Telegram Web Link
ጠቃሚ መረጃ 🌟🌟🌟🌟🌟 የ H + ፣ H ፣ 3G ፣ E እና 4G በይነመረብ ግንኙነት ትርጉም
ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሁሉ እርስዎ የተገናኙበትን የመረጃ አይነት ያሳያሉ እና ይህ በእያንዳንዱ ISP ፍጥነት እና ምልክት ምልክቶች ይለያያል ፡፡
ከዚህ በታች የእያንዳንዱ ግንኙነት ማጠቃለያ እና የማውረድ ፍጥነት ነው፡፡
G = 14 KB
E = 48 KB
3G = 395 KB
H = 1.75 KB/s
H+ = 21MB
4G = 37Mb

JOIN/SHARE

@techzone_ethio
@techzone_ethio
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያገኘሁትን wallaper ላካፍላችሁ

#share
@techzone_ethio
🔥 Wallpaper🔥

#share
@techzone_ethio
ኦርጂናልና ፌክ ሚሞሪ እንዴት በቀላሉ መለየት ይቻላል???

1. ኦርጂናል #ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን📲 ውስጥ በማስገባት #ፎርማት ማድረግ ነው።

☑️ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ ምንም ችግር ይጨርሳል👍 ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኢረር(Error) ቦክስ ያሳያቹና ይቋረጣል‼️

2.ሁለተኛው መንገድ ደሞ በ ኮምፒውተሮ💻 ወይም በስልኮ📲 ወደ ሚሞሪው ፋይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል።

☑️ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን ፊልም ወይም ሌላ ፋይል ወደገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዐት ማወቅ ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ ይወስዳል ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 ደቂቃ+ ሊወስድ ይችላል ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ😡 ነው ማለት ነው።

3. የሚሞሪው ፋይል የመያዝ አቅም

☑️ለምሳሌ 8GB ሚሞሪ ቢኖርዎት #Original ከሆነ ቢያንስ 7.4GB ይሆናል። ስለዚህ 7.4GB የሚሆን ፋይል ይላኩበት በትክክል ከተቀበለ #አስተማማኝ👍 ነው።

4. ስልካችን📲 ውስጥ በማስገባት SD insight የተባለ አፕ ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን አፑን ከታች አስቀምጥላችኋለው።

☑️ስልካችን ውስጥ ሚሞሪ አስገብተን ይህን አፕ ስንከፍተው #ስለ_ሚሞሪው ምርት መረጃ ካሳየን ሚሞሪው ኦርጂናል👍 ነው ማለት ነው ለምሳሌ ሲሪያል ቁጥር እና የት እንደተመረተ እናም ሌሎችን ማለቴ ነው ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ምንም አይነት መረጃ አያሳየንም ይህ ማለት ሚሞሪው የት እንደተመረተ እና ሲሪያል ቁጥር የለውም ማለት ነው ስለዚህ የማይታወቅ😡 ሚሞሪ ነው ማለት ነው፡
@techzone_ethio
@techzone_ethio
#Ethio_Tech_Zone_News

#የከሸፈው የሳይበር ጥቃት

‼️መቀመጫቸውን በግብጽ ያደረጉ ቡድኖች #የሳይበር ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ አድርገዋል!

መቀመጫቸዉን ግብጽ ያደረጉ ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ (Cyber_Horus Group)፣ አኑቢስ ዶት ሃከር (AnuBis.Hacker) እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ (Security_By_Passed) በተባሉ የሳይበር አጥቂዎች በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃት ሙከራ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ወንጀለኞቹ አርብ ሰኔ 12/2012 እና ቅዳሜ ሰኔ 13/2012 ከፍተኛ የሚባል የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ማድረጋቸውንና የ13 የመንግስት፣ 4 መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የድረ-ገጽን የማስተጓጎል ሙከራ ማድረጋቸውን #INSA አስታውቋል፡፡

ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከር እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ የሳይበር ጥቃት አድራሽ ቡድኖች ሃላፊነቱን የወሰዱ ሲሆን ዋና አላማቸዉም ከህዳሴው ግድብ ዙሪያ በተለይ በውሃ አሞላል ጋር በተያያዘ ሁሉን አቀፍ ተጽእኖ በሀገሪቱ ላይ ለመፍጠር በማሰብ እንደፈጸሙት ተገልጿል፡፡

የሳይበር ጥቃት የተሰነዘረባቸው ተቋማት አብዛኛዎቹ በድረ-ገጽ ግንባታ ሂደት ደህንነታችው ታሳቢ ያላደረጉ ተቋማት፤ በቀጣይነት የደህንነት ፍተሻ ያላደረጉ እና ከፍተኛ የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት የነበረባቸው መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አረጋግጧል፡፡

ምንጭ :- Ebs አዲስ ነገር

@techzone_ethio @techzone_ethio
com.humanlogic.sdi_17.apk
848.3 KB
💢 Sd Insight

V: 1.5.10(17)

ስለ ስልካችን storage እና ሰለ sd card memori ያችን ሙሉ መረጃ የሚሠጠን ቀለል ያለ አፕ ነው ፡፡

⚠️ በዚህ አፕ fake & original sd card memori መለየት እንችላለን ::

#share
@techzone_ethio
ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ
#Ethio_Tech_Zone_News #የከሸፈው የሳይበር ጥቃት ‼️መቀመጫቸውን በግብጽ ያደረጉ ቡድኖች #የሳይበር ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ አድርገዋል! መቀመጫቸዉን ግብጽ ያደረጉ ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ (Cyber_Horus Group)፣ አኑቢስ ዶት ሃከር (AnuBis.Hacker) እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ (Security_By_Passed) በተባሉ የሳይበር አጥቂዎች በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃት ሙከራ ማድረጋቸው…
#አሁን_በደረሰን_ዜና ❗️

#በመጨረሻም ስለ ግብፅ የሳይበር ጥቃት ከመንግስት ምላሽ አግኝተናል እንደሚከተለው እናቀርባለን ❗️

#ጥቃቱን_አክሽፈነዋል ❗️

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን #ኢመደኤ አስታወቀ❗️

⚡️የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ሰኔ 10፣ 12 ፣ 13 እና 14/2012 ዓ.ም መቀመጫቸዉን ግብጽ ያደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታውቋል።

⚡️የሳይበር ጥቃት ሙከራው የተቃጣው ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ (Cyber_Horus Group)፣ አኑቢስ ዶት ሃከር (AnuBis.Hacker) እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ (Security_By_Passed) በተባሉ የሳይበር አጥቂዎች አማካይነት መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

⚡️ወንጀለኞቹ ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጁ የቆዩ እና ኤጀንሲው ሲከታተላችው የነበሩ ሲሆን በይበልጥ አርብ ሰኔ 12/2012 እና ቅዳሜ ሰኔ 13/2012 ከፍተኛ የሚባል የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ማድረጋቸውን የገለጸው ኤጀንሲው በዚህ ጊዜ ዉስጥ የ13 የመንግስት፣ 4 መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የድረ-ገጽን የማስተጓጎል ሙከራ ማድረጋቸውን አስታውቋል፡፡

⚡️የሳይበር ጥቃት ሙከራው በሀገሪቱ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የደህንነት መስሪያ ቤቶች እና የግል ድርጅቶች ድረ-ገጽ ላይ ያነጣጠረ ነበር፡፡

⚡️ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከር እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ የሳይበር ጥቃት አድራሽ ቡድኖች ሃላፊነቱን የወሰዱ ሲሆን ዋና አላማቸዉም ከህዳሴው ግድብ ዙሪያ በተለይ በውሃ አሞላል ጋር በተያያዘ ሁሉን አቀፍ ተጽእኖ በሀገሪቱ ላይ ለመፍጠር በማሰብ እንደፈጸሙት ገልጸዋል፡፡

⚡️የሳይበር ጥቃት የተሰነዘረባቸው ተቋማት አብዛኛዎቹ በድረ-ገጽ ግንባታ ሂደት ደህንነታችው ታሳቢ ያላደረጉ ተቋማት፤ በቀጣይነት የደህንነት ፍተሻ ያላደረጉ እና ከፍተኛ የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት የነበረባቸው መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አረጋግጧል፡፡

⚡️ኤጀንሲው አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅት በማድረጉ ምክንያት እና ይህን መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት መከላከል ባይችል ኖሮ ጥቃቱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖሊቲካዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር የገለጸው ኤጀንሲው በመከላከሉም ሊደርሱ የሚችሉ ከፍተኛ አደጋዎችን ማስወገድ መቻሉን እና ይህንንም ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አሳውቋል፡፡

⚡️በቀጣይም መሰል ጥቃቶች በስፋት፤ በረቀቀ መንገድ እና ከተለያዩ ስፍራ ሊሰነዘር እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት .et domain ከመጠቀማቸው በፊት የድረ-ገጻቸውን ደህንነት አረጋግጠው እንዲጠቀሙ፤ ራሳቸውን ከሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት ለመከላከል እና አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚኖርባቸው ኤጀንሲው አሳስቧል።

⚡️ተቋማት ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር ያለባቸውን የደህንነት ተጋላጭነት መድፈን እንዳለባችው እና የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ጥቃት ሙከራ ሲያጋጥማቸውም ሆነ ሙያዊ ድጋፍ ሲያሻቸው ለኤጀንሲው በማሳወቅ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ አስታወቋል።

• ባለፉት ሁለት ቀናት ትብብር ላደረጉልን ተቋማት እና ግለሰቦች በተለይ ለኢትዮ ቴሌኮምና ለኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኤጀንሲው ምሰጋና አቅርቧል፡፡

© የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

@techzone_ethio
@techzone_ethio
‼️ Just for fun
#programmingJoke 😂
@techzone_ethio
🔎 ቀልጣፋ እና ስኬታማ ከጎግል መረጃ የመፈለጊያ ስልቶች 🔍
~~~~~~~~~~~~~~~~~
■Ethio tech zone■
~~~~~~~~~~~~~~~~~
የዘወትር የመረጃ መፈለጊያ የሆነው የጎግል ፍለጋችን ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ ስልቶችን ልንጠቁማችሁ ወደናል።

1⃣. ትክክለኛውን ቃል ለመፈለግ ቃሉን በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ማስገባት ለምሳሌ፡- “Android” በማለት ጎግል ብናደርግ ከዚሁ ጉዳይ ጋር ብቻ የተገናኙ መረጃዎችን በሰፊው እናገኛለን።

2⃣. ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ድረ ገጾች ለመፈለግ

በቅርጽም ሆነ በይዘት ተቀራራቢነት ያላቸውን ድረ ገጾች ለማግኘት ወይም እንደ እከሌ አይነቱን ድረ ገጽ ፈልግልኝ ለማለት related: የሚለውን አስቀድመን የድረ ገጹን አድራሻ እናስከትላለን፤

ለምሳሌ፡- ጎግልን related:amazon.com ብለን ብንጠይቀው ከአማዞን ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ድረ ገጾች ውጤት ይሰጠናል።

3⃣. ጎግል የምንፈልገውን ብቻ እንዲፈልግልን ደግሞ ከቃላቱ በፊት የሰረዝ ምልክትን መጠቀም አለብን።

ይህም በተለይ በርካታ ትርጉም ያላቸውን ነገሮች ስንፈልግ የማንፈልገውን ለይቶ በቀላሉ የምንፈልገውን ጉዳይ ማግኘት ያስችላል።

ለምሳሌ፡- terminator –movie ብለን ብንፈልግ የፍለጋ ውጤታችን ቴርሚኔተር ላይ ብቻ ያተኮረ እና ተርሚኔተር ስለተባለው ፊልም ፈጽሞ ያላካተተ ይሆናል።

4⃣. ድረ ገጾች ስለ አንድ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የሰሩትን በቀላሉ ለመፈለግ

አንድ ደረ ገጽ ስለሆነ ነገር ከዚህ በፊት የሰራቸውን ለመመልከት የምፈልገውን ቃል ከጻፍን በኃላ ክፍት ቦታ ሰጥተን site: ብለን በመጻፍ የምንጎበኘውን ድረ ገጽ አድራሻ በማስከተል መፈለግ፤

ለምሳሌ፡- barrack obama. Site: bbc.com ብለን ብንፈልግ ቢቢሲ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን በተመለከተ በድረ ገጹ ላይ ያወጣቸውን ዘገባዎች ለመመልከት እንችላለን።

5⃣. ትርጓሜዎችን ለመፈለግ

የፊደላትን ትርጓሜ ለማወቅ እና ተመሳሳይ ፍቺዎችን ለመፈለግ define: አስቀድመን ቃሉን መጻፍና መፈለግ የተሻለ ውጤት ያስገኝልናል።

ለምሳሌ፡- define:injera ብለን ጎግል ላይ ብንፈልግ ሰለ እንጀራ ዘርዘር ያለ መረጃ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ያለውን ትርጓሜ በስፋት ማግኘት እንችላለን።

በዚህ መንገድ የአንዳንድ ቃላትን ሰያሜ መነሻ እና ትርጉም ለማግኘትም ቀላል ነው።

6⃣. የተለያዩ የፋይል አይነቶችን ለማሰስ

ጎግል የፒዲኤፍ አልያም ፓወር ፖይንት ውጤቶችን እንዲሰጠን ለመጠየቅ የሚከተለውን አማራጭ እንጠቀማለን።

ለምሳሌ፡- “Scientific Journalism” filetype:pdf

7⃣. አዲስ የሆኑ እና ትኩረት የሳቡ አለማቀፍ ጉዳዮችን ለማግኘት

ከምንፈልገው ርዕሰ ጉዳይ በፊት የሃሽታግ ምልክትን ማስቀደም፤ ለምሳሌ #action2017 ብለን በመፈለግ በርካታ መረጃዎችን ማግኘት ያስችላል።

8⃣. በጎግል ወደ ሌላ ቋንቋ ለመተርጎም

ጎግል ትራንዝሌት ቃላቶችን ብቻ ሳይሆን ዘርዘር ያሉ ጽሁፎችንም ለመተርጎም ያስችላል።

ለምሳሌ፡- hello የሚለውን ቃል ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ለመተርጎም translate english to french hello በማለት ጎግል ላይ መፈለግ እንችላለን።

9⃣. የረሳናቸውን ፊደላት ለማስታወስ

ጎግል የዘነጋናቸውን ቃላት እንዲያስታውሰን ኤስትሪክስን (*) መጠቀም እንችላለን። ኤስትሪክስን መጠቀም በተለይ የረሳናቸውን የዘፈን ግጥሞች ለማስታወስ ይረዳል።

ለምሳሌ፡- “Come * right now * me” የሚለውም የዘፈን ግጥም ጉግል ብናደርግ “Come Together” የሚል ርዕስ ያለውን የቢትልስ ሙዚቃ ግጥም ውጤቶች ይሰጠናል።

🔟. የአየር ሁኔታ መረጃ ለማግኘት ደግሞ ዌዘር የሚለውን ቃል ከከተሞቹ አስቀድመን መፈለግ

ለምሳሌ:- weather Adiss ababa
═════════════════

👇🏾👇🏾
@techzone_ethio
╚═════❁✿❁ ═════╝
com.lyrebirdstudio.photo_editor_pro.apk
37.7 MB
👆👆👆👆👆
ፎቶአቹላይ እንደዚህ አይነት ኢፌክት ለመጨመር ይረዳቹሀል

#share
@techzone_ethio
የዳውሎድ ምልክቱን ሾፋቹት አ
🔥InstaMod 1ኛ ነው
InstaMod_v20_black.apk
42.3 MB
Instagram አፑን አጥፉትና ይሄን install አድርጉት

🔥ፎቶ zoom ማድረግ ትችላላቹ
🔥በpassword መቆለፍ ትችላላቹ
🔥ቪድዮዎችን በቀላሉ ዳውሎድ ማድረግ ያስችላቿል
🔥ምንም ማስታወቂያ የለውም

👌የሌለ ምርጥ ነው👌

#share
@techzone_ethio
likee-3-19-2.apk
67.6 MB
😘Like
አሪፍ አሪፍ አዝናኝ ቪድዮዎችን ታገኙበታላቹ ዝም ብላቹ መኮምኮም ነው

#share
@techzone_ethio
~~~~~~~~~~~~~~~
♤Ethio tech zone♤
~~~~~~~~~~~~~~~
📱የሞባይል ቫይረስ ወይም ማልዌር

✔️ የሞባይል ማልዌር ማለት የተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ በማነጣጠር ምስጢራዊ
የመረጃ ማፍሠስ የማበላሸት እና ሌሎችም ድርጊቶች የሚያደርግ ተንኮል አዘል
ሶፍትዌር ነው።
በገመድ አልባ ስልኮች ላይ ይበልጥ የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል እና
እንደተመለከትነው የውስብስብነታቸው መጨመር ቫይረሶች ወይም ማልዌር
የኤሌክትሮኒክስ ጥቃት ላይ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ይበልጥ አስቸጋሪ እየሆነ
መጥቷል
የተንቀሳቃሽ ስልክ ቫይረስ በመጀመሪያ በብራዚሉ የሶፍትዌር መሀንዲስ ማርኮስ
(Marcos Velasko) ነበር የተሠራው የእሱ ሃሳብ ግን ቨላስኮ በማንኛውም
ሠው ስልክ ላይ ሊሞከር የሚችል ለማስተማሪያነት የሚውል ቫይረስየተገኘው ነበር የፈጠረው፡፡
በቤተ ሙከራ የመጀመሪያው ቫይረስ የተሠራው ስፔን ውስጥ
ቲሞፎኒካ(Tifomonica) ይባል ነበር ይህንን ቫይረስ ያገኙት በሩስያ እና
በፊንላንድ የፀረ ቫይረስ ቤተ ሙከራ በሰኔ 2000 እ.ኤ.አ. ሲሆን በስፓኒሽ ቋንቋ
Tifomonica is fooling you በማለት በኢንተርኔት መልዕክት መላኪያ በር
በኩል ይልክ ነበር
ከዚያም በኋላ የተለያዩ ቫይረሶች ተሰርተዋል ግን ትኩረታችን
የጉግል አይነት አንድሮይድ ሶፍትዌር የሚጠቀሙ ስልኮች ላይ የሚሆነው ነው።

በነሐሴ 2010 እ.ኤ.አ የካስፐርስካይ(KasperSky) ቤተሙከራ trojan-
SMS.ANDROIDOS.FAKEPLAYER.A የተባለውን የትሮጃን ቫይረስ
አሳውቋል ይህ #ቫይረስ የጉግል ስርአተ ክወና የሚያካሂዱ ስልኮችን
የሚያጠቃ #ቫይረስ ሲሆን አንድሮይድ የመጀመሪያው የተንኮል ፕሮግራም ነበር እናም
ያለባለቤቱ እውቅና የፅሁፍ (SMS) መልዕክቶችን ወደ ተለያ ቁጥሮች ይልክ
ነበር።

🙏 መልካም ቅዳሜ 🙏

#share
@techzone_ethio
@techzone_ethio
Bilgates የሀይስኩል ተማሪ እያለ የኮምፒውተር ሲስተሙን በመስበር (Hack) በማድረግ ራሱን ብዙ ሴቶች ያሉበት ክላስ ለማስመዝገብ ሞክሮ ነበር። ምን ሊያደርጋቸው ነው ግን ???
🙊😁😁


@techzone_ethio
U will love this shit game its crazy
The Safest Free Software Download Sites for Windows

Ninite.
Softpedia.
FileHippo.
DonationCoder.
Download Crew.
FileHorse.
FilePuma.
SnapFiles.

@techzone_ethio
2025/07/06 06:19:27
Back to Top
HTML Embed Code: