ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
🚨📹 'በጣም ጥሩ ደወል' ነበር ሲሉ ትራምፕ ከፑቲን ጋር ያደረጉትን የስልክ ውይይት አወደሱ 💬 ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በዋይት ሃውስ ባደረጉት ንግግር የስልክ ውይይቱ "በጣም በጥሩ ሁኔታ አልፏል" ብለዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🚨 ፑቲን እና ትራምፕ "በሁለት ሳምንት ውስጥ" ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳሉት፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በቅርቡ ይገናኛሉ። ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀደም ሲል መነጋገራቸውን እና ለውይይቱ ጊዜና ቦታ ይወስናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አክለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

👏3❤2
የኔቶ አገራት የደህንነት አገልግሎቶች በአፍሪካና በሌሎች ቀጣናዎች አለመረጋጋትን በመፍጠር ተሳትፈዋል ሲሉ የሩሲው ባለሥልጣን ተናገሩ
የሩሲያ ፌዴራል ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አሌክሳንደር ቦርትኒኮቭ እንደተናገሩት፣ የምዕራቡ ዓለም ልሂቃን እነዚህን ኤጀንሲዎች የሚጠቀሙት መካከለኛው በምሥራቅ፣ በእስያ እና በአውሮፓ ጨምሮ አዲስ ዓለም አቀፍ የግንኙነት ማዕቀፍ እንዳይፈጠር ለማገድ ነው ብለዋል።
የእነዚህ ቡድኖች እንቅስቃሴ የጂኦፖለቲካ ባላንጣዎቻቸውን ለመጉዳት እና በአጋሮቻቸውና በነሱ ላይ ጥገኛ በሆኑ አገሮች ቁጥጥርን ለማጠናከር ያለመ ነው ሲሉ አክለዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ፣ እንደ ብሪክስ እና ሻንጋይ የትብብር ድርጅት ላሉ ተቋማት ትንሳኤ ምላሽ ለመስጠት የአውሮፓ-አትላንቲክ ቡድኖች የሚከተሉትን በመጠቀም የበቀል እርምጃ ይፈፅማሉ፡-
⚫️ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ፣
⚫️ የትጥቅ ግጭቶች፣
⚫️ የማዕቀቦች ጦርነት፣
⚫️ የቀለም አብዮቶች፤
⚫️ ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነት እና
⚫️ ፖለቲካዊ-ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ይገኙበታል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
የሩሲያ ፌዴራል ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አሌክሳንደር ቦርትኒኮቭ እንደተናገሩት፣ የምዕራቡ ዓለም ልሂቃን እነዚህን ኤጀንሲዎች የሚጠቀሙት መካከለኛው በምሥራቅ፣ በእስያ እና በአውሮፓ ጨምሮ አዲስ ዓለም አቀፍ የግንኙነት ማዕቀፍ እንዳይፈጠር ለማገድ ነው ብለዋል።
የእነዚህ ቡድኖች እንቅስቃሴ የጂኦፖለቲካ ባላንጣዎቻቸውን ለመጉዳት እና በአጋሮቻቸውና በነሱ ላይ ጥገኛ በሆኑ አገሮች ቁጥጥርን ለማጠናከር ያለመ ነው ሲሉ አክለዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ፣ እንደ ብሪክስ እና ሻንጋይ የትብብር ድርጅት ላሉ ተቋማት ትንሳኤ ምላሽ ለመስጠት የአውሮፓ-አትላንቲክ ቡድኖች የሚከተሉትን በመጠቀም የበቀል እርምጃ ይፈፅማሉ፡-
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5❤2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ፖሊስ ለራይላ ኦዲንጋን ሞት ሀዘን የተሰባሰቡ ሰዎች ላይ በመተኮሱ ቢያንስ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ የጸጥታ ኃይሎች የተቃዋሚ መሪው ራይላ ኦዲንጋን አስከሬን ለማየት የተሰበሰቡ ሰዎችን ለመበተን ተኩስ ከፍተዋል። አንዳንድ ሀዘንተኞች የደህንነት በሮችን ለማፍረስ ከሞከሩ በኋላ በካሳራኒ ስታዲየም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ግርግር…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇰🇪 በኬንያ ኦዲንጋ የስንብት ሥነ-ሥርዓት ላይ በተፈጠረ ሁከት ቢያንስ አራት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆሰሉ - መገናኛ ብዙኃን
በሟቹ የተቃዋሚ መሪ የስንብት ሥነ-ሥርዓት ላይ በካሳራኒ ስታዲየም የተሰበሰበው ከፍተኛ ሕዝብ፣ የደህነንት ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት መተኮሱን ተከትሎ መበተኑ ተዘግቧል፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በሟቹ የተቃዋሚ መሪ የስንብት ሥነ-ሥርዓት ላይ በካሳራኒ ስታዲየም የተሰበሰበው ከፍተኛ ሕዝብ፣ የደህነንት ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት መተኮሱን ተከትሎ መበተኑ ተዘግቧል፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤6🤔5🤬2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | ቻይና 'ሎንግ ማርች-8ኤ' ተልዕኮ 600ኛ የሎንግ ማርች የሳተላይት ሮኬት በስኬት አስወነጨፈች
ሮኬቱ የ12ኛውን ዝቅተኛ-ምህዋር የኢንተርኔት ሳተላይቶች ስብስብ በተሳካ ሁኔታ ወደተመደበላቸው ምህዋር ማስገባቱ የተልዕኮው ሙሉ ስኬት አሳይቷል። ይህ ሎንግ ማርች-8ኤ ሮኬት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሥራ ከጀመሩ ተመሳሳይ ሮኬቶች አራተኛው ነው።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ሮኬቱ የ12ኛውን ዝቅተኛ-ምህዋር የኢንተርኔት ሳተላይቶች ስብስብ በተሳካ ሁኔታ ወደተመደበላቸው ምህዋር ማስገባቱ የተልዕኮው ሙሉ ስኬት አሳይቷል። ይህ ሎንግ ማርች-8ኤ ሮኬት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሥራ ከጀመሩ ተመሳሳይ ሮኬቶች አራተኛው ነው።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤4👍3
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
🚨 ፑቲን እና ትራምፕ "በሁለት ሳምንት ውስጥ" ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳሉት፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በቅርቡ ይገናኛሉ። ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀደም ሲል መነጋገራቸውን እና ለውይይቱ ጊዜና ቦታ ይወስናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አክለዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ…
❗️ላቭሮቭ እና ሩቢዮ ዛሬ የስልክ ውይይት እንደሚያደርጉ የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
በፒተር ሲያሪቶ የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦
🔸 በሃንጋሪ የሚካሄደው የሩሲያ እና አሜሪካ ጉባኤ ቀን እና ዝርዝር ሁኔታዎች፣ በቀጣይ ሳምንት በሚደረገው የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባና ውጤት ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡
🔸 ሃንጋሪ የሩሲያ እና የአሜሪካ ውይይትን ደህንነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ናት፡፡
🔸 ቡዳፔስት ፑቲንንበክብር ትቀበላለች፤ እንዲሁም ወደ አገሪቱ የመግባት እና የመውጣት ነጻነታቸውንም ዋስትና ትሰጣለች፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በፒተር ሲያሪቶ የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦
🔸 በሃንጋሪ የሚካሄደው የሩሲያ እና አሜሪካ ጉባኤ ቀን እና ዝርዝር ሁኔታዎች፣ በቀጣይ ሳምንት በሚደረገው የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባና ውጤት ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡
🔸 ሃንጋሪ የሩሲያ እና የአሜሪካ ውይይትን ደህንነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ናት፡፡
🔸 ቡዳፔስት ፑቲንንበክብር ትቀበላለች፤ እንዲሁም ወደ አገሪቱ የመግባት እና የመውጣት ነጻነታቸውንም ዋስትና ትሰጣለች፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤4👍2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
🚨 ፑቲን እና ትራምፕ "በሁለት ሳምንት ውስጥ" ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳሉት፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በቅርቡ ይገናኛሉ። ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀደም ሲል መነጋገራቸውን እና ለውይይቱ ጊዜና ቦታ ይወስናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አክለዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ…
ቡዳፔስት እንደዚህ ዓይነት ስብሰባ ሊደረግባት የሚችል “በአውሮፓ ውስጥ ብቸኛዋ ምክንያታዊ ቦታ ናት" ሲሉ ጡረተኛው የእንግሊዝ ዲፕሎማት ኢያን ፕራውድ ኤክስ ገጻቸው ላይ ፅፈዋል።
ዲፕሎማቱ ሃንጋሪ የአሁኗ “የአውሮፓ ዲፕሎማሲ ማዕከል” እንደሆነችም ጠቁመዋል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ፑቲን የሩሲያ እና አሜሪካ ጉባኤ በቡዳፔስት እንዲካሄድ ትራምፕ ያቀረቡትን ሐሳብ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤7👎1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️በፑቲን እና በትራምፕ መካከል የሚደረግ ስብሰባ በሁለት ሳምንት ውስጥ ወይም ትንሽ ቆይቶ ሊካሄድ ይችላል - ክሬምሊን
የሁለቱ አገሮች መሪዎች ስብሰባውን ለማካሄድ ይሁንታቸው ከቸሩ፣ ላቭሮቭ እና ሩቢዮ አስቀድመው ዝግጅትን ማቀናጀት ይጀምራሉ ሲሉ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
የሁለቱ አገሮች መሪዎች ስብሰባውን ለማካሄድ ይሁንታቸው ከቸሩ፣ ላቭሮቭ እና ሩቢዮ አስቀድመው ዝግጅትን ማቀናጀት ይጀምራሉ ሲሉ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤7👍1
🇧🇫 ቡርኪና ፋሶ ለቀድሞ መሪዋ ቶማስ ሳንካራ መታሰቢያ ወርሃዊ ወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት አወጀች
ጠቅላይ ሚንስትር ሪምታልባ ዣን ኢማኑኤል ኡዴድራጎ የሳንካራን ግድያ 38ኛ ዓመት መታሰቢያን አስመልክቶ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንዳስታወቁት፣ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ለሳንካራ ክብር የሚሰጥ ወርሃዊ የማስታወሻ ሥነ-ሥርዓት በእያንዳንዱ ወር የመጀመሪያ ሐሙስ ቀን 10 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
👉 ዝግጅቱ የቡርኪና ፋሶን አብዮታዊ መሪ ተሞክሮ ለማክበር ወታደራዊ ሠራተኞችን፣ ዜጎችን እና ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን በአንድነት ያሰባስባል።
መርሃ ግብሩ የሚከተሉትን ዝግጅቶች ያካትታል፦
🔸 የጥበቃ ለውጥ፣
🔸 በአብዮታዊ ዩኒፎርም የሚደረግ ሰልፍ፣
🔸 የፈረስ ጉግስ ሥነ-ሥርዓት እና
🔸 የአበባ ጉንጉን የማኖር ሥነ-ሥርዓት ይገኙበታል።
ሁሉም እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱት ኦጋዱጉ በሚገኘውና ባለፈው ግንቦት ወር በተመረቀው፣ የሳንካራ እና የ12 አጋሮቻቸው አስከሬን ባረፈበት፣ እንደ ብሔራዊ የማስታወሻ ምልክት ሆኖ በቆመው ቶማስ ሳንካራ መታሰቢያ ስፍራ ላይ ነው።

🔥8❤3👏2👍1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️በፑቲን እና በትራምፕ መካከል የሚደረግ ስብሰባ በሁለት ሳምንት ውስጥ ወይም ትንሽ ቆይቶ ሊካሄድ ይችላል - ክሬምሊን የሁለቱ አገሮች መሪዎች ስብሰባውን ለማካሄድ ይሁንታቸው ከቸሩ፣ ላቭሮቭ እና ሩቢዮ አስቀድመው ዝግጅትን ማቀናጀት ይጀምራሉ ሲሉ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❗️ ፕሬዝዳንት ፑቲን ከሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ጋር የስልክ ውይይት አደርጉ - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
በዲሚትሪ ፔስኮቭ የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦
🟠 ክሬምሊን ስለ ፑቲን እና ኦርባን ውይይት ዝርዝር መረጃ በቅርቡ ይፋ ያደርጋል።
🟠 የፑቲን እና ትራምፕ ውይይትን የተመለከተ ወደ ኪዬቭ የሚላኩት የቶማሃውክ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች አቅርቦቶች ስጋት ቀንሶ እንደሆነ አሜሪካን ሊጠይቅ ይችላል።
🟠 ሩሲያ በዩክሬን ሰላማዊ እልባት ለማምጣት ዝግጁ ሆና መጠበቋን ትቀጥላለች።
🟠 የፑቲንእና ትራምፕ የውይይት ይዘት ከሚዲያዎች ምስጢር ሆኖ መቆየት አለበት።
🟠 ላቭሮቭ እና ሩቢዮ የስብሰባ ቦታቸውን በራሳቸው ያስታውቃሉ።
🟠 ፕሬዝዳንት ፑቲን ከሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ቋሚ አባላት ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት ይኖራቸዋል።
🟠 ፑቲን የራሺያ ቱደይ (አርቲ) ቡድንን በ20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ዝግጅታቸው ላይ በግላቸው መልካም ምኞታቸውን ሊገልፁ ይችላሉ።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በዲሚትሪ ፔስኮቭ የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏4❤2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️ ፕሬዝዳንት ፑቲን ከሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ጋር የስልክ ውይይት አደርጉ - የክሬምሊን ቃል አቀባይ በዲሚትሪ ፔስኮቭ የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦ 🟠 ክሬምሊን ስለ ፑቲን እና ኦርባን ውይይት ዝርዝር መረጃ በቅርቡ ይፋ ያደርጋል። 🟠 የፑቲን እና ትራምፕ ውይይትን የተመለከተ ወደ ኪዬቭ የሚላኩት የቶማሃውክ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች አቅርቦቶች ስጋት ቀንሶ እንደሆነ አሜሪካን ሊጠይቅ…
የሩሲያ እና የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ቀጣይ መገናኛ ከተማ ቡዳፔስት የመሆኗ ውሳኔ ምክንያታዊ እንደሆነ ብራዚላዊው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ራፋኤል ማቻዶ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
💬 “ሃንጋሪ ለረጅም ጊዜ በቅርብ ዓመታት ደግሞ በሮበርት ፊኮ ስር ካለችው ስሎቫኪያ ጋር ተቀላቅላ፣ በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ያለውን የበላይነት አካሄድ በመቃወም ረገድ የራሷን ሚና እየተጫወተች ነው። በኔቶ ውስጥም ቢሆን የተቃውሞ እና የጥበቃ ሚና ነበራት” ብለዋል ማቻዶ።
ነገር ግን ቡዳፔስትን መምረጥ የፖለቲካ ማዕከሉ ወደ ምሥራቅ እየተቀየረ መሆኑን የሚያጎላ ሲሆን፣ ውይይቱ እውነተኛ እድገት ካስገኘ ሃንጋሪ በአውሮፓ መድረክ አዲስ ጠቀሜታ ልታገኝ ትችላለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍6👏3❤2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️ኦርባን በቡዳፔስት ሊካሄድ የሚችለውን የሩሲያ እና የአሜሪካ ጉባኤ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ለማረጋገጥ ፈቃደኛ ናቸው ሲል ክሬምሊን አስታወቀ
በፑቲን እና በኦርባን የስልክ ውይይት ወቅት የተነሱ ተጨማሪ ዝርዝሮች ሐሳቦች፦
🔸 ፑቲን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ስላደረጉት ውይይት ዋና ዋና ይዘቶች ለሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርባንን አሳውቀዋል።
🔸 ፑቲን እንደተናገሩት፣ የሩሲያ ተወካዮች ከአሜሪካ ተወካዮች ጋር በሚያደርጉት ቀጣይ ግንኙነት፣ የዩክሬን ቀውስ በሰላም ለመፍታት የሚያስችሉ መንገዶችን ለመፈለግ እና ወደፊት የሩሲያ እና አሜሪካ ጉባኤ በሃንጋሪ ዋና ከተማ እንዲካሄድ በማሰብ፣ በቀጣይ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች አካሄድ ላይ ለመወያየት አቅደዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በፑቲን እና በኦርባን የስልክ ውይይት ወቅት የተነሱ ተጨማሪ ዝርዝሮች ሐሳቦች፦
🔸 ፑቲን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ስላደረጉት ውይይት ዋና ዋና ይዘቶች ለሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርባንን አሳውቀዋል።
🔸 ፑቲን እንደተናገሩት፣ የሩሲያ ተወካዮች ከአሜሪካ ተወካዮች ጋር በሚያደርጉት ቀጣይ ግንኙነት፣ የዩክሬን ቀውስ በሰላም ለመፍታት የሚያስችሉ መንገዶችን ለመፈለግ እና ወደፊት የሩሲያ እና አሜሪካ ጉባኤ በሃንጋሪ ዋና ከተማ እንዲካሄድ በማሰብ፣ በቀጣይ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች አካሄድ ላይ ለመወያየት አቅደዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍7👏3❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | የ"ጄን ዚ"* አለመረጋጋት በፔሩ ዋና ከተማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አደረገ
በአገሪቱ መዲና ሊማ የጡረታ አበል ማሻሻያ የሚጠይቁ የመንግሥት ተቃውሞዎች ረቡዕ ዕለት የተቀሰቀሱ ሲሆን፤ የማሻሻያ ጥያቄው ብዙም ሳይቆይ ፕሬዝዳንት ሆሴ ጄሪ ሥልጣናቸውን እንዲለቅቁ ጥሪ ወደማሳማት አድጓል።
ወጣቱ ትውልድ ሙስና እና እየጨመረ በመጣው ወንጀል ላይ እርምጃ አለመውሰዳቸውን በመጥቀስ ክስ አቅርቦባቸዋል።
* "ጄን ዚ" (Generation Z) እ.ኤ.አ. ከ1997 አእስከ 2012 ባለው ዓመት የተወለደ ትውልድ ነው፡፡ አሁን ላይ ከ13 – 28 ዓመት ይገኛል፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በአገሪቱ መዲና ሊማ የጡረታ አበል ማሻሻያ የሚጠይቁ የመንግሥት ተቃውሞዎች ረቡዕ ዕለት የተቀሰቀሱ ሲሆን፤ የማሻሻያ ጥያቄው ብዙም ሳይቆይ ፕሬዝዳንት ሆሴ ጄሪ ሥልጣናቸውን እንዲለቅቁ ጥሪ ወደማሳማት አድጓል።
ወጣቱ ትውልድ ሙስና እና እየጨመረ በመጣው ወንጀል ላይ እርምጃ አለመውሰዳቸውን በመጥቀስ ክስ አቅርቦባቸዋል።
* "ጄን ዚ" (Generation Z) እ.ኤ.አ. ከ1997 አእስከ 2012 ባለው ዓመት የተወለደ ትውልድ ነው፡፡ አሁን ላይ ከ13 – 28 ዓመት ይገኛል፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏3❤2
🇪🇹🇷🇺 በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ከዩራሺያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበረከተላቸው
🎓 ዓለም አቀፉ የዩራሻያን ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬቱን ርክክቡን በሩሲያ ፌዴሬሽን የመንግስት ዱማ (ፓርላማ) ውስጥ አካሂዷል።
አምባሳደሩም በበኩላቸው፤ ለሥራቸው ለተሰጣቸውን ከፍተኛ እውቅና በማመስገን፣ የሩሲያ-ኢትዮጵያን ትብብር ለማጠናከር እና የዩኒቨርሲቲውን ተግባራት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ሲል ኤምባሲው በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስነብቧል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🎓 ዓለም አቀፉ የዩራሻያን ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬቱን ርክክቡን በሩሲያ ፌዴሬሽን የመንግስት ዱማ (ፓርላማ) ውስጥ አካሂዷል።
ዲፕሎማውን ለአምባሳደሩ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ኬ.ፒ. ክሊሜንኮ-ቦግዳኖቭ እንደተናገሩት፣ የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው በሳይንስ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በዲፕሎማሲ፣ በጎ አድራጎት ሥራዎች እና በሕዝቦች መካከል ሰላምና ወዳጅነትን በማጠናከር ረገድ ላበረከቱት አስፈላጊ አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ነው።
አምባሳደሩም በበኩላቸው፤ ለሥራቸው ለተሰጣቸውን ከፍተኛ እውቅና በማመስገን፣ የሩሲያ-ኢትዮጵያን ትብብር ለማጠናከር እና የዩኒቨርሲቲውን ተግባራት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ሲል ኤምባሲው በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስነብቧል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤10👏8🔥4🥰2
🇪🇹 የኢትዮጵያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በ2018 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የ7.87 በመቶ እድገት አስመዘገበ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳስታወቀው፤ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ከሚገኙ ኢንቨስትመንቶች በሩብ ዓመቱ ከወጪ ንግድ ከ49 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ሲገኝ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 113 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።
በኮሚሽኑ በሩብ ዓመቱ ለ123 አዳዲስ የውጭ ፕሮጀክቶችና የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን የሰጠ ሲሆን ይህም ከ2017 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ26 በመቶ ብልጫ ተመዝግቧል።

❤5🙏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፑቲን የአርቲ ጣቢያ 20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አርቲ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያሰራጭ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሞስኮን አቋም የሚያንፀባርቅ ከመሆኑም በላይ በሩሲያ ያለውን ሰፊ የሕይወት ገጽታ ያሳያል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
"ራሽያ ቱዴይ (አርቲ) ሲጠነሰስ ጅምሮ፣ በዚህ ልክ ከፍ ይላል፤ ይህን ያህል የጥራት ደረጃ ላይ ይደርሳል እንዲሁም አሁን በያዘው መንገድ ያድጋል የሚል ሐሳብ አልነበረኝም" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
አርቲ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያሰራጭ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሞስኮን አቋም የሚያንፀባርቅ ከመሆኑም በላይ በሩሲያ ያለውን ሰፊ የሕይወት ገጽታ ያሳያል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤6👍6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#viral | ሩሲያዊቷ የሴንት ፒተርስበርግ እንስት ግዙፍ ዱባን እንደ ጀልባ ተጠቅማ በሐይቅ ላይ መንሸራሸሯ ግርምትን ፈጥሯል
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤9
🇪🇹 በትግራይ እና አፋር ክልሎች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከ43 ሺህ በላይ ሰዎች ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ
ጥቅምት 1 ቀን በተከሰተው የ5.7 መጠነ ልኬት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ አንዲት ሕጻን ሕይወቷ ሲያልፍ በዘጠኝ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአፋር ክልል በርሃሌ ወረዳን ጠቅሶ የአገር ውስጥ ሚዲያ አስታውሷል።
የአፋር ክልል እንዳስታወቀው፦
🔷 ከ1 ሺህ 400 በላይ ቤቶች፣
🔷12 ትምህርት ቤቶች፣
🔷 12 የጤና ጣቢያዎች እና
🔷 ከ150 በላይ የውሃ ማጠራቀሚያዎች ወድመዋል፡፡
የትግራይ አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ በበኩሉ፦
🔷 በመቀሌ ከተማ አቅራቢያ 40 መኖሪያ ቤቶች መፈራረሳቸ እና
🔷 ከ225 በላይ ነዋሪዎች መኖሪያ አልባ መሆናቸውን አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር እና የሚያስፈልገውን የእርዳታ መጠን ለመወሰን የግምገማ ቡድኖችን ወደ ስፍራው ማሰማራቱ ተዘግቧል።

❤13👍1🙏1