Telegram Web Link
የካሜሩን ተቃዋሚ እጩ ኢሳ ቲቺሮማ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን እንዳሸነፉ በመግለፅ ፖል ቢያ ወጤቱን እንዲቀበሉ አሳሰቡ

ኢሳ ቲቺሮማ በሰሜናዊ ካሜሩን ከምትገኘው ጋሩዋ ከተማ አሸናፊነታቸው "ግልጽ" እንደሆነ እና የሕዝብ ምርጫ "መከበር አለበት" ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል።

የካሜሩን የምርጫ ሕግ የምርጫ ጣቢያ ውጤቶች እንዲታተሙ ቢፈቅድም፤ የሕገ-መንግሥት ምክር ቤቱ የመጨረሻውን ቆጠራ በማረጋገጥ ይፋዊ ውጤቱን በጥቅምት 16፣ 2018 ማሳወቅ ይኖርበታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍5
አሜሪካ ለኪዬቭ ማቅረብ የምትችለው ከ20 እስከ 50 የሚደርሱ ቶማሃውክ ሚሳኤሎች ብቻ ነው ተባለ

ይህም ሀገሪቱ በአጠቃላይ 4 ሺህ 150 ያህል የቶማሃውክ ሚሳኤሎች ቢኖሯትም እንደሆነ የቀድሞ የፔንታጎን ባለሥልጣን ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

አቅርቦቶቹ በዩክሬን ግጭቱ ያለበትን ሁኔታ በጉልህ እንደማይለውጡትም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ይህ ግምገማ ፑቲን በጥቅምት ወር መጀመሪያ የተናገሩትን ግምት የሚያስተጋባ ነው።

👉 የቶማሃውክ ሚሳኤሎች ለኪዬቭ ከተላለፉ ሩሲያ የአየር መከላከያ ስርዓቶቿን ታጠናክራለች ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቀደም ሲል ተናግረዋል። በተጨማሪም የእነዚህ ሚሳኤሎች አጠቃቀም ቀጥተኛ የአሜሪካ ወታደራዊ ተሳትፎ ከሌለ የማይቻል እንደሆነና ይህም የሞስኮ እና ዋሽንግተንን ግንኙነት ይበልጥ ውጥረት ውስጥ እንደሚከተው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍76🔥2
ማሊና ሩሲያ የ65 ዓመታት የወዳጅነትና ፍሬያማ ትብብር በጋራ አከበሩ

ሞስኮና ባማኮ ጥቅምት 4 በሚውለው የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የምስረታ በዓል ላይ ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

🤝 የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላዬ ዲዮፕ በመተማመን፣ በጋራ መከባበር እና የበለጠ ፍትሐዊነት የሰፈነበት ባለብዙ ወገን የጋራ ራዕይ ላይ የተመሠረተ አጋርነትን እንደሚያፀኑ አጉልተው አንስተዋል።

ማሊ በ1960 ነፃነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ ከሩሲያ ድጋፍ ስታገኝ ቆይታለች፤ ይህም ትስስር በማሊ "የጋራ ትውስታ" ውስጥ ተቀርጿል ብለዋል፡፡

👉 ሩሲያ በበኩሏ በሳህል ክልል አሸባሪነትን በመዋጋት ረገድ ቁልፍ ተዋናይ ከሆነችው ማሊ ጋር ወታደራዊና የቴክኒክ ትብብርን ማጎልበት ላይ ትኩረት እንደምታደርግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ጠቁማለች።

በሩሲያ መሳሪያዎች እና አሠልጣኞች ድጋፍ የማሊ ኃይሎች በአክራሪ ቡድኖች ላይ ውጤታማ ዘመቻዎችን እያካሄዱ መሆኑን ሚኒስቴሩ አጽንዖት ሰጥቷል።

🤝 ባማኮ በአፍሪካ በተለይም በኢኮኖሚ ትብብር በሞስኮ ቅድሚያ የሚሰጣት አጋር እንደሆነችና ከማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ ጋር የሚሠራ የምክክር ማዕከል በሩሲያ የንግድ ምክር ቤት ውስጥ ለማቋቋም መታቀዱን ገልጿል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8👏4👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️የማዳጋስካር ፓርላማ ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊናን ለመክሰስ ድምፅ አሰጣጥ እያካሄደ ነው

ምክር ቤቱ በይፋ መፍረሱ ቢታወጅም ተወካዮቹ ድምጽ መስጠቱን ቀጥለዋል ሲሉ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍4😁1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️የማዳጋስካር ፓርላማ ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊናን ለመክሰስ ድምፅ አሰጣጥ እያካሄደ ነው ምክር ቤቱ በይፋ መፍረሱ ቢታወጅም ተወካዮቹ ድምጽ መስጠቱን ቀጥለዋል ሲሉ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❗️የማዳጋስካር ወታደራዊ ኃይል በፕሬዝዳንቱ ላይ ክስ መጀመሩን ተከትሎ ሥልጣን መቆጣጠሩን አስታወቀ

የሀገሪቱ ልዩ ወታደራዊ ክፍል (ካፕሳት) ተግባራዊ የሚሆኑ አንዳንድ እርምጃዎችን መዘርዘሩን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ጠቁመዋል፦

🟠 ከብሔራዊ ምክር ቤቱ በስተቀር ሁሉንም የመንግሥት አካላት መበተን፣
🟠 ሕገ-መንግሥቱን ማፍረስ እና አዲስ ሕገ-መንግሥት ለማጽደቅ ሕዝበ ውሳኔ ማካሄድ፣
🟠 አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾም፤ ከዚያም አዲስ መንግሥት ማቋቋም፣
🟠 እስከ ሁለት ዓመት የሚቆይ የሽግግር ወቅት።

መግለጫው የፕሬዝዳንቱ መኖሪያ ከሆነው ከአምቦትሲሮሂትራ ቤተ-መንግሥት የተሰጠ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍74
🇪🇹🇿🇲 ዛምቢያ በማር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መሥራት እንደምትሻ ገለፀች

🇺🇳 የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢትዮጵያ እና ዛምቢያን የማር ገበያ ሰንሰለት ትብብር ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በደቡብ ማዕከላዊ አፍሪካዊቷ ሀገር አዘጋጅቷል፡፡

🍯 በዚህ ወቅት ዛምቢያ ከአትዮጵያ ጋር እንደ ንብ ዘረመል፣ የበሽታ ቁጥጥር፣ የወጪ ንግድ ማረጋገጫ እና የንብ ቀፎ አስተዳደር ባሉ ዘርፎች የቴክኒክ ትብብር እንደምትሻ የሀገሪቱ የአረንጓዴ ኢኮኖሚና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ተጠባባቂ ቋሚ ፀሐፊ ራንፎርድ ሲሙምብዌ ገልፀዋል።

“ይህ ግንኙነት በደን ልማት እና ዘላቂ የግብርና እሴት ሰንሰለቶች፣ በተለይም በማር ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር እድል ይሰጣል” ብለዋል።


🌱 በኢትዮጵያ የዛምቢያ ተጠባባቂ አምባሳደር ቶም ሚሼሎ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ከ326 ሺህ ቶን በላይ ማር ማምረት እና በአረንጓዴ አሻራ ከ2011 ጀምሮ 40 ቢሊየን በላይ ዛፎችን መትከል እንደቻለች በማንሳት እውቅና ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን መሪ እና የግብርና ሚኒስቴር አማካሪ ግርማ ሙሉጌታ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል በዘላቂ እና ደን ላይ የተመሠረቱ ኢንተርፕራይዞች በተለይም በማር እሴት ሰንሰለት ዙሪያ የጋራ ፍላጎት እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍74
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️የማዳጋስካር ወታደራዊ ኃይል በፕሬዝዳንቱ ላይ ክስ መጀመሩን ተከትሎ ሥልጣን መቆጣጠሩን አስታወቀ የሀገሪቱ ልዩ ወታደራዊ ክፍል (ካፕሳት) ተግባራዊ የሚሆኑ አንዳንድ እርምጃዎችን መዘርዘሩን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ጠቁመዋል፦ 🟠 ከብሔራዊ ምክር ቤቱ በስተቀር ሁሉንም የመንግሥት አካላት መበተን፣ 🟠 ሕገ-መንግሥቱን ማፍረስ እና አዲስ ሕገ-መንግሥት ለማጽደቅ ሕዝበ ውሳኔ ማካሄድ፣ 🟠 አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር…
❗️የማዳጋስካር ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነት በሀገሪቱ ሕግ አስከባሪ ኃይል እና ሠራዊት በበላይነት ይመራል

የጋራ ምክር ቤቱ ከሠራዊቱ፣ ከሀገር ውስጥ ሕግ አስከባሪው እና ከብሔራዊ ፖሊስ መኮንኖች የተወጣጣ እንደሚሆን የብሔራዊ ደህንነትና መከላከያ ኤጀንሲ ኃላፊ ኮሎኔል ራንድሪያኒሪና ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። የከፍተኛ ሲቪል አማካሪዎች ተሳትፎን ያገለለ እንደማይሆን ጠቁመዋል።

በቀጣይ ቀናት ውስጥ ሲቪል መንግሥት እንደሚመሰረትም አረጋግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍6
🌍 አፍሪካ የባሕር ላይ የወደፊት እጣ ፈንታዋን መምራት አለባት - የኢትዮጵያ የማሪታይም ባለሥልጣን

"እኛ አፍሪካውያን ትልቅ አቅም አለን...በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥሩ የባሕር ላይ ሠራተኞች አቅራቢ መሆን እንችላለን። ስለተሳትፎ ብቻ አይደለም፤ መሪ መሆን አለብን፤ በአፍሪካዊነት መሳተፍ አለብን" ሲሉ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋ ከአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


ማሪታይም "የማይታይ መሠረተ ልማት" መሆኑን አጽንኦት የሰጡት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ለአፍሪካ የሎጂስቲክስና የንግድ ኮሪደሮች መሠረት ነውም ብለዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በር ባይኖራትም በንቃት የባሕር ላይ ሠራተኞችን እያሰለጠነች እና የሰማያዊ ኢኮኖሚ አቅሟን እያሰፋች መሆኑን ገልጸዋል።

🎯 ከ7 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ የማሪታይም ሠራተኞች በዓለም አቀፍ መርከቦች ላይ እየሠሩ ሲሆን የሥልጠና ፕሮግራሞችንም በመጨመር ኢትዮጵያ አህጉራዊ አቅሟን ወደ ቀጣናዊ ጥንካሬ በመቀየር ራሷን የወደፊት የማሪታይምና የሎጂስቲክስ ማዕከል አድርጋ ለማስቀመጥ አልማለች፡፡

በሰው ሠራሽ አሰተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8😁3
ከስደት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት፡ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ለአፍሪካ ሉዓላዊነት
Sovereignty Sources
🌍 👑#SovereigntySources |ከስደት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት፡ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ለአፍሪካ ሉዓላዊነት

በቅኝ ግዛት ዘመን አፍሪካ ነፃ እንድትወጣ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ትልቅ ሚና ተጫውተዋል — የአፍሪካ ሀገራት እርስ በርስ መተሳሰርና ውስጣቸውን ማጠናከር አለባቸው '' ሲሉ በወለጋ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ምሁሩ ዶ/ር ጉተማ ዳንኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


📻 ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የአፍሪካ ዲያስፖራዎች በመላው ዓለም ቁልፍ ሚና በተመለከተ በወለጋ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ምሁሩ ዶ/ር ጉተማ ዳንኤልን አነጋግሯቸዋል። ከምዕራባዊያን እርዳታ ተላቅቆ የውስጥ አቅምን ለማጎልበትና ከድህነት ለመውጣት የሚደረግ ትግልን በተመለከተ በክፍል ሁለት ከፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች መምህሩ ሀዋቂ በቀለ ጋር የተደረገው ቆይታም ሌላኛው ጉዳያችን ነው።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ፡-

⚡️ከቴሌግራም ሳይወጡ ፕሮግራሙን ያዳምጡ                                          

⚡️ በድረ ገጻችን

👉 ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts AfripodsDeezerPocket CastsPodcast Addict Spotify

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🙏3
🇪🇹 የኢትዮጵያ እምቅ የታዳሽ ኃይል ሀብት በአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ መነቃቃትን ፈጥሯል - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

‎ሀገሪቱ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍን በፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመደገፍ ውጤታማ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች ያሉት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሐሰን ናቸው፡፡

◻️ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ለማምረት የሚያስችል የተፈጥሮ ማዕድናት እንዳሏት፣

◻️ የተለያዩ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎች በዘርፉ ለመሠማራት እንቅስቃሴ እንደጀመሩ፣

◻️ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን የተለያዩ ሀገራት ኩባንያዎች እየሳበ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

❗️ ኢትዮጵያ አማራጭ የታዳሽ ኃይል አቅርቦት ያላት ሀገር መሆኗን ለማሳየት በአዲስ አበባ የሚካሄደውን “አፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ 2025” የተሰኘ አህጉራዊ ኹነት በአዳማ አንድ የንፋስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ የማስተዋወቅ ሥራ ተከናውኗል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ኤም23 አማፂያን የተኩስ አቁም ክትትል ማዕቀፍ ለመዘርጋት የዶሃ ስምምነትን ተፈራረሙ

"ይህ ማዕቀፍ ቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነቱን አፈፃፀም በመቆጣጠር፣ ተላልፈው የተገኙ ጥሰቶችን በመመርመር እንዲሁም በማረጋገጥ፤ ግጭቶች ዳግም እንዳይቀሰቀሱ ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመነጋገር ዕድል ይፈጥራል" ሲል የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።


ኳታር ለሰላም "ቁልፍ እርምጃ" በማለት ያደነቀችውን ይህን ማዕቀፍ ዶሃን ጨምሮ አሜሪካ እና የአፍሪካ ኅብረት ይከታተሉታል።

🕊 ይህ የመግባቢያ ውል በምስራቅ ኮንጎ ያለውን ግጭት በዘላቂነት ለማስቆም ያለመውን የሐምሌ ወር የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ የመጣ ነው።

በሰው ሠራሽ አሰተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6👍5
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️የማዳጋስካር ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነት በሀገሪቱ ሕግ አስከባሪ ኃይል እና ሠራዊት በበላይነት ይመራል የጋራ ምክር ቤቱ ከሠራዊቱ፣ ከሀገር ውስጥ ሕግ አስከባሪው እና ከብሔራዊ ፖሊስ መኮንኖች የተወጣጣ እንደሚሆን የብሔራዊ ደህንነትና መከላከያ ኤጀንሲ ኃላፊ ኮሎኔል ራንድሪያኒሪና ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። የከፍተኛ ሲቪል አማካሪዎች ተሳትፎን ያገለለ እንደማይሆን ጠቁመዋል። በቀጣይ ቀናት ውስጥ ሲቪል…
❗️የማዳጋስካር ከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ የጦር ሠራዊት ኮሎኔል በፕሬዝዳንትነት ሀገሪቱን እንዲመሩ ጥሪ አቀረበ

በማዳጋስካር ስላለው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች፦

🟠 ወታደራዊ ኃይሉ የብሔራዊ ምክር ቤቱ፤ ፕሬዝዳንት ራጆሊናን ለመክሰስ ድምጽ ከሰጠ በኋላ ሥልጣን መያዙን አስታውቋል።

🟠 የሀገሪቱ ልዩ ወታደራዊ ክፍል (ካፕሳት) ተግባራዊ የሚደረጉ እርምጃዎችን ዘርዝሯል፦

የሴኔት እና የከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ፈርሷል፤ የብሔራዊ ምክር ቤቱ ግን እንደተጠበቀ ነው።
ሕገ-መንግሥቱ ተሽሯል፤ ለአዲስ ሕገ-መንግሥት ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል።
አዲስ መንግሥት ከመመሥረቱ በፊት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሾማል።
እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ የሽግግር ወቅት።

🟠የሀገሪቱ የሕግ አስከባሪ ኃይል እና ሠራዊቱ የማዳካስካር ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነትን በጋራ ይቆጣጠራሉ።

ምክር ቤቱ ከሠራዊት፣ ከሕግ አስከባሪ ኃይሉ እና ከብሔራዊ ፖሊስ የተውጣጡ መኮንኖችን ያቀፈ ይሆናል ሲሉ የካፕሳት ኃላፊ ኮሎኔል ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
የከፍተኛ ሲቪል አማካሪዎች ተሳትፎ አይገለልም።

🟠 የብሔራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ራጆሊናን ከሥልጣን ለማውረድ ድምጽ ከሰጠ በኋላ በቅርብ ቀናት ውስጥ የሲቪል መንግሥት እንደሚመሠረት ኮሎኔል ራንድሪያኒሪና ማክሰኞ ዕለት ከፕሬዝዳንታዊ መኖሪያ ቤት አምቦትሲሮሂትራ ቤተ-መንግሥት ሆነው ተናግረዋል።

🟠 ራጆሊና ሰኞ ዕለት ሀገሪቱን ለቀው የወጡ ሲሆን ከሀገር ውጭ ከማይታወቅ ስፍራ ሆነው ባደረጉት ንግግር ሥልጣን ለመልቀቅ አሻፈረኝ ብለው ነበር።

🟠 የፓርላማ አባላት እሳቸውን ለመክሰስ ድምፅ ለመስጠት ሲዘጋጁ ራጆሊና ማክሰኞ ዕለት የብሔራዊ ምክር ቤቱን መፍረስ አወጁ።

🟠 ልዩ ወታደራዊ ክፍሉ (ካፕሳት) በ2009 አንድሪ ራጆኤሊና ወደ ሥልጣን እንዲመጡ ደግፏል። በወቅቱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የአሁኑ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ማርክ ራቫሎማናና የተቃዋሚ መሪ ነበሩ።

🟠 መስከረም 25 ቀን በውሃና በኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በሂደት የፕሬዝዳንቱን ሥልጣን መልቀቅ ወደመጠየቅ ተሸጋግሯል።

🟠 በኬንያ እና ኔፓል የአዲሱ ትውልድ "ጀነሬሽን ዜድ" እንቅስቃሴዎች ተነሳስተው፤ ከተቃውሞዎቹ ጀርባ ያሉት ወጣቶች ድህነትንና ሙስናን አውግዘዋል።

🟠በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሠረት በተቃውሞዎቹ ቢያንስ 22 ሰዎችን ሲገድሉ ከመቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል። የማዳጋስካር መንግሥት ይህን ቁጥር በመቃወም 12 ሰዎች ብቻ መሞታቸውን ተናግሯል።

🟠 የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ፤ "ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በመጣስ ከተደራጀ ስብሰባ የሚመጣ ማንኛውም ውሳኔ" "ባዶ እና ከንቱ" እድርጎ እንደሚቆጥረው አስጠንቅቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4😁2👍1👎1
🇪🇹 ኢትዮጵያ የባሕር መሀንዲሶችን አሠልጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበች እንደምትገኝ ተገለፀ

🏫 በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሠልጥነው በውጪ ሀገራት ከተቀጠሩት ኢትዮጵያውያን የማሪታይም ምሩቃን መካከል፤ 26ቱ በዓለም ትልልቅ የዘርፉ ተቋማት በከፍተኛ ኃላፊነት፣ አማካሪነት እና ባለሞያነት እየሠሩ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ተቋሙ ከሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሜካኒካል እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና የተመረቁ ምሩቃንን መልምሎ ለ6 እና ለ9 ወራት በማሠልጠን የማሪታይም ዘርፍ ባለሞያዎችን እያበቃ ይገኛል ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

🌐 የማሪታይም መሀንዲሶቹ ከውጪ ሀገራት በመጡ መምህራን ዓለም አቀፍ መስፈርት ያሟላ ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ይህንን ሥራ ከጀመረ 12 ዓመታት አስቆጥሯልም ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏125😁3
የብሪክስ የወይን ምርት ጉባኤ የሩሲያ የወይን ዘርፍ ፎረም አካል ሆኖ ይካሄዳል - የሩሲያ የወይን አምራቾች ማህበር

የማህበሩ ኃላፊ እና የሮሲያ ሴጎድኒያ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ቡድን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዲሚትሪ ኪሴሌቭ፤ የብሪክስ የወይን ጠጅ ጉባኤ በወይን ጠጅ ምርት ውስጥ ያለውን የሀገራት ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ይህም የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦

🟠 ሳይንሳዊ እውቀት፣
🟠 የክህሎት ልውውጥ፣
🟠 የምርት ሰንሰለቶች፣
🟠 የመሳሪያዎች ምርት፣
🟠 የወይን ጠጅ ቱሪዝም፣
🟠 ተመጣጣኝ በረራዎች።

🌍🌍🌍 በብሪክስ ሀገራት ባለሙያዎች እና በወይን ጠጅ ኢንዱስትሪ መካከል ያለው ዓለም አቀፍ ትብብር እየተሻሻለ እንደሆነና አብዛኞቹ ደግሞ ጥሩ የወይን ጠጅ ገበያ እንቅስቃሴ እና የዳበሩ ብሔራዊ የወይን ጠጅ ኢንዱስትሪዎች እንዳሏቸው ኪሴሌቭ ተናግረዋል።

“ለብሪክስ መስራች ሀገራት፤ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ፤ የትብብር እቅድ በማቅረብ ጀመርን። ከእነዚህ ሀገራት እያንዳንዳቸው የራሳቸው የወይን እርሻ እና የወይን ጠጅ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች አሏቸው። በአጠቃላይ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ በማዳበራችን እድለኞች ነን። ከፍተኛ ፍላጎት አለ” ሲሉ አክለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አፍሪካ ጥሬ ዕቃ ሳይሆን ጥሬ አቅም ነው ወደ ውጭ ስትልክ የኖረችው - የኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊ እና የመርከብ አገልግሎት ወኪሎች ማኅበር

📌 የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ዳዊት ውብሸት፤ ነፃ የንግድ ቀጣናው የአፍሪካ ሀገራት እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች ግብይትን ለማሳደግ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ጠንካራ የግብይት ባሕል አለመኖር የአኅጉሪቱ ዕድገት ዋነኛ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል። የትኛው ሀገር ምን አለው የሚለውን ለይተን ወደ ራሳችን ገበያ ከማምጣት ይልቅ የላክነው ጥሪ ዕቃ እሴት ተጨምሮበት ሲመጣ መልሰን እንገዛ ነበር" ብለዋል።


🌍 የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ተሳትፎን ማሳደግ ለአኅጉሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ያለቱን አበርክቶም አውስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5😁2
የሻርም ኤል ሼክ የሰላም ጉባኤ ኔታንያሁን ከአደጋ ያወጣ ነው - ባለሙያ

በአልጄሪያ አም ሲላ መሐመድ ቡዲያፍ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አህመድ ሩዋጅያ፤ ጉባኤው "ለእስራኤል መንግሥት ቀደም ሲል መደበኛ ግንኙነትን ይደግፉ ከነበሩ የአረብ ሀገራት ዳግም የመገናኘት እድልን የሰጠ ነው” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

☝️ ይሁን እንጂ፤ "ይህን ግንኙነት የሚፈልጉት ሀገራትም ቢሆኑ ታላቋን እስራኤልን የማስፋፋት፣ ማለትም አብዛኞቹን የአረብ ሀገራት የመዋጥ ዕቅዱን ባልተወው የእስራኤል መንግሥት ስጋት ውስጥ በመሆናቸው መደበኛ ግንኙነቱ አይሳካም" ብለው እንደሚያምኑ ባለሙያው ጠቁመዋል።

ሩዋጅያ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በአሸማጋዮች አማካኝነት የተደረሰውን “ተሰባሪ” ስምምነት "ፍፁም እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ የተንጠለጠለ" ሲሉ ገልጸውታል።

🕊 ሆኖም ስምምነቱ ለፍልስጤም ሕዝብ "እረፍት" እና "ትንሽ ተስፋ" ይሰጣል በማለት አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😁31👍1👎1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአፍሪካ ወጣቶችን መጪው ዘመን ለሚጠይቀው ክህሎት ማዘጋጀት ይገባል - የደቡብ አፍሪካ ምክትል ትምህርት ሚኒስትር

📌 ሚሚ ጎንደዌ፤ የአፍሪካ ሀገራት በዲጂታል ክህሎት የበለፀጉ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን በስፋት ለማፍራት፤ የአኅጉሪቱን የቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ በትኩረት መተግበር አንዳለባቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"አኅጉሪቱን ከተቀረው ዓለም ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ የዲጂታል ክህሎት መሠረታዊ ጉዳይ ነው። ስትራቴጂው የቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠናን በማስፋት ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ለማብዛት ያግዛል" ብለዋል፡፡


በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ክህሎት ሳምንት የአፍሪካ አህጉራዊ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ 2025-34 ይፋ ሆኗል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
3👍1
የብራዚል ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸውን ሥራዎች አደነቁ

የሀገሪቱ የግብርናው ዘርፍ ኢኒሼቲቮች አበረታች መሆናቸውን ሉላ ዳሲልቫ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በጣልያን ሮም እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም የምግብ ፎረም ጎን ለጎን በተካሄደው 2ኛው የግሎባል አሊያንስ ኢኒሼቲቭ የሀገራት ትብብር መድረክ ላይ ነው፡፡

በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ በበኩላቸው፤ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት መገኘት መቻሉን አንስተዋል፡፡

ለዚህም የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን በማሳያነት በመጥቀስ፤ የእንቁላል፣ ወተት፣ ማርና ዓሣ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር መደረጉን አብራርተዋል፡፡

በ2024 በብራዚል የተጀመረው ግሎባል አሊያንስ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያ ጨምሮ በርካታ ሀገራትን ያቀፈ የትብብር ጥምረት ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
12👎10👏3🤩2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አፍሪካ በባሕርተኞች ሥልጠና ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲኖራት መሥራት ይገባል - የዘርፉ ምሑር

📌 አፍሪካዊያን በባሕር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያላቸውን ተጽዕኖ ለማሳደግ፤ መንግሥታት አኅጉሪቱ በዘርፉ ዓለም አቀፍ የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና በምታገኝበት አግባብ መሥራት እንዳለባቸው በናይጄሪያ የጆማሪን የባሕር ጥናት እና ምርምር ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኬኔት ኤፒዴል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"አሁን ላይ አፍሪካዊያን ባሕርተኞች የምንወስዳቸው ሥልጠናዎች በአብዛኛው በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የላቸውም። ስለዚህም እያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር በዓለም አቀፉ የባሕር ኃይል ድርጅት ውስጥ ባሉ አጋሮች ላይ ግፊት ማድረግ አለበት" ብለዋል።


በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው አህጉር አቀፉ የማሪታይም ጉባኤ ላይ በርካታ ቁልፍ ተዋንያን በዘርፉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ጋዛን ስናይ ሞተን ቢሆን ብለን ነበር፤ ግን መልሰን እንገነባታለን"

በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ወደ ቤታቸው የተመለሱ ፍልስጤማውያን ህመም እና ኪሳራ ቢኖርባቸውም እንደ አዲስ ለመጀመር ቁርጠኛ እንደሆኑ ይናገራሉ።

“እጅ አንሰጥም። በሀገራችን እንኖራለን” ሲል የተፈታው እስረኛ አህመድ አሊ ተናግሯል።


📹👆🏽 የጋዛ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ስለተሰማቸው ስሜት፣ ከሚወዷቸው ጋር ስለነበረው ግንኙነት፣ ከእምነት እና የመኖር ፍላጎት በስተቀር ምንም የቀረ ነገር ወደሌለበት ሥፍራ መመለስ ምን ማለት እንደሆነ ከስፑትኒክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
17😁6🙏2
2025/10/23 07:30:05
Back to Top
HTML Embed Code: