Telegram Web Link
ብርቅም ድንቅም....😍

ሁለቱም ለጥበብ የተፈጠሩ በጥበብ የኖሩ ጥበበኞች።
ሁለቱም የሚዋደዱ እጅጉን የሚከባበሩ..!
ትላንት ቀደምኩ የሌለው ዛሬም በለጥኩሽ የሌለው እውነተኛ መከባበር እና ንጹህ ፍቅር!

አንዲት የጥበበኛ ልጅ ከትምርት ቤት ስትመለስ አሜሪካን አገር በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ቴዲ አፍሮን ስታየው ማመን አልቻለችም። ከቤት ወጥታ እየጮኸች "ታምናላችሁ ቴዲ አፍሮ እኛ ቤት ነው ያለው..." እያለች ደጋግማ በደስታ ጮኸች። ቴዲ አፍሮም አረጋግቷት "ከእኔ በላይ ያንቺ እናት ዝነኛ ነች እኮ እኛም እሷን ስናይ እንደነግጣለን.." ቢላት "አትቀልድ" የሚል አይነት ምላሽ ሰጠችው። ቴዲ አፍሮ ግን ስታየው እራሷን መቆጣጠር ያቃታትን ወላጅ እናቷን እጅጉን ይወዳታል። ያከብራታልም። ያቺ ሴት ጀግናዋ አለም ፀሐይ ወዳጆ ነች። አለምዬም ለቴዲ ያላት ፍቅር ድንቅ ነው። ከልጇ ለይታ አታየውም።

https://youtu.be/EiEt08fDp0Q
#ኢትዮጵያ_ወደ_ፍቅር የተሰኘው በመዲናችን አዲስ አበባ የካቲት 14/2012 ዓ.ም የተዘጋጀው ግዙፍ እና ታሪካዊ ኮንሰርት ላይ የነበራችሁ ነገ የዚህን ታሪካዊ ኮንሰርት አንደኛ አመቱን ለማሰብ ስለወደድን በዕለቱ ፎቶ ያላችሁ ከታች በተቀመጠው የቴሌግራም ሊንክ በመጠቀም የእናንተን ፎቶ፣ የትኬቱን ፎቶ እና ሌሎችም ኮንሰርቱን የሚገልጹ ማናቸውንም ፎቶና ቪዲዮ ብታደርሱን መልሰን ወደ ብዙኃኑ እናደርሳለን!
የቴሌግራም አድራሻ...
https://www.tg-me.com/nigus_multimedia
በዚህ ወር ሌላ ድንቅ ታሪክ በአዲስ አበባ መዲና

ከአስራ አምስት አመታት በፊት የሬጌ የሙዚቃ ንጉሥ ቦብ ማርሊ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል መታሰቢያው በአዲስ አበባ በደማቁ ይከበራል። በወቅቱ ከተለያዩ ዓለማት ብዙ እንግዶች የመጡ ሲሆን አንጋፋ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኞችም ተጋብዘዋል። ከጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ እጅግ በደመቀ ሙዚቃ ቀኑ ተፈጸመ። በዕለቱ ቴዲ አፍሮ በተዘጋጀው ግዙፍ መድረክ ላይ ሲረግጥ የሬጌው መንፈስ ከፍ ብሎ ዳንኪራ መታ። ወቅቱ በኢትዮጵያ ትልቅ የፖለቲካ ትኩሳት የተጫረበት ሲሆን። ቦታው እና ወቅቱ ላይ ቴዲ አፍሮ ሲጨመርበት ታሪካዊ ዳራው ጎላ።

ነገሩ እንዲህ ነው... ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በመስቀል አደባባይ ተገኝተው የመስቀል በዓልን በታላቅ ድምቀት አክብረውበታል። በሰራዊቶቻቸው ትርዒት እና በታቦታቱ ግርማ በምዕመኑ ዕልልታ መስቀል አደባባይ የመድመቅ እና የመልካም መንፈስ መመንጫ መሆንን የለመደች በመሆኗ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ትውስታ አላት።

በመቀጠል የመጣው የደርግ መንግስት ታቦትና ንጉሡ በክብር የረገጡትን ቦታ ደም እረጨበት። ብዙ መፈክሮችን አሰማባት። በወቅቱ አጠራራ ሽብር ነዛበት። ቀጣዩ መንግስት ኢኃዴግም ቀይሽብርተኞችን ለማሰብ በቦታው ሙዚየም ተከለበት።

አሁን 1997 ዓ.ም ነው። በቦታው በታሪክ የተከሰቱ እውነቶችን ጠንቅቆ የከተበ መፅሐፍ ሊነበብ መድረኩ ላይ ቆመ። ጃ ያስተሰርያል የሚለውን ግጥም አንዱን አንጓ እንደሚከተለው ቀይሮት ዘፈነ።

"ግርማዊነታቸው ከዚህ አደባባይ
በዙፋን ተቀምጠው ዛሬ ኖረው ባላይ
የሬጌ ዘውድ አርጎ እዩት መንፈሳቸው
ሲከበር ልደቱ ቦብ ማርሊ ልጃቸው"

ይኼን ስንኝ አጢኖ ላደመጠው ቅኔው እልፍ ነው። የማይቋጩትን ቅኔ መፍታት ለኔ አይሆንምና በግርድፉ ግን ጃኑሆይ እዛ አደባባይ ቆመው እንደነበሩ ጠቅሶ ዳግም ስማቸውን ባለም ያነሳው ልጃቸው በዛው አደባባይ ላይ ልደቱ ሲከበር መሆኑን ጠቆመ።

በዚሁ ወር ከአስራ አምስት አመታት በኋላ የካቲት 14/2012 ዓ.ም ቴዲ አፍሮ ዳግም በመድረኩ ላይ ነገሠበት። ነገሰበት ስልህ በአፍሪካ ታይቶ የማይታወቅ ግዙፍ ኮንሰርት አዘጋጀ እያልኩህ ነው። የአዲስ አበባ መግቢያ በሮች ላይ በጠቅላል ትልቅ ፍተሻ ተደረገ። ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ 6 መንገዶች ተዘግተው ኸደ 200 ሺ የሚጠጉ አድናቂዎች ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ለሚጀምር ሙዚቃ ሰልፍ ይዘዋል። በአከባቢው የቲሸርት እና የባንዲራ ሽያጮች ሰፈሩን አድምቀውታል። ሁሉም ሰው በጥሩ መንፈስ አንድ ሰው ለማየት በዚያ ቦታ ተሰብስቧል። ከተለያዩ አገራት በዚህ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ብዙ አድናቂዎቹ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ፣ ከአረብ አገራቶች እና ከአፍሪካ መጥተው ለመታደም በቅተዋል። እንዲሁም ከሐረር፣ ከድሬደዋ፣ ከናዝሬት፣ ከባህርዳር፣ ከጎንደር፣ ከጅማ፣ ከአሰላ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ ከተሞች እና ከሌሎችም ስፍራ በመምጣት በዚህ ግዙፍ ፕሮግራም ላይ ለመታደም በቅተዋል።

ቴዲ አፍሮ በየትም ስፍራዎች ካቀረባቸው ኮንሰርቶች ይኼኛው ግዙፉ ሲሆን በሙያው የሚገኙ ሌሎች አርቲስቶችም የቴዲ አፍሮን ዝና ያመኑበት ብሎም አርቲስቱ በዋዛ የሚተካ አለመሆኑን ያረጋገጡበት አጋጣሚ ሆኗል። ሌላው ታዳሚው ለአርቲስቱ ካለው ፍቅር እና አክብሮት የተነሳ ፍጹም ሰላማዊ በመሆን ያ ሁሉ ህዝብ ተሰብስቦ በሰላም መጠናቀቁ የታዳሚውን ፍፁም የሆነ ስነምግባር ያመለክታል። ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋና ይገባል።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

ሊንኩን በመክፈት በዕለቱ የነበረውን ሙዚቃ እና በአንድ ዩትዩበር የተተረከውን የዕለቱን አስደሳች ውሎ ያድምጡ....
#የካቲት14

https://youtu.be/w6jPX4ita5M
ዘፈን እንዲህ ነው... ሁለት መቶ ሺ ሰው በአንድ ቦታ አስጨፍረኽ ስታበቃ ድንገት ደግሞ መዝፈን ያምርህና ሁለት ሞቶ ሰው የማይሞላበት ስፍራ ላይ ተገኝተ ትዘፍናለ። በቴዲ አፍሮ ደረጃ ክለብ ላይ መዝፈን ከባድ ሊሆን ይችላል። የአገራችን አርቲስቶችም ይኼንኑ ነው የሚያንጸባርቁት። ክለብ /ከተፋ ይሉታል/ መስራት አማራጭ እስኪገኝ እንጂ ተገቢ አይደለም ይላሉ። ቴዲ አፍሮ ደግሞ ስራ ክቡር መሆኑን በተግባር ሲያረጋግጥ በክለብ ድንገት ተገኝቶ ይዘፍናል። ይኼ በድንገት የተገኘ ቪዲዮ ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜያት ይኼንን ተግባር ፈጽሟል።

ጎበዝ ሰራተኛ በሚሰራው ስራ ሳይሆን በሚፈጽመው ስህተት ነው የሚያፍረው። እርሱም ስህተቱን መድገም ልክ ሲመስለው ነው። ከዛ በዘለለ አርሶ አደር ብትሆን ወዛደር፤ ነጋዴ ቢሆን ሸማኔ፤ የቢሮ አልጋይ ቢሉ ወያላ፤ ጥበቃ ብትሆን የሆቴል ማናጀር፤ ዘፋኝ ቢሉህ ተዋናይ፤ የአገሪ መሪ ብትሆን የቀበሌ ሊቀመንበር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ካህን ብትሆን አልያ ደብተራ፤ ዋናው ቁም ነገሩ በታማኝነት ለእውነት እና ለለውጥ መስራት ላይ ነው። ከዚህ በተቃራኒ ሙያህን ካልመነዘርከው ከአንዱ የሚበልጥ ከሌላው የሚያንስ ሙያ የለም። ሁላችንም በሙያችን ለአገራችን እናስፈልጋታለን!

https://youtu.be/PmV7rjm97Ko
Forwarded from Amleset Muchie
#እንኳንማርያምአሜን

ይህ ግጥም ቴዲ አፍሮ ለባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ሁለተኛ ልጃቸውን /የማርያ ቴዎድሮስን/ ስትወልድ የደረሰላት ግጥም ነው።

✔️እንኳን ማርያም አሜን! ✔️

ከፍቅር ፀንሳ ልጅን ያህል ፀጋ፣
ወልዳ ተኝታለች ባልተቤቴ ካልጋ!
ግቡና ጠይቋት አጎበር ገልጣችሁ፣
ሁለት ሆና ሚስቴን ታገኟታላችሁ!
እኔ ሳልሳዊ ነኝ የቤቱ አባወራ፣
'ዕፁብ ዕፁብ' በሉ ይህን ድንቅ ስራ፣
በእናት መሬት ላይ በአባት ገበሬ ህፃን እየዘራ፣
የአንድ አምላክ ሚስጥሩ ሶስት ሆኖ ሲስራ።
"መኑ ከመ አምላክ" የሚካኤል ስሙ፣
እንደ እግዚያብሄር ያለ ማንም የለም ሲሆን የቃሉ ትርጉሙ፣
ራስን እንዳ አዲስ ወልዶ ለመድገሙ፣
የማርያም ነው'ና ሴትነት ቀለሙ።
እንግዲህም አንቺ....
አስመላሽ ነሽና ሲገሰግስ እድሜ በልጅ እያደስሽ፣
መልክ የምታሳዪ እንዳ አዲስ ወልደሽ።

እንኳን ማሪያም አሜን፤ እንኳን ማሪያም አሜን፣
ምስጋና ይድረሰው አንድ ላደረገዉ ስምሽና ስሜን።
የውለታሽን ዳር፤
በቃላት ለመግለፅ ስላቃተው አቅሜን፣
ይሁንሽ ስጦታ 'ሚቀጥለው ዘፈን ከገለፀው ልቤን....

አሜን!!

(ቴዲ አፍሮ: ህዳር 12, 2007 ዓ.ም)

ቴዲ አፍሮ በግጥሙ ውስጥ ባለቤቱን #አስመላሽ እያለ ይጠራታል። ይህ የሆነው በትግርኛ 'አምለሰት' ማለት 'አስመለሰች' ማለት በመሆኑ ነው። የሚካኤል ትርጉምን የሚያነሳው ደግሞ የመጀመሪያ ልጁ ስም ሚካኤል በመሆኑ ነው። በግጥሙ መጨረሻ የጋበዛት ሙዚቃ ደግሞ የንዋይ ደበበን 'አሜን' የሚውን ሙዚቃ ሲሆን ቴዲ አፍሮ "እንደዚህ ሙዚቃ ባለቤቴን የሚገልፅ የለም" ይላል!

ምስሉ በመጫን በድምፅ የቀረበውን ያድምጡ...

https://youtu.be/iOryB_YRiL8
አምለሰት ሙጬ እ.ኤ.አ በ2004 ሚስስ ዩኒቨርስቲ በመሆን ያሸነፈች ሲሆን፣ በ2006 የሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የማዕረግ አሸናፊ ናት። ተዋናይ፣ ሞዴል፣ የፊልም ዳይሬክተር እና ፀሐፊ የሆነችው አምለሰት ሙጬ በኒው ዮርክ ፊልም አካዳሚ እና በጆርናሊስም በ uuc. ውስጥ የፊልም ሥራን ተምራለች።

በዘጠናዎቹ መጀመሪያ ላይ በሞዴሊንግ ዘርፍ በገሃድ ወደ አርት የተቀላቀለችው አምለሰት ሙጬ በኢትዮጵያ የፊልም ስራዎች ውስጥ ብቁ ከሚባሉ ባለሙያዎች ተርታ የምትመደብ ጠንካራ ሴት አርቲስት ነች። አርቲስት እና ፕሮዲውሰር አምለሰት ሙጬ በኢንዱስትሪው ላይ በተዋናይነት፣ በዳይሬክተርነት፣ በሞዴልነት እንዲሁም በፕሮዲውሰርነት እና በጽሑፍ የምትሳተፍ ሲሆን ለአገር ግንባታ እንዲሁም የማህበረሰባዊ ሀላፊነቷን በሚደንቅ ሁኔታ የምትወጣ አርቲስት ነች።

አመለሰት ሙጬ ከሰባት አመት በፊት በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ዝናው የናኘ ሚሊየነር እና ከዓለማችን ፕሮዲውሰሮች የራሱን ዓልበም ፕሮዲውስ በማድረግ የ15ኛ ደረጃን ከያዘው ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ጋ ትዳር በመመስረት የሁለት ልጆች እናት ለመሆን የበቃች ሲሆን በቅርቡም ሶስተኛ ልጃቸውን የፀነሰች ስለመሆኗ በተለያዪ ሚዲያዎች በስፋት እየተዘገበ ይገኛል። አምለሰት ሙጬ ከአገር ውስጥ ሚዲያ አልፋ በተደጋጋማ ከBBC ጋ ቃለ መጠይቅ ያደረገች እጅግ የተከበረች የኪነ ጥበብ ሰው ነች። በተጨማሪም ማያ የተሰኘ የፊልም ድርጅት አቋቁማ በማናጀርነት እየሰራች ትገኛለች።

ሀበሻ ሞዴሊንግን ይቀላቀሉ..
@aradacasting
ገዓት /ገንፎ/ የአጥር ወፍ አትስማሽ...

ምጡን ያቅልልሽ...!
2025/07/06 05:24:00
Back to Top
HTML Embed Code: