል የዘገዩ ዉጊያዎችን የሚያፋጥን ጀግና ነው፤ እናንተም የዚህ ክፍል አባል ለመሆን ፈቅዳችሁ መምጣታችሁ ደስ ያሠኛልና ጠንክራችሁ ሠልጥኑ፡፡" ሲሉ አበረታትተዋል።


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
12😁10🔥2😢2
❗️በዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተጎዱ የውጭ የኃይል አቅርቦት መስመሮችን የመጠገን ሥራ በአካባቢው የተኩስ አቁም ከተደረገ በኋላ መጀመሩን ግሮሲ አስታወቁ

የዓለም አቀፉ የኑክሌር ኃይል ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በኤክስ አካውነታቸው ላይ በሰጡት መግለጫ፣ "ከአራት ሳምንት መቋረጥ በኋላ የዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተጎዱትን የውጭ የኃይል መስመሮች የመጠገን ሥራ እንዲቀጥል በአካባቢው የተኩስ አቁም ቀጣናዎች ተቋቁመዋል" ብለዋል።


የውጭ ኃይልን ወደ ነበረበት መመለስ ለኒውክሌር ደህንነት ወሳኝ ነው ሲል ኤጀንሲው ገልጿል።

"ሁለቱም ወገኖች ውስብስብ የሆነውን የጥገና ዕቅድ ለማስፈጸም ከኤጀንሲው ጋር ገንቢ በሆነ መንገድ ተሳትፈዋል" ሲሉ ግሮሲ አክለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5🙏3
🇮🇷⚛️ ኢራን ከዚህ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች አትገደድም ተባለ

🔊  የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2231 ጊዜው አልፏል፤ ይህም በኢራን ላይ ተጥለው የነበሩትን ሁሉንም የፀጥታው ምክር ቤት ገደቦች ያቋርጣል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አባስ አራግቺ "ኢራን የኒውክሌር መስፋፋት መከላከያ ስምምነት ፈራሚ እንደመሆኗ፣ በቀጥታ በስምምነቱ ስር መሠረት ባሉ መብቶቿና ግዴታዎቿ ብቻ ትገደዳለች" ብለዋል።

አክለውም "ይህም በኒውክሌር መርሃ ግብሯ መጠን ላይ ምንም ዓይነት ገደብ አለመኖሩን፤ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የሚደረግ ትብብርም በአጠቃላይ የጥበቃ ስምምነት ማዕቀፍ ውስጥና በኢራን ፓርላማ በቅርቡ በፀደቀው ሕግ መሠረት ብቻ መሆኑን ያጠቃልላል" ብለዋል።


👉 እ.ኤ.አ. በ2015 የፀደቀው የተመድ የፀጥታው ምክር-ቤት ውሳኔ 2231፣ የጋራ ሁሉን አቀፍ የድርጊት መርሃ ግብር የኒውክሌር ስምምነት በዛሬው ዕለት ከጥቅም ውጭ ይሆናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7😁1
❗️የሩሲያ ኃይሎች በዶኔትስክ ሕዝቦች ሪፑብሊክ የፕሌሽቼየቭካ መንደር ተቆጣጠሩ

👉 ከቅርብ ወራት ወዲህ የሩሲያ ጦር ኃይሎች በዶንባስ ክልል እና ባሻገር በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ መንደሮችን ተራ በተራ ነጻ እያወጣ በከፍተኛ ፍጥነት ወደፊት እየገሰገሰ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
9👍6👏2
ሩሲያ-አላስካ መተላለፊያ መስመር የአዋጭነት ጥናት እየተካሄደ ነው ሲሉ የሩሲያ ባለሥልጣን ተናገሩ

ሩሲያን ከአላስካ የሚያገናኝመተላለፊያ (መሿለኪያ) መስመር ለመገንባት የሚያስችል የአዋጭነት ጥናት ከስድስት ወራት በፊት መጀመሩን የፕሬዝዳንት ፑቲን ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪቭ በኤክስ ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ዲሚትሪቭ በተጨማሪም የሩሲያና የቻይና የባቡር ድልድይ ስኬትን አጉልተው አሳይተዋል፤ በዚህም የጭነት መስመሮችን ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ በማሳጠር እንደ ስኬታማ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ምሳሌነት አቅርበውታል።

የመጀመሪያው ምስል በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ነው

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5
2025/10/19 16:56:26
Back to Top
HTML Embed Code: