Telegram Web Link
🇲🇦 ሞሮኮ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኗ የተቀዳጀውን ታሪካዊ የዓለም ዋንጫ ድል በሀገር አቀፍ ደረጃ አከበረች

⚽️ የሞሮኮ ከ20 ዓመት በታች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን እሁድ ምሽት በቺሊ በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲናን 2 ለ 0 በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮንነት ዘውድ ጭኗል፡፡

በተጨማሪም ሞሮኮ ከ42 ዓመት በኋላ በፊፋ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አርጀንቲናን ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ብሔራዊ ቡድን ሆናለች።

🎉 ሞሮኳውያን በጭፈራ፣ በእንባ፣ በእልልታ፣ በዝማሬ እና በመኪና ጥሩምባ በከፍተኛ የደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው የአንበሶቹን ድል አክብረዋል።

ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምሥሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
34👍4
#viral| አሳዛኝ ክስተት በሆንግ ኮንግ፦ የቱርክ የጭነት አውሮፕላን በደረሰበት የመንሸራረት አደጋ የሰው ህይወት ጠፋ

ሰኞ ማለዳ የቱርክ ቦይንግ 747 የጭነት አውሮፕላን በሆንግ ኮንግ አየር ማረፊያ ከማኮብኮቢያ ወጥቶ ከፓትሮል መኪና ጋር እንደተጋጨ የቻይና ሚዲያ ዘግቧል።

አራቱም የአውሮፕላኑ ሠራተኞች የተረፉ ሲሆን ሁለት የአየር ማረፊያው ሠራተኞች ወደ ውቅያኖስ ተወርውረው በደረሰባቸው ጉዳት ህይወታቸው አልፏል። ባለሥልጣናት በአደጋው መንስኤ ዙሪያ ምርመራ ጀምረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😢6😱54👍1🕊1
🛤 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢኮ ቱሪዝም ባቡር ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ

መሠረተ ልማቱ የሶፍዑመር ዋሻና ሎጅ ፕሮጀክቶችን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ እየተገነባ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ አሁን የመጀመሪያው ምዕራፍ 2 ኪ.ሜ ግንባታ እንደተጠናቀቀ የኢትየጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

የኢኮ ቱሪዝም ባቡሩ፦
◻️ በኢትዮጵያውን የተሠራ ነው፣
◻️ በውስጡ 50 ሰዎችን መያዝ ይችላል፣
◻️ 10 ሰዎችን ለከፍታ የመልከዓምድር ዕይታ ማስተናገድ ይችላል፣
◻️ ቀጣይ ምዕራፍ የባቡር መስመር ግንባታው በሂደት ላይ ነው፡፡

🗣 ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ሥራው የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን፣ የኢንዱስትሪ መንደሮችን፣ የግብርና ምርቶችን ለማጓጓዝ የሚያስችል የባቡር ሀዲድ ዝርጋታን ያለ ውጭ ጥገኝነት ለመከወን አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11👍7🙏3🥴1
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የምግብ ዋጋ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ረሃብን ለመዋጋት ብሔራዊ ጥሪ አቀረቡ

🥙 በደቡብ አፍሪካ ከ15 እስከ 16 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቂ የምግብ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው ሲሪል ራማፎሳ በሳምንታዊ ሪፖርታቸው ገልጸዋል።

ድህነትን እና የምግብ እጦትን መቅረፍ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ቁልፍ ተግባር መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

"ደቡብ አፍሪካ የምግብ እና የውሃ መብት በሕገ-መንግሥት ከተደነገገባቸው እና ዜጎች ይህን መብት እንዲያስከብሩ የሕግ ስርዓት ካስቀመጡ 29 ሀገራት ተርታ ትጠቀሳለች" ብለዋል።


👉 በየዕለቱ ዘጠኝ ሚሊዮን ተማሪዎችን የሚመግበውን እንደ የትምህርት ቤት ምገባ ያሉ ፕሮግራሞችን ቢያነሱም ከፍተኛ የሥራ አጥነት እና የዋጋ ንረት የቤተሰቦችን በጀት እየተፈታተነ መምጣቱን ራማፎሳ ጠቁመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍71🔥1
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለከፍተኛ ደረጃ ምክክር እና ቴክኖሎጂ ጉብኝት ወደ ሞስኮ አቀኑ

ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ማክሰኞ እንደሚወያዩ ይጠበቃል ሲል በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንጭ ለስፑትኒክ ገልፀዋል።

ጉዞው ተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ ስብሰባዎችን እና በሩሲያ ዋና የፈጠራ ማዕከል ስኮልኮቮ ጉብኝትን ያካትታል ሲሉ ምንጩ አመልክተዋል።

ይህ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የቅርብ ግዜ የጠበቀ እና የከፍተኛ ደረጃ ግንኙነት የሚያስቀጥል ነው።

🟠 በመስከረም ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሞስኮ የዓለም አቶሚክ ሳምንት ፎረም ላይ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ተገናኝተው ለቀጣይ ስብሰባቸው አዲስ አበባ እንዲመጡ ጋብዘዋቸዋል። ሁለቱ ወገኖች ለኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የድርጊት መርሃ-ግብርም ተፈራርመዋል።

🟠 ባለፈው ዓመት የካቲት ወር የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ከኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው የፑቲንን ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርበዋል። በጉብኝቱ የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ተረጋግጧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8😁2
የዕድል በሮችን መክፈት፡ የአፍሪካ የምጣኔ ሐብት ሉዓላዊነት
Sovereignty Sources
🛠🌍 #SovereigntySources |የዕድል በሮችን መክፈት፡ የአፍሪካ የምጣኔ ሐብት ሉዓላዊነት💡🌱

''አፍሪካ የተለያዩ የተፈጥሮ ኃብት አላት። ይህ ደግሞ ለኢንዱስትሪያላይዜሽን ሂደት ትልቅ አስተዋፅዖ ቢኖረውም ቅኝ ግዛት የምጣኔ ሀብት እድገት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሮ አልፏል። ይህ ደግሞ እንደ ትልቅ ጫና የሚቆጠር ነው።'' ሲሉ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንታል ስተዲስ መምህሩ ዶ/ር ፍራፊስ ሀይሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


📻 ሶቨርኒቲ ሶርስስ ሁለት ጉዳዮችን በሚዳስስበት በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ አፍሪካ በኢንዱስትሪ ራሷን ስለመቻል እና የምጣኔ ሀብት ሉዓላዊነትን ስለሚፈጠርበት ጉዳይ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲስ መምህሩ ዶ/ር ፍራፊስ ሀይሉን አነጋግሯቸዋል። በክፍል ሁለት ከምዕራባዊያን እርዳታ ተላቅቆ የውስጥ የማሪታይም ተቋምን መሠረት በማድረግ ስለሰማያዊ ኢኮኖሚ በዚሁ ፕሮግራም በክፍል ሁለት የኢትዮጵያ ማሪታይም የስልጠና ተቋም የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የስልጠና ልማት ኃላፊ ስዩም ትዕግስቱ ጋር የተደረገው ቆይታም ሌላኛው ጉዳያችን ነው።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

⚡️ከቴሌግራም ሳይወጡ ፕሮግራሙን ያዳምጡ                                          

⚡️ በድረ ገጻችን

👉 ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts AfripodsDeezerPocket CastsPodcast Addict Spotify

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
1👍1
ኪዬቭ በዩክሬን ግጭት ላይ ያላት አቋም በቅራኔዎች የተሞላ በመሆኑ ለሰላማዊ መፍትሄ አስተዋጽኦ አያደርግም - ክሬምሊን

በተቃራኒው ሩሲያና ፑቲን በዩክሬን እልባት ዙሪያ የያዟቸው አቋሞች ወጥና የታወቁ መሆናቸውን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍4
❗️የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ከታህሳስ 23፣ 2018 ጀምሮ የሩሲያ ጋዝ በአባላቱ በኩል ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይተላለፍ የሚያዘውን እገዳ አጸደቀ

ምዕራባውያን ሃይድሮካርቦኖችን ለመግዛት አሻፈረን በማለታቸው ከባድ ስህተት እንደሠሩና የሩሲያን ነዳጅና ጋዝ በሦስተኛ ወገን አማካኝነት በከፍተኛ ዋጋ ለመግዛት ግዴታ ውስጥ በመግባታቸው በአዲስ ጥገኝነት ውስጥ መውደቃቸውን ሩሲያ በተደጋጋሚ አጽንኦት ሰጥታ ገልጻለች።

ስፑትኒክ የዩሮስታት መረጃን ተንትኖ እንዳመለከተው ሩሲያ በነሐሴ ወር የአውሮፓ ህብረት ሦስተኛዋ ከፍተኛ የጋዝ አቅራቢ ነበረች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6😱3👎1
🚆 የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ዘርፍ ልኅቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

ቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ 62 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው የልኅቀት ማዕከል፤ ለምስራቅ አፍሪካ ባለሙያዎች ፈር ቀዳጅ የሥልጠና መዳረሻ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ኢንስቲትዩት ገልጿል፡፡

98 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ ይደረግበታል የተባለው ይህ ተቋም፤ የአፍሪካ ኅብረት 2063 አጀንዳ አካል የሆነውን ክልላዊ ውህደት እውን በማድረግ ረገድ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍63👎1
ለፕሬዝዳንት ፑቲን እና ትራምፕ ግንኙነት ብዙ 'የቤት ሥራ' ይቀራል - የክሬምሊን ቃል አቀባይ

ዲሚትሪ ፔስኮቭ የሰጡት ቁልፍ መግለጫዎች፡-

▪️ ሞስኮ መጪው የፑቲን-ትራምፕ ስብሰባ በሩሲያ-አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ለመወያየት መዋል አለበት ብላ ታምናለች፡፡

▪️ ሞስኮ መጪው የሩሲያ-አሜሪካ የመሪዎች ስብሰባ ለዩክሬን ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት እድል ይፈጥራል ብላ ተስፋ ታደርጋለች፡፡

▪️ በሩሲያ-አሜሪካ የመሪዎች ጉባኤ የዘለንስኪ ተሳትፎ ዙሪያ በአሁኑ ጊዜ ዝርዝር መረጃ የለም፡፡

▪️ የሩሲያ-ዩክሬን ግጭትን በአሁናዊ የጦር ግንባር ላይ የማስቆም አስቻይነት በሞስኮ-ዋሽንግተን ግንኙነቶች በተደጋጋሚ ተነስቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6👍2🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral| ህንድ አስደናቂ የባሕር ኃይል እና የአየር ኃይል ብርታቷን አሳየች

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሀገሪቱን የዲዋሊ በዓል ምክንያት በማድረግ ህንድ ሠራሹን አይ.ኤን.ኤስ. ቪክራንት የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ የላቁ አቅሞች በሚያሳያው ኤግዚቢሽን ላይ ተሳትፈዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍9😁3
ችግር የፈጠራ እናት ናት፦ የታካሚዎች መቆጣጠሪያ (ሞኒተር) የሠራው ኢትዮጵያዊ ዶክተር

📌 በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ኒራቅ የጤና ጣቢያ እየሠራ የሚገኘው ዶክተር ዮሐንስ ዘሪሁን፤ የህክምና መሳሪያ ጉድለት ለፈጠራው መነሻ እንደነበር ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ገልጿል፡፡ በመቆጣጠሪያ እጥረቱ ምክንያት ታካሚውን ያጣበትን አጋጣሚም አጋርቶናል፡፡

🔋🔌 ሞኒተሩ በባትሪ እና በኤሌክትሪክ የሚሠራ ነው፡፡

“የምኖረው ከአዲስ አበባ 800 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኝ ከተማ ውስጥ ነው። በጦርነት እና በተፈጥሮ አደጋዎች በጣም የተጎዳ ነው፡፡ በከተማው በአግባቡ ኤሌክትሪክ አናገኝም። በዚህ ምክንያት የኃይል ምንጭ ለሞኒተሩ ችግር እንዳይሆን በኤሌክትሪክም ሆነ በባትሪ እንዲሠራ አድርጌዋለሁ፡፡


የተበላሹ የህክምና መሳሪያዎች እና የተጣሉ ብረቶችን በመጠቀም የተሠራው ሞኒተር አሁን ላይ በጤና ጣቢያው አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡

“ልዩ የሚያደርገው ዋጋው ርካሽ ነው። ተመጣጣኝ ነው፣ ለመጠገንም ቀላል ነው እንዲሁም ለጤና ጣቢያ የተመቸ ነው፡፡”


❗️ ዶክተር ዮሐንስ ሁለት ፈጠራዎችን፤ የኦፕሬሽን ክፍል ጠረጴዛ እና የአንጀት ካንሰር ታካሚዎች የሰገራ ማስወጫ መሳሪያ፤ ሠርቶ ለቅዱስ ፓውሎስ የህክምና ኮሌጅ አበርክቷል፡፡ እንዲሁም ከባለደረባው እና ከአስተማሪው ጋር በመሆን ሦስት ፈጠራዎችን እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጾልናል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏23👍85
በፑቲን እና ትራምፕ መካከል በአላስካ የተደረገው ስብሰባ ለወደፊት ግንኙነቶች መሠረት እንደጣለ ማሳየት በሞስኮ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ሪያብኮቭ ቁልፍ መግለጫዎች፦

◻️ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የአሜሪካ አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ በቀጣይ በሚኖራቸው ግንኙነት የኢኮኖሚ ጉዳዮችን ጨምሮ በሩሲያ-አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ይካሄዳል፡፡

◻️ የሁለትዮሽ ግንኙነት ችግሮችን ለመፍታት በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ውይይት የሚደረግበት ቀን ገና አልተወሰነም። ሪያብኮቭ ከዚህ ቀደም ሦስተኛው ዙር የሩሲያ-አሜሪካ ውይይት ከጸደይ ወቅት መጨረሻ በፊት እንደሚካሄድ ተናግረው ነበር።

◻️ በዩክሬን ያለው ሁኔታ እና ምዕራባውያን ለኪዬቭ የሚያደርጉት ድጋፍ በመጪው የላቭሮቭ-ሩቢዮ ውይይት ማዕከላዊ ርዕስ ይሆናል።

◻️ በቅርቡ በላቭሮቭ እና ሩቢዮ መካከል የስልክ ውይይት ይጠበቃል።

◻️ በላቭሮቭ-ሩቢዮ የመገናኛ ቦታ ዙሪያ ስምምነት አልተደረሰም፤ ጉዳዩ አሁንም እየታየ ነው።

◻️ ከአሜሪካ ጋር በተለያዩ መስመሮች የሚደረጉ ግንኙነቶች ያለማቋረጥ ቀጥለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍62
የናይጄሪያ ጦር በነዳጅ ስርቆት የተሠማሩ 28 ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል፤ አራት ሕገ-ወጥ የማጣሪያ ጣቢያዎችን ዘጋ

🇳🇬🛢 በነዳጅ የበለጸገው የናይጀር ዴልታ ክልል ውስጥ ባካሄደው የሁለት ሳምንት ሰፊ ዘመቻ፤ ከ290 ሺ ሊትር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኙ የነዳጅ ምርቶችን እንደወረሰ የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት አስታውቋል።

ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 9 በተካሄደው የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ የተሰረቀ ድፍድፍ ነዳጅ እና የተጣሩ ምርቶችን በማዘዋወር ላይ የተሳተፉ በርካታ መርከቦችንና የጭነት መኪናዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል ሲሉ የ6ኛው የጦር ሠራዊት ክፍል ተጠባባቂ የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል ዳንጁማ ዮናስ ዳንጁማ ገልፀዋል።

👉 ወታደራዊ ባለሥልጣናት የሠራዊቱን ስኬት አሞካሽተው፤ በናይጄሪያ ደቡባዊ ክልሎች ከድፍድፍ ነዳጅ ስርቆት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን ለመዋጋት እየተደረገ ያለው ጥረት ጥብቅ ክትትል እንደሚያስፈልገው አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5👏1
2025/10/23 02:23:52
Back to Top
HTML Embed Code: