Telegram Web Link
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ቤተሰብ🥰
ቴዲዬ ልዑል እግዚአብሔር ዘርህን አብዝቶ ይባርክ። ብዙ የሆንክላትን ቅድስት ኢትዮጵያን የሚወዱ ሀይማኖታቸውን ፈጽመው የሚጠብቁ ይሁኑልህ። በኩራት በኖርክባት አገር ላይ በተግባራቸው እጥፍ ድርቡን የምትከበርባቸው ይሆኑልህ ዘንድ ቅዱሥ የሆነ እግዚአብሔር በጥበብና በሞገሥ ያሳድግልህ!
ሰምዐቱ አቡነ ጴጥሮስ
(ሐምሌ 22/1928 አዲስ አበባ

"እኔ ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ውርደትን እፀየፋለሁ። አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ስለሆኑ ቢፈልጉ ጣሊያንን ከፈለጉም ሌላ ፋሽስት መቀበል ይችላሉ።

"ቅድስት አገሬ ምድሯን ባንዳ እንዳይረግጠው ወራሪም እንዳይዘው ገዝቻለሁ። አገሬ ዘላለማዊ ነፃነት እንዲኖራት እናንተ ፋሽስቶች እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ባውቅም ሁሉንም ስለ አገሬ ክብር እቀበለዋለሁ። ግን የሞት ፅዋን የምቀበለው ለኢትዮጵያ ዘላለማዊ ነፃነት ነው። "

ሰምዓቱ አቡነ ጴጥሮስ በስምንት አልሞ ተኳሽ የጣሊያን ፋሽስት ወታደሮች በጥይት ተደብድበው ሊሞቱ ባለመቻላቸው እንደገና በሦስት አልሞ ተኳሾች ጭንቅላታቸው በጥይት ተመቶ እንዲሞቱ ተደረገ።

የአቡነ ጴጥሮስ ንግግሮች

"ይህች የቆማችሁባት ምድር ለእብሪተኞች ረመጥ እንደ እሳት የምታቃጥል መሆኗን ብታውቁ ምን ያህል በሃዘን ጥርሳችሁ እየተፋጨ በተንገጫገጨ ነበር፣ ግን ግብዝ ሆናችኋል በኃይላችሁ ተማምናችኋል..."

"እኔየምፈራው የሰው ሰይፍ አይደለም የእናንተ ጉልበት የእናንተ እብሪት ትንሽ ጉም ነው፣ ትንሽ ንፋስ የሚበትነው ነው እና የፋሽስትን ኢጣልያንን የበላይነት ከምቀበል ሞቴን እመርጣለሁ።"

"ወደ እግዚያብሔር እጆቿን የዘረጋችውን ቅድስት ሃገሬን እብሪተኛ ሲደቀድቃት እንዲኖር አልፈቅድም። እምነቴም ይህን በፍፁም አይፈቅድልኝም"

ሰምዐቱ አቡነ ጴጥሮስ ከሚገደሉበት ስፍራ ላይ ሲደርሱ አራቱን ማዕዘን በመስቀላቸው ባረኩ። በሕዝቡም ፊት ቆመው "ፋሺስቶች የሀገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት አይምሰላችሁ። ሽፍታ ማለት ያለሀገር መጥቶ የሰውን ሀገር የሚወር ይህ በመኻከላችሁ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው። የኢትዮጵያም መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን።" ብለው ተናገሩ።

አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ሊቀበሉ በተዘጋጁበት ሰዓት የተናገሩት ከዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ የተወሰደ።

ዘለዓለማዊ
የአባታችን የአቡነ ጴጥሮስ በረከታቸው ይደርብን!
መልካም ዜና...!

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ለቴዲ አፍሮ የክቡር ዶክተሬት ማዕረግ ሊሰጠው ነው። ዛሬ ሴኔቱ ባደረገው ስብሰባ ለአርቲስቱ የዶክትሬት ማዕረግ እንዲሰጠው አጽድቋል።

የኔ አንበሳ ከዚህ በኋላ በብዙ ማዕረጋት ትዋብ ዘንድ እመኛለሁ። የክብር ዶክትሬት ማዕረጉም ከጎንደር በመሆኑ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ንጉሡ በሰላም ገብቷል...!

መጣሁልሽ ጎንደርዬ...💚💛❤️
ስለ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን...

ቴዲ አፍሮ ዛሬ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬቱን ተቀብሏል። የክቡር ዶክትሬቱን በይፋ ከተቀበለበት ሰዓትም ጀምሮ የሙሉ ስም አጠራሩ "ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን" ሆኗል። ይኽ አርቲስት ለዚህ ክብር የበቃው ለዘመናት በአገራዊ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊ እና በሀይማኖታዊ ጉዳይች ላይ በጽኑ ተግቶ በመስራቱ እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ደብዝዞ እንዳይቀር ይልቁንም ኢትዮጵያዊነት እንዲገዝፍ ለአመታት በሙያው በመትጋቱ ነው። ይኼንንም እውነት የጎንደር ዩኒቨርስቲ በጽሁፍ አርቅቆ ለታዳሚያን ተርኳል። የውኃ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ለቴዲ አፍሮ ያላቸውን አክብሮት ሲገልጹ "ወንድሜ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ እንኳን ደስ ያለህ.." በማለት ነበር።

ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በመርኃ ግብሩ ላይ ለቤተሰብቹ ለጓደኞቹ ለባለቤቱና የክብር ዶክትሬት ላበረከተለት ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅት ከባድ የጭንቀት ወቅት እንደሆነ ገልጾ ይኼ ወቅት እንደ እናቶች ምጥ ነው ከከባድ ምጥ በኋላ ነፍሰ ጡር ሴቶች ልጅ ወልደው እንደሚገላገሉ ሁሉ ኢትዮጵያም ከዚህ ጭንቅ በኋላ ፍጹም ሰላም ትሆናለች በማለት ምኞቱን ጭምር አስተላልፏል። አክሎም ለዘመናት ኢትዮጵያን በጎሳ እና በዘር ከፋፍሎ ያዳከማት ኃይል ዳግም የቀደመውን እድል እንዳያገኝ ሆኖ መሞቱን በመግለጽ ወጣት ተማሪዎች በተለይም በብዙ ልፋት ለተመረቁ አገር ተረካቢዎች የኢትዮጵያን ጉዳይ አደራ ብሏል።

ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በአድናቂዎቹ በጓደኞቹ እንዲሁም በዘመድ አዝማዶቹ ታጅቦ ወደ ጎንደር የገባ ሲሆን በከተማው ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። የጎንደር ህዝብም ባገኘው አጋጣሚ ለክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ያለውን ፍቅር እና አክብሮት ገልጾለታል። በዚህ እለት በመላው ዓለም የሚገኙ አድናቂዎቹ እና የመገናኛ ብዙኃን የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱን በሰፊው ሲያሰራጩ ውለዋል።

ማሳሰቢያ

ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ወደ ፕሮግራሙ ስፍራ እንዲገኝ የተቀጠረለት ሰዓት 4:00 ሰዓት ሲሆን የመድረክ መሪው በተደጋጋሚ ስሙን ሲጠራ የቆየ በመሆኑ በአንዳድ ግለሰቦች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቴዲ አፍሮ እንዳረፈደ ተደርጎ ሊወራ ችሏል። እውነታው ግን አርቲስቱ ሰዓቱን ፍጹም አክበሮ በቦታው ተገኝቷል።

የግርጌ ማስታወሻ እና ምስጋና...!

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዲ አፍሮ በተበረከተለት የክቡር ዶክትሬት ፍጹም ደስተኛ የሆነ ሲሆን አድናቂዎቹ እና ቤተዘመዱ ሁሉ የጎንደር ዩኒቨርስቲን ከነመላው አመራሩ ያመሰግናል። በተጨማሪም በጎንደር ከተማ በቆየንበት ወቅት በማንኛውም ሁኔታ ለተባበራችሁን እና ለትብብር ዝግጁ መሆናችሁን ለገለጻችሁልን በጠቅላላ እንዲሁም ለመላው የጎንደር ህዝብ ልባዊ ምስጋናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ዓለማችን ላይ በየዘመኑ ድንቅ የተባሉ ጥቂት ሰዎች አሉ። በየዘመኑም ይፈጠራሉ። ለኔ በዚህ ዘመን ካንተ በቀር አንድ ሁለት ብዬ የምቆጥረው ሌላ ሰው የለኝም። አገሬ በጭንቅ ከተዋጠችበት ዘመን ጀምሮ የልጆቿን እና የሰንደቋን ነገር ችላ ሳትል እጅህን ወደ ነበልባል እሳት የሰደድክ አንተ ብቻ ነህ። አንተ "ለኔ" ብሎ አማርኛ አታውቅም። አንተ "ለኔ" ብሎ ግብዝነት አይነካካህም። በኪነ ጥበቡም ዘርፍ የዓለም የድል /የበላይነት/ ሰንጠረዥን በሩጫ ብቻ ሳይሆን በሙዚቃም አድቅቆ አንደኛ መሆን እንደሚቻል ብቻህን ታግለ፤ ድልንም አስመዝግበ አሳይተኸናል። አገሬ ከፍላ የማትጨርሰው የአንተ እዳ አለባት! ለወገኔ አመስግኖክ የማይፈጽመው ደግነትን አሳይተኸዋል። ኢትዮጵያ ባንተ ተግባር ለዘለዓለም ትኮራለች። ታሪኳን የዘከርክ፤ ክብሯን ያሳሰብክ፤ ድሏን ያበሰርክ ጀብዷንም የመሰከርክ ድንቅ እና ፍጹም ጥበበኛ ልጇ አንተ ነህ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን... እ...ን...ወ...ድ...ኃ...ለ...ን!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
2025/07/03 09:23:58
Back to Top
HTML Embed Code: