Telegram Web Link
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል የሆነው ወጣት የቴዲ አፍሮን ኢትዮጵያ የተሰኘውን ሙዚቃ ሲጫወት

https://youtu.be/cD30bSzW7E0
ዛሬ ጎልምሰ አይደለም እኔ አንተን የማውቅህ። ያኔ ገና እነ አቦጊዳን ስታዜም እንጂ! ያኔ ገና ባይገርምሽ እያልክ በተንቀሳቃሽ ምስል ስትመጣ እንጂ። ያኔ ነው...! ስትጀምር ጀምሮ ያለ አንዳች ማመንታት በለጋ ልቤ መርጬኃለሁ። ከእናት እና ከአባቴ በቀር ሌላ ሰው መውደድ ሳላውቅበት በፊት አንተን በኃይል ወድጄኃለሁ። በያንዳዱ ጉዞዎችህ አብሬ ቆሚያለሁ! ብዙ አልፈ ብዙ ተጋፍጠ የራስህን ቤት መመስረት ችለኃል። የራስህን ጎጆ ሳትመሰርት የሌሎችን ጎጆ ቀልሰኃል። ከአብራክ የወጡ ልጆች ሳይኖሩህ ለሌሎች ልጆች አባት ሆነኃቸዋል። የብዙ ምስኪኖችን እንባ አብሰኃል። ለወገኖቻችን የዋልከውን የሰው ልጅ ቢቆጥረው ያጎለዋል በማይረሳው በእግዚአብሔር ዘንድ ግን በክብር ተቀምጧል።

በወጣትነት ዘመንህ ዝና ሸውዶ የገንዘብ መብዛት አታሎህ ከምትወደው እና ከሚወድህ ህዝብህ አልነጠለኽም ነበር። ትላንትም ዛሬም ስለ ወገኖችህ መጎሳቆል የሚሰማህን የቅርብ አይደለም የሩቅም ያውቀዋል። በዝምታክ ውስጥ ያለውን ጩኸት እንሰማለን። አገርህን ወገንህን ወደህ ዋጋ ከፍለኃል። የማይገባህን ሁሉ በህይወትህ አስተናግደኃል። አገሬን ወገኔን ባትል በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ዓለም ላይ የሚኖርህ ተጽኖ ቀላል አልነበረም። አንተ ግን ፍቅር በልጦብህ ከእኛ ጋ ኖርክ። በተሰጠክ ጸጋ ልክ ሳይሆን በኛ ኑሮ ልክ አዘገምክ። ስለሰጠኸን ሁሉ እናመሰግናለን!

የብዙዎች አባት የድኃዎች እንባን አባሽ የሆንከው የአገር ባለውለታው ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ እ...ን...ወ...ድ...ሀ...ለ...ን...!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

Photo credit #ጆሲ /Artist/

https://youtu.be/cD30bSzW7E0
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንጋፋው እና በዓለም ዙሪያ ትልቅ ተቀባይነት የነበረው፤ በአገራችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የራሱን አሻራ ያሳረፈው፤ የምንወደው እና የምናከብረው በአርቲስት አለማየሁ እሸቴ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለመላው የአገራችን ህዝቦች እና ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን።

ነፍስ ይማር!
በሀገራችን የዘመናዊ ሙዚቃ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ከነበሩት ስመ ገናና እና አንጋፋ ድምፃውያን መካከል ግንባር ቀደም የነበረው ታላቁ የሙዚቃ ሰውና የሙያ አባታችን ድምፃዊ ዓለማዬሁ እሸቴ ድንገተኛ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማኝን ኀዘን ስገልፅ በተሰበረ ልብና ጥልቅ በሆነ የኅዘን ስሜት ነው።
ጋሽ ዓለማዬሁ ከ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ከ60 ዓመታት በላይ ባስቆጠረው የሙዚቃ ሕይወቱ የተጫወታቸው ሕዝብን አስተማሪ፣ ታሪክን ነጋሪ፣ ሰላምን ዘማሪ፣ ትውልድን ቀራጭና ሀገርን አወዳሽ የሆኑት ዘመን ተሻጋሪ ታላላቅ ስራዎቹ በተለይ በዚህ ሙያ ውስጥ ላለነው የሙዚቃ ባለሙያዎች ዘርፈ ብዙ ትርጉም አላቸው።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኅትመት ታሪክ የመጀመሪያውን የግል ሸክላ በማሳተምና የመጀመሪያውን ዘመናዊ የግል የሙዚቃ ባንድ ከሙያ አጋሩ አርቲስት ግርማ በየነ ጋር ( ግርማ ዓለም ባንድ/ ግርማና ዓለማዬሁ) በማቋቋም ፈር ቀዳጅ የነበረው ጋሽ ዓለማዬሁ በድንገት በአካል ቢለየንም ዘመን በማይሽራቸውና ትውልድ በሚቀባበላቸው ስራዎቹ ሲታወስና ሲዘከር ይኖራል።

ለመላው ቤተሰቦቹ፣ ለሙያ አጋሮቹ፣ ለሙዚቃው አፍቃሪዎቹና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እየተመኘሁ፤ ፈጣሪ ነፍሱን በአፀደ ገነት እንዲያኖርልን ከልብ እመኛለሁ።

ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
መልካም አዲስ አመት!

በቅድሚያ ለመላው የአገራችን ህዝቦች እንኳን ለኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

ኢትዮጵያ አገራችን የራሷ የሆነ የቀን መቁጠሪ ቀመር ያላት ታሪካዊት አገር ነች። ይህችን ታላቅ አገር አባቶቻችን በብዙ መስዋዕትነት ዳር ድንበሯን አስከብረው፣ ባህልና ወጓን ጠብቀው፣ ቋንቋችንን ከነ ፊደሉ አውርሰውናል። እኛም በአደራ የተቀበልናትን ይህችን ታላቅ አገር ለቀጣይ ትውልድ የማስረከብ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር አለብን።

አባቶቻችን በዘመናቸው ተከባብረው እና ተዋደው የውስጥ ችግሮቻቸውን በሰለጠነ መልኩ እየፈቱ ይህችን አገር ለኛ ያስረከቡት ከጸብ ይልቅ ፍቅር እንደሚበልጥ ተሰብከው ሳይሆን በህገ ልቦና ፍቅር የእግዚአብሔር መንገድ መሆኑን ስለተረዱ ነው። እኛም ከነሱ መልካሙን ነገር በመድገም የተሻለች አገር ለመገንባት እንድንጥር እመኛለሁ።

በዚህ አዲስ ዓመት ላለፉት አመታቶች በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ቀውስ ብሎም በጎጠኝነት መንፈስ የተነሳ ብዙ ጸያፍ ዜናዎችን የሰማው ጆሯችን መልካም እና የሠላም ወሬን የሚሰማበት ዘመን ይሁንለት! በተለያዩ ሁኔታዎች የተጎዱ ወገኖቻችን ካሉበት መከራ ተላቀው ቀሪ ህይወታቸውን በደስታና በተድላ የሚያሳልፉበት፣ በስደት ህይወት ያሉ፣ በእስር ቤት የሚሰቃዩ ወገኖቻችን ወደየቤታቸው የሚመለሱበት መልካም ዘመን ይሁንልን።

እኛም በየግላችን እርስ በእርሳችን እየተጋገዝን አቅመ ደካሞችን በቻልነው መጠን እየደገፍን መጪውን አዲስ ዓመት በፍቅር እና በሰላም እንድንጨርሰው እግዚአብሔር ዘመኑን ባርኮ ይጀምርልን።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
@
አባትየው...😍
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን...❤️
የስድስት አመት ምኞት ተፈጸመ።

ከስድስት አመት በፊት በግል የፌስቡክ ፔጄ ላይ ቴዲ አፍሮ የክቡር ዶክትሬት እንደሚገባውና በዛ ማዕረግ ሲጠራ መስማትም እንደናፈቀኝ ጠቅሼ ለጥፌ ነበር። ምኞቴ ሰምሮ ቴዲ አፍሮ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የክቡር ዶክትሬቱን ሲቀበል ይኼንን ጽሁፍ ለመለጠፍ ፈልጌ በወቅቱ ስላጣሁት "እንዲህ ብዬ ነበር.." ብቻ ብዬ ሀሳቤን በጽሁፍ አስፍሬ አለፍኩ። ዛሬ ግን ፌስቡክ በዕለቱ የአመቱን ማስታወሻ በሚያስቀምጥበት ሰሌዳ ላይ የዛሬ ስድስት አመት ይኼን ለጥፈ ነበር ብሎ ፊት ለፊት አስቀመጠልኝ።

የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል ነውና ቴዲ አፍሮ ለዚህ ክብር እንደሚበቃ ከአነሳሱ መገመት ለኔ ለምወደው አይደለም ለምቀኞቹም አይጠፋቸውም።

የክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ሆይ አገሬን በሙዚቃው ዘርፍ በዓለም ደረጃ አስጠርተኃልና ስምህን የጥበብ አፍቃሪያን በትልቅ ክብር ይጠሩታል። አንተ በዘመናችን ለሙዚቃ ምልክት ለመሆን በቅተኃል። ግጥምና ዜማ ባንተ ይመዘናል እንጂ ያንተን የሚገመግም ጥበበኛ እስኪጠፋ ድረስ ለቀኃል። ዝቅ ብለ የጀመርካት ጥበብ ከፍ አድርጋኃለች። የልብህ ቅንነት የአንደበትህ መጣፈጥ በሚሊየኖች ልብ ውስጥ የንጉስነት ማዕረግን አጎናጽፎሃል። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል የለፋህበት ሙያ አንተ ምልክቴ ነህ ሲል አክብሮኃል።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ለውዴ ውዱ ነሽ

በጎደለ ሞልተሽ፤ በጠፋው ተክተሽ፣
ሲዝል አበርትተሽ፤ ግራውን ደግፈሽ፣
የብቸኝነት ጉዞውን፤ በጥንድ ቀይረሽ፣
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው፤ መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣ እራስሽን ደግመሽ።

መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ብሩክቲ እናት?
ሁሌም አብራው ያለች፤ እየሆነች ብርታት፣
ለብላቴናው ክብሩ፤ ለልቡም ዘውድ ናት።

እንደ ግጥሜ ርዕስ፤ እንደ ስንኝ ቋጠሮ፣
እንደ ጠቢብ ቅኔ፤ እንደ ፀሐይ ኑሮ፣
ልብሽ ብሩህ ነው፤ ዘውትር የሚፈካ፣
መልክሽ በለስ ነው፤ ውዴ ባንቺ 'ረካ።

የሰጠሽው ፀጋ፤ የሰማይ ላይ መና፣
እንደ ምድር ሃመልማል፤ የፈካ ነውና፣
ልቡን ፍቅር ሞላው፤ ደስታውም አበበ፣
ለውዴ ውዱ ነሽ፤ በመልክሽ ተዋበ!

እንደ ከዋክብ ብዙ፤ እንደ ጀምበር ውብ፣
አንድ ሰው እልፍ ነው፤ ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ፤ ሁሉን የሆንሽለት፣
ጤና ይስጥሽ አምላክ፤ ዘላለም ኑሪለት!

እንደ ምድር አሸዋ፤ እንደ አባይ ጅረት፣
አንድ ሰው ብዙ ነው፤ ፍቅር ከሞላበት!
በዝተሽ አበዛሽው፤ በርተሽ አፈካሽው፣
ከፊትም ከኋላም፤ በሁሉም ከበሽው።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
2025/07/02 00:42:01
Back to Top
HTML Embed Code: