Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
✔️ፍቅር
✔️ትዳር
✔️ስኬት
✔️ግርማ ሞገስ
✔️በሰዎች መወደደ
✔️ጥበብ እና እውቀት
✔️ዓለም አቀፍ ዝና
✔️ደግነት እና ቸርነት
✔️ሀብት እና ጤና
✔️እምነት እና ኩራት
✔️ጽናት እና ትዕግስት
✔️ድፍረት እና ውሳኔ
✔️ብልሃት እና ራዕይ
✔️መውደድ እና በብዙ መወደድ
ሁሉም በአንድ ለአንተ ተሰጥቶሃል። ይገባሃልም። እንወድኃለን ጀግናችን! ሁሌም ደስተኛ ሆነህ ሳይህ ደስ ይለኛል። የሚሊዮኖች ደስታ ካንተ ደስታ ጋ የተሳሰረ ነው። መልካም ዘመን ንጉሥ ሆይ...💚💛❤️

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ ከዛሬ 111 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 1902 ዓ.ም ተወለዱ። ታዋቂው ደራሲ፣ አርበኛ ክቡር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ ሲሆን የተወለዱት ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረ ኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል።
የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ።
ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።
የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።
ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች ከሰባት አመታት በኋላ ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።
ሀዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ሲያተኩር፤ በጊዜው የነበረውን ወግና ልማድ ይገልጻል።

👍1
ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን የልደት በዓሏን ለምታከብረው በተለይም ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታቶች በሙያዋ ኢትዮጵያን በዓለም ማስጠራት የቻለችው የግጥም እና ዜማ ደራሲዋ ብሎም የውብ ድምፅ ባለቤት የሆነችውን አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባውን /ጂጂ/ መልካም ልደት ለማለት እንወዳለን!
እንደሚታወቀው ጂጂ በሙዚቃዎቿ ፍቅርንና አንድነትን የሰበከች ኢትዮጵያዊነትን አጉልታ የዘመረች በሙያዋ ትልቅ የሚባል ታሪክን የሰራች ብርቱ እንስት ናት። ስራዎቿም ዘውትር በልባችን ይኖራሉ! በዚሁ አጋጣሚ ጂጂ ወደ ስራ ተመልሳ በረቂቅ ሀሳቦቿና በውብ ድምጿ የምንደሰትበት ቀን ቅርብ ይሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን!
ልዑል እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አምላክ ነውና መልካሙን ሁሉ እንመኝልሻለን!

የህይወት ገጠመኝ /የቴዎድሮስን ስም ስለማውረስ/
የክብር ዶክተር አርቲስት ሻምበል ለማ ጉያ በ92 ዓመታቸው በዛሬዋ ዕለት ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚህች ዓለም በሞት መለየታቸውን በመስማታችን ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል።
ለሰዓለዊ ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው የሻምበል አድናቂዎች እና ወዳጅ ዘመዶች በጠቅላላ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እያወጅን ለአርቲስቱ ስርየተ ነፍስ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ብሎም ለውድ ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን!
የተከበሩ ሻምበል ለማ ጉያ በሙያቸው እጅጉን የረቀቁ ሰዓሊ እና የቅርፃ ቅርፅ ባለሙያ ሲሆኑ በይበልጥ በቆዳ ላይ ስዕል እጅጉን የታወቁ የአገራችንን የስዕል ጥበብ ከፍ ያደረጉ ባለሙያ ነበሩ። እኒህ ሰዓሊ 5 ልጆችን በህይወታቸው ያፈሩ ሲሆን አራቱ ልጆቻቸው በስዕል ስራ ላይ የተሰማሩ ጥሩ ሰዓሊያን ናቸው። ከዚህም ባለፍ በአሜሪካን አገር የአርት ትምህርቷን አጠናቃ በኒውዮርክ ከተማ የስዕል ኤግዚቢሽን እና በደቡብ አፍሪካ ላይ ስዕሏን ያሳየች ሴት ልጅ አላቸው። እኒህ ብርቱ አርቲስት ከቴዲ አፍሮ ህይወት ጋ የተያያዘ አንዳች የህይወት ገጣኝም አላቸው።
ገጠመኙን አንዳች ብዬ መገደብ አልፈልግም ዘለዓለማዊ ክስተት በሚለው ቀየርኩት። ነገርየው እንዲህ ነው። የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ሰዎች ከ44 ዓመታት በፊት በህብረት ወደ ደብረዘይት አቀኑ። እኒያ ከአዲስ አበባ ደብረዘይት የገቡ የኪነ ጥበብ ሰዎች ከአርቲስት ለማ ጉያ ስዕሎች ውስጥ ለየ አንዳዳቸው ስጦታ ይበረከትላቸው ጀመር።
በወቅቱ ስጦታ ሲበረከትላቸው ከነበሩ አርቲስቶች መኃል በወቅቱ ታዋቂ እና ፕሮፌሽናል ተወዛዋዥ የነበረችው አርቲስት ጥላዬ አራጌ /የቴዲ አፍሮ እናት/ ትገኝ ነበርና በአጋጣሚ የአፄ ቴዎድሮስ ስዕል ለዕርሷ ደረሳት። ስዕሉን እጅግ ስለወደደቸው እዚያው ለአርቲስት ለማ ጉያ እንዲህ አለቻቸው። እርጉዝ ነኝ ልጄ ወንድ ከሆነ ቴዎድሮስ ነው የምለው ብላ ቃሏን ሰጥታቸው ወደ አገሯ ተመለሰች።
እንደ ምኞቷም ወንድ ሆነላት እንደ ቃሏም ቴዎድሮስ ብላ የልጇን ስም ሰየመች። ከአመታት በኋላም ይኼንን ገጠመኟን ለሚዲያ አወጣችው። ይኼንን የሰሙት ሰዓሊ ለማ ጉያ "..ያኔ ለቴዲ አፍሮ እናት የሰጠኋት ስዕል ኮፒው ነው ይኼ ልጅ አድጎ ታዋቂ ሆኗል። ስለምን ትክክለኛውን /Original/ ስዕሉን ከሙዚየም አውጥቼ አልሰጠውም..." ብለው በማሰብ ለቴዲ አፍሮ ዋናውን ስዕላቸውን ከሙዚየም በማውጣት ቴዲ አፍሮ ከእስር ከተፈታ በኋላ አበረከቱለት።
በወቅቱም የክብር ዶክተር አርቲስት ሻምበል ለማ ጉያ እንዲህ ብለው ነበር... "ሁላችሁም የአፄ ቴዎድሮስን ታሪክ ታውቃላችሁ ይኼንን ስዕል ለቴዲ አፍሮ ያበረከትኩት የጀግንነት ጉዞውን በዚሁ እንዲቀጥል ስለምፈልግ ነው። ብለው ተናግረው ነበር። ቴዲ አፍሮም "...ከአርቲስት ለማ ጉያ ለእናቴ ተበርክቶላት የነበረው የቅጂ ስዕል ሳሎን ቤታችን ውስጥ እስከ 23 ዓመቴ ድረስ በክብር ተሰቅሎ ተቀምጦ ነበር ዛሬ ደግሞ ዋናውን ስዕል ከእርሳቸው እጅ በመቀበሌ እጅጉን ደስተኛ ነኝ" ሲል አውስቷል።
በድጋሚ ለአርቲስቱ ወዳጅ ዘመዶች እና ለአድናቂዎቻቸው በጠቅላላ መፅናናትን ይስጥልን። የክብር ዶክተር አርታስት ሻምበል ለማ ጉያንም ነፍሥ ከፃድቃኑ ተርታ ይመድብልን።
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በተለያዪ የሀገራችን ክፍሎች በተደጋጋሚ ጊዜ በዜጎች ላይ አላግባብ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ
እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ ባልተገባ መንገድ ተስፋፍተው መቀጠላቸውን ተያይዞ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በዋናነት መጠበቅ ያለበትና ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ለጉዳዩ አስፈላጊውን ትኩረት ሰጥቶ አግባብ ያለዉ መንግስታዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣና መሰል ጥቃቶች ዳግመኛ እንዳይፈፀሙ የሚጠበቅበትን የቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በጥብቅ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
በዚህ አጋጣሚ በነዚህ ጥቃቆች ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲምር እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናት እንዲሆንላቸው ከልብ እመኛለሁ።
ፍቅር ያሸንፋል!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

መታደል እኮ ነው ጎበዝ! አትግደል ብሎ ሲጽፍ ገዳይ ካህን እንዳየ አጋንንት እንዲህ ሲጮኽ ማየት! ኧረ ምኑን ሞገስ ቢሰጠው ነው..? እንደው ምኑን ግርማ ቢያለብሰው ነው..? ተው ሲል ሺ የሚንጫጫለት..?
ለማንኛውም አስታዋሽ ያሻቸዋልና ከስድብ ውጪ እንዲያው እንደ ቆርቆሮ ከመጮኽ ባለፈ ለወገናቸው ቅንጣት ታክል ውለታን ላልዋሉ ግለሰቦች /ቆርቆሮዎች/ ይኼንን ፅሑፍ ጀባ ለማለት ወደድኩ..!
ቴዲ አፍሮ ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸውን ተግባሮች ፈፅሞም ያልፈፀመ ያህል የሚሰማው ሩሩህ ሰው ነው። የቴዲ አፍሮ ገንዘቦች በተለያዩ ቦታ ተበልተው የሚቀሩ ሲሆኑ ከኮንሰርት ስራ አንስቶ እስከ ሲዲ አከፋፋዮች ድረስ በአግባቡ ገንዘቡን ከፍለውት አያውቁም። ይኼም ሆኖ ቴዲ አፍሮ ለገንዘብ ብሎ ፍርድ ቤት መቆምን የማይወድ ሰው ነው። ሌላው የቴዲ አፍሮ አስደናቂ ነገር በአጋጣሚዎች የተቸገሩ ሰዎችን ሲያገኝ ከ10 ሺ እስከ 100 ሺ ብር በቼክና በጥሬ ተቆጣሪ ገንዘቦችን ሸጎጥ አድርጎ የመሄድ ብዙ ልምድ አለው። ብዙ ብዙ ያልተሰሙ ለመፃፍም አመቺ ያልሆነ ቸርነቶችን አድርጓል። እስኪ ከብዙ በጢቂቱ እንመልከታቸው...
✔ ሐምሌ 30,1998 ዓ.ም በድሬዳዋ ደርሶ
በነበረው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ30 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።
✔ ጥቅምት 1,2002 Elshaday Relief and Development ባዘጋጀውና ከ50 ሺህ በላይ ህዝብ በተገኘበት የአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንሰርት ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ
አሰባስቦ ሙሉ ገቢውን ለእርዳታ ድርጅቱ ገቢ ያደረገ ሲሆን በእለቱ ለአበበች ጎበና ሕፃናት ማሳደጊያ 100 ሺህ ብር እና ለታላቁ ደራሲ ለይልማ ገ/አብ የወርቅ ብዕር ሸልሟል።
✔ጥቅምት 23,2002 በህመም ላይ ትገኝ ለነበረችው ማንአልሞሽ ዲቦ መታከሚያ ይሆን ዘንድ 20 ሺህ ብር አበርክቷል።
✔ ጥቅምት 17,2004 የወጣት አስመሮም ኃይለ ሥላሴን ነፍስ ለማዳን ለሶማሊያ ሽማግሌዎች 700 ሺህ ብር ከፈሎ የወገኑን ህይወት አተረፈ። ይህ ወጣት 700 ሺ ብሩን ካልከፈለ ስቅላት ተፈርዶበት ነበር። ቴዲም መረጃውን በመፅሄት ላይ ነበር አንብቦ ፈጥኖ የደረሰለት። እጅግ አስደናቂው ነገር ደግሞ እጁ ላይ የነበረው ገንዘብ እጅግ ጥቂት ከመሆኑ የተነሳ ከጓደኞቹ ተበዳድሮ ነው ብሩን ያሟላው።
✔ጥቅምት 17,2004 ለኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበር የ200 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጎ ለማህበሩ ያለውን አጋርነት አሳየ። ማህበሩም የምስጋና ምስክር ወረቀት
ሰጥቶታል።
✔የአራት ኪሎ ወጣቶች ከአልባሌ ሥፍራ ይርቁ ዘንድ በአባቱ ስም ተቋቁሞ ለነበረው የእግር ኳስ ቡድን ለአራት አመታት በየአመቱ ግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
✔በራሱ አነሳሽነት ለአበበ መለሰ ኮንሰርት በማዘጋጀት የአርቲስቱን ህይወት ከህልፈት ታደገ።
✔ጥቅምት 2005 ቀድሞ ይማርበት ለነበረው ቤቲልሄም ት/ቤት የኮምፒውተር እና የሙዚቃ መሣሪያ ድጋፍ አደረገ።
✔በተለያየ ግዜያት በተዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ እንደዚሁም እዛው ድረስ በመሄድ ለወ/ሮ አበበች ጎበና ህፃናት ማሳደጊያ ከመቶ ሺ ብር በላይ የገንዘብ እርዳታ በተደጋጋሚ አበርክቷል።
✔ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ባስመረቀችው አረንጋዴ መሬት ዶክመንተሪ ፊልም ምርቃት ላይ በእንጨት ለቀማ ይተዳደሩ ለነበሩ እናት የ 20ሺብር ቼክ ሰጧቸዋል።
✔እንደዚሁም ለተለያዩ ድምፃዊያን ግጥም እና ዜማ በነፃ አድሏል።
✔መስከረም 10,2011 ዓ.ም ከቡራዩ የተፈናቀሉ ወገኖችን ሄዶ በመጎብኘት የ1 ሚሊዮን ብርም ድጋፍ አድርጓል።
✔ከሶስት አመታት በፊት ሊቢያ ላይ በአሸባሪው isis ሰማዕትነትን የተቀበሉ ወገኖቻችንን ቤተሰቦች ከባለቤቱጋ ለቅሶ በመድረስ የብርም ድጋፍ አድርጓል።
✔በሰለሞን ቦጋለ እና በሳምሶን /ቤቢ/ ለሚመራው "ህብረት ለበጎ ለአንድነት" ለተሰኘው የመረዳጃ ማህበር ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ አበርክቷል።
✔በአዲስ አበባ በተለይም የኳስ ሜዳ ልጆችን እና የሌላ አከባቢ ስራ አጥ ወጣቶችን አሰባስቦ በማደራጀት ስራ የሚጀምሩበትን ግማሽ ሚሊየን ብር አብርክቶላቸዋል።
✔አርቲስት ጌዲዮን ዳንኤልን እና የደጃች ባልቻ ቤተሰቦችንም በገንዘብ እረድቷል።
✔በጥር ወር 2010 ዓ.ም ባህር ዳር ላይ ኮንሰርቱን ለማቅረብ ባቀና ጊዜ ገዳማቶችን ሲጎበኝ ለገዳሙ ገንዘብ አበርክቷል። እንዲሁም በዚሁ አመት ከባለቤቱ ጋ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በማቅናት 100 ሺ ብር ሰቷል።
✔በ2010 ዓ.ም ሚያዝያ ወር ላይ በዕለተ ትንሳኤ /ፋሲካ/ በዳግማዊ አጤ ምኒልክ ሆስፒታል ታመው የተኙ ወገኖችን ሙሉ ቤተሰቡን ይዞ በመሄድ የገንዘብ እርዳታ አድርጓል። ሁለቱ ህፃናት ሳይቀሩ ብር እና ፍራፍሬዎችን ለታማሚዎቹ በማበርከት በዚህ የመልካም ምግባር ላይ ተሳትፈዋል።
✔ቴዲ አፍሮ ለአድናቂዎቹም ቢሆን የኮንሰርት መግቢያ ትኬቶችን በገንዘቡ ገዝቶ /ከ200/ በላይ የሚያበረከት ነው። ይኼም አሁን በዋለው ገበያ ከ100 ሺ ብር የማያንስ ነው።
✔️የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ 1.2 ሚሊዮን ብር በድጋፍ ለዘመቻው ለተቋቋመው ኮሚቴ አስረክቧል።
✔️ የካቲት 14 በመስቀል አደባባይ ከታሪካዊው ግዙፍ ኮንሰርት ከተገኘው ገቢ አዲስ አበባ መስተዳድር ለሚያደርገው በጎ ተግባር እንዲውል ሙሉ የኮንሰርት ገቢውን ድጋፍ አድርጓል።
✔️ ከቡራዩ ለተፈናቀሉ የጋሞ ህዝቦች የተጠለሉበት ስፍራ ድረስ በመሄድ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
እነኚህ በመጠኑ ያስታወስኳቸው ሲሆኑ ከላይ ለመጥቀስ እንደ ሞከርኩት ቴዲ አፍሮ ብዙ ያልተሰሙ ግለሰቦች ብቻ የሚያውቋቸው እርዳታዎችን ያደርጋል። ለዛሬ በዚኽ እንቋጨው እና ሌሎች ቴዲ አፍሮ በህይወቱ የዋላቸውን መልካም ምግባሮች ለመዳስስ እንሞክራለን። ቴዲ አፍሮን የምንወደው በምክኒያት ነው። ይኼንን ሁሉ ሲያደርግ ብሔር አይቶ አልነበረም። ሰብዓዊነት አስገድዶት እንጂ! አሁንም ነገም ለህዝብ ድምፁን ያሰማል ያለውን ይሰጣል..!