Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
ሰው መውደድ ቢያደክም እኔን ይደክመኝ ነበር። አንተን ማድነቅ እና አንተን መውደድ ቢጎዳ ኖሮ እኔ እጎዳ ነበር። ግን ፍቅር ማንንም ጎድቶ አያውቅም። ማንም ቢሰነዝር የቱም ቢከነዳ አልደነግጥም። ከአቋሜም አያዛንፈኝም። አንተን ግን እምቢ እንድልህ እንኳን አቅም አጣለሁ...! ብዙዎች አብዝተው የሚወዱህ፣ የሚያደንቁህም አሉ! የኔ ይለያል ወይንም ይበልጣል ብል ድፍረት ሊመስል ይችላል ግን ለራሴም እስኪደንቀኝ ድረስ አምርሬ እወድኃለሁ። ጥቃትህ ያንገበግበኛል። አንድ የእናቴን ልጅ የበደሉት ያህል የደረሰብህ ነገር ሁሉ ይቆጠቁጠኛል። ቴዲሻ ደስታህን እና ስኬትህን ዘወትር እመኛለሁ።
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
https://www.tg-me.com/PoetTataAfro
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
https://www.tg-me.com/PoetTataAfro
ለአፍሪካ የ44 አመታት የብርሃን ጮራ! ግርማዊ ቀዳማዊ አጤ ኃይለ ስላሴ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
በ1884 ዓ.ም በወርሃ ሐምሌ 16 /ኪዳነ ምህረት/ ዕለት ልጅ ተፈሪ ሐረር ውስጥ በምትገኝ ኤጀርሳ ጎሮ በተሰኘች አከባቢ /ሰፈር/ ተወለዱ። ልጅ ተፈሪ እናት እና አባታቸውን በልጅነት እድሜያቸው ያጡ ሲሆን አባታቸው የምኒልክን ዙፋን ይወርሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ራስ ተፈሪ መኮንን ሐረርጌን ለ6 አመታት አስተዳድረዋል። አባታቸው ልዑል ራስ መኮንን ልጃቸው ትምህርት ገና ሲጀምሩ ፈረንሳይኛ ቋንቋን እንዲያጠኑ ስላደረጓቸው ራስ ተፈሪ ፈረንሳይኛን አቀላጥፈው ይናገራሉ። የልጅ እያሱ መንግስት ወድቆ በምትኩ ንግስተ ነገስት ዘውዲቱ ዙፋን ሲይዙ ራስ ተፈሪ መኮንን በ25 አመታቸው ገደማ አልጋ ወራሽ ሆኑ።
ተፈሪ መኮንን በአልጋ ወራሽነት ሥልጣን ላይ በነበሩበት የ13 ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በውጭ ፖሊሲ በኩል አገሪቱን ወደ ዘመናዊ አስተዳደር ለማምጣት፣ በአውሮፓ ለመጀመርያ ጊዜ በከፍተኛ ባለሥልጣን ደረጃ ጉብኝት በማድረግና በአገር ውስጥ ከነበሩ ኤምባሲዎች ጋርም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማጠናከር ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገቡ ታላላቅ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያን በዓለም አቀፉ የመንግሥታቱ ማኅበር ቀደምት አፍሪካዊት ሀገር በማድረግ በአባልነት አስመዝግበዋታል፡፡ በአገር ውስጥም አንፃራዊ ዘመናዊነት እንዲፈጠር ለማድረግ ያደረጉት ጥረት በቀላሉ የሚገመት አልነበረም፡፡
በቁመት አጭር ከሚባሉት ተርታ የሚሠለፉት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እጅግ መልከ መልካም ሲሆኑ በእነዚያ በጣም እረጃጅም በሆኑት ክብር ዘበኞቻቸው መካከል ሆነው ሲታዩ የእሳቸው ግርማ ሞገስ ነበር ጎልቶ የሚታየው፡፡
የ44 ዓመታት ረጅም ዘመን የንጉሠ ነገሥትነት አመራራቸው በአብዛኛው የተረጋጋና ሰላም የሰፈነበት ሲሆን፣ በግላቸውም የሚከተሉት ፍልስፍና እንዲሁ የሰከነ ነበር፡፡ ማለዳ ቤተ ክርስቲያንን ከመሳለም የሚጀምረው የየዕለቱ ተግባራቸው የውጭ አገር ከፍተኛ ባለሥልጣኖችን በመቀበል የልማት መሠረት ለመጣል፣ በሕዝባቸው መሀል በመገኘት የተመራቂዎችን ልብስ ለብሰው ወጣቶችን በመመረቅ፣ የታመሙትን በሆስፒታሎች ላይ እየዞሩ በመጎብኘት፣ እርዳታቸውን ለሚሹ በመድረስ፣ በዓለም አቀፍም ሆነ በአገር አቀፍ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ጋዜጣዊ መግለጫ የመስጠት ተግባሮቻቸው ጎልተው የሚታዩ ነበሩ፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ለየት የሚያደርጋቸው ታድያ ይኼ ሁሉ ሲከናወን የባህርይ መለዋወጥ አለመታየቱ እና ፍፁም ትዕግስተኛ በመሆናቸው ነበር፡፡ በፖለቲካዊ አለመግባባቶች እና በጭቅጭቆች መኃልም እንኳን ከስሜታዊነት የጸዱ በተረጋጋ ስሜት በጥዑም አንደበታቸው የሚሰማቸውን በመመለስ የተካኑ ፍፁም ትሁትም ነበሩ።
ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ በስሜት የማይነዱ ከአፋቸው ክፉ ቃል እንዳይወጣ እጅግ የሚጠነቀቁ እያንዳዱ ተግባራቸው በማስተዋል የሆነ ታላቅ የፖለቲካ ሰው ስለመሆናቸው ሀገር የመሰከረላቸው ጨዋ ንጉሥ ነበሩ። ከወረራው በኋላ የሁለቱን ኃያላን አገራት በኃሪ በማቻቻል ለሀገራቸው ሉዓላዊነት የከፈሉት መስዋዕትነት፣ ለሀገራቸው በሚበጀው መንገድ መሄዳቸው ብሎም ባደጉት አገራት የሚገኙ ፖለቲከኞች ካቀዱት እና ከገመቱት በተለየ መልኩ የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ በማሻሻላቸው የአዕምሯቸው ልህቀት እጅጉን የበሰለ እና ተግባራቸውም የሚደነቅ ነበር።
ንጉሡ እንደ ሰው ልጆቻቸውን በቀበሩ ጊዜ ወላድ ይፍረደኝ ብለው በአደባባይ አንብተዋል። አልቅሰውም አስለቅሰዋል። ለሌሎች ደስታን በመስጠት ቤትና ኑሮን በመመስረት የሚታወቁት እኚሁ ንጉሥ በህይወት ዘመናቸው ከባድ ሀዘን አስተናግደዋል። እርግጥም ጃኑሆይ ከልጅነት ዘመናቸው ጀምሮ እናታቸውን በማጣት ካደጉም በኋላም አባታቸው በማረፋቸው ሀዘናቸው የበዛ ነበር። ጃኑሆይ በሁለት ዘመን ሰዎች መኃል ተሰቃይተዋል። /በፊት በነበረው መኳንንት እና እሳቸው በፈጠሩት የተማረ ኃይል።/ የሆነው ሆኖ ንጉሡ ነገሮችን ማመጣጠን የሚችሉ ናቸውና ለ44 አመታት የድካም ጉዞ ተጉዘው ከኢትዮጵያም አልፈው ለአፍሪካ የለውጥ ፋና ሆነዋል። ጠያቂ ትውልድ አፍርተዋል። ዘመናዊት አፍሪካን አንፀው ሉዓለዊነቱን ለሚጠብቅ ህዝብ አባት ሆነዋል። በመላው አፍሪካ የአባትነት ምክራቸው ተቀባይነትን አግኝቷል። በመላው ዓለም ላይ በቆሙበት መድረክ ሁሉ ቃላቸው ከመሬት ጠብ ሳይል በተግባር ተፈፅሟል። የሀያላኑን ሀገር መንግስታት በሚፈትኑት ንግግሮቻቸው በዓለም ህዝብ ተደንቀዋል። ታላላቅ ጋዜጦች አክብረው አወድሰዋቸዋል።
ግርማዊ ቀዳማዊ አጤ ኃይለ ሥላሴ ትጠፋለች ትወድማለች የተባለችን አፍሪካን ወደ መኖር ቀይረዋል። ጥቁሮችን ከሰቆቃ ህይወት ደግፈው በማውጣት አፍሪካ ችግሯን በራሷ የምትፈታ አህጉር እንድትሆን የአውሮፓ እና የተቀሩ ዓለም መንግስታትን ተጋፍጠዋል። ጥቁሮች እንደ ኢትዮጵያ የራሳቸው ንጉሥ እንዲኖራቸው ያደረጉት ትግል ፍሬ አፍርቶ መላው የአፍሪካ ተወላጅ እንደ ወንድማማች እጅ ለእጅ ተያይዞ እንዲደጋገፍ በማድረጋቸው በዘመናቸው ታላቅ የአህጉር አባት ለመሆን በቅተዋል። ዛሬም ድረስ በዓለም ያለ የጥቁር ህዝብ በአባትነታቸው ይኮራል። አፍሪካም የነፃነት አባቷን ዘውትር ታወድሳለች።
የእኚህን ታላቅ ንጉሠ ነገሥት 129ኛ የልደት በዓል ለማክበር እንኳን አደረሰን ለማለት እወዳለሁ። 🎂🎂🎂 #አባብዬ እንኳን ተወለዱልን!!

ቴዲዬ ልዑል እግዚአብሔር ዘርህን አብዝቶ ይባርክ። ብዙ የሆንክላትን ቅድስት ኢትዮጵያን የሚወዱ ሀይማኖታቸውን ፈጽመው የሚጠብቁ ይሁኑልህ። በኩራት በኖርክባት አገር ላይ በተግባራቸው እጥፍ ድርቡን የምትከበርባቸው ይሆኑልህ ዘንድ ቅዱሥ የሆነ እግዚአብሔር በጥበብና በሞገሥ ያሳድግልህ!
ሰምዐቱ አቡነ ጴጥሮስ
(ሐምሌ 22/1928 አዲስ አበባ
"እኔ ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ውርደትን እፀየፋለሁ። አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ስለሆኑ ቢፈልጉ ጣሊያንን ከፈለጉም ሌላ ፋሽስት መቀበል ይችላሉ።
"ቅድስት አገሬ ምድሯን ባንዳ እንዳይረግጠው ወራሪም እንዳይዘው ገዝቻለሁ። አገሬ ዘላለማዊ ነፃነት እንዲኖራት እናንተ ፋሽስቶች እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ባውቅም ሁሉንም ስለ አገሬ ክብር እቀበለዋለሁ። ግን የሞት ፅዋን የምቀበለው ለኢትዮጵያ ዘላለማዊ ነፃነት ነው። "
ሰምዓቱ አቡነ ጴጥሮስ በስምንት አልሞ ተኳሽ የጣሊያን ፋሽስት ወታደሮች በጥይት ተደብድበው ሊሞቱ ባለመቻላቸው እንደገና በሦስት አልሞ ተኳሾች ጭንቅላታቸው በጥይት ተመቶ እንዲሞቱ ተደረገ።
የአቡነ ጴጥሮስ ንግግሮች
"ይህች የቆማችሁባት ምድር ለእብሪተኞች ረመጥ እንደ እሳት የምታቃጥል መሆኗን ብታውቁ ምን ያህል በሃዘን ጥርሳችሁ እየተፋጨ በተንገጫገጨ ነበር፣ ግን ግብዝ ሆናችኋል በኃይላችሁ ተማምናችኋል..."
"እኔየምፈራው የሰው ሰይፍ አይደለም የእናንተ ጉልበት የእናንተ እብሪት ትንሽ ጉም ነው፣ ትንሽ ንፋስ የሚበትነው ነው እና የፋሽስትን ኢጣልያንን የበላይነት ከምቀበል ሞቴን እመርጣለሁ።"
"ወደ እግዚያብሔር እጆቿን የዘረጋችውን ቅድስት ሃገሬን እብሪተኛ ሲደቀድቃት እንዲኖር አልፈቅድም። እምነቴም ይህን በፍፁም አይፈቅድልኝም"
ሰምዐቱ አቡነ ጴጥሮስ ከሚገደሉበት ስፍራ ላይ ሲደርሱ አራቱን ማዕዘን በመስቀላቸው ባረኩ። በሕዝቡም ፊት ቆመው "ፋሺስቶች የሀገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት አይምሰላችሁ። ሽፍታ ማለት ያለሀገር መጥቶ የሰውን ሀገር የሚወር ይህ በመኻከላችሁ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው። የኢትዮጵያም መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን።" ብለው ተናገሩ።
አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ሊቀበሉ በተዘጋጁበት ሰዓት የተናገሩት ከዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ የተወሰደ።
ዘለዓለማዊ
የአባታችን የአቡነ ጴጥሮስ በረከታቸው ይደርብን!

መልካም ዜና...!
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ለቴዲ አፍሮ የክቡር ዶክተሬት ማዕረግ ሊሰጠው ነው። ዛሬ ሴኔቱ ባደረገው ስብሰባ ለአርቲስቱ የዶክትሬት ማዕረግ እንዲሰጠው አጽድቋል።
የኔ አንበሳ ከዚህ በኋላ በብዙ ማዕረጋት ትዋብ ዘንድ እመኛለሁ። የክብር ዶክትሬት ማዕረጉም ከጎንደር በመሆኑ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል።