Telegram Web Link
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
🔍 የሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ለፑቲን እና ትራምፕ ውይይት ለምን ተመረጠች?   የሩሲያ እና የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ቀጣይ መገናኛ ከተማ ቡዳፔስት የመሆኗ ውሳኔ ምክንያታዊ እንደሆነ ብራዚላዊው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ራፋኤል ማቻዶ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። 💬 “ሃንጋሪ ለረጅም ጊዜ በቅርብ ዓመታት ደግሞ በሮበርት ፊኮ ስር ካለችው ስሎቫኪያ ጋር ተቀላቅላ፣ በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ያለውን የበላይነት…
❗️ኦርባን በቡዳፔስት ሊካሄድ የሚችለውን የሩሲያ እና የአሜሪካ ጉባኤ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ለማረጋገጥ ፈቃደኛ ናቸው ሲል ክሬምሊን አስታወቀ

በፑቲን እና በኦርባን የስልክ ውይይት ወቅት የተነሱ ተጨማሪ ዝርዝሮች ሐሳቦች፦

🔸 ፑቲን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ስላደረጉት ውይይት ዋና ዋና ይዘቶች ለሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርባንን አሳውቀዋል።

🔸 ፑቲን እንደተናገሩት፣ የሩሲያ ተወካዮች ከአሜሪካ ተወካዮች ጋር በሚያደርጉት ቀጣይ ግንኙነት፣ የዩክሬን ቀውስ በሰላም ለመፍታት የሚያስችሉ መንገዶችን ለመፈለግ እና ወደፊት የሩሲያ እና አሜሪካ ጉባኤ በሃንጋሪ ዋና ከተማ እንዲካሄድ በማሰብ፣ በቀጣይ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች አካሄድ ላይ ለመወያየት አቅደዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍7👏32
📌 ዜናዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ፣ ነገር ግን እዚሁ በስፑትኒክ አፍሪካ፡፡ ያንብቡን:

▪️ በእንግሊዝኛ – Telegram | X
▪️ በፈረንሳይኛ – Telegram | X
▪️ በአማርኛ – Telegram | X
▪️ በስዋሂሊ – X

#social
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral  | የ"ጄን ዚ"* አለመረጋጋት በፔሩ ዋና ከተማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አደረገ

በአገሪቱ  መዲና ሊማ የጡረታ አበል ማሻሻያ የሚጠይቁ የመንግሥት ተቃውሞዎች ረቡዕ ዕለት የተቀሰቀሱ ሲሆን፤ የማሻሻያ ጥያቄው ብዙም ሳይቆይ ፕሬዝዳንት ሆሴ ጄሪ ሥልጣናቸውን እንዲለቅቁ ጥሪ ወደማሳማት አድጓል።

ወጣቱ ትውልድ ሙስና እና እየጨመረ በመጣው ወንጀል ላይ እርምጃ አለመውሰዳቸውን በመጥቀስ ክስ አቅርቦባቸዋል።

* "ጄን ዚ" (Generation Z) እ.ኤ.አ. ከ1997 አእስከ 2012 ባለው ዓመት የተወለደ ትውልድ ነው፡፡ አሁን ላይ ከ13 – 28 ዓመት ይገኛል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏32
🇪🇹🇷🇺 በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ከዩራሺያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበረከተላቸው

🎓 ዓለም አቀፉ የዩራሻያን ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬቱን ርክክቡን በሩሲያ ፌዴሬሽን የመንግስት ዱማ (ፓርላማ) ውስጥ አካሂዷል።

ዲፕሎማውን ለአምባሳደሩ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ኬ.ፒ. ክሊሜንኮ-ቦግዳኖቭ እንደተናገሩት፣ የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው በሳይንስ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በዲፕሎማሲ፣ በጎ አድራጎት ሥራዎች እና በሕዝቦች መካከል ሰላምና ወዳጅነትን በማጠናከር ረገድ ላበረከቱት አስፈላጊ አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ነው።


አምባሳደሩም በበኩላቸው፤ ለሥራቸው ለተሰጣቸውን ከፍተኛ እውቅና በማመስገን፣ የሩሲያ-ኢትዮጵያን ትብብር ለማጠናከር እና የዩኒቨርሲቲውን ተግባራት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ሲል ኤምባሲው በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስነብቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
9👏8🔥4🥰2
🇪🇹 የኢትዮጵያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በ2018 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የ7.87 በመቶ እድገት አስመዘገበ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳስታወቀው፤ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ከሚገኙ ኢንቨስትመንቶች በሩብ ዓመቱ ከወጪ ንግድ ከ49 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ሲገኝ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 113 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።

በኮሚሽኑ በሩብ ዓመቱ ለ123 አዳዲስ የውጭ ፕሮጀክቶችና የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን የሰጠ ሲሆን ይህም ከ2017 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ26 በመቶ ብልጫ ተመዝግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5🙏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፑቲን የአርቲ ጣቢያ 20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

"ራሽያ ቱዴይ (አርቲ) ሲጠነሰስ ጅምሮ፣ በዚህ ልክ ከፍ ይላል፤ ይህን ያህል የጥራት ደረጃ ላይ ይደርሳል እንዲሁም አሁን በያዘው መንገድ ያድጋል የሚል ሐሳብ አልነበረኝም" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።


አርቲ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያሰራጭ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሞስኮን አቋም የሚያንፀባርቅ ከመሆኑም በላይ በሩሲያ ያለውን ሰፊ የሕይወት ገጽታ ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6👍6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#viral  | ሩሲያዊቷ የሴንት ፒተርስበርግ እንስት ግዙፍ ዱባን እንደ ጀልባ ተጠቅማ በሐይቅ ላይ መንሸራሸሯ ግርምትን ፈጥሯል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8
🇪🇹 በትግራይ እና አፋር ክልሎች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከ43 ሺህ በላይ ሰዎች ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

ጥቅምት 1 ቀን በተከሰተው የ5.7 መጠነ ልኬት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ አንዲት ሕጻን ሕይወቷ ሲያልፍ በዘጠኝ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአፋር ክልል በርሃሌ ወረዳን ጠቅሶ የአገር ውስጥ ሚዲያ አስታውሷል።

የአፋር ክልል እንዳስታወቀው፦

🔷 ከ1 ሺህ 400 በላይ ቤቶች፣

🔷12 ትምህርት ቤቶች፣

🔷 12 የጤና ጣቢያዎች እና

🔷 ከ150 በላይ የውሃ ማጠራቀሚያዎች ወድመዋል፡፡

የትግራይ አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ በበኩሉ፦

🔷 በመቀሌ ከተማ አቅራቢያ 40 መኖሪያ ቤቶች መፈራረሳቸ እና

🔷 ከ225 በላይ ነዋሪዎች መኖሪያ አልባ መሆናቸውን አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር እና የሚያስፈልገውን የእርዳታ መጠን ለመወሰን የግምገማ ቡድኖችን ወደ ስፍራው ማሰማራቱ ተዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
12👍1🙏1
🇪🇹🇮🇳 ኢትዮጵያ እና ሕንድ የመጀመሪያውን የጋራ የመከላከያ ትብብር ስብሰባ በኒው ዴልሂ አካሄዱ

ስብሰባው በሕንድ የመከላከያ ሚኒስቴር አሚታብ ፕራሳድ እና በኢትዮጵያ የመከላከያ የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የጋራ ሊቀ -መንበርነት ተመርቷል።

ሁለቱ ወገኖች በመካሄድ ላይ ያለውን የመከላከያ ትብብር ገምግመው፦

🔶 በሥልጠና፣
🔶 በጋራ ወታደራዊ ልምምዶች፣
🔶 በሕክምና ትብብር እና
🔶 በመከላከያ ኢንዱስትሪ ተሳትፎ ዙሪያ ለአዲስ ትብብር የሚሆኑ መንገዶችን ተወያይተዋል።

🤝 ሁለቱም ልዑካን ቡድኖች የመከላከያ ትብብር እንቅስቃሴዎችን የበለጠ ለማሳደግ እና ለማስፋት መስማማታቸውን የሕንድ መንግሥት የፕሬስ ኢንፎሜሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8👎2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የካሜሩን ተቃዋሚ እጩ ኢሳ ቲቺሮማ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን እንዳሸነፉ በመግለፅ ፖል ቢያ ወጤቱን እንዲቀበሉ አሳሰቡ ኢሳ ቲቺሮማ በሰሜናዊ ካሜሩን ከምትገኘው ጋሩዋ ከተማ አሸናፊነታቸው "ግልጽ" እንደሆነ እና የሕዝብ ምርጫ "መከበር አለበት" ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል። የካሜሩን የምርጫ ሕግ የምርጫ ጣቢያ ውጤቶች እንዲታተሙ ቢፈቅድም፤ የሕገ-መንግሥት ምክር ቤቱ የመጨረሻውን ቆጠራ በማረጋገጥ ይፋዊ ውጤቱን…
🇨🇲 🗳 የካሜሮን የድህረ ምርጫ ውጥረት፤ የድምፅ ቆጠራ ኮሚሽን እርምጃ ወስዷል

👉  33 አባላት ያሉት ይህ የምርጫ አካል በጥቅምት 2 የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድምጾችን የመቁጠር ኃላፊነት አለበት።

👉 ትናንት በካሜሩን የምርጫ ምክር ቤት ይፋ የተደረገው አወቃቀር ፤ በ58ቱ የመምሪያ ኮሚሽኖች የቀረቡ ቃለ-ጉባኤዎችን የማሰባሰብ ሥራን ያካትታል።

👉 ይህ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የኮሚሽኑ የመጨረሻ ውጤቶች ሪፖርት እስከ ጥቅምት 16 ድረስ የማወጅ ሥልጣን ወዳለው ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ምክር ቤት ይላካል።

በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ አሁንም ውጥረት የበዛበት ነው፡፡ ለ43 ዓመታት በሥልጣን ላይ ያሉት የ92 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ስምንተኛ የሥልጣን ዘመን ሽተዋል፡፡

ይፋዊ ውጤት ከመታወቁ በፊት፣ የካሜሩን "ናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንት" እጩ የሆኑት ኢሳ ችሮማ ባካሪ አሸናፊ መሆናቸውን አውጀዋል። ባለሥልጣናትን በምርጫ ማጭበርበር የከሰሱ ተቃዋሚዎች በዱዋላ እና ድሻንግ ተቃውሞዎችን አስነስተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4
🇪🇹 🇹🇷 ኢትዮጵያ እና ቱርክ የገበያ ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ

🤝 ለኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ወሳኝ አካል የሆነውን ስምምነት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ፣ ከአፍሪካ የቱርክ የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከቱርክ አቻቸው ፕሮፌሰር ሾማር ቦላት ጋር ተፈራርመዋል።

ሚኒስትሩ ይህ ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደታችን ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለዋል። አክለውም ከሌሎች አባል አገራት ጋር የሚደረገው የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ግማሹ በቴክኒክ ደረጃ መጠናቀቁን ጠቅሰው ከሌሎች ጋርም የድርድር ሂደቱ በተሳካ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።


የዓለም ንግድ ድርጅት 6ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ በቅርቡ ውጤታማ በሆነ ስኬት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ለ7ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባም ዝግጅቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ የትስስሩ ገፁ አስነብቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5👏5👎4🔥2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ፑቲን የአርቲ ጣቢያ 20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ "ራሽያ ቱዴይ (አርቲ) ሲጠነሰስ ጅምሮ፣ በዚህ ልክ ከፍ ይላል፤ ይህን ያህል የጥራት ደረጃ ላይ ይደርሳል እንዲሁም አሁን በያዘው መንገድ ያድጋል የሚል ሐሳብ አልነበረኝም" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። አርቲ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያሰራጭ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሞስኮን አቋም የሚያንፀባርቅ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፑቲን የአርቲ ቡድን እውነትን ለመከላከል ላሳየው የማይናወጥ ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገለፁ

አርቲ ሥራውን በመሠረታዊነት ወደ አዲስ ደረጃ የማሳደግ ፈታኝ ተልዕኮ ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን፣ በቦልሾይ ቴአትር የጣቢያውን 20ኛ ዓመት አስመልክቶ ንግግር እንዳደረጉት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ ቻናሉ ይህንን በሚያስደንቅ ሁኔታ አሳክቷል።

👉 ፕሬዝዳንቱ አርቲ ሥራዎቹን በተሳካ ሁኔታ ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ በማድረጉ አወድሰውታል።

እሳቸው እንዳስተዋሉት፣ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን የመረጃ የበላይነታቸውን ለረጅም ጊዜ ሲጠቀሙበት ከርመዋል፤ አሁን ግን "በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አርቲን ያምናሉ።"

"የትኛውም ጠቅላይነት ፈጥኖም ሆነ ዘግይቶ ማብቃቱ አይቀርም፡፡"


ፑቲን አጽንዖት ሰጥተው እንደተናገሩት፣ "ሩሲያ ሁል ጊዜ የምታስጠብቀው ሉዓላዊነቷ ለሰዎችን ተጨባጭ እና ያልተዛባ መረጃ የማቅረብ ችሎታ ላይ የተመሠረተ ነው።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍8👏42
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ፑቲን የአርቲ ቡድን እውነትን ለመከላከል ላሳየው የማይናወጥ ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገለፁ አርቲ ሥራውን በመሠረታዊነት ወደ አዲስ ደረጃ የማሳደግ ፈታኝ ተልዕኮ ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን፣ በቦልሾይ ቴአትር የጣቢያውን 20ኛ ዓመት አስመልክቶ ንግግር እንዳደረጉት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ ቻናሉ ይህንን በሚያስደንቅ ሁኔታ አሳክቷል። 👉 ፕሬዝዳንቱ አርቲ ሥራዎቹን በተሳካ ሁኔታ ወደ አዲስ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ላይ አርቲ በዓለም ዙሪያ የታወቀ ዓለም አቀፍ ብራንድ ነው - ፑቲን

“ባለፉት 20 ዓመታት በመገናኛ ብዙኃን ምህዋር ውስጥ በርካታ ሁነቶች ተከስተዋል፡፡ ይህ ሙሉ ዘመን ሲሆን፣ የሩሲያ ቱዴይ (RT) ቻናል ከሐሳብነት ተነስቶ ዛሬ በዓለም ዙሪያ የታወቀ ዓለም አቀፋዊ ሥም (ብራንድ) ሆኗል።

ንቁ፣ ፈጣሪ እና ጠንካራ ቡድናችሁን ለከፍተኛ የሙያ ብቃታችሁ እንዲሁም ለሙያችሁና ለግዴታችሁ ታማኝ በመሆናችሁ አመሰግናለሁ።

በዓለም አቀፉ የመረጃ ዘርፍ እውነትን በመከላከል ረገድ ደፋርና ቆራጥ በመሆናችሁም አመሰግናለሁ።”


አርቲን (RT) ያገዱ የምዕራባውያን ልሂቃን ምላሽን ኃላቀር ሲሉ ገልጸውታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏113💯3
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
🇪🇹🇷🇺 በሞስኮ የኢትዮጵያ ባሕሎች የደመቁበት የፊልሃርመኒክ አዳራሽ ድግስ በኢትዮጵያ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነትና በሻኩራ ፕሮዳክሽን አስተባባሪነት ወደ ሞስኮ ያቀናው ኪን-ኢትዮጵያ ቡድን በሩስያ ሁለተኛ መድረኩን በልዩ ድምቀት ተካሂዷል። በመድረኩ የኢትዮጵያን ቱባ ባሕል የሚያሳዩ ባሕላዊ ሙዚቃ፣ ውዝዋዜ፣ የባሕል አልባሳት ትዕይንተ-ፋሽን እንዲሁም የሰርከስ ትርዒት ቀርቧል። ዝግጅቱን ሩሲያውያን፣…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹🇷🇺በሩሲያ የአገራቱን ወንድማማችነት ይበልጥ የሚያጸና ቆይታ ነበርን - ድምጻዊ ወንድዬ አበበ

🎭 የኪን ኢትዮጵያ የባህል እና ኪነ-ጥበብ ቡድን አባሉ፣ ጉዞው የአገሪቱን ታሪክ፣ ባህል እና እሴት በጥልቀት በማሳየት፣ ሩሲያዊያን ስለኢትዮጵያ ያላቸውን መልካም ምናብ አካል ያለበሰ መሆኑን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጿል።

🗣 "መድረኩ ሩሲያዊያን በበጎ የሚስሏትን ኢትዮጵያን በጥበብ ያዩበት ነው። የባህል ልውውጡ የአገራቱን የረጅም ዘመናት ወዳጅነት ወደ ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የማሳደግን አስፈላጊነትን አረጋግጧል፡፡" ብሏል።


📌ወንድዬ ኮንታ በሩሲያ ቆይታው ስለተመለከታቸው አስደናቂ ጉዳዮችም አካፍሎናል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
13👎6🥰2👏2
2025/10/21 11:20:37
Back to Top
HTML Embed Code: