Telegram Web Link
የለውጥ ዋጋ: ዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋምና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
The Rising South
🇪🇹💰|#TheRisingSouth|የለውጥ ዋጋ: ዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋምና ኢትዮጵያ

📻 በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የአለምዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍን) እና የኢትዮጵያን ግንኙነት፣ የኢኮኖሚ እድገት ዋሰትና ይሆን ወይስ የዕዳ ወጥመድ የሚለውን እንመረምራለን። ለዚህም ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ክቡር ገና እና በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ጋብዘናቸዋል፡፡

እንደ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት (FDI) እና የወጪ ንግዳችን መጠን መጨመር ያሉ ትክክለኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጮች እስካልተፈጠሩ ድረስ፣ የውጭ ምንዛሪ ችግር ተፈቷል ልንል አንችልም። ሲሉ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ክቡር ገና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡


ኢትዮጵያ የለውጥ ዉጥኗን ለማሳካት ምን ማድረግ አለባት ?

ይህንን [በብድር የተገኘ] ገንዘብ በአገልግሎት ዘርፍ ላይ ማባከን አይገባም። [...]የኢኮኖሚውን ምርታማነትና የውጪ ንግድ አቅም ለማሳደግ በማኑፋክቸሪንግ እና በግብርና ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይገባል። ሲሉ በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡


🔊 ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡፡

⚡️ከቴሌግራም  ሳይወጡ ውይይቱን ያዳምጡ

⚡️
በድረ ገጻችን

👉
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast Addict Spotify
6👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሩሲያ ስትራቴጂካዊ የቱ-95ኤምኤስ ሚሳኤል ተሸካሚዎች በጃፓን ባሕር ገለልተኛ ውኆች ላይ የታቀደ በረራ ማካሄዳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

የውጭ ተዋጊ ጄቶችም በበረራ መስመሩ የተለያዩ ነጥቦች ላይ ተሸካሚዎቹን አጅበዋቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏142
🇬🇭 ጋና በመላ አገሪቱ የሚገኙ የውሃ አካላትን ለመደገፍ 300 ማዕድን ማውጫ ፈቃዶችን ሰረዘች

የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ኢማኑኤል ኮፊ-አርማህ ቧህ፣ በአክራ በተካሄደ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት፤ ይህ ውሳኔ በሕገ-ወጥ ማዕድን ማውጣት የተጎዱ ደኖችን እና የውሃ ክምችቶችን ወደ ነበሩበት ከመመለስ የመንግሥት ሰፊ ዕቅድ ጋር የሚጣጣም ነው።

ብዙ ቁጥር ያላቸው ወንዞችና ጅረቶች እንዲሁም የውሃ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ዋና የውሃ ምንጮች ተበክለዋል፤ ይህም በዝናባማ ወቅት አልፎ አልፎ የውሃ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲዘጉ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

ቧህ ሚኒስቴሩ ይህን ቀውስ ለመፍታት የተሟላ ስትራቴጂ ተግባራዊ ማድረጉን የገለጹ ሲሆን ስትራቴጂው የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦

🟠 የአካባቢ ጥበቃ ደንቦችን ማስፈጸም፣

🟠 የችግኝ ተከላ ተነሳሽነቶችን ማስተዋወቅ፤

🟠 ለቁጥጥር እና ለአመራር ቴክኖሎጂን መጠቀም፤

🟠 ህዝብን ማስተማር እና ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ እንዲሁም

🟠 የማዕድን ዘርፉን ማሻሻል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4👏2🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇺🇸 እስራኤል ዌስት ባንክን ጠቅልላ አትይዝም ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮመሰል እርምጃዎች "አጠቃላይ የጋዛ የሰላም ሂደትን አደጋ ላይ ይጥላል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል      
                            
በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5👎5🤔2👏1
የመጀመሪያው የብሪክስ የወይን ጠጅ ጉባኤ በሩሲያ የወይን ፎረም ላይ ይካሄዳል - የሩሲያ የወይን ጠጅ አምራቾች ማኅበር

ጉባኤው በብሪክስ አገራት ውስጥ ባሉ የወይን ጠጅ አምራቾች፣ የወይን ተክል አብቃዮች እና የወይን ቱሪዝም ዘርፍ ተወካዮች መካከል ውጤታማ የሆነ ከአገራት ትብብር ልማት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን እንደሚወያይ የሩሲያ የወይን ተክል አብቃዮችና ወይን ጠጅ አምራቾች ማኅበር አስታውቋል።

🍷 እንደ ማኅበሩ፣ የብሪክስ አባል አገራት የወይን ጠጅ አምራቾች እና ነጋዴዎች ህዳር 2 በሞስኮ ይሰበሰባሉ።

ሩሲያ በወይን ጠጅ ምርት ዕድገት ምጣኔ በዓለም ላይ ካሉ ሦስት ቀዳሚ አገራት መካከል አንዷ መሆኗ የተጠቀሰ ሲሆን፤ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የወይን ጠጅ ኢንዱስትሪ ዓለም አቀፍ ትብብር በብሪክስ አገራት ውስጥ በንቃት እያደገ ነው፤ ከእነዚህም አገራት ውስጥ ብዙዎቹ በወይን ጠጅ ገበያ ውስጥ አዎንታዊ ተለዋዋጭነት እያሳዩ ነው።

ማኅበሩ አፅንኦት ሰጥቶ እንደገለጸው፣ "በሩሲያ የወይን መድረክ ላይ የብሔራዊ ወይን ጠጅ አምራቾች ማኅበራት ተወካዮች እና የሩሲያ መንግሥታዊ ኤጀንሲዎች ስብሰባ ምስጋና ይግባውና፣ እ.ኤ.አ. በ2024 በሩሲያ የወይን መድረክ ላይ የቀረበው በብሪክስ አገራት የወይን ጠጅ አምራቾች እና ነጋዴዎች መካከል የትብብር ጥያቄ ቅርፅ እየያዘ መጥቷል"


በእንግሊዘኛ ያንብቡ


 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
16😁3
🇰🇪 ኬንያ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ዕውቀትና አቅም ለማሳደግ አዲስ ፈንድ አስጀመረች

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንዳስታወቁት፣ መንግሥት የንግድ ሥራ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ለመርዳት በመላ ኬንያ ለሚገኙ 600 ሺህ ሴቶች  ሥልጠና ይሰጣል።

ይህ ፕሮግራም የሚካሄደው "የመንግሥት ግዥ ዕድል ተደራሽነት" በሚለው ማዕቀፍ ውስጥ ነው። ይህ ማዕቀፍ ሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ የጤና ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በመንግሥት ግዥ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለመጨመር የተወሰነ የመንግሥት ኮንትራቶችን ድርሻ ለእነርሱ መመደብ የሚያስችል ነው።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🥰51
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇷🇺 🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ በሶቪዬት ድጋፍ በተቀጣጠለው ነፃነት የመጣውን የሰላምና የነጻነት ጉዞዋን ለማስቀጠል ትፈልጋለች - የኤኤንሲ ግምጃ ቤት ኃላፊ

የደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ግምጃ ቤት ኃላፊ ዶ/ር ግዌን ራሞክጎፓ፣ በደቡባዊ አፍሪካ ነጻነት ውስጥ የሶቪዬት እና የሩሲያ ሚናን በሚመለከት ከተዘጋጀ ዐውደ ርዕይ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገሩት፣ ለነፃነት የተደረገው ትግል በተናጠል  መንገድ አልተካሄደም። ዛሬ የሚደረገው የሰላምና ብልጽግና ፍለጋም እንዲሁ በተናጠል መልኩ መሆን የለበትም።

ዶ/ር ግዌን ራሞክጎፓ በኤኤንሲ እና አጋሮቹ በሆኑት በሶቭዬት ሕብረት፣ ቻይና፣ ኩባ እና ሌሎች መካከል በነበረው ታሪካዊ ትስስር ላይ አስተያየታቸውን አጋርተው የሚከተለውን አጽንዖት ሰጥተዋል፦

“ለሰላምና ለፍትሕ በሚደረገው ትግል ትብብራችንንና አጋርነታችንን የፈጠርን እኛ፤ ሰላምን መጠበቃችንን እና... ለዓለም ሕዝቦች የጋራ ብልጽግናን በጋራ ማስቀጠላችንን ለማረጋገጥ አሁንም ቢሆን እነዚያን ትብብሮች መፍጠር አለብን።”


አክለውም ወጣት ደቡብ አፍሪካውያን ከታሪክ ጥንካሬ እንዲያገኙ አሳስበዋል፦

“ታሪክ በጣም አስፈላጊ ነው... ስለዚህም ግጭቶችን ምን እንደፈጠራቸው፣ ግጭቶቹን ምን እንዳነሳሳቸው እና እነዚያን ፈተናዎች ተሻግረን ሰላምን እንዴት መፍጠር እንደቻልን ትምህርት እንድንወስድ ይረዳናል።”


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6🥰1
ሩሲያ ለግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ቦታ የማብለያ አስረከበች - ሮሳቶም

“የኒውክሌር ማብለያ (ሬአክተር) ገጠማ በመጪው ሕዳር ወር መጀመሪያ ላይ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ ቡድኖቻችንም የፕሮጀክቱን ቁልፍ ምዕራፍ ለማሳካት ሳይሰለቹ እየሠሩ ነው” ሲሉ የግብፅ የኒውክሌር ኃይል ጣቢያዎች ባለሥልጣን ሊቀመንበር ሸሪፍ ሄልሚ ተናግረዋል።


የሩሲያ ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ እንዳመለከተው፤ የማብለያው ክብደት ከ330 ቶን በላይ ነው።

ፕሮጀክቱ በኩባንያው ንዑስ ድርጅት በሮሳቶም "አውቶሜትድ ኮንትሮል ሲስተምስ" እየተከናወነ ነው።

👉 የኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አራት 1ሺህ 200 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ ቪቪኢአር-1200 ማብለያ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን፣ የሦስተኛ ትውልድ (ጄኔሬሽን III+) የደህንነት መስፈርቶችን ያሟላል። ሮሳቶም የኒውክሌር ነዳጅን ከማቅረብ በተጨማሪ፣ ለመጀመሪያዎቹ አስር ዓመታት ለሚሠሩ ሠራተኞች ሥልጠና በመስጠት እና ለተጠቀሙበት ነዳጅ የማጠራቀሚያ መፍትሄዎችን በማቅረብ ይረዳል ተብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👀114
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
🚨🇷🇺🇺🇸 የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ከሩሲያ ልዩ ፕሬዝዳንታዊ መልዕክተኛ ጋር ዛሬ አሜሪካ ውስጥ እንደሚገናኙ አክሲዮስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል በእንግሊዘኛ ያንብቡ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
የፕሬዝዳንት ፑቲን ልዩ መልዕክተኛ ዲሚትሪቭ በአሜሪካ ድርድር ከመጀመራቸው በፊት የሰጡት መግለጫ ቁልፍ ነጥቦች፤

🟠 ይህ ወደ አሜሪካ ያደርጉት ጉብኝት ከረጅም ጊዜ በፊት ታቅዶ የነበረ ሲሆን በዋሽንግተን በቅርብ ጊዜ በተወሰዱ ወዳጅነት የጎደላቸው እርምጃዎች ምክንያት አልተሰረዘም።

🟠 በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል የኢኮኖሚ ትብብር ሊኖር የሚችልበት አቅም አሁንም አለ፤ ነገር ግን የ የሚሆነው "ሩሲያ ያላትን ጥቅም በአክብሮት ከተያዘ ብቻ" ነው።

🟠 ሩሲያ በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለውን "ማንኛውንም ቀጥተኛ ውይይት" ለማስተጓጎል በአውሮፓ እና በእንግሊዝ "ብዙ ሙከራዎችን" እያስተዋለች ነው። ሩሲያ ከአሜሪካ ወገን ጋር ውይይቱን ትቀጥላለች እና አቋሟን በግልጽ ታሳውቃለች።

🟠 ማዕቀቦች እና ወዳጅነት የጎደላቸው እርምጃዎች የሩሲያን ኢኮኖሚ "በፍፁም አይነኩም"። በተቃራኒው "በአሜሪካ የነዳጅ ማደያዎች ወደ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ይመራሉ"።

🟠 አዳዲስ ማዕቀቦች በመጣሉ ምክንያት የነዳጅ ገበያው ዋጋ "ቀድሞውኑ ጨምሯል እናም መጨመሩን ይቀጥላል።"

🟠 የአሁኑ የአሜሪካ አስተዳደር ለማስረፅ የሚሞክራቸው የባይደን "ሐሰተኛ ትርክቶች" አልሠሩም። አንድ ሰው "ባይደንን መሆን" እና የቀድሞ ባለሥልጣናትን "የከሸፉ" አቀራረቦችን መከተል የለበትም ሲሉ ዲሚትሪየቭ አጽንዖት ሰጥተዋል።

🟠 ዩክሬን "በእንግሊዝ እና በአውሮፓውያን ጥያቄ" ሰላማዊ ውይይትን እያደናቀፈች ነው፤ ድርድሮችን በማዘግየት እና ጉዳዮችን ለመፍታት ፈቃደኝነት እያሳየች አይደለም።

🟠 ዲሚትሪቭ "ከበርካታ የአስተዳደሩ ተወካዮች" ጋር፣ በዝግ በሮች የሚደረጉትን ጨምሮ ብዙ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ። ውይይቱን እንዴት መቀጠል እንደሚቻል ይወያያሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍85🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | የቻይና ዩናን ግዛት ሰማይን አድምቆ የታየው አስደማሚ የቀስተ ደመና ብርሃን

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8🙏3
ማዳጋስካር የአገዛዝ ለውጥን በተመለከተ የሕዝብን ምላሽ ለመለካት የሚያስችል መድረክ አስጀመረች - ዘገባዎች

በውጤቶቹ ላይ በመመሥረት፤ የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ የግምገማ ኮሚሽን ሕዝቡ ለአዲሱ መንግሥት ያለውን አቋም ይቀርጻል።

👉 የማኅበረሰቡ ተወካዮች አስቀድሞ ከሚከተሉት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተዋል

🟠 ከአዲሱ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና፣

🟠 ከጠቅላይ ሚኒስትር ሄሪንትሳላማ ራጃኦናሪቬሎ፣

🟠 የማዳጋስካር ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት (የፓርላማ ታህታይ ምክር ቤት) እና ሴኔት (የፓርላማ የላዕላይ ምክር ቤት) እና

🟠 ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከእንቅስቃሴዎች የተውጣጡ አክቲቪስቶች።

አሁን ላይ ማኅበረሰቡ በማዳጋስካር ስላለው የሥርዓት ለውጥ ፣ ለወደፊት በሚከተለው አቀራረብ ላይ ሪፖርት እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ለማሰባሰብ የነባር ዜጎችን አስተያየት ለመሰብሰብ አስበዋል።

☝️  የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ፣ እንደ አፍሪካ ሕብረት ሁሉ፣ ለመፈንቅለ መንግሥቱ እውቅና አይሰጥም። በተጨማሪም፣ በጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከሥልጣን የተወገዱት አንድሪ ራጆኤሊና ባለፈው ዓመት ነሐሴ 17  የማኅበረሰቡ የዚህ ዓመት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ነበር።

ተልዕኮው በመጪው ሰኞ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
3👎1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ የፈጠራ ሥራዎችን እውን ለማድረግ እርዳታ እና ፈንድ የመጠበቅ ባህልን ማረም አለብን - ኬንያዊት የፈጠራ ባለሙያ

ኖራ ኪማቲ፣ በአፍሪካ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በውስጥ አቅም መሥራት የመቻል እሳቤን በትውልዱ ሥነ-ልቦና ውስጥ ማስረጽ እንደሚገባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች።

ንግግርን ወደ ምልክት ቋንቋ የሚቀይር ሮቦት መሥራቷን የገለፀችው ባለሙያዋ፣ ፈጠራው መስማት ለተሳናቸው ሕፃናት ከፍ ያለ እገዛ እንዳለውም ታነሳለች።

🗣 "ቴክኖሎጂው መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ ሥርዓተ ትምህርቶች ውስጥ እንዲካተቱ ያግዛል።" ብላለች።


📌የአፍሪካ ሕብረት የኢኖቬሽን ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5🙏32
🇭🇺🇷🇴 የማጣሪያ ፋብሪካ ፍንዳታዎች ሃንጋሪ እና ሮማኒያ ከሩሲያ ጋር ላላቸው ግንኙነት ኔቶ የጣለባቸውን ቅጣት ያሳያል

🗣 የጂኦፖለቲካል ተንታኝ የሆኑት ኮሜ ካርፔንቲየር ዴ ጉርደን፣ በሃንጋሪ እና ሮማኒያ በሚገኙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ላይ በቅርቡ ስለደረሱት ፍንዳታዎች ለስፑትኒክ ሲናገሩ፤ “በተለያዩ የአውሮፓ ክፍሎች ውስጥ በጣም ንቁ የሆነ የዩክሬን የጥፋት መረብ አለ” ብለዋል።

🟠 ፍንዳታዎቹ አውሮፓ በኔቶ የሚራገበውን የአሜሪካን አጀንዳ እየፈፀመች በመሆኑ የሃንጋሪን እና የሮማኒያን “ከሩሲያ ጋር ያለውን የኃይል ግንኙነት” ለማስቆም የተደረገ የአውሮፓ “ሆን ተብሎ የተፈፀመ የማፍረስ ተግባር” አካል ሊሆኑ እንደሚችሉ አልገለጹም።

🟠 ተንታኙ ምዕራባውያን የስትራቴጂክ ዓላማዎቻቸውን በሕገወጥ መንገድ እንዲያሳኩ የሚረዳ “ሰፋ ያለ አጀንዳ” ሊኖራቸው እንደሚችል ጠቁመዋል።

💬 ጉርዶን አጽንዖት ሰጥተው ሲናገሩ፣ “ዓላማዎቹ በአንድ በኩል ሩሲያ ገቢ እንዳታገኝ በማድረግ የዩክሬን ግጭት ‘እንዲያልቅ እና ምናልባትም ለምዕራባውያን ጥያቄዎች እንድትገዛ’ ማስገደድ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአውሮፓን መከላከያ ተጋላጭ ማድረግ ነው፤ ይህም በአሜሪካ፣ በእንግሊዝ እና በኔቶ በሚመራው "አንግሎ-ሳክሰን" ፍላጎት ላይ የበለጠ ጥገኛ ያደርገዋል” ብለዋል።


🟠 በሌላ በኩል፣ ፍንዳታዎቹ “ሃንጋሪን እና ሮማኒያን ለወደፊት ስለሚኖሩ ባላጋራነርት የከፋ መዘዞች ለማስጠንቀቅ” የታሰበ የኔቶ ቅጣት ሊሆን ይችላል ብለዋል።

💬  “ሃንጋሪ ከሩሲያ ጋር ስላላት አጠቃላይ ግንኙነት፣ በተለይም ከሞስኮ ስለምታገኘው የኃይል አቅርቦት ከአውሮፓ ሕብረት ጋር በግልጽ ጠብ ውስጥ ናት” ያሉት ጉርደን፣ ሮማኒያ ደግሞ “ከአውሮፓ ሕብረት የበለጠ ነፃነትን ለማግኘት ወይም ምናልባትም ከእሱ ለመውጣት እና ከሩሲያ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራት የሚፈልግ ጠንካራ የሕዝባዊ ኃይል አላት” ብለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11😡1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | የሩሲያ መዘምራን 'የጌታ ፀሎት' የተሰኘውን ዝማሬ በስዋሂሊ በመዘመር መነጋገሪያ ሆነዋል

🌍🎶 በሴንት ፒተርስበርግ የሚገኘው የማይኒንግ ዩኒቨርሲቲ መዘምራን ያሳዩት አስደናቂ ሕብረ-ዝማሬ በስፋት ተሰራጭቷል። “ባባ የቱ” ወይም የ“ጌታ ጸሎት” በስዋሂሊ በአፍሪካዊ ብቸኛ አቀንቃኝ ታጅቦ ያቀረቡት ዝማሬ በሦስት ቀናት ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዕይታዎችን አግኝቷል።

“የእኛ ልዩ ተሳትፎ በስዋሂሊ ቋንቋ ማቅረባችን ነው” ሲል የመዘምራን ቡድኑ ኦንላይን ላይ አጋርቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
18🙏5👍2😁1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📹በሩሲያ የሚገኘው የኡጋንዳ ኤምባሲ  የሀገሪቱን 63ኛ የነጻነት ቀን አከበረ

👆ምስሉን ያጋራው በስፍራው  የተገኘው  የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ነው

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5👍1
አራት የአፍሪካ አገራት ከዓለም አቀፉ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር "ግራጫ" ዝርዝር ውስጥ ተሰረዙ

በፓሪስ የሚገኘው የፋይናንስ እርምጃ ግብረ ኃይል (ኤፍ.ኤ.ቲ.ኤ) የአፍሪካን የፋይናንስ መልካም ስም ከፍ የሚያደርግ ትልቅ እርምጃ በመውስድ ቡርኪና ፋሶ፣ ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካን ከ"ግራጫው ዝርዝር" በይፋ አስወግዷቸዋል። ይህ ዝርዝር ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርንና አሸባሪዎችን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎችን መዋጋት ላይ ድክመት ያለባቸውን እና ከፍተኛ ክትትል የሚደረግባቸውን አገሮች የሚያመለክት ነው።

🌍 ለአራት የተሃድሶ መሪዎች አዲስ ምዕራፍ

🇧🇫 ቡርኪና ፋሶ

ቡርኪና ፋሶ እ.ኤ.አ. ከ2021 ጀምሮ ዝርዝሩ ውስጥ ከገባች በኋላ ፀረ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርንና አሸባሪዎችን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎችን የመዋጋት ሥርዓቷን በከፍተኛ መጠን አሻሽላለች። አገሪቱ የፋይናንስ ተቋማትን ቁጥጥር ከፍ አድርጋለች፤ የባለቤትነት ግልጽነትን ጨምራለች፤ እንዲሁም የሕግ አስከባሪና የፍትሕ አቅሟንም አጠናክራለች።

በተጨማሪም ለሕግ ጥሰቶች የሚጣሉ ቅጣቶችን ይበልጥ በማጥበቅ በተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅት አሻሽላለች።

🇲🇿 ሞዛምቢክ

ሞዛምቢክ እ.ኤ.አ በ2022 ዝርዝሩ ውስጥ ከተካተተች በኋላ፣ የአደጋ ተጋላጮችን በመለየት በእነርሱ ላይ የተመሠረተ ቁጥጥር፣ የፋይናንስ መረጃ ልውውጥ እና የባለቤትነት መረጃ አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አሳይታለች።

ባለሥልጣናቱ የተቀናጀ የሽብርተኝነት ፋይናንስ ስጋት ግምገማ በማካሄድ ብሔራዊ የሽብርተኝነት ፋይናንስ መከላከል ስትራቴጂን መተግበር ጀምረዋል፤ ይህም ለፋይናንስ ደህንነት ጠንካራ ቁርጠኝነትን ያሳያል።

🇳🇬 ናይጄሪያ

እ.ኤ.አ. በ2023 ዝርዝሩ ውስጥ የተካተተችው ናይጄሪያ በፋይናንስ ሥርዓቷ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን በፍጥነት ዘግታለች። ቁልፍ ለውጦቹም የብሔራዊ ስጋት ግምገማዎችን ማዘመን፣ የፋይናንስና ፋይናንስ ነክ ያልሆኑ ዘርፎችን በጥብቅ መቆጣጠር፣ እንዲሁም የባለቤትነት ደንቦችን አፈጻጸም ማጠናከርን ያካትታሉ።

ባለሥልጣናቱ ሕጋዊ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተግባራትን በመጠበቅ፤ የሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርንና አሸባሪዎችን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎች ምርመራዎችንና ክሶችን ጨምረዋል።

🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ

ደቡብ አፍሪካ ከዝርዝሩ መሰረዟ እ.ኤ.አ በ2023 ከተደረጉት ጥልቅ ተሃድሶዎች በኋላ የተገኘ ትልቅ የፖሊሲ ስኬት ነው። አገሪቱ ውስብስብ የፋይናንስ ወንጀሎችን በመመርመር ፣ በመክሰስ፣ ውጤታማ ቅጣቶችን በመጣል፣ እንዲሁም በሽብርተኝነት ላይ ያነጣጠሩ የፋይናንስ እርምጃዎችን በማስፈጸም ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች።

የተቋማት ቅንጅት መጠናከርና የባለቤትነት ግልጽነት መሻሻልም ለስኬቷ ማዕከላዊ ነበሩ።

📈 በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የታየ እድገት

ኤፍ.ኤ.ቲ.ኤ ከሥርዓቱ ጋር ለመጣጣም እየሠሩ ባሉ ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገሮች ላይ የታየውን ቀጣይ እድገትም እውቅና ሰጥቷል፡-

🇩🇿 አልጄሪያ: በአደጋ ላይ የተመሠረተ ቁጥጥር፣ የባለቤትነት ግልጽነት እና አሸባሪዎችን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀል ቁጥጥርን ማሻሻል ላይ እየገፋች ነው።

🇦🇴 አንጎላ: የስጋት ግንዛቤን፣ የባንክ ያልሆኑ ዘርፎችን ቁጥጥር፣ እንዲሁም ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርንና አሸባሪዎችን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎች ምርመራዎችን ማጠናከር ላይ ትገኛለች።

🇨🇲 ካሜሩን: በተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅት በማሻሻልና ቁጥጥርንና የንብረት ወረሳ ዘዴዎችን አጠናክራለች።

🇨🇮 ኮት ዲቯር: የፋይናንስ መረጃ አጠቃቀምን በመጨመርና የፋይናንስ ወንጀሎችን ከአደጋ ግምገማዋ ጋር በሚጣጣም መልኩ የሕግ ቁጥጥር እያደረገች ነው።

🇨🇩 ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፤ የሽብርተኝነት ፋይናንስ ምርመራዎችን በማሳደግ እና በአደጋ ላይ የተመሠረተ ቁጥጥርን በማጠናከር ላይ።

🇰🇪 ኬንያ: በአደጋ ስጋት ላይ የተመሠረተ ቁጥጥር፣ የባለቤትነት መረጃ አሰባሰብ እና በየተቋማት መካከል ባለው የሽብርተኝነት ፋይናንስ ትብብር ላይ እድገት እያደረገች ነው።

🇳🇦 ናሚቢያ: የአፈጻጸም አቅምን በማጎልበትና በፋይናንስ መረጃና በሕግ አስከባሪ አካላት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ላይ።

🇸🇸 ደቡብ ሱዳን: የፋይናንስ ቁጥጥር የቁጥጥር ማዕቀፎችንና አቅምን እየገነባች ነው፤ ሆኖም ተጨማሪ እድገት ያስፈልጋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
8👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ልማትን የመደገፍ አቅም በአግባቡ መጠቀም ይገባል - ባለሙያ

ኬንያዊት የፈጠራ ባለሙያ ሊኔት ካሞቶ፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ የአፍሪካን ዕድገት እና የሕዝቦቿን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የላቀ እገዛ እንዳላቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጻለች።

🗣 "ለምሳሌ በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ለአርሶ አደሮች የአፈር እርጥበት እና ሌሎች መረጃዎችን ማድረስ ትችላለህ። ከልክ ያለፈ ዓሣ የማጥመድ ሁኔታን ለመከላከልም የመረጃ አቅርቦት ላይ የሚሠሩ ቴክኖሎጂዎች አለ።" ስትል አስረድታለች።


የፈጠራ ባለሙያዋ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት አጠቃቀም ላይ መታረም አለባቸው ያለቻቸውን ነጥቦችም ጠቅሳለች።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍4
🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢነርጂ እና መስኖ አገልግሎት የሚውሉ መካከለኛ እና ከፍተኛ ግድቦች እንደሚመረቁ አስታወቁ

የኢትዮጵያው መሪ ፕሮጀክቶቹ በሚቀጥሉት ወራት እንደሚመረቁ፣ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማን አስመልክቶ በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ገልፀዋል።

ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ በርካታ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ያሉት በጠንካራ የክትትል እና የቁጥጥር ሥራ መሆኑን በንግግራቸው አመላክተዋል።


በቀጣይ ለመመረቅ ወረፋ የሚጠብቁ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ጠቁመው፤ "እንልፋ እንትጋ ከልፋታችን ውጪ የሚለወጥ ሀገር አይኖርም የሚለው እሳቤ ለዚህ ውጤት በእጅጉ አግዟል፡፡" ማለታቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍117😁3👎2👏1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
💀 የአሜሪካ መንግሥት በይፋ ተዘጋ 💬 ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ "በመዘጋቱ ብዙ መልካም ነገሮች ሊመጡ ይችላሉ። እኛ ያልፈለግናቸውን ብዙ ነገሮችን ማስወገድ እንችላለን። እነሱም የዲሞክራት ነገሮች ይሆናሉ" ብለዋል። ኮንግረስ ለአዲሱ የሒሳብ ዓመት በጀት ማጽደቅ አልቻለም። 💵   በውጤቱም የፌደራል ኤጀንሲዎች ገንዘብ ማውጣት አይችሉም፤ የመንግሥት ሠራተኞች ያለ ክፍያ ፈቃድ ላይ ይደረጋሉ እና የጤና…
🔍  የአሜሪካ መንግሥት መዘጋት ለ42 ሚሊዮን አሜሪካውያን የምግብ እርዳታን ሊያቋርጥ ነው - ሪፖርት

የአሜሪካ የግብርና ሚኒስቴር ማስታወሻ እንደሚያሳየው፣ አሁን ባለው የመንግሥት መዘጋት ወቅት የድንገተኛ ጊዜ ገንዘቦች  ለምግብ አቅርቦት እገዛ ጥቅሞች አይውሉም፤ ይህም ከጥቅምት 1 ጀምሮ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰጠውን የምግብ እርዳታ አደጋ ላይ ይጥላል ሲል አክሲዮስ ዘግቧል።

ሚኒስቴሩ፣ የተመደበለት ገንዘብ ለተፈጥሮ አደጋዎች የተያዘ እንደሆነ በመግለጽ፣ ግዛቶች ወጪዎቹን ቢሸፍኑም እንኳ ገንዘባቸው ተመላሽ እንደማይደረግቸም አብራርቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
3🤔2👎1
🌍 አፍሪካ ፣ ልዩ ምርጫ ይህን የመልዕክት መለዋወጫ 'ፎልደር' ከአህጉሪቱ አዳዲስ ዜናዎች ከሚገኙበት ቻናሎች ላይ ይጨምሩት ⤵️

👉👉 https://www.tg-me.com/addlist/lwYcxR-tjCBiODBi 👈👈

#social
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥3🙏1
2025/10/27 15:22:19
Back to Top
HTML Embed Code: