Telegram Web Link
1, ልክ እንደ orginal page አይነት fake page በመስራት የተጠቃሚው password ወይም የተለያዩ ነገሮችን የመጥለፊያ ዘዴ ምን ተብሎ ይጠራል?
Anonymous Quiz
21%
SQL INJECTION
44%
PHSHING
18%
BRUTE FORCING
16%
DDOS ATTACK
ከላይ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት የአለማችን የመጀመሪያው ካሜራ የተተመነለት ዋጋ ስንት ነበር?
Anonymous Quiz
33%
$ 9999
19%
$ 50
29%
$ 25
19%
$ 999
3. ከላይ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት " የኮምፒውተር አባት " በመባል የሚጠራው ማን ነበሩ::
Anonymous Quiz
48%
Charles Babbage
21%
Ada Lovelace
21%
Alan Turing
10%
Herman Hollerith
4, እንደዚ በስፋት የምንጠቀምበትን ኢንተርኔት የሚቆጣጠረው ማን ነው?
Anonymous Quiz
12%
CIA & FBI
13%
7ቱ ኃያላን ሀገራት
46%
17 ሰዎች
28%
NASA
ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ
በቀጣይ ለጥያቄ ቁጥር 4 ማብራሪያ...... #share @techzone_ethio @techzone_ethio @techzone_ethio
🔆ለመሆኑ ኢንተርኔትን የሚቆጣጠረው ማነው

የኢንተርኔትን ደህንነት የሚቆጣጠሩት 14 ሰዎች እንደሆኑ ታውቁ ኖሯል?

❇️ እነዚህ በተለያየ የአለም ክፍል የሚኖሩ ሰዎች ይህን የሚፈጽሙት #በከፍተኛ_ሚስጥር የተያዙ ሰባት የቁልፍ ቁጥሮችን በተናጠል በ 3 ወር እየተቀያየሩ በመያዝ ነው። ይህ ከሳይንስ ፊክሽን ላይ የተወሰደ ታሪክ እንጂ እውነት ላይመስል ይችላል።

❇️ "crypto officers" በሚል ስም የሚጠሩት እነዚህ 14 ግለሰቦች "internet corporation for assigned names and numbers (ICANN) የሚባል ለድረ ገጾች የ #IP አድራሻ ሰውኛ ትርጉም ያለው አድራሻ የሚሰጥና የማስተደደር ስልጣን ያለው ተቋም አባላት ሲሆኑ ዋና ኋላፊነታቸውም የ Domain name system (DNS) አሰራርን የሚያስተናግዱ የኮምፕዩተር #ሰርቨሮችን በከፍተኛ ደረጃ ምንም እክል እንዳይገጥማቸው መጠበቅ ነው።

❇️በ ኦክቶበር 2016 ዲን በተሰኘ ኩባንያ ላይ #በሀከሮች👨‍💻 በተሰነዘረ ጥቃት አማዞንን እና ትዊተርን ጨምሮ በርካታ ድረ ገጾች ጥቃት ደርሶባቸው ለደቂቃዎች ተቋርጠው ነበር።

የ DNS አገልግሎት

#DNS አሰራር ዋና ተግባር በሰው ጭንቅላት መነበብ የሚችልን (ለምሳሌ www.amazon.com) የድረገጽ አድራሻ በኮምፒዩተር መነበብ ወደ ሚችል (ለምሳሌ http፡//173.252.110.27) የ Ip አድራሻ መቀየር ነው። ይህ አሰራር ባይኖር ኖሮ እያንዳንዷን ለመጠቀም የምንፈልገውን ድረገጽ ከላይ በተጠቀሰው አይነት የ IP አድራሻ አስታውሰን መጠቀም ይኖርብን ነበር።

ሀከሮች ተሳክቶላቸው የዲን ኩባንያን ባጠቁበት መንገድ የ ICANN ቤተመረጃ ሰብረው መግባት ቢችሉ በአጠቃላይ የአለምን የኢንተርኔት አሰራር መቆጣጠር ይችላሉ። ለምሳሌ ሰዎችን ትክክለኛ ወዳልሆነና ገንዘባቸውን ሊያዘርፋቸው ወደሚችል የባንክ መሳይ ድረገጽ አታለው ሊወስዷቸው ይችላል።

🔵ለዚህም ነው ይህ ከፍተኛ ጥበቃ የሚያስፈልገው የ DNS server አንድ ሰው ብቻ እንዲቆጣጠረው ላለማድረግ ሰባት ሰዎች ለየብቻ በሚይዙት ልዩ የሚስጥር ኮድ ተቆልፎ🔐 አንድ ላይ ተገናኝተው በአንድነት #ሲያቀናብሩት ብቻ መስራት በሚችል አሰራር ይጠበቃል።

🔴ሌሎች ሰባት ሰዎች ደግሞ በተጠባባቂነት የተመረጡ የሚስጥር ቁልፎች ተሰጥቷቸው #በተጠባባቂነት ይቆያሉ::

#$ha®

@techzone_ethio
@techzone_ethio
ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ
Photo
✳️ የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "Backup" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንደምንችል እስኪ ትንሽ ለማየት እንሞክር::

◽️ በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች ለመያዝ የሚውሉ መገልገያዎችን እንጠቁምዎ:-

◽️ ፍሎፒ ዲስክ /Floppy Disk/:- ትንሽና አነስተኛ መጠን ያለው ዲስክ ሲሆን አቅሙም 1.4 MB ነው፡፡ ጠቃሚ መረጃዎችን በፍሎፒ ዲስክ ለመያዝ በርካታ ዲስኮች ያስፈልጉናል፡፡ የድሮ ኮምፒውተሮች በብዛት ፍሎፒ ዲስክ መጠቀሚያ የነበራቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚመረቱ ኮምፒውተሮች አብዛኞቹ አገልግሎቱ የላቸውም፡፡

◽️ ዚፕ ድራይቭ /Zip Drive/፡- ዚፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር MB መጠን ያላቸው ፋይሎችን /data/ የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ዚፕ ድራይቮችን ለመጠቀም የግድ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካት /hook up/ ይኖርባቸዋል፡፡

◽️ ቴፕ ድራይቭ / Tape Drive/፡- ቴፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር GB (በሺዎች የሚቆጠር MB) መጠን ያላቸው ፋይሎችን ይይዛል፡፡ ይህም ተጨማሪ ድራይቭ በመሆኑ የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት ይኖርበታል፡፡

◽️ ሲዲ በርነር /CD Burner/፡- ሪከርድ የሚያደርጉ ሲዲዎች /CD-Rs/ እስከ 700 MB የሚሆኑ ፋይሎች የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ አሁን ላይ የምንጠቀምባቸው አብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ሲዲ በርነር /CD Burner/ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹም ዲቪዲ በርነር /DVD Burners/ አላቸው፡፡ ዲቪ ዲ አር ኤስ /DVD-Rs/ እስከ 4.7 GB ፋይል የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ስለዚህ በአማራጭ የመጠባበቂያ ፋይል መያዣ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡

◽️ ፍላሽ ድራይቭ /Flash Drive/፣ የ ኤስ ቢ ድራይቭ /USB Drive/ እና ተምብ ድራይቭ /Thumb Drive/፡- ለአንድ ነገር የተለያየ ስያሜ ቢኖርም በኮምፒውተሮቻችን የዩ ኤስ ቢ /USB/ ፋይል መቀበያ በኩል በቀላሉ የሚሰኩ ተነቃይ ድራይቨሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ድራይቨሮች ከ10 MB የሚጀምሩ ሲሆን 1 GB፣ 2 GB፣ 4 GB፣ 8 GB፣ 16 GB፣ 32 GB፣ 64 GB … እያሉ አሁን ላይ 4TB ፋይል የመያዝ አቅም ያላቸው ፍላሽ ድራይቮች በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍላሽ ዲስኮች በቀላሉ በኪስ የሚያዙና ተንቀሳቃሽ ቢሆኑም በቀላሉ ወድቀው ሊጠፉ የሚችሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡

◽️ ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ /External hard Drive/:- ኤክስተርናል ሀርድ ድርይቭ በኮምፒውተር ሲስተሞቻችን ውጪ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ፋይሎችን የምናስቀምጥበት መሣሪያ ነው፡፡ ይህ መሣሪያ /Drive/ ፋይሎችን ይዞ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል እና ከኮምፒውተራችን ጋር በዩ ኤስ ቢ /USB/፣ በፋየርዋየር /Firewire/ ኮኔክሽን ወይም በገመድ አልባ /wirelesely/ ሊገናኝ የሚችል ነው፡፡

◽️ ታይም ማሽን /Time Machine/፡- Time Mac ለተጠቃሚዎች አማራጭ የኤክስተርናል ፋይል መጠባበቂያ መያዣ መንገድ ነው፡፡ ይህ መጠባበቂያ መያዣ ዘዴ ለ24 ሰዓት በቀጥታ ፋይሎቻችንን ለማስቀመጥ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ፋይሎች ተረስተው ለጉዳት እንዳይጋለጡ ያግዛል፡፡ ታይም ማሽን በመጠባበቂያው የሚይዘው የተመረጡ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ድራይቨሩን ነው፡፡

◽️ ኔትወርክድ የሆነ የመረጃ ማካማቻ /Networked Attached Storage/:- ይህ ከአንድ በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮች በኔትወርክ ተገናኝተው መረጃ የሚቀመጥበት ሥርዓት ሲሆን ይህም በስርዓት የተደረደሩ፣ ያልተደጋገሙ የፋይል ማከማቻ ኮኒቲነሮችን እና በርካታ የዲስክ ድራይቭ አካላትን የያዘ ነው፡፡ ይህም በፍጥነት መረጃ ለማግኘት፣ በቀላሉ መረጃዎችን ለማስተዳደርና ለማስተካከል የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡

◽️ ስውር የበይነ መረብ መረጃ ማከማቻ /Cloud Storage/:- ይህ የፋይል ማከማቻ ዓለም አቀፍ የመረጃ ማከማቻ ሥርዓት ሲሆን በኔትወርክ አማካኝነት በመገናኘት መረጃዎቻችን ክላውድ ተብሎ በሚጠራ የመረጃ መጠባበቂያ ሥርዓት /Cloud Server/ ውስጥ የምናስቀምጥበት መንገድ ነው፡፡ በርካታ የክላውድ ማማቻ ዓይነቶች በበየነ-መረብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እነዚህም በነጻ ወይም በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ iCloud፣ Dropbox፣ Google Drive እና OneDrive የታወቁ የመረጃ ማከማቻ መንገዶች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ የሚከማቹበት ሥፋራ በመራጃ በለቤቶቹ ቁጥጥር ሥር ባለመሆኑ የመረጃዎቹ ደህንነት አስተማማኝ እንደስጋት ይታያል፡፡

◽️ ፕሪንት ማድረግ /Printing/:- ምንም አንኳን መረጃዎቻችን በሶፍት ኮፒ የምናስቀምጠውን የህል የተማቹ ባይሆኑ ኮምፒውተሮቻችን በተለያየ ምክንያት ለቀናት አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙበት አጋጣሚ ቢፈጠር ፕሪንት ያደረግናቸው ፋይሎች እጅጉን ይጠቅሙናል፡፡

@techzone_ethio
@techzone_ethio
@techzone_ethio
5, ከኮምፒውተር memory measurement units ውስጥ ትልቁ unit ምን በመባል ይታወቃል
Anonymous Quiz
31%
Terra byte
23%
Geop byte
24%
Peta byte
23%
Bronto byte
Geop byte is the highest measurement unit.

#share
@techzone_ethio
#Tech_Facts

⚡️1Petabyte ለ13.3 አመታት ሙሉ #HD ቪዲዩ መቅዳት📹 ያስችላል።

#አስገራሚ ነው!

@techzone_ethio // @techzone_ethio
Spotify- Premium v8.5.68.904_build_62134459-Mod.apk
31.3 MB
🆔 Spotify Premium v8.5.68.904 Final + Mod Lite [Latest]

♻️ You Can Listen to Artists And Albums, Or Create Your Own Playlist of Your Favorite Songs.


@techzone_ethio
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
መልካም አዲስ አመት!!
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዲሱ አበባየሁሽ 🌼🌼🌼

ሆ ብለን ገባን ሆ ገባን
(ሆ ብለን ገባን ሆ ገባን )
እርሶ አሉ ብለን

አበባየሁሽ...... ለምለም (2)
ባልንጀሮቼ...... ለምለም
ቁሙ በርቀት....... ለምለም
ማክስ ሰርቼ........ ለምለም
ቤት እስክቀመጥ..... ለምለም
እንኳን ጓንትና...... ለምለም
የለኝ ሳኒታይዘር...... ለምለም
ከደጅ አድራለሁ..... ለምለም
ትንሽ ካሣለኝ....... ለምለም
አስሎ አስሎ..... ለምለም
ካስነጠሰኝ..... ለምለም
እገባለሁኝ...... ለምለም
እናት ኳረንቲን..... ለምለም

አደይ በላይፍ ቦይ እጅሽ ታጠቢ
(አደይ በላይፍ ቦይ እጅሽ ታጠቢ)
አደይ ለ20 ሰከንድ እጅሽ ታጠቢ
(አደይ ለ20 ሰከንድ እጅሽ ታጠቢ)

ሽቴ አበባ ሽቴ አበባዬ ( አዬ ሽቴ አበባዬ)
ሽቴ አበባ ስትለኝ ከርማ (አዬ ሽቴ አበባዬ)
ጥላኝ ጠፋች ኮረንቲን ገብታ ( አዬ ሽቴ አበባዬ)

ይጠበቅ ርቀት የማምዬ ቤት
ይቀመጥ ሳኒታይዘር ካባብዬ በር
ይለበስ የአፍ ጭንብል ኮሮናን ለመግደል
ይታጠብ እጃችን ከኮቪድ ለመዳን



ከብረው ይቆዩ ከብረው
ባመት ኳረንቲን ወጠው
30 ሳኒታይዘር ገዝተው
የአፍ ጭንብሎን ለብሠው
እጆን ለ20 ሰከንድ ታጥበው
2 ሜትርም ርቀው
ምልክቱንም አውቀው
ካዩ ምልክቱን ደውለው
የመ ህጎችን ጠብቀው
ከብረው ይቆዩን ከብረው
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

#share
@techzone_ethio


🌻🌻🌻እንኳን
🌻🌻🌻🌻ለአዲሱ
🌻🌻🌻🌻🌻አመት 2013
🌻🌻🌻🌻🌻🌻አደረሳችሁ
🚩 የስልኮች ባትሪ ቶሎ የሚያብጥበት ምክኒያትቶች

1-ባትሪ በመልቲ ቻርጅ ማድረግ📵
2-ስልክን ለረጅም ጊዜ ቻርጅ ላይ ማቆየት💈
3-ስልክን ቻርጅ ላይ ሰክቶ ለረጅም ስዓት መጠቀም🔌
4-ኦሪጅናል ባትሪዎችን አለመጠቀም⚠️
5-ኦሪጅናል ባልሆኑ ቻርጀርኦች ስልክን ቻርጅ ማድረግ⚠️

#share
@techzone_ethio
⚡️⚡️ዛሬ ይዘን የመጣነዉ ሁሉም ሰዉ ስልኩ ላይ ሊኖረዉ የሚገባ አሪፍ የሆነ አፕሊኬሽን ነዉ

🔰ስሙ -Google Lens ይባላል።

🤔ይህ አፕሊኬሽን ምንም አይነት የማናዉቀዉን ነገር በቀላሉ እንድናዉቅ ይረዳናል።

ለምሳሌ:

🔴መኖሪያ ቤታቹ አከባቢ የሚገኙ ማንኛዉም አይነት እቃዎች መረጃቸዉን ለማግኘት፣ የምንጠቀማቸዉ የመድሀኒት አይነቶች እና ምንነቱን መረጃ ለማግኘት፣ ሌሎችንም ስራዎች ይሰራል።

🔵ይህን አፕሊኬሽን ለመጠቀም ስልኩ አሪፍ የሆነ የካሜራ ጥራት ቢኖረዉ ይመረጣል ምክንያቱም እኛ ስለፈለግነዉ ነገር መረጃ ስንፈልግ ያንን ነገር ፎቶ ማንሳት ስለሚያስፈልግ ነዉ።

🔴Mobile Data(Package ቢሆን ይመረጣል) ወይም #WIFI አስፈላጊ ነው።

🔵የምንፈልገውን ነገር #ፎቶ_ካነሳን በኋላ ከኢንተርኔት🌐 ጋር ማገናኘት ይኖርብናል።



#share
@techzone_ethio
@techzone_ethio
2025/07/03 16:40:55
Back to Top
HTML Embed Code: