☆☆ስለ ቦብ ማርሊ በጥቂቱ☆☆
#BobMarley76
ሮበርት ኔስታ ማርሊ /ቦብ ማርሊ/ እ.ኤ.አ Feb 6/1945 ተወልዶ May 11/1981 በ36 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ቦብ ማርሊ እናቱ ሴዴላ ቡከር የምትባል ጥቁር ጃማይካዊት ስትሆን አባቱ ደግሞ ኖርቫል ማርሊ የተባለ ነጭ እንግሊዛዊ ነበር። የሙዚቃ ሕይወቱንም የጀመረው በ1960ዎቹ ፒተር ቶሽ እና በኒ ዌይለር ከተባሉ ጓደኞቹ ጋር ዘ ዌይለርስ የተባለ ቡድን በመመስረት ነበር። ከዚያም ከደጋፊ ዘፋኞቹ አንዲቱ የነበረችውን ሪታ ማርሊን በማግበት 5 ልጆች አፍርቷል። ከነዚህ ውስጥ አንዱ ዚጊ ማርሊ በራሱ የተዋጣለት የሬጌ ዘፈን ተጫዋች ነው። ከቦብ ማርሊ ታላቁ የሙዚቃ ስራ "ኖ ውማን ኖ ክራይ" /ቃል በቃል ሲተረጎም/ "አንድም ሴት አታልቅስ" የሚለው ነበር። በርግጥም ሮበርት ኔስታ ማርሊ/ቦብ ማርሊ/ በአገሩ በጃማይካ እንደ ታላቅ ጀግና የሚቆጠር ሰው ነው። ብሎም ዘፈኖቹ ስለ ፍቅር ከመተረክ ይልቅ ወደ ፖለቲካና ወደ ሃይማኖት ያጋደሉ ስለነበር በዓለም ተቀባይነትን አግኝቷል። እንዲሁም የሬጌን ሙዚቃ ምት ከኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዳሴ ላይ ቀንጭቦ በመውሰድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ እንዲሆን ያደረገ ታላቅ ሙዚቀኛ ነበር። እስካሁንም ድረስ ተፈቃሪነቱ የቀጠለ.. /መቼም የማይጠፋ የፍቅርን እሳት በሰው ልብ ውስጥ ለኩሶ የሔደ ሙዚቀኛ ነው።
እ.ኤ.አ በ1978 ዓ.ም /የዛሬ 43 አመት ግድም/ አንጋፋው የሬጌ ስልት ፈጣሪና አቀንቃኝ የሆነው ቦብ ማርሊ አንድነትን ለመስበክ ባዘጋጀው "One Love Peace" በተሰኘው ኮንሰርት ላይ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የጀማይካ ዋና ከተማ በሆነችው በኪንግስተን ላይ እጅ ለእጅ አጨባብጦ ጦር ያልፈታውን ነውጥ በሙዚቃው በመፍታት ማስታረቅ ተችሎት ነበር። ይህም ሁነት በአርቲስቱ እና በጀማይካ የፖለቲካ ሂደት ታሪካዊ አጋጣሚ ለመሆን የበቃ ታላቅ ድል ለመሆን ችሏል። በጊዜውም በተለያዩ ዓለም አቀፍ መፅሄቶች ላይ "ሬጌ እና ፖለቲካ" በሚል ርዕስ ሰፊ ሽፋንን ይዞ ለመላው ዓለም ዜናው መሰራጨት ችሎ ነበር።
"እጅ ለእጅ አሲዞ ድሬድ ላኩ
ፀበኛ ፓርቲዎች ታረቁ
ሰው ያረገፈ ፀብ እንደሳር
አከሸፈው ማርሊ በጊታር..."
#ቴዲ_አፍሮⓇ
ቦብ ማርሌ በ1978 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. መጨረሻ ላይ ወደ አፍሪካ በመምጣት ኬንያን እና ኢትዮጵያን ጎብኝቷል። በኢትዮጵያም ሻሸመኔ በመሄድ በንጉሰ ነገሥቱ ለራስተፈሪያን በስጦታ የተበረከተችላቸው ርስትና ሃይማኖታዊ ቤታቸውን ጎብኝቷል። ቦብ ማርሊ በወቅቱ ላንጋኖ እና አዲስ አበባንም ጎብኝቶ ነበር። ይኽ ምርጥ የሬጌ አቀንቃኝ ዘጠነኛ አልበሙን “Survival”ን በ1979 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በበጋ ወራት ለቋል። በአልበሙ ፖለቲካዊ አቋሙን ያንፀባረቀበት ነበር። በዚህ አልበም የፓን አፍሪካ አንድነትን ያቀነቀነበት ሲሆን ሠፊ ተደማጭነትንና ከበሬታን ተቀዳጅቶበታል። በተለይ በዚህ አልበም ውስጥ “Africa Unite” እና “Zimbabwe” የተሠኙት ሙዚቃዎቹ አፍሪካውያንን ጮቤ ያስረገጡ ነበሩ። ቦብ ማርሌ በ1974 'No Women No Cry' የሚለውን ሙዚቃ ሲለቅ ለግጥሙና ለሙዚቃው ክሬዲት የሰጠው ኪንግሰተን ከተማ የደሆች መኖሪያ በሆነችው ትረሬንች ታውን ውስጥ ለድሆች የነጻ መመገቢያ (ሱፕ ኪችን) ለነበረው ጓደኛው ቪንሰንት ፎርድ ነበር። ሀሳቡ የድሆቹ ምግብ ቤት ከሙዚቃው ሽያጭ የማያቋረጥ ገቢ እንዲያገኝ ነው።
ፎርድ ከጥቂት አመታት በፊት (2008) ዐርፏል። የድሆቹ ምግብ ቤት እነሆ እስከ ዛሬ ድረሰ ያልተቋረጠ ገቢ አለው።!
ይህ ታላቅ ሰው በህይወት ቢቆይ ዛሬ ከተወለደ 76ኛ ዓ.ም የልደት በዓሉን ያከብር ነበር። እኛም ለዚ ባለ ውለታችን /ለሬጌው የሙዚቃ ንጉስ እና የቢሊዮኖችን አስተሳሰብ ለቀየረው ሮበርት ኔስታ ማርሊ/ መወለድህ መልካም ነው ብለናል። ቦብ ከመሞቱ ጥቂት ሴኮንዶች በፊት ለልጁ ለዚጊ የተናገረዉ የመጨረሻ ቃል «ገንዘብ ህይወትን አይገዛም» የሚል ነበር።
ቦብ ባንድ ወቅት በህይወት እያለ ስለሚያቀነቅነው የሙዚቃ ስልት ተጠይቆ ሳለ ከኢትዮጵያ ጋር በማገናኘት ከተናገረው....
➜ ጋዜጠኛ>> «የሬጌ ሙዚቃ ስልት እንዴት ተፈጠረ? የማንስ ነው?»
➜ ቦብ>> «ሬጌ እኮ በጃማይካውያን ሳይንቲስቶች አማካኝነት ከኦርቶዶክስ ቤ/ክርስትያን መንፈሳዊ የከበሮ ምት ዜማ (bit of z drum in z orthodox church's spiritual ceremony) በመጠቀም ተቀናብሮ እና ጣፍጦ የተፈለሰፈ ወይም derived የሆነ የንጉሱ (z king's) ሙዚቃ ነው!» ሲል ቃሉን ሰቷል።
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
''የ'ምዬን አፈር አቅምሱኝ ካለ
ቃሉ ቢፈፀም እስኪ ምናለ
የሙት ኑዛዜው እንዳይረሳ
አምጪው ሪታ የቦብን እሬሳ
በባንዲራው ፊት ለኢትዮጲያ ሐገሬ
ቃል ግቢ መተሽ እሪታ ማርሌ.."
#TeddyAfro
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

ከኢትዮ እስከ ሱዳን ታሪክ በዚህ ወር..
የካቲት 12/2006 ዓ.ም ሱዳኖች አንጋፋ እና አንቱ ለሚሉት ለታላቅ የጥበብ ሰው ለሆነው ለመሐመድ ዋርዲ መታሰቢያ ትልቅ ፕሮግራም አዘጋጁ። በተቻላቸው መጠን እንግዶችን ከጎረቤት አገሮች ጋበዙ። የእነርሱም ትላልቅ የኪነ ጥበብ ሰዎች እና ባለስልጣኖች ሁሉ ተሰበሰቡ። ቴዲ አፍሮ ሱዳን እንደ ገባ በአፍሪካ አገራት ለመሪዎች የሚደረግ ትልቅ አቀባበል ተደረገለት።
በወቅቱ ለሱዳንች ከኪነ ጥበብ ሰዎች እና ከባለ ስልጣናቱ ሁሉ የላቀው የክብር እንግዳቸው ቴዲ አፍሮ ነውና ውድ ሽቱ እና ጌጣ ጌጥን ሸለሙት። ከፕሮግራሙ በኋላ በትላልቅ ባለ ስልጣኖች እና አንቱ በተባሉ የኪነ ጥበብ ሰዎች ቤትም የክብር እንግዳ ሆኖ ተጠራ። በዛም ውድ ሽቱ እና የከበሩ ንዋያትን በስጦታ አበረከቱለት።
የካቲት 12/2006 ዓ.ም ካርቱም ከተማ ከኢትዮጵያ በመጣ በትልቅ እንግዳ የተደሰተች ትመስልለች። ሱዳናውያኑ ኢትዮጵያዊ ጀግናን ለማየት ጓጉተዋል። በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያውያኖችም የአበሻን ልክ የኢትዮጵያውያንን ወኔ የሚያንጸባርቀው ወገናቸው በተሰደዱበት አገር መጥቷልና ደሰሰታቸው ወደር አልነበረውም።
ቴዲ አፍሮን ተቀብለው ወደ ማረፊያው ሲወስዱት ዋናው መንገድ ከተሽከርካሪ ፀድቶ በብዙ የመንግስት መኪናዎች እና ሳይረን ሳውንድ የተገጠመላቸው ዘመናዊ የፖሊስ ሞተሮች መንገዱን በማጣራት ቴዲ አፍሮን አጅበውት ወደ ፕሮግራሙ ስፍራ ወሰዱት።
ምሽቱን ቴዲ አፍሮ በሱዳኒ የሙዚቃ ባንድ በሞላው መድረክ ላይ ወጥቶ የአንጋፋውን የመሐመድ ዋርዲን ዘፈን ማቀንቀን ጀመረ። ሰበርታ ይሰኛል የዘፈኑ ርዕስ... ይኼ ሙዚቃ ለሱዳኖች ልክ እኛ ጃ ያስተሰርያልን እንደምንወደው የሚወዱት ሙዚቃቸው ነው። በቴዲ አፍሮ አዛዚያም አይደለም ሱዳኒ የኔም ልብ ተናውጦ ነበር። በቃ ድንቅ አድርጎ ዘፈኑን ተጫወተው። ለሱዳኖች የሚደንቀው ቴዲ አፍሮ የመሐመድ ዋርዲን ዘፈን እንዲህ አስውቦ መጫወቱ ነው። ለእኔ ግን የሚደንቀኝ ቴዲ አፍሮ በ1990-1991 ባለው አመት ነበር ይኼንን ዘፈን አጥንቶት የነበረው። ከዛ ጊዜ በኋላ ደግም ሲጫወተው ከ16-17 አመት አልፎት ነበር።
ከ15 ዓመት በፊት የተጠናን የሌላ አገር ሙዚቃ አስታውሶ መጫወት ማለት ምን ያለው ድንቅ ተሰጥኦ እንደሆነ ለመመስከር ከሳምንት በፊት አጥንተው አዝማች እየዘለሉ ዜማ እየሸራረፉ ግጥም እየናዱ የሚዘፍኑ ዘፋኞችን ማየት በቂ ነው። ቴዲ አፍሮ በዕለቱ መድረክ ላይ ወጥቶ የመሐመድ ዋርዲን ዘፈን እንዲዘፍን ሲጠየቅ ሁኔታውን ባለቤቱ አምለሰትን ሲያማክራት ውጣና ተጫወት ብላ የገፋፋችው እሷ ነበረች። እርሱም የሚስቱን ቃል ተቀብሎ መድረኩ ላይ ቢቆም የመታሰቢያ ፕሮግራሙ የሰርግ ያህል ደመቀ።
በዕለቱ የነበረውን የአቀባበል ሁኔታ እና በቀጣይ ቀናቶች ውስጥ ያቀረበውን የመድረክ ስራ ይመልከቱ...
https://youtu.be/BQDRAPZ6Q0U

እግዚአብሔር ቸር አምላክ ነው። ትዳርን ባርኮ! ጤና አድሎ! ደስታና ተድላን ለሰው ልጆች ሲሰጥ አይሰስትም። የሚሳነው ነገር የለምና ሁሉን ያደርጋል። በደስታ ላይ ደስታ ይሁንላችሁ ሲል ቤቱን በልጅ ይሞላል። ይህ በረከት ለእግዚአብሔር እንጂ ለማንም አይቻለውም። ለሚወዱት እና ለሚፈሩት እግዚአብሔር ሁሉን ያዘጋጅላቸዋል ሁሉን ይፈጽምላቸዋል። ዘለዓለማዊ ክብርና ምስጋና ለልዑል እግዚአብሔር ይሁን!
https://youtu.be/MZXFvFBEH60
https://youtu.be/MZXFvFBEH60
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
ሚኩ እና የማርያም ታናሻቸውን እየጠበቁ ነው....😍
https://youtu.be/mDkSxDXiUoU
https://youtu.be/mDkSxDXiUoU