Telegram Web Link
ላንተ የሚሰሰት ነገር የለኝም። በፍጹም አይኖረኝምም። ዛሬም ልክ የዛሬ 20 አመት የነበረው ፍቅሬ አሁንም አለ። ሳያረጅም ይቀጥላል...!

መቼም ወደ ልጅነቱ በኃሳብ ነጉዶ ያን ብሩህ ዘመን አስታውሶ የማይደሰት የለም። እኔም ወደ ልጅነቴ ስነጉድ የሚቀድመው ትዝታዬ፤ ሔዋን እንደ ዋዛ፣ አቦጊዳ፣ እንደ ቢራቢሮ እና ለማን ልማሽ የተሰኘው ሙዚቃክ እና ልብን የሚያባባው ድምጽህ ነው።

የሰው ልጅ ህይወቱ ከሆነ ነገር ጋ ይቆራኛል የኔም ህይወት ከሙዚቃዎችህ ጋ ትልቅ ትስስር አላቸው። በየእድሜ ደረጃቸው የኔን እድሜ ያስታውሱኛል። ሁሉንም ሳደምጣቸው ትክክለኛ ስሜት ውስጥ እኔን ከመንከር ልቀው በተለቀቁበት ዘመን የነበረውን እያንዳዱን የህይወቴን ጉዞ ያስታውሱኛል። ዛሬ እስኪመስለኝ ድረስ በኃሳብ ሰረገላ ካለፈው ዘመን ወስደው በሐሴት ያናውዙኛል። ደስታን በሚሰጥ ስሜት ያቆዩኛል። የወጣትነት እድሜ በከፍተኛ ድብርት ለመጠቃት የተጋለጠ ነው። ይኼ ስሜት ሲጀማምረኝ ማስወገጃው ጸሎትና ያንተ ሙዚቃዎች ናቸው። ...ሊገለጽ በማይቻል መልኩ የሆነ ነገር ከላዬ ተገፎ ደግሞ የሆነ ኃይል ስጎናጸፍ ይታወቀኛል። የቱንም ያህል እየጮኸ ቢደመጥ የማይሰለቸኝ ያንተ ሙዚቃ ብቻ ነው።

የሌላ ሰው ስራ ሆኖ የሶስት ደቂቃ ሙዚቃ ለመስማትና ከማልወደው ሰው ጋ አንድ ሲኒ ቡና ጠጥቶ ለመጨረስ የሚጨንቀኝ ሰውዬ አምስቱንም አልበሞችህን አድምጬ የመድረክ ስራዎችህን አጣጥሜ ነጠላ ዜማዎችህን እያደመጥኩ በተለቀቁበት ዘመን እየተንሸራሸርኩ ደስታዬን ሳጣጥም ጊዜውም ሰዓቱም እንደምን ነጎደ ቢሉኝ አላውቅም።

ከሰባት አመቴ ጀምሮ ከማውቃቸው እስከ አሁንም ለ20 አመታት አብረውኝ ከዘለቁ በጣት ከሚቆጠሩ ግለሰቦች መኃል አንዱ እና ዋነኛው አንተ ነህ! ስለምወድህ፣ ስለማከብርህ፣ ስለምሳሳልህም ጭምር ደስተኛ ነኝ።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ነፍስዎ በሰላም ትረፍ...
#አፄ_ዮሐንስ_4ኛ...

"ጎንደር ሃይማኖት ቆማ ስታለቅስ
አንገቱን ሰጠላት ዳግማይ ዮሐንስ"

ለአገር ዳር ድንበር መጽናት በምጽዋ ተዋድቀው አንገታቸውን ለአገራቸው በክብር የሰጡ፤ ታላቁ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን ልደታቸው ነው።

አፄ ዮሐንስ አራተኛ ከሹም ተንቤን ምርጫ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ሥላስ ድምፁ ሐምሌ 5 ቀን 1825 ዓ.ም በትግራይ ተምቤን ልዩ ስሙ ማይ በሀ ተብሎ በሚታወቀው ሥፍራ ተወለዱ።

አጼ ዮሐንስ በአጼ ቴዎድሮስ የተጀመረውን የአንድነት ሥራ አስቀጥለዋል። የሀገራችንን ዳር ድንብር ከውጪ ወራሪ ኃይል ጠብቀዋል። በተለይ በጉንደትና በጉራዕ አሁንም ቢሆን እየዳነፋችብን የምትገኘውን የግብጽን ጦር ድል አድርገው የሀገሬን አፈር በጫማቸው እንኳን ይዘው እንዳይወጡ በሚል እግራቸውን አሳጥበው ከኢትዮጵያ ድንበር አባረዋል።

አጼ ዮሐንስ ለኢትዮጵያ ልዩ ክብር እና ፍቅር ነበራቸው። ይህም አሁን ድረስ በሚጠቀስ ዘመን አይሽሬ አባባላቸው እንዲህ ተገልጾ በጉልህ ይታያል፥ "የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ፥ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት። ሁለተኛ ክብርህ ናት። ሦስተኛም ሚስትህ ናት። አራተኛ ልጅህ ናት። አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር ፥ የዘውድ ክብር፥ የሚስት ደግነት፥ የልጅ ደስታ፥ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነስ።"

ጃኑሆይ እንኳንም በታላቂቷ ኢትዮጵያ ላይ ንጉሥ ሆነው አለፉ።
በመወለድህ ከሚደሰቱት በላይ እደሰታለሁ። ልደትህን በማክበር ደስ ከሚሰኙም በላይ ደስ እሰኛለሁ። በአንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን በድፍን ኢትዮጵያ እና አድናቂዎችህ ባሉበት የዓለም ጥግ ሁሉ ልደትህ በድምቀት እንዲከበር እመኛለሁ።

ቴዲዬ አድርግ ብለኸኝ እምቢ ብዬ አላውቅም። አዘኸኝ እምቢ ያልኩህ ትዕዛዝህ የለም። አይኖርምም። ልከኸኝ የዘገየውበት ቀን የለም። የኔ ጉዳይ ይቆይ ይዋል እንጂ ያንተን ፈጽሚያለሁ። ወደፊትም በደስታ እፈጽማለሁ። ሁሌም ደስ እያለኝ እታዘዝኃለሁ።

አንበሳዬ ቅን ነህና ሀሳቤን ትረዳለኽ! ድካሜንም ዋጋ ትሰጠዋለኽ! ሀሳብህ ከማንም በላይ ይገባኛል። ለዘመናት አንተን በብዕሬ ሳመሰግንህ እና የማውቀውን እውነት በተረዳሁት ልክ ያለ ስስት ስከትብ እና ለወዳጆችህ ሳደርስ ኖሪያለሁ። ይኼም የሚቀጥል ተግባሬ ነው።

በዚህች ቀን እኔ የመልካም ምኞት መግለጫዬን ቀድሜ ማድረስ ሲገባኝ ስልክህ ሲቀድመኝ ድንጋጤው አይጣል ነው። ለአንዲት ደቂቃም ቢያወሩህ ቁም ነገር አዘል ቀልድህ የማያስቀው ብርቱ የለም።

እወድኃለሁ! አከብርኃለሁ! መልካም ልደት አንበሳዬ!

ከፍጹም አክባሪ ወንድምህ!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

Graphics by፦ (#ጉዱ_ካሳ)
እንዳንቺ አይነት ሚስት ለቴዲ አፍሮ ታስፈልገው ነበር። እሱን የምትደግፍ አብራው የምትቆም። የምትንከባከበው። እግዚአብሔር ይመስገን እንደ እናት የሆንሽለትን አንቺን ሰጠው። የሶስት ልጆች አባት አደረግሽልን። አሁንም እግዚአብሔር ይመስገን!

አንዳዴ ለካ ቃላትም የሚያከብሩትን ሰው ለመግለጽ አቅም ያጣሉ... ኤሚዬ አንቺን ከዚህ በፊት እንዲህ ብዬሽ ነበር...

"እንደ ግጥሜ ርዕስ፤ እንደ ስንኝ ቋጠሮ፣
እንደ ጠቢብ ቅኔ፤ እንደ ፀሐይ ኑሮ፣
ልብሽ ብሩህ ነው፤ ዘውትር የሚፈካ፣
መልክሽ በለስ ነው፤ ውዴ ባንቺ 'ረካ።"

እውነቴን ነበር ልብሽ ብሩህ ነው።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ሁሌም በማይሰሰት ፍቅር እወድኃለሁ። ለሰው ልጆች ሁሉ ያለኽ አክብሮት እና ምስጋናክ አቅም ይነሳኛል። ጤናህን አብዝቶ ይስጥህ!

ግን ይኼን ልበልኽ... እንደሚወዱህ ከነገሩክ በላይ አብልጬ እወድኃለሁ። እንደሚያከብሩህ ከነገሩክ በላይም አከብርኃለሁ። መውደዴን በአንደበቴ ብቻ ሳይሆን በተግባር እየገለጽኩ በአደባባይም እየመሰከርኩ ለዘመናት ኖሪያለሁ። ይኼ የሚቀጥል ተግባሬ ነው። ለአጼ ቴዎድሮስ ገብርዬ፣ ለአጤ ምኒልክ ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ላንተ ደግሞ እኔ አለሁልህ!

እወድኃለሁ!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
2025/07/03 14:57:22
Back to Top
HTML Embed Code: