Telegram Web Link
🎮best android game🎮
#share
@techzone_ethio
🌟Dream League Soccer 2020 v7.41 (Mod)🌟

📋Dream League Soccer 2020 puts you in the heart of the action with a fresh look and brand new features! Build your dream team from over 3,500 FIFPro licensed players and take to the field against the world’s best soccer clubs! Rise through 8 divisions whilst enjoying full 3D motion-captured player moves, immersive in-game commentary,…📋

📁Category: #Sports

✤Join @techzone_ethio
📱በሞባይሎ ኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? 😡በሞባይሎ ላይ እነዚህን ማስተካከያዎች ያድርጉ👀

👥 ኢትዮ ቴሌኮም ወደ 60 ሚሊዮን የሚገመቱ ደንበኞች እንዳሉት ይነገርለታል። ከእነዚህ መካከል ደግሞ 17 ሚሊዮን ያህሉ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርኔት አገልግሎትን ይጠቀማሉ።

📶 ኢትዮ ቴሌኮም ዝቀተኛ በማይባል ዋጋ ኢንተርኔትን ለተጠቃሚዎች ከሚያደርሱ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።

🤔 ምናልባትም እርሶም ''አሁን የገዛሁት ኢንተርኔት ከምኔው አለቀ?'' ''ካርድ ዛሬ አይደል እንዴ የሞላሁት ወዴት ሄደ?'' ብለው እራሶን ጠይቀው ሊሆን ይችላል።

በአንድሮይድ አና በአይኦኤስ ስልኮቻችን ላይ አንዳንድ ማስተካካያዎች በማድረግ የኢንተርኔትን ወጪ መቀነስ የሚቻልበትን መንገድ እንጠቁማችሁ።

በቅደሚያ አንድሮይድ አና አይኦኤስ ምንድናቸው?

🔱 አንድሮይድ በጉግል የተሰራ የተለያዩ የሞባይል አይነቶች የሚጠቀሙበት የመተግበሪያ ስርዓት ነው። ለምሳሌ ሳምሰንግ፣ ሁዋዌ፣ ኤል ጂ (LG) እና ቴክኖን የመሳሰሉ ሞባይሎች አንድሮይድ የተባለውን የመተግበሪያ ስርዓትን ይጠቀማሉ።

አይኦኤስ (iOS) በአፕል የተሰራ ሲሆን አይፎን፣# አይፓድ እና አይፓድ ተች የሚጠቀሙበት የመተግበሪያ ስርዓት ነው።

🌀 እንደ ፌስቡክ እና ዋትሰአፕ የመሳሰሉ በዕለት ተለት በምንጠቀምባቸው መተግባሪያዎች ላይ ቀላል ማስተካከያዎችን በማድረግ እንዴት የኢንተርኔት ወጪያችንን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንደምንችል እንጠቁማችሁ።

❇️ፌስቡክ (Facebook)

🎦 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፌስቡክ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በራሳቸው ጊዜ እንዲጫወቱ ፍቅዷል። ይህም ብዙ ዳታን ይጠቀማል። ተንቀሳቃሽ ምስሎች በራሳቸው ጊዜ እንዳይጫወቱ ለማድረግ (Video Autoplay off) ለማድረግ፡-

☑️ በአንድሮይድ ስልኮች ላይ ይህን ይከተሉ፡ ሴቲንግ ኤንድ ፕራይቬሲ (Setting and Privacy) >ዳታ ሴቨር (Data Saver) የሚለውን On ያድርጉ።

✔️ በአይኦኤስ (አይፎን) ላይ ይህን ይከተሉ፡ ሴቲንግ (Setting) >ሚዲያ ኤንድ ኮንታክት (Media and Contact) >ቪዲዮ ኤንድ ፎቶስ (Video and Photos) >አውቶ ፕለይ (Auto-play) >ኦን ወይፋይ ኮኔክሽን ኦንልይ (On Wi-Fi connections only) የሚለውን On ያድርጉ።

📌 ከዚህ በተጨማሪም በአንድሮይድ ስልኮች ላይ አነስተኛ ዳታ የሚጠቀመውን ፌስቡክ ላይት (Facebook Lite) የተባለውን የፌስቡክ ስሪት መተግበሪያን ከጉግል ፕለይ ላይ በማውረድ መጠቀም ይቻላል።

🌐 ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ፌስቡክ የሚለውን መተግበሪያ ከመጠቀም ይልቅ እንደ ኦፔራ ሚኒ (Opera Mini) ያሉ የኢንተርኔት መቅዘፊያ መተግበሪያዎችን (Internet Browser Apps) በመጠቀም የዳታ ወጪን መቀነስ ይቻላል።

📌 ያስታውሱ ፌስቡክን በፌስቡክ ላይት ወይም በመተግበሪያዎች ስጠቀሙ የፌስቡክ ማራኪነት እና አማራጮች ሊቀንሱ ይችላሉ።

🗣 ዋትስአፕ (WhatsApp)

🟢 ስንት የዋስትአ ግሩፕ (ቡድን) ውስጥ አሉ? በዋትስአፕ የሚላክሎት ፎቶ እና ቪዲዮ በፎቶ ጋለሪ ውስጥ አለ ማለት ብዙ የሞባይል ዳታ እየተጠቀሙ ነው። ዋትስአፕ የሚጠቀመውን የዳታ መጠን ለመቀነስ ይህን ይከተሉ።

🔶 የዋትስአፕን ሴቲንግ (Setting) ይክፈቱ >ዳታ ኤንደ ስቶሬጅ ዩሴጅ (Data and Storage Usage) >ከዚያም ሰሌክት ሚዲያ አውቶ ዳዎንሎድ ኦፕሽንስ (Select Media Auto Download Options) የሚለውን በመምረጥ >ዌን ዩዚንግ ሞባይል ዳታ (When Using Mobile Data) የሚለውን በመጫን ''ኖ ሚዲያ (No Media)'' በሚለው ይቀይሩት።

🔴 በይበልጥ ዋትስአፕ የሚጠቀመውን ዳታ ወጪ ለመቀነስ ኮል ሴቲንግ (Call Setting) ከሚለው በታች ያለውን ሎው ዳታ ዩዜጅ (Low Data Usage) መምረጥ ይቻላል።

👁‍🗨 ዩቱዩብ (YouTube)

♨️ በዩቱዩብ ቪዲዮችን መመልከት ብዙ ዳታ ይወስዳል። በሞባይል ዳታ ቪዲዮን መመልከት ካስፈለጎው ግን የሴቲንግ ምልክቷን በመጫን 240p ወይም 144p ላይ በማድረግ በአነስተኛ ጥራት በመመልከት እስከ 60 በመቶ ሊያወጡ የሚችሉትን የHD (720p) የዳታ መጠን መቀነስ ይችላሉ።

© ሌላው አማራጭ የቪዲዮ ባለመብት ፍቃድ ካለ የወደድነውን ቪዲዮ ከዩቱብ ላይ የዋይፋይ አግልግሎት ያለበት ቦታ ላይ በማውረድ ለ30 ቀናት የለ ኢንተርኔት ደጋግምን መመልከት እንችላለን።

📌 በስልኮቻችን ላይ ተጭነው የሚገኙ መተግበሪያዎች በፈጣሪዎቻቸው በተለያየ ጊዜ በአዳዲስ ቅጂዎች ይሻሻላሉ። መተግበሪያዎቹን ለማሻሻል የሞባይል ዳታን መጠቀም ብዙ የኢንተርኔት ወጪን ያስከትላል። ስለዚህም የዋይፋይ (Wi-Fi) አገልግሎት ባለበት ቦታ ብቻ ማሻሻል ይመከራል።

🔰 መተግበሪያዎችን ለማሻሻል ዋይፋይን ብቻ ለመጠቀም የሚከተሉትን ቅድመ ተከተሎች ይከተሉ።

🔵 አንድሮይድ ስልኮች ላይ፡ ጉግል ፕለይ ስቶር (Google Play Store) >ሴቲን (Setting) >አውቶ አፕዴት አፕስ (Auto-update apps) >አውቶ አፕዴት አፕስ ኦቨር ዋይፋይ ኦንልይ (Auto-update apps over Wi-Fi only) የሚለውን On ያድርጉት።

ለአይፎን ስልኮች ላይ፡ ሴቲንግ (Setting) >አይቲዩንስ & አፕ ስቶር (iTunes & App Stores) >ዩዝ ሞባይል ዳታ (Use Mobile Data) የሚለውን Off ያድርጉት።

🔵 የእርሶ ስልክ አንድሮይድ መተግበሪያ ስርዓትን የሚጠቀም ከሆነ በስልኮ ላይ የሚከተሉትን ማስተካከያዎች በማድረግ የኢንተርኔት አጠቃቀሞው ላይ ገደብ ሊያደርጉ ይችላሉ።

Setting > Network & Internet > Data Usage > Data Saver >

@techzone_ethio

👥share: @techzone_ethio

@techzone_ethio
✳️ ይህንን ያውቁ ኖሯል?

◽️ Sony በ1998፡ ሰዎች ልብስ ለብሰው እያለ እርቃናኛቸው እንደሆኑ በማስመሰል የሚያሳዩ 700,000 ካምኮደሮች በስህተት ወደ ገበያ አቅርቦ ነበር!

◽️ የኮምፒተር ሳይንቲስቶች (Computer Scientists) እስከ 2050 ተግባራዊ ይሆናል የተባለለት ሰዎች የሚያሰቡትን ነገር ከጭንቅላታቸው ዳውሎድ አድርገው ኮምፒተር ላይ ሚያስቀምጡበት ቴክኖሎጂ በመስራት ላይ ናቸው!

◽️ Zip Bomb የተባለ ኮምፒተር ቫይረስ ዚፕ (Zip) ሲደረግ 42 KB (ኪሎባይት ሲሆን) Unzip ሲደረግ 4.5 ፔታባይት (Petabyte, ወይም አንድ ሚልዮን ጊጋባይት (GB) ሳይዝ ይኖረዋል!

◽️ Y2K (Year 2000 ለማለት) በ2000 (እ.ፈ.አ) ይከሰታል ተብሎለት የነበረው የኮምፒተሮች የቀን አቆጣጠር መንገድን ያቃውሳል የተባለለትና የኮምፒተር ፕሮግራመሮች ዐመተ ምህረቶችን በሁለት ዲጅት መጻፍ መሰረት ያደረገው Computer Bug በ2038 ይፈጠራል! (ለምሳሌ 1999 ለማለት 99 ብሎ መጻፍ)

@techzone_ethio
✳️ ከኮምፒተራችን ላይ ምናጠፋቸው ፋይሎች ወዴት ነው የሚሄዱት?

◽️ ኮምፒተራችን ምንም ነገር አያጠፋም። ያጠፋነው የሚመስለን ፋይል ሁሉ እዛው ሀርድ ዲስካችን ላይ ነው ሚቀመጠው!

◽️ ፋይል አጠፋን የምንለው የፋይላችን መኖር ሲነግረን የነበረን (Pointer የሚባል ዳታ) ጠቋሚው (Pointer), እንዲጠፋ የፈለግነውን ፋይል መጠቆሙን እንዲያቆምና ወደ ሌላ አዲስ አድራሻ እንዲጠቁም ስለምናደረገው ነው!

◽️ የጠፋብንን ፋይል መመለስ የሚቻለውም ፋይሉ ተቀምጦበት የነበረው ቦታ ላይ ኮምፒተሩ መልሶ ሌላ ፋይል እስካላስቀመጠበት ሲሆን፣ ምስጢር ነክ የሆኑ ፋይሎችን የያዙ ኮምፒተሮች ፎርማት ከማረግ ሰባብሮ ከጥቅም ውጪ ማድረግ የሚመከረውም በዚህ ምክንያት ነው!

@techzone_ethio
​​​✳️ Quantum Computing ምንድነው?

◽️ Quantum Computer: የQuantum Mechanics ሀሳቦችን በመጠቀም አሁን ካሉት ኮምፒተሮች በፍጥነትና በተሻለ መልኩ ስራውን ሚከውን የኮምፒተር ዐይነት ነው!

◽️ አሁን ዓለም ላይ ያሉት ኮምፒተሮች በሙሉ ዳታዎችን ለማስቀመጥ ሆነ ለማስተላለፍ Binary Digit ተብሎ በሚጠራው የ 0 እና 1 ስብስብ የሆነው Streams of Bits (ባጭሩ Bits) ተጠቅመው ነው. .. ስእሎች, ቪድዮዎች, ሙዚቃዎች ብሎም ማንኛውም ኮምፒተሮች ላይ ያሉት ዶክመንቶች በBit መልኩ ነው ሚቀመጡት!

◽️ Quantum Computeሮች በሌላ መልኩ ዳታዎች ሚያስተላልፉትም ሆነ ሚያከማችሁት Bit ተጠቅመው ሳይሆን Qubits በሚባሉት የ 0 እና 1 ስብስቦች በመጠቀም ነው!

◽️ Bit እና Qubit ሚለያቸው፣ Bit ብለን የጠራናቸው ወይ 0 ወይ 1 በመሆን ነው ሚቀመጡት! Qubits ሚባሉት ግን እንደ Bits ለየብቻ 1 እና 0 መሆን ይችላሉ ደግሞም በተመሳሳይ ቦታና ግዜ 1ም 0ም ሆነው መቀመጥ ይችላሉ፥ ይህ Superposition ተብሎ ይጠራል ! አሁን በምንጠቀማቸው ኮምፒተሮችና በQuantem Computers መሃል ያለው ትልቁ ልዩነትም ይሄኛው ነው!

◽️ ለምሳሌ አንድ ካሲኖ (Casino) ውስጥ ገብታችሁ ከምታገኙት ኮምፒተርጋ አንበሳና ሰው (በBit ሲገለጽ Head=1 and Tail=0) ጨዋታ ብትጫወቱ የማሸነፍም የመሸነፍም እድላችሁ 50/50 ነው ሚሆነው። ኮምፒተሩ Quantum Computer ቢሆን ግን የማሸነፍ እድላችሁ ዜሮ ይሆናል ምክንያቱም Qubit 1ም 0ም መሆን ስለሚችል አንበሳ ስትጥሉ ሰው,ሰው ስትጥሉ ደሞ አንበሳ እየጣለ ስለሚያሸንፋችሁ!

◽️ አሁን በዋነኝነት የIBM ሪሰርቸሮችን ጨምሮ ብዙ ኩባንያዎች Quantum Computing ላይ ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም፥ በሜዲካል፣ ኬሚስትሪና ኮምፒቲንጉ አለም ያበረክተዋል ተብሎ ከታሰበለት አላማ ብዙም እምርታ አላሳየም!

◽️ Quantum Computers በዚህኛው ትውልድ ለገበያም ሆነ ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሎ ባይታሰብም፣ ለመጪው ትውልድ አሁን እየተጠቅምንባቸው ያሉት ኮምፒተሮች ግን የሞባይል ስልክ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲጀመር ብዙዎች ሲይዙት እንደነበር ሰማኸኝ በለው (Nokia) ስልክ ታሪክ እንደሚሆኑ አትጠራጥሩ!

@techzone_ethio
ውድ የEthio tech zone ቤተሰቦች ሰሞኑን በስራ ጉዳይ እና በተለያዩ የግል ጉዳዮች ምክንያት ሳይመቸኝ ስለቀረ ነበር::
ነገሮች ሲስተካከሉልኝ እመለሳለሁ::

ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ🙏🙏 እንጠይቃለን::

#share
@techzone_ethio
@techzone_ethio
😄ሰብሰብ ብላችሁ(ግን ተራርቃችሁ😜) መጫወት የምትችሏቸውን #ምርጥ የ Android Multiplayer ጌሞች🎮 እንለቃለን።

#በቀጣይ...

@techzone_ethio
Overload Online PvP car shooter.apk
101.8 MB
Overload Online PvP car shooter
#share
@techzone_ethio
በቀጣይ ደግሞ እጅግ ተወዳጅነትን ያገኘው PUBG mobile አሪፍ online mulitplayer ጌም እንለቅላችኃለን::

#stay_tuned

@techzone_ethio
✳️ PUBG MOBILE - NEW MAP: LIVIK

▪️Apk + Obb

▫️How Install

🔺Click ‘install’ Apk File
🔺Wait for the APK to install. Do not run the application yet.
🔺Copy the OBB File /Android/obb/com.tencent.ig/obb_file*

»» File Size : 1.95GB
»» Version : 0.19.0
»» Req : Android 5.1.1 UP + Ram 2
»» Developer : Tencent Games
»» Updated : July 07, 2020
»» CPU : ARM-v7a 86, 64

#share
@techzone_ethio
2025/07/04 06:28:13
Back to Top
HTML Embed Code: