Telegram Web Link
ተሸንፌ የወደድኩህ...

እቺ ምስኪን አገሬ ሳይኖራት ሳይተርፋት መምህር ቀጥራ ትምህርት ቤት ገንብታ ያስተማረቻቸው ምሁሮች እውር ሆነውባት ያውቃሉ። ከትቢያ አንስታ እውቀት ዘርታባቸው ሰው አርጋቸው ስታበቃ ስጋዋን ሊበሉ ደሟን ሊጠጡ እያጋሱ ተነስተውባታል። አንተ ግን "የአባቶቼ አደራ የሆንሽ ቅድመ አያቶቼም የደም ዋጋ የከፈሉልሽ አገር ነሽና የኔም ነፍስ ለሉዓላዊነትሽ መረጋገጥ ቢገበር ደሜም ቢፈስልሽ ላንቺ የሚሰሰት አንዳችም የለኝም።" ብለኽ ዘለዓለማዊ ቃልኪዳን ያኖርክላት ይመስል በዚህ ጥልቅ ስሜት ውስጥ ሆነ ያለ በደልህ መከራ እንደ ጅረት ሲፈስብህ፤ አንዱ ቁስልህ ሳይሽር ሌላ ቁስል እያበጁብህ መቆም እንኳን እንዳትችል ፈተኑህ።

ፍጹም ሰላምን ለሌሎች ለሚመኘው ልብህ ከፉበት። ደግነትን እንደ ማህተሙ አጥብቆ የያዘውን ስብዕናህን ተጠየፉት። አንተ ግን አንደበትህ ክፉ ሳይናገር እግርህም ለስደት ሳይገሰግስ የደማ ልብህን በአገርህ አፈር አከምከው። የወገንህን መጎሳቆል እያየች በሀዘን የተዋጠች ነፍስህን እያባበልክ ጥሩ ቀን እስኪመጣ ታገስክ። የፍቅርህ የጥልቀት ልኬቱ አንተ እንጂ ለሌላ ሰው ለመረዳት ቀላል አይደለም። እግዚአብሔር ላንተ በስፋትም፣ በልህቀትም፣ በግዝፈትም ከሌላ ልቦች ሁሉ ለይቶ የፈጠረልህ እስኪመስለኝ ድረስ በኩራትና በትዕግስት የተሞላች ልብህን እደነቅባታለሁ።

ላንተ ከወርቅ የከበረ የኦፓል፣ የኤመራልድ፣ የዳይመንድ እና የሩቢ ፈርጥ ያለው ከነዚህም የተበጀ ዘውድ ቢጫንልህ ያንስሃል እንጂ በፍጹም አይበዛብህም። የኔ ኩሩ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሰጡ ሹመቶች ላንተ ይገቡኃል። የአገሬ አርቲስቶች አርቲስት በመሆናቸው እና በሙያቸው መኩራትም ካለባቸው አንተ በዘርፉ መገኘትህ ትልቁ ምክኒያታቸው ሊሆን ይገባል።

አይ እኔ በልቤ ያለን ሁሉ ለመጻፍ ስታገል ከዐይምሮዬ እየገዘፈ እጨነቃለሁ...! ብቻ እውነት በሆነ መውደድ እወድኃለው! ስላንተ በእጅጉ እጨነቃለሁ። ደስታህን መካፈል ሳይሆን መደሰት እችልበታለሁ። ዝም ብዬ እወድኃለው ብዬ ባወጋ መመጻደቅ ነው የሚሆንብኝ። አንተን ተሸንፌ ነው የወደድኩ! ጥበብህ፣ ሀሳብህ፣ ግጥምህ፣ ዜማክ፣ ደግነትህ፣ ትሁትነትህ፣ መልክህ፣ ቁመትህ፣ ኩራትህ፣ ወኔህ፣ አነጋገርህ፣ አሳሳቅህ፣ ቁምነገርህ ወዘተርፈ ባህሪያቶችህ እኔን አሸንፈውኝ ወድጄኃለው! ቅንጣት እንኳ የሚጠላ ነገር ባንተ ላይ ሳጣ እደነቃለሁ። ከፍቅሬ በላይ የምሸልምህ ውድ ነገር የለኝምና እ..ወ..ድ..ኃ..ለ..ሁ!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ቴዲ አፍሮ ጎዳና

ለዘመናት ኢትዮጵያዊነት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ማህበረሰቡን በአገር ፍቅር ሲያነቃቃ እና በመልካም ምግባሮች ሲቀርጽ የኖረው ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮ ካሳሁን በጎንደር ከተማ ላይ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በር እስከ ኮሌጅ ማዞሪያ ያለው የአስፓልት መንገድ የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን ጎዳና ተብሎ ተሰይሞለታል። የመንገዱ ስም ከዚህ በኋላ ቴዲ አፍሮ ግዳና እየተባለ ይጠራል።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
Channel photo updated
"አስተሳሳሪ ምልክት"

✍️(አሮን ሙሉጌታ)

ዛሬ ላይ እንደ ሀገር የት ነን? አለም እንድህ ይለናል ፦ኢትዮጲያ የሰው ዘር መገኛ ፤ ቀደምት ስልጣኔን ያስተማረች ፤ የጀግኖች ሀገር ፤ በማንም ያልተደፈረች በባርነት ያልተገዛች ሀገር ኢትዮጲያ ::

እኛ ግን ዛሬ የት ነን? አለም ከሗላችን ተነስታ ወደ ኋላ ትታን ሂዳለች ኋላ ቀርተናልም ፤ እኛ ምንም ሳንሰራ በአባቶቻችን ገድል እየፎከርን ፤ ከሰው ህይወት ርስት ፣ ጥቅም በልጦብን ፤ የኔ ብቻ ትክክል የኔ ብቻ የበላይ እየተባባልን ፤ ጥላቻ ነግሶ የቀደመው ተከባብሮ መኖርና መቻቻል ተረስቶ ፤ በዚች ምድር ዘላለም እንደምንኖርባት አስበን ጥለናት እንደምንሄድ እና እንግዳ መሆናችንን ረስተን አይደለም ለፀብ ለፍቅር የማይበቃ ጊዜያችንን አሁን ባለንበት ሁኔታ ለኛ ፀፀትን አትርፈን ለመጪው ትውልድ ጥላቻን አውርሰን አሁንም ከኛ የባሰ ራስ ወዳድ ትውልድ እንዳንፈጥር እሰጋለሁ!

አንድ የሚያደርገን ታሪክ እየተፋቀ የሚያለያዩን ትንሽ ታሪኮች ደምቀው በሚፃፉበት በዚህ ዘመን ሁሉን በአንድነት ለማስተሳሰር የሚታትር አለም ስለሚያወራላት ኢትዮጲያ ፤ ወዳኋላ ለቀረችው ኢትዮጲያ እንደሳት የሚበላው ከልቡ የሚቆረቆር ሰው አውቃለሁ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)...
.. .ለዚህም ነው "የመጪው ዘመን ፊት ናት መሪ፣ ዛሬ አለም ቢላት ኋላ ቀሪ" ብሎ ያዜመላት በሄደበት ስሟን ጠርቶ የማይጠግበው አንድነታችነን አብዝቶ የሚሻ ሀገር ወደቀድሞው ገናንነቷ እንድትመለስ በሚችለው ሁሉ የሚታትር እንደ አባቱ ቴዎድሮስ (መይሰው ካሳ)ሀገሩ ከሰለጠኑት ሀገሮች ተርታ እንድትሰለፍ ፤ ስልጣኔን አስተምራ እንደካሮት ቁልቁል ላደገች ሀገር የሚያመው እሱ ነው እሱ ብቻ ከፍቅርና አንድነት ግምጃ ተራቁተን ባዶ በቀረንበት በዚህ ዘመን፣ እንደ ኢትዮጵያዊ፤ የቀረን አስተሳሳሪ ምልክት፣ አንድ ግለሰብ ብቻ መሆኑን ስናይ ደግሞ ሆድ ያስብሳል ቂምን ይቅርታ እንባባል አንድ እንሁን ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል ይላል ሰውዬው ዘረኝነትን ቀብረን አንድነትን የምናነግስበት ቀን እሩቅ አይሆንም የሚል እምነት አለኝ ከሁሉም ነገር ፍቅር ይበልጣል ፍቅር ያሸንፋል ::

ዘጽአት ለኢትዮጵያ ወደ ተስፋ ጉዞ
ባህሩን የሚያሻግር አንድ ሙሴ ይዞ
ቅርብ ነው አይርቅም የኢትዮጵያ ትንሳኤ
በአንድነት ከገባን የፍቅር ሱባኤ

ከከፈልክልን ዋጋ አንፃር ሁሉ ነገር ያንስብሀል እንጅ አይበዙብህም መልካም ነገሮች ሁሉ ለአንተ ይገቡሀል ክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን!

በያላችሁበት ሰላም ፍቅር ጤና ለናንተ ለሀገሬ ልጆች! ♦️አሮን
የእኔን ጩኸት በአደባባይ መሰከሩት...

አንጋፋው ገጣሚና የዜማ ደራሲ ሙሉ ገበየሁ ስለ ቴዲ አፍሮና ስለ ኪነጥበቡ እንዲህ አሉ....

"ምናልባትም በዚ ሙያ ብዙ አንጋፋ ሙያተኞች ጥረዋል ደክመዋል ለፍተዋል። ሙያተኞቹም በዋዛ ፈዛዛ አልፈዋል። ይኼ ሙያ ከጥንተ ጀምሮ ሲወድቅ ሲነሳ፣ ክብር አጥቶ፣ ለሙያው ትኩረት ሳይሰጠው፣ ክብር ተነፍጎ፣ ለባለሙያውም ፍቅር ሳይሰጠው ኖሮ ኖሮ ኖሮ አሁን ላይ ህዝቡ ለሙያው የሚሰጠው ፍቅር እየበለጠ ትኩረት እና አክብሮት እንዲሰጠው ዋጋ እንዲሰጠው እንደ ቴዲ አፍሮ ክስተት ሆኖ ሙያው የተፈጠረ ሰው በመገኘቱ በአገር ደረጃ የቀደሙትንም ዋጋ ያስከበረ ለጥበቡ ፈርጥ የሆነ ሰው ነው። ቴዲ አፍሮ ጥበብን አክብሯት ጥበብም አክብራዋለች።"

የኔ ኩሩ የኔ ቀብራራ የአገሬ ሙያተኞች በሙያቸው መኩራት ካለባቸው ሙያው ላይ አንተ ስላለ መሆን አለበት ብዬ በግልጽ ከትቤ ነበር። እነሆ የመከበራቸው ምክኒያት የሙያውም መግዘፍ ምክኒያት አንተ ነህ። ይኼ የኔ ስሜት ብቻ ሳይሆን አንተ የምታከብራቸው ሰዎች እውነተኛ ቃል ነው። ይኼ እውነት የተነገር አልያም የሚነገር ብቻ አይደለም ይልቁንም በራሱ ጸንቶ የቆመ ልሸሽገው ቢሉ የማይ ሸሸግ አላወራውም ቢሉ አፍ አውጥቶ የሚናገር በራሱ የጸና ብሎም የገዘፈ እውነት ነው። ለዚህም ነው በአደባባይ ቆመው አንጋፋዎች የኔን ጩኸት ያሰሙት። ይኼንን የጸና እውነት ሙያተኞች አንደበታቸውን ከፍተው ለሀቅ በመመስከራቸው ደስ አለኝ። እኔ ወዳጅህ ሁሌም ባንተ የምኮራ ሰው ነኝ። የከፈልካትን እያንዳንዷን ዋጋ ስለማውቅ ስላንተ እውነት ለመመስከር በፍጹም አልሰንፍም። ገና ብዙ ክብር ብዙ ፍቅር ብዙ አድናቆት አብረን እናያለን። በቁመህ የውለታክ ዋጋ እስኪከፈልህ ድረስ ብዕራችን በነጻነት እውነታውን ይከትባል።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
የአጤ ምኒልክ እና የእቴጌ ጣይቱ የልደት በዓል መታሰቢያ

#የዝግጅት_አቅራቢዎች ፥ ጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉ፣ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም፣ ያሬድ ሹመቴ ፣ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ፣ ቶማስ አድማሱ፣ ሙሉጌታ ታዬ እንዲሁም ሕብረቀለም የቴአትር ቡድን ናቸው::

#ቀን- ማክሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም
#ሰዓት - ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ
#ቦታ- ዋቢ ሸበሌ ሆቴል
#አዘጋጆች - የእምዬ ምኒልክ ወዳጆች
- አርማ ሕትመትና ማስታወቂያ
ማሳሰቢያ...
መግቢያው በነፃ ነው:: ከኮቪድ ጋር በተያያዘ የሚገኘውን ሰው መገደብ አስፈላጊ በመሆኑ የመግቢያ ካርድ 22 ጎላጎል ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ አርማ ማስታወቂያ እና ስታዲየም አካባቢ መንገድ ትራንስፖርት ፊትለፊት አዳም ፀጉር ቤት ሄደው በነፃ ይውሰዱ።
መጣና መጣና ደጁን ልንጠና
መጣና ባመቱ እንዴት ሰነበቱ
ክፈት በለው በሩን የንጉሱን*፪
ሙልሙል በላት ንግስቲቱን የቡሄውን

ሆያ ሆዬ ጉዴ ቴዲ ነው ኩራቴ...*፪

ሆያ ሆዬ......... ሆ
እዛማዶ.....ሆ
ነብር ይዘላል...ሆ
እዚህ ማዶ.....ሆ
አንበሳ ይዘላል.....ሆ
የኛማ ቴዲ.....ሆ
ፍቅርን ይዘምራል...
ሆያ ሆዬ ጉዴ ቴዲ ነው ኩራቴ....፪

ይሄ የማነው ቤት...."ሆ" የኮራ የደራ...."ሆ"
የቴዲ ነው ወይ...."ሆ" የዛ የቀብራራ...."ሆ"
እንደ ባሮ ውሃ ...."ሆ" ፀጥ ረጭ ያለው...."ሆ"
እንደ መቅደላ አቀበት..."ሆ" ክብሩ ያየለው...."ሆ"
የኛማ ቴዲ ...."ሆ" የዘመን ዘውድ አለው!

ሆያ ሆዬ ጉዴ ጨዋታ ነው ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያ ሆዬ ጉዴ ቴዲን ቴዲን ቴዲን ቴዲን ይላል ሆዴ..
ተው ጥራልኝ እና...ሆ አይኑን ልየው...ሆ
እንደ ሌት ኮከብ...ሆ የሚያበራው...ሆ
ከሩቅ ይስባል...ሆ የቴዲ ግርማው።

ክፈት በለው ተነሳ ያንን አንበሳ!...
ክፈት በለው ተነሳ ቴዲ ነው አንበሳ

ተው ስጠኝ እና ልሂድልህ
እንደ አረጀ ጅብ አልጭውብህ
ያረጀ ጅብስ ጮሆ ያባራል
እንደኔ ያለው ሺ አመት ይወድሃል!

ሆያ ሆዬ ጉዴ ብሯን ብሯን ብሯን ብሯን ይላል ሆዴ
ሆያ ሆዬ ነው የምንለው*፪
ኢትዮጵያ ሀገሬ ...."ሆ" ደስ ይበልሽ ...."ሆ"
ቡሄው በአልሽ ...."ሆ" ደረሰልሽ ...."ሆ"

አመት አውደ አመት ድገምና አመት ድገማና
የቴዲዬን ቤት ድገምና አመት ድገምና
ወርቅ አዝንብበት ድገምና አመት ድገምና
የነጭ ጤፍ ዘርፋፋ የወለዱት ይፋፋ
የነጭ ጤፍ ደግ ደግ የወለዱትም ይደግ
የገብስ እስር ዘለላ ቴዲን የጠላው ይጠላ
የጥንጅት ጢስ መአዛ የቴዲ ወዳጁ ይብዛ።

ክበር በሙዚቃ ንገስ በሀገር ማንም አይናገር
ክበር በክራር ክበር ጥፍ የጠላክ ይርገፍ።

ግጥም ሀገረሰብ እና @PoetTataAfro
የቴዲ አፍሮ እና የአምለሰት ሙጬ ሶስተኛዋ ልጅ አምስት ወር ሞላት...😘😘😘

https://youtube.com/c/NegusMultimedia
2025/07/01 18:18:59
Back to Top
HTML Embed Code: