ክቡር ዶክተር አርቲስት ሻምበል ለማ ጉያ ዛሬ ግብዓተ መሬታቸው ተፈጽሟል። ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለሙያ አድናቂዎቻቸው በጠቅላላ መፅናናትን እንመኛለን!
እግዚያር ነፍሣቸውን ከጻድቃን ማረፊያ ያድርግልን!
እግዚያር ነፍሣቸውን ከጻድቃን ማረፊያ ያድርግልን!
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
ኢ-ሰብዓዊ በደሎችን እያወገዘ ኢትዮጵያዊነትን እየሰበከ፤ የተቸገሩን በገንዘብ እየረዳ፤ የአገር ባለውለታዎችን እና የዘመኑ ሰማዕታትን ለቅሶ እየደረሰ፤ በደስታውም በሐዘኑም ከድሃ ወገኑ ጋ በመሆን አንባ ገነኖችን አድቡ እያለ ይኸው ዘመን ሲቀይር እርሱ ግን ጥቅም ሳይለውጠው ዛሬም አገሬን ወገኔን እያለ በበላይነት ከእኛ ዘንድ አለ። ወደፊትም ይኖራል! የፅኑ አቋም ባለቤት ነውና ከአገራችን ትንሳኤ ተከፋይም ነው። ከሚወዱት ጋ በፍቅር ይሻገራል። ለሚወዳቸው ዋጋ ይከፍላል። ከኋላ ሳይሆን ከፊት እየቀደመ መስዋዕትነቶችን ሁሉ ከፍሎ ለአመታት በታማኝነት ከኛጋ የተጓዘ ታላቅ ባለ ውለታችን ነው!
ቴዲ አፍሮ እ..ን..ወ..ድ..ኃ..ለ..ን..!
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ቴዲ አፍሮ እ..ን..ወ..ድ..ኃ..ለ..ን..!
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
"..አንድ በጣም ስሜትን የሚነካ ታሪክ ላስታውስህ። በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል ለዘመናት ያላበራው ግጭት፣ ጥፋት እና ሃዘን አሁንም ከየእለቱ ዜና ጠፍቶ አያውቅም። ነገሩ የሙስሊሞች በዓል የሚከበርበት ቀን ላይ ያጋጠመ ነው። የታሪካቸው ቅርበት ያህል የብዙዎቹ ኑሮም ቅርብ ለቅርብ ነው። ከመንገዱ ወዲህ ፍልስጤማውያን ከመንገዱ ወዲያ ደግሞ እስራኤላዊያን ይኖራሉ። ጥዋትም ከሰዓት በኋላም ማዶ ለማዶ ይተያያሉ። ፋታ የሌለው ጥርጣሬ ግን በሰላም እንዲተያዩ አላደረጋቸውም።
እናም በዚያ የበዓል ቀን አባት ለልጁ አዲስ ልብስ ገዝቶለታል አዲስ መጫወቻም አምጥቶለታል። በተገዛለት መጫወቻ የተደሰተው ህፃን አዲስ ልብሱን እንዳደረገ ከቤት ውጭ ይጫወታል። ቦታው ትንሽ ከፍ ያለ ነው። ወደ 'ታች ብዙም ሳይርቅ የእስራኤላዊያን መንደር አለ። ከመሃል ባለው መንገድ ላይ ለጥበቃ የተመደቡ የእስራኤል ወታደሮች አካባቢውን ይቃኛሉ። ከወታደሮቹ አንዱ ከጉብታው አካባቢ የሰው እንቅስቃሴ ሲመለከት አደጋ ተሰማው። የተነጣጠረ መሳሪያም ታየው። ሳይቀድመኝ ልቅደም ብሎ ይተኩሳል። አባቱ የገዙለትን ውሃ የሚረጭ ሽጉጥ ይዞ ሲጫወት የነበረው ህፃን በጥይት ተመታ።
አባት የተኩስ ድምጽ ሰምቶ በድንጋጤ ከቤት ወጥቶ ይመጣል። ልጁ ወድቋል! የእስራኤል ወታደሮችም ተጠግተው አይተዋል። የተነጣጠረ መሣሪያ የመሰላቸው ነገር ውሃ የሚረጭ ሽጉጥ መሆኑን ሲያዩ ደነገጡ። ህፃን መጉዳታቸውን ሲያዩ አዘኑ። በአስቸኳይ ሄሊኮፕተር ተጠርቶ ልጁ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ።
ነገር ግን ወደ ሆስፒታል የተወሰደውን ህፃን ለማዳን ሃኪሞች ቢጣጣሩም አልተሳካላቸውም። ህይወቱ አለፈ። ይሄ አባት ከዚያች ቅጽበት በኋላ ምን አይነት ሰው እንደሚሆን አስበው..?
በሀዘን የተመታው አባት፤ ሃኪሞቹን ጠየቃቸው.. “የልጄ ልብ ንፁህ ነው ወይ..?” አላቸው። ያልጠበቁት ጥያቄ ነው፡፡ “አዎ ጤናማ ነው” አሉት። “እንግዲያውስ፣ በልብ ህመም ለሚሰቃዩ እስራኤላዊ ሕፃን አስተላልፉለት” አላቸው። ያልተለመደ በጣም አስገራሚ ታሪክ ነው። ሁሉም ሰው ውስጥ ይብዛም ይነስ በጐ ነገር አለ። አደገኛነት ብቻ ሳይሆን ታላቅነትም የሚወለደው እንዲህ ካለ ጥልቅ ጉዳት ውስጥ ነው። ምክንያቱም ፍቅር ሳይሰቃይ አያሸንፍምና...."
#ቴዲ_አፍሮ

👍1
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
#ፍቅር
ሌሎች በሁለት ዓመታት ውስጥ ሺ ቃል ሲለዋውጡ በአንደበታቸው ሲስቱና ዋሾ ቀጣፊ ሲሆኑ አይተናል አስተውለናል። የተከተሏቸውን አሳፍረው የደገፏቸውን አሸማቀው አይተናቸዋል። አንተ ግን ለ20 ዓመታት አንድ ቃል "ፍቅር ያሸንፋል" እንዳልክ ፀንተክ ኖረካል። የተደራረቡ የመከራ መዓቶች አንደበትህን ሳያስቱህ፣ ቃልህን እንድትሽር አቅም ሳያሳጡህ በአቋምህ ፀንተ ከአገርህ እና ከወገንህ ጋ እስከ አሁን ድረስ አለህ! ያስጀመርከንን ጉዞ አቋርጠኸ ተስፋችንን ስላልነጠከን ፍፁም በሆነ ፍቅር እንወድሃለን!! በመከራህም በደስታህም አብረንህ ልንሆን የማይታጠፍ ቃልኪዳን አለን! እንደወደድከን እንወድሃለን!
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ስዕል በ #CherryAkaGoodie

#ማራኪዬ
በምስራቅ ፀሐይ ወጥቶ እሲፈካ ሠማይ
ካንሶላው ገብቼ እኔ አልተኛም ብታይ
በናፍቆትሽ እምባ እየራሰ አልጋዬ
ካላቺ አቅቶኛል ማደር ለብቻዬ
ማራኬዬ ማራኪዬ አንቺ የልቤ ጉዳይ
መልክሸ ሁሌም ካይኔ ላይ ነው፤
ሌትም ቀንም ብታይ (2x)
ማርኮ መማር ነበር የጀግና ሞገሱ
ከሩቅ አስረሸ ልቤን የት ያምልጥ ከራሱ
የጎደለው ከአርባ ስንት ይሆን እጣዬ
ካላንቺ አልሞላ አለኝ እርጂን ማራኪዬ
ማር ማር ይላል ሁሌ አፌ ሲጠራሽ
ማር ማር ይላል እያቆላመጠ፣
ማር ማር ይላል አይኖር ያለንቺ፣
ማር ማር ይላል እድሜ እየጣፈጠ
መች ጠገብኩሽና እኔ ሌት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሸ ፀንቶብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ሥራዬ (2x)
....
....
ስዕል #CherryAkaGoodie
በምስራቅ ፀሐይ ወጥቶ እሲፈካ ሠማይ
ካንሶላው ገብቼ እኔ አልተኛም ብታይ
በናፍቆትሽ እምባ እየራሰ አልጋዬ
ካላቺ አቅቶኛል ማደር ለብቻዬ
ማራኬዬ ማራኪዬ አንቺ የልቤ ጉዳይ
መልክሸ ሁሌም ካይኔ ላይ ነው፤
ሌትም ቀንም ብታይ (2x)
ማርኮ መማር ነበር የጀግና ሞገሱ
ከሩቅ አስረሸ ልቤን የት ያምልጥ ከራሱ
የጎደለው ከአርባ ስንት ይሆን እጣዬ
ካላንቺ አልሞላ አለኝ እርጂን ማራኪዬ
ማር ማር ይላል ሁሌ አፌ ሲጠራሽ
ማር ማር ይላል እያቆላመጠ፣
ማር ማር ይላል አይኖር ያለንቺ፣
ማር ማር ይላል እድሜ እየጣፈጠ
መች ጠገብኩሽና እኔ ሌት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሸ ፀንቶብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ሥራዬ (2x)
....
....
ስዕል #CherryAkaGoodie
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
☞እምዬ ምኒልክ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ ፍቅር ነበራቸው፡፡ ስሟን ጠርተው እርዳታዋን ሽተው ያፈሩበት አንድም ቀን አልነበረም፡፡
፡
ታላቋ የእንጦጦ ማርያም ደብር ታንጻ በምርቃቷ ቀን ከባድ ዝናብ መጥቶ ድግሱ ሊበላሽ ቢል እምዬ ምኒልክ ለእመቤታችን የልመና ደብዳቤ ጽፈው አስፈሪው ደመና ተገፎ ብሩህ ቀን ሆኖላቸዋል፡፡
፡
ጦሩ በዘመናዊ መሳሪያ የደረጀ ወታደሩ በዘመናዊ የውጊያ ስልት የሰለጠነ የኢጣሊያ ሰራዊት ሀገራችንን ሊወር ቢመጣ እምዬ ምኒልክ በእመቤታችን ስም ምለው በጠሩት ዘመቻ ኋላ ቀር በተባለው የጥቁር ጦር ነጭ ወራሪውን ድል አድርገዋል፡፡
፡
☞ለስሟ መጠሪያ ለጸሎት ማድረሻ ብለው እምዬ ምኒልክ በመሰረቷቸው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አብያተክርስቲያናትም ገና ከግንባታቸው ጀምሮ ብዙ ተአምራት ተደርገዋል ፡፡
፡
የእንጦጦ ማርያም ስትሰራ ለጧፍ ማብሪያ ተብሎ ከውጭ ሀገር የመጣ ባለብዙ መስታወት የሻማ መሰኪያ ከቤተመቅደሱ ጣሪያ ጫፍ ወድቆ አንድም ሳይሰበር ከመሬት ተግኝቷል፡፡
፡
አጼ ምኒልክ ሰራተኛቸውን ሁሉ ሰብስበው የአዲስ ዓለም ማርያምን በሚያሰሩ ጊዜም በረጅም ከፍታ ላይ ይገኝ የነበረ ርብራብ ተሰብሮ ሁሉም ሰራተኞች ወደ መሬት ወድቀው በአንዳቸውም ሰውነት ላይ ግን ጭረት እንኳን ሳይገኝ በተአምራት ተርፈዋል፡፡
፡
ወዘኩሉ ዘተግብረ በእንተ ንጽሐ ልቡ ለዳግማዊ ምኒልክ እስመ ታፈቅሮ እምኩሎሙ ነገሥት፡፡
፡
ምንጭ፦ ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ በጸሐፌ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ
- ታሪከ ነገሥት ከምኒልክ ፩ይ እስከ ምኒልክ ፪ይ በመ/ር ደሴ ቀለብ

👍2❤1
ቴዲ አፍሮ በአንድ ወቅት ስለ መጀመሪያ ልጁ ስለ ሚካኤል ቴዎድሮስ እንዲህ ብሎ ነበር...
"...እግዚአብሔርን እና ሀገሩን መውደድ አለበት። እግዚአብሔር አባቱ ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ እናቱ ነች። ሁለቱ ከህይወቱ መጥፋት የለበትም። ያ ካልሆነ እኔም አባቱ እናቱም እናቱ መሆኗ ልክ አይመጣም።"
#ቴዲ_አፍሮ®
እኛም እንላለን... እውነት ነው ልጆች በመውደድ ተቀርጸው በሀይማኖት'ና በስርዓት ታንጸው ሲያድጉ ለአገራቸው እና ለወገናቸው መፍትሄ የሚሆኑ አልሚ ዜጋ ይወጣቸዋል። ኖረው ያተርፋሉ! ደግፈውም ያሻግራሉ! ከፍቅር ከራቁ ከሀይማኖት እና ከስርዓት ከተለዩ ግን መና ይሆናሉ! ባህል እና ወጋቸውን አጥብቀው ካልያዙ እንዲሁ እንደ ከንቱ ሆነው ባክነው ይጠፋሉ።
አባታችሁ በሚመኝላችሁ ምግባር ታንፃችሁ፤ እሱ የደከመላትን አገር እና የተንገላታለትን ህዝብ የምታገለግሉ ቁምነገረኞች ትሆኑ ዘንድ አምላከ ቅዱሳን በጥበብ እና በሞገሥ ያሳድጋችሁ!

መልካም ዜና Spotify የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መሸጫ እና ማጫወቻ የሆነው የInternet ድርጅት በ2020 ትልቅ ተደማጭነት ካላቸው አርቲስቶች መኃል የኛውን Teddy Afro ተጠቃሽ አድርጎታል። በምስሉ ላይ መመልከት እንደሚቻለው። ሙዚቃዎቹ ለ293.4K /ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ሺ አራት መቶ/ ሰዓታት ታይተዋል። ይኼውም 82 አገራት የሚገኙ አድናቂዎቹ የተመለከቱት ሲሆን በዚህ ዓመት ከታዩ ሌሎች ሙዚቃዎች ውስጥ 5,748 ሰዎች ከሌሎች ተመራጭ አርቲስቶች ይበልጥ እንዳደመጡለት እና 34,962 ሰዎች እየደጋገሙ ሙዚቃዎቹን እንዳጫወቱለት ተገልጿል። እንደሚታወሰው ከሶስት ዓመት በፊት 2010 ዓ.ም በቢልቦርድ ላይ ከዓለማችን አንደኛ ተብሎ የወጣው የኢትዮጵያ ሙዚቃ አልበም በዚሁ ድርጅት የቀረበ ነበር።
አሁንም ለቴዲ አፍሮ እና ለኢትዮጵያችን የኪነ ጥበብ እድገት ትልቅ ስኬትን እንመኛለን...!