መች ነው በቃ የሚልሽ?
እንባ ያዘለው አይንሽ
ፍርሃት ያልበገረው አንቺነትሽ
ድምፅ አልባ የሆነው ጣርሽ
ለፈተና ያልተንበረከከው ጉልበትሽ
መከራ ያጠቆረው ፊትሽ
ብቸኝነት ያከሳው ገላሽ
ማንም ተነስቶ ሊሞግት ሲሞክርሽ
በሴትነትሽ ብቻ ጣት ሲቀሰርብሽ
ዘለፋና ትችት ሲፈራረቅብሽ
ያለ ሚዛናዊነት ፈራጁ በዝቶብሽ
ሃይ ባዩ ጠፋና አለሁኝ የሚልሽ
ፍርደ ገምድሉ በዝቶ ያም ያም ሲያዝብሽ
ኧረ አንቺስ መች ይሆን በቃ ግን የሚልሽ
ተፃፈ ታኅሣሥ ጥር 3/2016
ናትናኤል ኃይሌ
SMC (sante)
C-2
@talentofmedstu
መታሰቢያነቱ ፍትሕ ላጡ እሕቶቻችን
እንባ ያዘለው አይንሽ
ፍርሃት ያልበገረው አንቺነትሽ
ድምፅ አልባ የሆነው ጣርሽ
ለፈተና ያልተንበረከከው ጉልበትሽ
መከራ ያጠቆረው ፊትሽ
ብቸኝነት ያከሳው ገላሽ
ማንም ተነስቶ ሊሞግት ሲሞክርሽ
በሴትነትሽ ብቻ ጣት ሲቀሰርብሽ
ዘለፋና ትችት ሲፈራረቅብሽ
ያለ ሚዛናዊነት ፈራጁ በዝቶብሽ
ሃይ ባዩ ጠፋና አለሁኝ የሚልሽ
ፍርደ ገምድሉ በዝቶ ያም ያም ሲያዝብሽ
ኧረ አንቺስ መች ይሆን በቃ ግን የሚልሽ
ተፃፈ ታኅሣሥ ጥር 3/2016
ናትናኤል ኃይሌ
SMC (sante)
C-2
@talentofmedstu
መታሰቢያነቱ ፍትሕ ላጡ እሕቶቻችን
👍8👏1
አስመሳይ ነሕ በለው!
ማን ነው አቅም ኖሮት ሌላውን የሚተች
እራሱን መርምሮ የሚቀስር ታቶች
ኃጢያት የሌለበት በስራው ሚመፃደቅ
በደለኛ እያለ ሌላውን ሚያሸማቅ
ባልሰራው ወንጀል ንፁውን ሲወነጅል
ጥፋቱን ከልሎ ለመኖር ሲያስመስል
ከጎኑ ያለውን ዞር እያለ ሲያማ
ተንኮልን ሲሸርብ ከክፋት ሲያስማማ
እፍኝት ማይሞላ ተግባርን ሳይኖረው
ያን ይሔን ሲያነሳ አንዱንም ሳይቀረው
ሲያብጠለጥለው ጉድለት እየፈለገ
የሰራውን ነውር በአንተ እየሸሸገ
ለእንደዚ አይነቱስ ጆሮሕን አትስጠው
ያንተን አለም አስስ አስመሳይ ነሕ በለው
ናትናኤል ኃይሌ
SMC C2
ተፃፈ ጥር 8/2016
@talentofmedstu
ማን ነው አቅም ኖሮት ሌላውን የሚተች
እራሱን መርምሮ የሚቀስር ታቶች
ኃጢያት የሌለበት በስራው ሚመፃደቅ
በደለኛ እያለ ሌላውን ሚያሸማቅ
ባልሰራው ወንጀል ንፁውን ሲወነጅል
ጥፋቱን ከልሎ ለመኖር ሲያስመስል
ከጎኑ ያለውን ዞር እያለ ሲያማ
ተንኮልን ሲሸርብ ከክፋት ሲያስማማ
እፍኝት ማይሞላ ተግባርን ሳይኖረው
ያን ይሔን ሲያነሳ አንዱንም ሳይቀረው
ሲያብጠለጥለው ጉድለት እየፈለገ
የሰራውን ነውር በአንተ እየሸሸገ
ለእንደዚ አይነቱስ ጆሮሕን አትስጠው
ያንተን አለም አስስ አስመሳይ ነሕ በለው
ናትናኤል ኃይሌ
SMC C2
ተፃፈ ጥር 8/2016
@talentofmedstu
👍6❤2👏1
https://telegra.ph/%E1%89%B0%E1%89%A0%E1%8B%B5%E1%8B%AC-%E1%8B%AD%E1%89%85%E1%88%AD%E1%89%B3-01-26
@talentofmedstu
@talentofmedstu
Telegraph
ተበድዬ ይቅርታ
ልብ የወለደው ወግ🙃 ብዙ በህይወት ያሉ ነገሮች እስካላጣናቸው ድረስ ትክክለኛ ዋጋቸውን ስለመረዳታችን እጠራጠራለሁ። ለብዙ ጊዜያት ስኖር ሀሳቤ ታፍኖብኝ አያውቅም ነበርና መናገርና መሰማት ምን አይነት እፎይታ እንዳለው ለመረዳት ጊዜ ፈጅቶብኛል፤የደረሰበት ያውቀዋልና ይፍረደኝ። በጣም ጠንካራ የምባል ሴት ባልሆንም ያ የምወደው አባቴ ግን መቼም ቢሆን ለመብቴ እንድቆም በጨዋነት አሳድጎኛልና የሚሳካ መስሎኝ…
👍2🔥1
ማን ነው የተረዳው (ቁ.3)
የረገጥከው መሬት ያለፍከው መከራ
ቀላል አይባልም ኢንዲ የሚወራ
ጦር ካቆሰለው አካሉን ከጎዳው
የውስጥህን ሕመም ማን ነው የተረዳው?
የትላንት መካሪ አለው የምትል ለሰው
አጣሁኝን ማታውቅ ለሁሉ የምትደርሰው
ተረተህ እጅ ብትሰጥ ጊዜ ጣለህና
ወዳጆችህ ራቁ አበደ አሉና
እርግጠኛ ሆነው በእነርሱ ጤንነት
በአንተ መንገዳገድ ስምህን ቀየሩት
በሕመም ላይ ሕመም እየጨማመሩ
ባገኙት አጋጣሚ ሊያጠፉህ መከሩ
አንተ ወንድ እኮ ነህ አያሉ ሲያወኩ
በተሳሳተ እሳቤ ጥላቻን ሲሰብኩ
ፆታ እየመረጡ ምኑም ሳይገባቸው
ስንቱ ከቤት ቀረ ደርሰን ሳንረዳቸው
ሊያበረቱህ ሲቻል ሕመምክን አባሱ
እርግማን አድርገው ሲገፉህ ሲያንኳሱ
ቡቱቶህን አይተው ሊያዩህ ተጠየፉ
ፊታቸውን አጥቁረው ተረማምደው አለፉ
መጨረሻው ይህነው ወንድ ሆኖ መታመም
አዎ...በእኛ ማህበረሰብ የሚረዳህ የለም
እናም ተስፋ አትቁረጥ ፈልግ ራስህን
በሌላ የተኩትን ቀይረው ስምህን
መታሰቢያነቱ በአእምሮ ሕመም ላሉ
ናትናኤል ኃይሌ
SMC C2
@talentofmedstu
የረገጥከው መሬት ያለፍከው መከራ
ቀላል አይባልም ኢንዲ የሚወራ
ጦር ካቆሰለው አካሉን ከጎዳው
የውስጥህን ሕመም ማን ነው የተረዳው?
የትላንት መካሪ አለው የምትል ለሰው
አጣሁኝን ማታውቅ ለሁሉ የምትደርሰው
ተረተህ እጅ ብትሰጥ ጊዜ ጣለህና
ወዳጆችህ ራቁ አበደ አሉና
እርግጠኛ ሆነው በእነርሱ ጤንነት
በአንተ መንገዳገድ ስምህን ቀየሩት
በሕመም ላይ ሕመም እየጨማመሩ
ባገኙት አጋጣሚ ሊያጠፉህ መከሩ
አንተ ወንድ እኮ ነህ አያሉ ሲያወኩ
በተሳሳተ እሳቤ ጥላቻን ሲሰብኩ
ፆታ እየመረጡ ምኑም ሳይገባቸው
ስንቱ ከቤት ቀረ ደርሰን ሳንረዳቸው
ሊያበረቱህ ሲቻል ሕመምክን አባሱ
እርግማን አድርገው ሲገፉህ ሲያንኳሱ
ቡቱቶህን አይተው ሊያዩህ ተጠየፉ
ፊታቸውን አጥቁረው ተረማምደው አለፉ
መጨረሻው ይህነው ወንድ ሆኖ መታመም
አዎ...በእኛ ማህበረሰብ የሚረዳህ የለም
እናም ተስፋ አትቁረጥ ፈልግ ራስህን
በሌላ የተኩትን ቀይረው ስምህን
መታሰቢያነቱ በአእምሮ ሕመም ላሉ
ናትናኤል ኃይሌ
SMC C2
@talentofmedstu
👍5🔥1
ሱዳናዊ ነህ? አለችኝ
ያው ተለማማጅ ሐኪምም አይደለው? ዛሬ ግዳጅ(duty😂) ነበረኝ። በሰንበቱ! ግዳጅ ግዳጅ ነው። በማንኛውም ሰዓት ሥራ ገብተህ መሥራት አለብህ። ሰንበት፣ በዓል፣ ዕረፍት ሚባል ነገር የለውም። ትላንት ፕሮፌሰር አታላይ አለም(Professor of psychiatry) በአንድ መድረክ ሲናገሩ ወደ ጦር ግንባር ግዳጅ ብዙ ጊዜ የሚሄዱት የአጠቃላይ ቀዶ ጥገና ሐኪሞች፣ የአጥንት ቀዶ ጥገና ሐኪሞች፣ እና የድንገተኛ ሕክምና ሐኪሞች ናቸው። ሻቢያ ኢትዮጵያን በሚወርበት ጊዜ ግን በወቅቱ የሐኪም እጥረት ስለነበር የስነ አዕምሮ(Psychiatrists) ሐኪሞችም ከባዶ ይሻላል በሚል ለግዳጅ በሔሊኮፕተር ጭነውን አሥመራ ድረስ ወስደውን ነበር ብለዋል። ስለ ግዳጅ መተንተን አይደለም ዋና ሃሳቤ።
እና ታካሚዎቼን በየክፍላቸው ገብቼ Single intern round (የጤና ባለሞያዎች ይገባችኋል) ካደረኩ በኋላ ወደ መዶለቻችን ስመለስ አንድ የስራ ልብስ ያለበሰች አስታማሚ የምትመስል ሴትዮ ከአንዲት ነርስ ጋር ዶልተው ጠበቁኝ። Staff መሆኗ ነው። የኮሌጃችን ዲን አማካሪ ናት። ከዚያ ዘው ማለቴን አይታ ዶክ "how are you?" አለችኝ እኔም። Hi!, I'm good. And you? አልኳት። ከዚያ "Are you from Sudan?" አለችኝ። ቀለል ያለች ቀልድ ጣል ላርግ ብዬ No, I'm from Uganda አልኳት። አይይ ዩጋንዳ አባባልህ ኢትዮጵያዊ ያስመስልብሃል😂 ና እስቲ 14 ቁጥር ላይ ስላለችው patient ንገረኝ ዘመድ ነገር ናት አለችኝ። ሆ! ከመጀመሪያውኑ እንዴት ኢትዮጵያዊ አልመሰልኩሽም? ስላት "አይ colorህ አይመስልም።" ብላኝ እርፍ። አሁን እውነት ሱዳን ብሔድ ቀዮ እያሉ የዘረኝነት ጥቃት አያደርሱብኝም ብለሽ ነው? ወይም ደግሞ አሜሪካዊ መስያቸው እንደ ሰፈራችን ልጆች ዶላር ዶላር እያሉ ቁም ስቅለን አያወጡትም ብለሽ ነው? ልላት ብዬ ማንነቷን ሳላውቅ አፍ አልካፈትም አልኩና ዋጥ አደረኩ።
ከዚያ የጠየቀችኝን ጥያቄ በቆንጆ የሕክምና ቋንቋ አስረድቼ¡(ግራ አጋብቼ) ላኳት። እርግጠኛ ነኝ አልገባትም። የትኛውም የጤና ባለሞያ 6 ወር ከሕክምናው ዓለም ከራቀ ከዜሮ እንደመጀመር በሉት። ደግ አደረኩ። ጥቁር ኢትዮጵያውያንኮ መኖር አልቻልንም። No more✊ ያስብላልኮ ይኼ።
ደህና እደሩ!
@NK_arts
@talentofmedstu
ያው ተለማማጅ ሐኪምም አይደለው? ዛሬ ግዳጅ(duty😂) ነበረኝ። በሰንበቱ! ግዳጅ ግዳጅ ነው። በማንኛውም ሰዓት ሥራ ገብተህ መሥራት አለብህ። ሰንበት፣ በዓል፣ ዕረፍት ሚባል ነገር የለውም። ትላንት ፕሮፌሰር አታላይ አለም(Professor of psychiatry) በአንድ መድረክ ሲናገሩ ወደ ጦር ግንባር ግዳጅ ብዙ ጊዜ የሚሄዱት የአጠቃላይ ቀዶ ጥገና ሐኪሞች፣ የአጥንት ቀዶ ጥገና ሐኪሞች፣ እና የድንገተኛ ሕክምና ሐኪሞች ናቸው። ሻቢያ ኢትዮጵያን በሚወርበት ጊዜ ግን በወቅቱ የሐኪም እጥረት ስለነበር የስነ አዕምሮ(Psychiatrists) ሐኪሞችም ከባዶ ይሻላል በሚል ለግዳጅ በሔሊኮፕተር ጭነውን አሥመራ ድረስ ወስደውን ነበር ብለዋል። ስለ ግዳጅ መተንተን አይደለም ዋና ሃሳቤ።
እና ታካሚዎቼን በየክፍላቸው ገብቼ Single intern round (የጤና ባለሞያዎች ይገባችኋል) ካደረኩ በኋላ ወደ መዶለቻችን ስመለስ አንድ የስራ ልብስ ያለበሰች አስታማሚ የምትመስል ሴትዮ ከአንዲት ነርስ ጋር ዶልተው ጠበቁኝ። Staff መሆኗ ነው። የኮሌጃችን ዲን አማካሪ ናት። ከዚያ ዘው ማለቴን አይታ ዶክ "how are you?" አለችኝ እኔም። Hi!, I'm good. And you? አልኳት። ከዚያ "Are you from Sudan?" አለችኝ። ቀለል ያለች ቀልድ ጣል ላርግ ብዬ No, I'm from Uganda አልኳት። አይይ ዩጋንዳ አባባልህ ኢትዮጵያዊ ያስመስልብሃል😂 ና እስቲ 14 ቁጥር ላይ ስላለችው patient ንገረኝ ዘመድ ነገር ናት አለችኝ። ሆ! ከመጀመሪያውኑ እንዴት ኢትዮጵያዊ አልመሰልኩሽም? ስላት "አይ colorህ አይመስልም።" ብላኝ እርፍ። አሁን እውነት ሱዳን ብሔድ ቀዮ እያሉ የዘረኝነት ጥቃት አያደርሱብኝም ብለሽ ነው? ወይም ደግሞ አሜሪካዊ መስያቸው እንደ ሰፈራችን ልጆች ዶላር ዶላር እያሉ ቁም ስቅለን አያወጡትም ብለሽ ነው? ልላት ብዬ ማንነቷን ሳላውቅ አፍ አልካፈትም አልኩና ዋጥ አደረኩ።
ከዚያ የጠየቀችኝን ጥያቄ በቆንጆ የሕክምና ቋንቋ አስረድቼ¡(ግራ አጋብቼ) ላኳት። እርግጠኛ ነኝ አልገባትም። የትኛውም የጤና ባለሞያ 6 ወር ከሕክምናው ዓለም ከራቀ ከዜሮ እንደመጀመር በሉት። ደግ አደረኩ። ጥቁር ኢትዮጵያውያንኮ መኖር አልቻልንም። No more✊ ያስብላልኮ ይኼ።
ደህና እደሩ!
@NK_arts
@talentofmedstu
👍12❤6
በልኬ ለክተው በአቅሜ እንደ ሰፉት፣
በቁመቴ አስምረው ልክ እንደ ለቀቁት፣፣
ሰርተው እንዳመጡት እንደ ቅዱ ልብሴ፣
ልክ እንደ ውቡ እና የክቱ ቀሚሴ፣
ያንተን ነፍስ ብቻ ሊለብስ ይሻል ነፍሴ።
✍️smr
AMU C2
@talentofmedstu
በቁመቴ አስምረው ልክ እንደ ለቀቁት፣፣
ሰርተው እንዳመጡት እንደ ቅዱ ልብሴ፣
ልክ እንደ ውቡ እና የክቱ ቀሚሴ፣
ያንተን ነፍስ ብቻ ሊለብስ ይሻል ነፍሴ።
✍️smr
AMU C2
@talentofmedstu
❤10👏1
መልኳን አየሁና ቀርቤ ባወራት
ስባ አስቀረችኝ ይቺንስ ምን ይሏት
አይቼ ሳልጨርስ ከእግር እስከራሷ
ውበቷን ሳልጨረስ ፈዘዝኩ በጥርሷ
ፈገግታዋ አስቀረኝ ሌላውን እንዳላይ
የኔ መልከመልካም ከሁሉ አማላይ
ቢታደሉት እንጂ እንዴት ይጋፉታል
ከማድነቅ ውጪ ሌላ ምን ይባላል
ናትናኤል ኃይሌ
Natnael
SMC C2
@talentofmedstu
ስባ አስቀረችኝ ይቺንስ ምን ይሏት
አይቼ ሳልጨርስ ከእግር እስከራሷ
ውበቷን ሳልጨረስ ፈዘዝኩ በጥርሷ
ፈገግታዋ አስቀረኝ ሌላውን እንዳላይ
የኔ መልከመልካም ከሁሉ አማላይ
ቢታደሉት እንጂ እንዴት ይጋፉታል
ከማድነቅ ውጪ ሌላ ምን ይባላል
ናትናኤል ኃይሌ
Natnael
SMC C2
@talentofmedstu
❤2👍1
ስቅለት
አመጣጥህ ባይደንቅ ሆታ ባያጅበው ፣
አገባብህ ባይሆን ንጉስ ያሳወጀው፣
ከደጅ መምጣትህ አጀብ ባያስብለን፣
የጀግና እግር ሆኖ ጉድ ነው ባያሰኘን፣
አሰነባበትህ ክፉኛ አሳመመን።
✍️smr
AMU C2
@talentofmedstu
አመጣጥህ ባይደንቅ ሆታ ባያጅበው ፣
አገባብህ ባይሆን ንጉስ ያሳወጀው፣
ከደጅ መምጣትህ አጀብ ባያስብለን፣
የጀግና እግር ሆኖ ጉድ ነው ባያሰኘን፣
አሰነባበትህ ክፉኛ አሳመመን።
✍️smr
AMU C2
@talentofmedstu
❤9👍1
Forwarded from 𝖉𝖗. 𝖉𝖊𝖇𝖔𝖑 (ዳግ)
በኢንተርን ምዘና የተጻፈ መስፈርት የለም!!!!
የጎንደር ኢንተርን ተማሪዎችን በተመለከተ ከሰሞኑ የተፈጠሩ...
https://telegra.ph/%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%89%B0%E1%88%AD%E1%8A%95-%E1%88%9D%E1%8B%98%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8C%BB%E1%8D%88-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%88%88%E1%88%9D-05-29
Telegram
@debolteam
LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/dr-debol/
የጎንደር ኢንተርን ተማሪዎችን በተመለከተ ከሰሞኑ የተፈጠሩ...
https://telegra.ph/%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%89%B0%E1%88%AD%E1%8A%95-%E1%88%9D%E1%8B%98%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8C%BB%E1%8D%88-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%88%88%E1%88%9D-05-29
Telegram
@debolteam
https://www.linkedin.com/company/dr-debol/
Telegraph
በኢንተርን ምዘና የተጻፈ መስፈርት የለም
#ኢንተርን #UoG “ በኢንተርን ምዘና የተጻፈ መስፈርት የለም ” - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተርን ሀኪሞች “ ቢሮ መጥተው ይጠይቁ ” - ዩኒቨርሲቲው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2016/17 ዓ/ም ኢንተርን ሀኪሞች ፦ - በኢንተርንሽፕ ምን ያህል መስራትና መማር እንዳለብን፣ - ምን መስራትና ምን እውቀት ማምጣት እንዳለብን፣ - በኢንተርን ምዘና የተፃፈ ሰዓትና መስፈርት ባለመኖሩ መፍትሄ እንዲሰጣቸው…
❤3🔥2
Forwarded from 𝖉𝖗. 𝖉𝖊𝖇𝖔𝖑 (𝖉𝖆𝖓𝖎 𝖉𝖊𝖇𝖔𝖑)
"ሂፖክራቲክ ኦዝ"
***
የአባታችን ትዕዛዝ የቃል ኪዳኑ ቃል
በአንክሮ ላጤነው ምስጢሩ ይደንቃል
ከትእዛዛቱ ውስጥ አንደኛው ያይላል
መርዳት ባትችል እንኳ ሰው አትጉዳ ይላል
***
እናም ይህ መኃላ
ሂፖክራቲክ ኦዝ ሲመነዘር ቃሉ
አንድምታው ሲፈታ ሲራቀቅ ወንጌሉ
...
አንድም*
ከነፍሰጡር ሞት ጋር ዓይንህ አይላመድ
በሀጥአኑ መንገድ እግርህ አይራመድ
ፈውስ ሆነህ ተፈጥረህ ከመርዝ አትዛመድ
...
አንድም*
መሪዎች ለገንዘብ ለሹመት አድልተው
መድኃኒት የሌለው ባዶ ቤት ገንብተው
ውኃና መብራቱን ድራሹን አጥፍተው
የጤና ሽፈኑን ምንትስ አድርሰናል ብለው ሲሸልሉ
በሥልጣን መከታ በልዝብ አንደበት ህዝብን ሲያታልሉ
በድብቅ መሳሪያ ታካሚን በሴራ በተንኮል ሲገድሉ
ትውልድ ከሚያመክኑ ነፍሰ ገዳዮች ጋር አትሸርብ ሴራ
<<እንቢ ለታካሚ>> ብለህ ተንጎራደድ ፎክርና አቅራራ
ታሪክ የማይረሳው ትልቅ ጀብዱ ስራ
የሚል ይመስለኛል
ይህን የሰሙ ግን ኢቲክሱን ጥሰሃል እያሉ ያሙኛል
*
ተላልፈንም እንደሁ
በደሙ እያማገች በላቡ ቀቅላ
ሀገር እንደ ድመት ውድ ልጇን ስትበላ
በደል ልኩን ሲያልፍ ግድቡ ሲሞላ
ህገ-አምላክ ይጣሳል እንኳ.. .....
*
©ግጥም-ዶ/ር ጌታነህ ካሴ
@debolteam
***
የአባታችን ትዕዛዝ የቃል ኪዳኑ ቃል
በአንክሮ ላጤነው ምስጢሩ ይደንቃል
ከትእዛዛቱ ውስጥ አንደኛው ያይላል
መርዳት ባትችል እንኳ ሰው አትጉዳ ይላል
***
እናም ይህ መኃላ
ሂፖክራቲክ ኦዝ ሲመነዘር ቃሉ
አንድምታው ሲፈታ ሲራቀቅ ወንጌሉ
...
አንድም*
ከነፍሰጡር ሞት ጋር ዓይንህ አይላመድ
በሀጥአኑ መንገድ እግርህ አይራመድ
ፈውስ ሆነህ ተፈጥረህ ከመርዝ አትዛመድ
...
አንድም*
መሪዎች ለገንዘብ ለሹመት አድልተው
መድኃኒት የሌለው ባዶ ቤት ገንብተው
ውኃና መብራቱን ድራሹን አጥፍተው
የጤና ሽፈኑን ምንትስ አድርሰናል ብለው ሲሸልሉ
በሥልጣን መከታ በልዝብ አንደበት ህዝብን ሲያታልሉ
በድብቅ መሳሪያ ታካሚን በሴራ በተንኮል ሲገድሉ
ትውልድ ከሚያመክኑ ነፍሰ ገዳዮች ጋር አትሸርብ ሴራ
<<እንቢ ለታካሚ>> ብለህ ተንጎራደድ ፎክርና አቅራራ
ታሪክ የማይረሳው ትልቅ ጀብዱ ስራ
የሚል ይመስለኛል
ይህን የሰሙ ግን ኢቲክሱን ጥሰሃል እያሉ ያሙኛል
*
ተላልፈንም እንደሁ
በደሙ እያማገች በላቡ ቀቅላ
ሀገር እንደ ድመት ውድ ልጇን ስትበላ
በደል ልኩን ሲያልፍ ግድቡ ሲሞላ
ህገ-አምላክ ይጣሳል እንኳ.. .....
*
©ግጥም-ዶ/ር ጌታነህ ካሴ
@debolteam
👍5
እኔ ማን ነኝ
እኔ ማን ነኝ ሰውን የምተች
ላይ ያለውን የማይ ወደ ታች
ባልዋለበት ስም ሰጥቼ
የራሴን እውነት ቀለም ትቼ
ያሉኝን ሁሉ ተቀብዬ
የምፈርጅ ተቻኩዬ
አድርግ ያሉኝን እሺ የምል
በሽንገላ የምታለል
የሌለውን እያስመሰልኩኝ
ስንቱን አነሳው ስንቱን ጣልኩኝ
ጣት ምቀስር ነገሩን ሳላውቅ
ሳወላዳ ከሚዛን ስርቅ
ድፍረት ኖሮኝ ከሰው ከቆምኩኝ
በቃ እኔ ነኝ ሰው አታርጉኝ....
ዶ/ር ናትናኤል ኃይሌ
@talentofmedstu
እኔ ማን ነኝ ሰውን የምተች
ላይ ያለውን የማይ ወደ ታች
ባልዋለበት ስም ሰጥቼ
የራሴን እውነት ቀለም ትቼ
ያሉኝን ሁሉ ተቀብዬ
የምፈርጅ ተቻኩዬ
አድርግ ያሉኝን እሺ የምል
በሽንገላ የምታለል
የሌለውን እያስመሰልኩኝ
ስንቱን አነሳው ስንቱን ጣልኩኝ
ጣት ምቀስር ነገሩን ሳላውቅ
ሳወላዳ ከሚዛን ስርቅ
ድፍረት ኖሮኝ ከሰው ከቆምኩኝ
በቃ እኔ ነኝ ሰው አታርጉኝ....
ዶ/ር ናትናኤል ኃይሌ
@talentofmedstu
👍5❤1
.................
ምኞት እንደማይገድ በድንገት ሰምቼ፣
አጋር ፍለጋ በምናቤ ዓለም ቆምኩኝ
ተመኝቼ፣
ከተራራው ማዶ፣
ጉቶ ላይ ቁጭ ብዬ ሳስበው ለአፍታ ፣
አንተን መሳይ ወዳጅ በህሊናዬ ውስጥ ሰራው በጨረፍታ፣
ህሊናዬም ቢያጣ በምድር ላይ አንተን፣
ብሩሼን አነሳው ልሰራው ገፅህን።
ከምኞቴ መዝገብ ምስልህን ጠቅሼ፣
ከብዙ ቀለሞች ውበትን ተውሼ፣
እጅግ ባለ ግርማ ፣ደግሞ ባለ ሞገስ፣
ከርቀት የሚታይ የቁመናህ ደንደስ ፣
አድርጌ ከተብኩህ ውበትን መዝዤ ሰሌዳ ወጥሬ፣
አንተን እያቀለምኩ ከህሊዬ ባህር ብሩሼን ነክሬ።
ይህ አልበቃ ቢለኝ ፣፪×
ብዕሬን አነሳው ልገጥም ስላንተ፣
ቃላትን ፍለጋ ውስጤ እየዋተተ፣
ምስልህ ባይገልፅልኝ ጸባይህን አጉልቶ፣
ታማኝነትህን፤ታዛዥነትህን፤
ወዳጅ ምሆንህን ባይከስት አምልቶ፣
ቅኔ እየዘረፍኩኝ ስንኞች ፃፍኩልህ፣
ሠናይ ውእቱ አንተ ፣ሸጋ ውዕቱ አንተ፣ እያልኩ ዘረፍኩልህ።
ይህም አልበቃኝም!
ዜማ እያዜምኩኝ አንጎራጎርኩልህ፣
ስለ ጨዋነትህ ፣ሰው ወዳጅነህ፣
ጨዋታ አዋቂ ብልህ መሆንህን፣
እያንጎራጎርኩኝ እየደረደርኩኝ፣
ብቻ ምን ልበልህ !
በምኞቴ ዓለም እግዜሩን መስዬ፣
በበጎው ነገር ሁሉ እሳምሬ ኩዬ፣
በህሊናዬ ዓለም አብዝቼ ስራቀቅ፣
አንተን እያሰብኩኝ ካንተ ወዲያ ስንቅ፣
እያሽምነሞንኩህ አንተን እያሞገስሁ፣
በማይጨበጥ ዓለም ታማኝ ወዳጅህ ሆንሁ።
እንደው ግን ሳጤነው ሳስበው ስራዬን፣
ግዘፍ ነስተህ ብትኖር ብታውቅ፣ መጠበቤን፣
ምትል ይመስለኛል
" ለኔም፣እንከን የለሽ አርገሽ ስሪልኝ ሔዋኔን።"🤭
✍️ smr , AMU CII
@talentofmedstu
ምኞት እንደማይገድ በድንገት ሰምቼ፣
አጋር ፍለጋ በምናቤ ዓለም ቆምኩኝ
ተመኝቼ፣
ከተራራው ማዶ፣
ጉቶ ላይ ቁጭ ብዬ ሳስበው ለአፍታ ፣
አንተን መሳይ ወዳጅ በህሊናዬ ውስጥ ሰራው በጨረፍታ፣
ህሊናዬም ቢያጣ በምድር ላይ አንተን፣
ብሩሼን አነሳው ልሰራው ገፅህን።
ከምኞቴ መዝገብ ምስልህን ጠቅሼ፣
ከብዙ ቀለሞች ውበትን ተውሼ፣
እጅግ ባለ ግርማ ፣ደግሞ ባለ ሞገስ፣
ከርቀት የሚታይ የቁመናህ ደንደስ ፣
አድርጌ ከተብኩህ ውበትን መዝዤ ሰሌዳ ወጥሬ፣
አንተን እያቀለምኩ ከህሊዬ ባህር ብሩሼን ነክሬ።
ይህ አልበቃ ቢለኝ ፣፪×
ብዕሬን አነሳው ልገጥም ስላንተ፣
ቃላትን ፍለጋ ውስጤ እየዋተተ፣
ምስልህ ባይገልፅልኝ ጸባይህን አጉልቶ፣
ታማኝነትህን፤ታዛዥነትህን፤
ወዳጅ ምሆንህን ባይከስት አምልቶ፣
ቅኔ እየዘረፍኩኝ ስንኞች ፃፍኩልህ፣
ሠናይ ውእቱ አንተ ፣ሸጋ ውዕቱ አንተ፣ እያልኩ ዘረፍኩልህ።
ይህም አልበቃኝም!
ዜማ እያዜምኩኝ አንጎራጎርኩልህ፣
ስለ ጨዋነትህ ፣ሰው ወዳጅነህ፣
ጨዋታ አዋቂ ብልህ መሆንህን፣
እያንጎራጎርኩኝ እየደረደርኩኝ፣
ብቻ ምን ልበልህ !
በምኞቴ ዓለም እግዜሩን መስዬ፣
በበጎው ነገር ሁሉ እሳምሬ ኩዬ፣
በህሊናዬ ዓለም አብዝቼ ስራቀቅ፣
አንተን እያሰብኩኝ ካንተ ወዲያ ስንቅ፣
እያሽምነሞንኩህ አንተን እያሞገስሁ፣
በማይጨበጥ ዓለም ታማኝ ወዳጅህ ሆንሁ።
እንደው ግን ሳጤነው ሳስበው ስራዬን፣
ግዘፍ ነስተህ ብትኖር ብታውቅ፣ መጠበቤን፣
ምትል ይመስለኛል
" ለኔም፣እንከን የለሽ አርገሽ ስሪልኝ ሔዋኔን።"🤭
✍️ smr , AMU CII
@talentofmedstu
❤6👍2
Art Meets Medicine: Calling on Health Professionals to Participate in Talent Initiative
.
Apply & Join us!
.
MAC-Ethiopia in collaboration with Team_Debol
@debolteam
@talentofmedstu
https://telegra.ph/The-envisioned-call-06-27
.
Apply & Join us!
.
MAC-Ethiopia in collaboration with Team_Debol
@debolteam
@talentofmedstu
https://telegra.ph/The-envisioned-call-06-27
Telegraph
Art Meets Medicine: Calling on Health Professionals to Participate in Talent Initiative
#MAC // Medicos' Art Club was established in November 2018 G.C by Dagmawi Mulugeta, also known as #DMF, during his tenure as a medical student at Jimma University. Dr. Dagmawi is currently pursuing an MSc in Biomedical Science in Italy, complementing his…
❤1
አዎ ይቻላል!!!
MAC-Ethiopia 🇪🇹 🩺
ዶ/ር በፀሎት
https://telegra.ph/%E1%8A%A0%E1%8B%8E-%E1%8B%AD%E1%89%BB%E1%88%8B%E1%88%8D-06-29
MAC-Ethiopia 🇪🇹 🩺
ዶ/ር በፀሎት
https://telegra.ph/%E1%8A%A0%E1%8B%8E-%E1%8B%AD%E1%89%BB%E1%88%8B%E1%88%8D-06-29
Telegraph
አዎ ይቻላል
አዎ ይቻላል! ዶ/ር በፀሎት ከበደ እባላለሁ የህክምና ምሩቅ ነኝ ፤ ስመረቅ ግን ሐኪም ብቻ ሳይሆን ጸሀፊም ሆኜ ጭምር ነበር። ታድያ ይህ የመጻፍ ዝንባሌዬ ከየት መጣ? በርግጥ ቀድሞውኑ ውስጤ ከልጅነት አብሮኝ ያደገ መክሊት ቢሆንም በህክምና ትምህርት ውስጥ ሳልፍ የገጠሙኝ ከባድ ክስተቶች ግን ውስጤ ለነበረው ስጦታ ልክ እንደ የሳጥኑ መክፈቻ ቁልፍ ነበር የሆኑልኝ። እነዚህ ከባድ ክስተቶች ምን ነበሩ? በህይወት…
👍3