Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇺🇬 ኡጋንዳ ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ቀን ጥር 7 እንዲሆን ወሰነች

በቀጣዩ ምርጫ ለተጨማሪ የሥልጣን ዘመን የሚወዳደሩትና ከ1978 ጀምሮ ሥልጣን ላይ የሚገኙት የ80 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዩሪ ሙሴቬኒ ያለፉትን ምርጫዎች አጭበርብረዋል በሚል ክስ ካቀረቡባቸው የ43 ዓመቱ ሙዚቀኛ እና ፖለቲከኛ ቦቢ ዋይን ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ በተቃዋሚው የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጎታል፡፡

🗳 ስድስት ሌሎች እጩዎችም በውድድሩ ውስጥ የሚሳተፉበት ሲሆን ኡጋንዳውያን ፕሬዝዳንቱን እና የፓርላማ አባላትን ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ናቸው።

የሙሴቬኒ ደጋፊዎች ለሀገሪቱ መረጋጋትና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ሲገልጹ፤ ተቃዋሚዎች ግን ጭቆናን፣ ሙስናን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይጠቅሳሉ።

📈 መንግሥት በሚቀጥለው ዓመት የሚጀመረው የድፍድፍ ነዳጅ ምርት ወደ ውጭ በመላክ የሀገሪቱን የዕድገት ምጣኔ እንደሚያሳድግ ይጠብቃል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6😁1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጋዛ ስምምነት ሂደት ከተጠበቀው በላይ  እየሄደ ነው - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት

ሁሉም ሀገራት ከድህረ ጦርነቱ በኋላ ጋዛን መልሶ ለመገንባት እገዛ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ጄ.ዲ. ቫንስ የእስራኤል-ሀማስ ስምምነት ሁለተኛ ምዕራፍ ውይይትን ለመጀመር እስራኤል ሲደርሱ
በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

"ይህ የገንዘብ ድጋፍ፣ የመልሶ ግንባታ እርዳታ ወይም የዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ሊሆን ይችላል፤ የሰላም ሂደቱን አፈጻጸም እና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ከተለያዩ አካላት ጋር መነጋገር" ሲሉም አክለዋል።


👉 የትራምፕ ልጅ ባለቤት ጃሬድ ኩሽነር እና የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ሰኞ ዕለት እስራኤል ደርሰዋል። ጉብኝታቸው መስከረም 30 ተግባራዊ የሆነው የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሷል አየተባለ ባለበት ወቅት የመጣ ነው።

እሁድ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ሀማስ በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ተኩስ በመክፈት የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል ሲል ከሷል። የእስራኤል ጦር በአጸፋው በጋዛ የሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ የሀማስ ኢላማዎችን አጥቅቷል።

ℹ️ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የግብፅ ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ፣ የኳታር አሚር አል ታኒ እና የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን ጥቅምት 3 ቀን ተፈራርመዋል። በዚህም ሀማስ 20 ታጋቾችን እንዲለቅ እና እስራኤልም ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንድትፈታ ሆኗል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍8👎54🕊2👏1
የ92 ዓመቱ ፖል ቢያ የካሜሩንን ምርጫ ለስምንተኛ ጊዜ አሸነፉ

🇨🇲🗳 የወቅቱ ፕሬዝዳንት ምርጫውን 53.66% ድምጽ በማግኘት እንዳሸነፉ ለሕገ-መንግሥት ጉዳዮች ምክር ቤት የቀረበው ይፋዊ ውጤት አሳይቷል።

የቅርብ ተቀናቃኛቸው ኢሳ ቲቺሮማ ባካሪ በ18 በመቶ ነጥብ ርቀው 35% ድምጽ አግኝተዋል።

👉 ስምንተኛ የሥልጣን ዘመናቸው የ43 ዓመት ፕሬዝዳንትነታቸውን ያራዘመ ሆኗል።

ሕገ-መንግሥታዊ ምክር ቤቱ በመጪዎቹ ቀናት የመጨረሻውን ውጤት በይፋ ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🤣36😁2111😢5👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📹 “ግዜዬን ማባከን አልፈልግም” - ትራምፕ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በቡዳፔስት ስለሚደረገው የዋሽንግተን እና ሞስኮ ውይይት ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱ ተናግረዋል፡፡

በሁለት ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔያቸውን እንድሚያሳውቁ ገልፀዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5🥰5😁54
🇰🇪🇸🇳 ኬንያ እና ሴኔጋል ታሪካዊ ከቪዛ-ነጻ የጉዞ ስምምነት ተፈራረሙ

ስምምነቱን ተከትሎ የሁለቱም ሀገራት ዜጎች እስከ 90 ቀናት ድረስ ያለቪዛ መጓዝ ይችላሉ። የዲፕሎማቲክ እና መደበኛ ፓስፖርት ያላቸው ሰዎች ያለቪዛ ወደ የትኛውም ሀገር መግባት፣ መቆየት እና መሸጋገር ይችላሉ።

ፕሬዝዳንት ሩቶ የትብብሩን ሰፋ ያለ ራዕይ በንግግራቸው አጽንኦት ሰጥተውታል፦

“በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት በሰላም፣ በፀጥታ፣ በኃይል፣ በንግድ እና በውጭ ጉዳይ ያለንን የጋራ ትብብር አረጋግጠናል። ይህ ስምምነት በሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር ያጠናክራል እንዲሁም ቱሪዝምንና ንግድን ያሳድጋል” ብለዋል።


🤝 ከቪዛ ስምምነቱ ባሻገር መሪዎቹ የንግድ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ፣ የትራንስፖርት እና ዲጂታል መሠረተ ልማቶችን ለማሳደግ እንዲሁም ኬንያ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጀት በተሰናዳችበት ወቅት በስፖርት ልማት ለመተባበር ቃል ገብተዋል።

🌍 በተጨማሪም ፍትሐዊ ውክልና ለማረጋገጥ እና በዓለም አቀፍ አስተዳደር ውስጥ የአፍሪካ ድምጾች እንዲሰሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማትን ስለማሻሻል ተወያይተዋል።

ፕሬዝዳንት ባሲሩ ፋዬ ጉብኝታቸውን አስመልክቶ በኤክስ ገፃቸው ላይ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦

“ወደ ኬንያ ያደረግኩት ይፋዊ ጉብኝት በእርካታ ተጠናቋል...ይህ ጉብኝት በሴኔጋል እና በኬንያ መካከል ያለውን ወንድማዊ የወዳጅነት ግንኙነት ለማጠናከር እና ለአዲስ የትብብር አድማስ መንገድ ለመክፈት አስተዋፅዖ አድርጓል።”


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍97
🇳🇬 በናይጄሪያ ነዳጅ የጫነ የታንከር ትራክ ፈንድቶ ከ30 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

በሀገሪቱ ካቻ ከተማ አስተዳደር ኤሳ በሚባል አከባቢ በደረሰው አደጋ ቢያንስ 35 ሰዎች ሲሞቱ 46 ሌሎች ቆስለዋል።

ፍንዳታው የተከሰተው ነዋሪዎች መሬት ላይ ከወደቀው ታንከር ነዳጅ ለማውጣት ሲሞክሩ እንደሆነ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ዘግበዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😱43🕊2
ሩሲያ ዛፖሮዥዬ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን ከኪዬቭ ጥቃት ለመጠበቅ የዓለም አቀፉን የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እርዳታ ጠየቀች

ሞስኮ የኒውክሌር ማመንጫውን የውጭ ኃይል አቅርቦት ወደነበረበት ለመመለስ የተኩስ አቁም እንዲመቻች ድርጅቱን መጠየቋን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለስፑትኒክ አስታውቋል።

👉🏽 አስቸጋሪ እና ፈታኛ ምክክር ከተደረገ በኋላ ይህን ለማድረግ ከዩክሬን የጸጥታ ዋስትና መገኘቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

🏭 የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው በዩኒቶች ብዛትና በተገጠመለት አቅም በአውሮፓ ትልቁ ሲሆን እያንዳንዳቸው አንድ ጊጋዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው ስድስት ዩኒቶች አሉት።

❗️በጥቅምት 2014 የዛፖሮዥዬ ክልል እና የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው የሩሲያ አካል መሆን ችለዋል። በዩክሬን ጥቃት በተደጋጋሚ ኢላማ የሚደረገው የኃይል ማመንጫው፤ በቅርቡም ጉዳት ደርሶበት በአቅራቢያው ወደምትገኘው ከተማ የሚተላለፈው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጧል ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8🤣1
🌍 አፍሪካ ዘላቂ ልማት እንድታሳካ ፖለቲካዊ ሉዓላዊነቷን ልታረጋግጥ ይገባል - ምሁር

📌 አህጉሪቱ ወጥ የሆነ የእድገት አቅጣጫ ሊኖራት እንደሚገባም በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ፍራፊስ ሃይሌ (ዶ/ር) ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡

💬 “ፖለቲካዊ ሉዓላዊንት ካለን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ እንችላለን። የሚጠበቅብን ያልተቆራረጠ፣ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማይቆም ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪያዊ እድገት እንዲኖረን ማድረግ ነው። አረንጓዴ ቴክኖሎጂ፣ ሰርኩላር ኢኮኖሚ ላይ መሥራት ከቻልን ኢንዱስትሪና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነታችንን ማስጠበቅ የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም። ይሄን እንደ ራዕይ መያዝ አለብን።”


ሲያክሉም ኢኮኖሚን ዘርፈ ብዙ ማድረግ ከጥገኝነት የተላቀቀ ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደሚያስችል አንስተዋል፡፡

💬 “ሌላኛው በተለይ ግብርና ላይ ጥገኛ ከመሆን ኢኮኖሚውን ወደ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቴክኖሎጂ ሰፋ ማድረግ፤ ይሄ ሁሉ ደግሞ አንድ ላይ ሲደመር ከዓለም ገበያ መዋዠቅ ይጠብቀናል፤ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት ያስችለናል” ብለዋል።


በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6👍3
🇺🇬 ኡጋንዳ ውስጥ በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ የ63 ሰዎች ህይወት አለፈ

📍ሁለት አውቶብሶችና አራት መኪናዎች ላይ የደረሰው አደጋ፤ ረቡዕ ንጋት ዋና ከተማዋን ካምፓላን ከጉሉ ጋር በሚያገናኘው አውራ ጎዳና ላይ እንደተከሰተ ተገልጿል።

👉 ፖሊስ አሳዛኙን ክስተት አስመልክቶ በሰጠው ማብራሪያ፤ አደጋው የአንዱ አውቶቡስ ሹፌር የጭነት መኪናን ለመቅደም ሲሞክር እንደደረሰ ጠቁሟል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ በተቃራኒ መስመር የነበረ ሌላ አውቶቡስም ተመሳሳይ የመቅደም ሙከራ ሲያደርግ እንደነበር አመልክቷል።

አውቶቡሶች ፊት ለፊት ተጋጭተዋል፡፡ የአንደኛው አውቶብስ አሽከርካሪ ግጭቱን ለማስወገድ ያደረገው እንቅስቃሴ በአቅራቢያ የነበሩ መኪኖች ቁጥጥር እንዲያጡ እና ለበርካታ ግዜ እንዲገለባበጡ አድርጓል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😢114
2025/10/27 15:18:45
Back to Top
HTML Embed Code: