Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
"የአጥር ወፍ አትስማሽ!"
በአገራችን ኢትዮጵያ ካሉን ባህሎች አንዱ ነፍሰ ጡር ሴትን መጠየቅና መጎብኘት አንዱ ነው። ለነፍሰ ጡር ሴት ከእናቶች ምክር ይሰጣታል። "ይኼን ብዪ ይኼን ጠጪ... ኧረ ብርድ እንዳይመታሽ፣ ተንቀሳቀሺበት ወዘተ.."
መውለጃዋ በቀረበ ጊዜ ወዳጆቿ፣ ጓደኞቿ ብሎም ጎረቤቶቿ የገንፎ እና የአጥሚት እህሎችን ያዘጋጁላታል። እየተዘፈነ እህል በየ አይነቱ ይፈተጋል። በጥቅሉ ወደ ምድር ውድ የሆነ የሰው ልጅን ልታመጣ ነውና ከእናት ከአባቷ በተጨማሪ ወዳጅ ዘመዶቿ በደስታ ይመላሉ። እግዚአብሔር ባርኮ ልጅ ሊወለድ ነውና ነፍሰጡሯን ሴት ሁሉም ይንከባከባታል። አቅም በፈቀደ ሁሉ አምሮቷ ይፈጸማል። አንዷ ቅቤውን፣ አንዷ ወተቱን ሌላኛዋ ምግቡን እያረጉ ሁሉም ይጠቋታል። በመንገድ ሳይቀር ለነፍሰ ጡሮች ቅድሚያ ይሰጣል።
ነፍሰ ጡሯ ሴት መውለጃዋ በዳረሰ ጊዜ የገንፎ እህል ተፈጭቶ ወደ ቤት ሲገባ ሴት ጎረቤቶች፣ ጓደኞቿና ዘመድ አዝማድ ሁሉ ተጠርቶ ገንፎ ይበሉና "የአጥር ወፍ አትስማሽ" ብለው ይመርቋታል። ይኼም አጥር ላይ ያለች ወፍ ከጎረቤትም በጣም የቀረበች ስለሆነች ድምፅን ቶሎ ስለምትሰማ ነው። ምጥ በመጣ ግዜ ነፍሰ ጡሯ ህመሙ ሳይጠናባት ጩኸቷን ሌላ ሰው ይቅርና የቅርቧ የአጥር ወፍ እንኳን ሳትሰማት በሰላም ትውለድ ማለት ነው። ምጧን ቀላል እንዲያደርግላት መመኘት ማለት ነው።
ከወለደችም በኋላ በአራስ ቤት ሆና እጅግ ይንከባከቧታል። የልጇን ገላ ማጠብ የእናቷ እና የሌሎች የአዋቂዎች ስራ ይሆናል። በአራስ ቤት ሆና ሁሉ እየመጣ "እንኳን ማርያም ማረችሽ" ይላል። ኋላም የክርስትና ዕለት ድግስ ተደርጎ ነድያንን እና ወዳጅ ዘመድን ጠርቶ እየተበላ ይኼንን ድንቅ ነገር ላደረገ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይቀርባል።
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

Forwarded from አራዳ ሞዴል & ተዋናይ Casting
ሴት ልጅ /ነፍሰ ጡር/ ከመውለዷ በፊት ጓደኞቿ፣ ሙዜዎቿ፣ ጎረቤቶቿ እና ዘመዶቿ ተሰብስበው ገንፎ ይበላሉ። /የገንፎ ፕሮግራም ይደረጋል/ ያም በትግሪኛ ገዓት ተብሎ ይጠራል። ሴቶቹም ምጥሽ ይቅለል ብለው ሲመርቁ "ማርያም ተገላግልኪ" ብለው ይመርቋታል። ይኼም ማርያም ምጥሽን ታቅልለው ማለት ነው። የአጥር ወፍ አትስማሽ እንዲሉ!
https://www.tg-me.com/aradacasting
https://www.tg-me.com/aradacasting
Forwarded from Yared Negu Official via @like
ትልቅ ሀሳብ /ቴዲ አፍሮ/
ትልቅ ሀሳብ የተሸከሙ ሰዎች ሀሳብን ሳይገልጡ ቢያልፉ ኪሳራ ነው። ድንቅ ሀሳብ የገለጡ፣ ከሀሳብ ጋ የታገሉ፣ መፍትሄ አዘል ሀሳብ ያሳደጉ ደግሞ ድንቅ ናቸው። ዘመን እንዳይረሳቸው ዘመን የሚያህል ሀሳባቸው በየዘመኑ እየጎላ ያንጸባርቃል። ቴዲ አፍሮ የዕልፍ ሀሳቦች ባለቤት ነው። ዕልፍ አዕላፍ የነጠሩ ረቂቅ ሀሳቦች ከእርሱ ይመነጫሉ በዕርሱ ይገለጣሉ። እኒያ የገዘፉ ሀሳቦቹ በሁሉ እንዲወደድ አበቁት።
ቴዲ አፍሮ በማንነቱ ኮርቶ የሚያኮራ አገራችንን በዓለም መድረክ በመልካም ያስጠራ! ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ እድገት ብሩህ ተስፋን የሚያልም፣ ለኔ ብቻ ሳይሆን ለወገኔ ብሎ የሚጨነቅ፤ በቃሉ የጸና ድንቅ የአገራችን እንቁ ልጅ ነው።
ቴዲያችን ለኢትዮጵያ እና ለኪነ-ጥበቧ እድገት ታስፈልጋለህና እረጅም እድሜ ከጤና ጋ እንመኝልኃለን!
ፍቅር ያሸንፋል..!
ያሬድ ነጉ

አርቲስት ቴዲ አፍሮ የቴዎድሮስ አበባው /ቴዲ ቡናማው/ ባለቤት ለሆነችው ህይወት ስልክ በመደወል በወጣቱ ባለቤቷ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ እሷምን አፅናንቷታል።
በእውነት የሆነ የሰዎች አይዞህ ባይነት በኃዘን የተሰበረን ልብ ይጠግናል። ከእውነት የሆነ ማጽናናት በልብ ያለን ሀዘን ሽሮ በደስታ ይመላል። አሁንም ለቤተሰብቹ ለጎደኞቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።
ቴዎድሮስ አበባውንም በገነት ከቅዱሳን ጋ ነፍሱን ያሳርፍልን ዘንድ የቅዱሳን ወዳጅ የድሆች አባት የሆነ ሐያሉ እግዚአብሔር መልካም ፍቃዱ ይሁን!
በእውነት የሆነ የሰዎች አይዞህ ባይነት በኃዘን የተሰበረን ልብ ይጠግናል። ከእውነት የሆነ ማጽናናት በልብ ያለን ሀዘን ሽሮ በደስታ ይመላል። አሁንም ለቤተሰብቹ ለጎደኞቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።
ቴዎድሮስ አበባውንም በገነት ከቅዱሳን ጋ ነፍሱን ያሳርፍልን ዘንድ የቅዱሳን ወዳጅ የድሆች አባት የሆነ ሐያሉ እግዚአብሔር መልካም ፍቃዱ ይሁን!
Forwarded from አራዳ ሞዴል & ተዋናይ Casting
እውቋ ሞዴል፣ ተዋናይት የፊልም ጸኃፊ፣ ዳይሬክተር የሆነችው አርቲስት አምለሰት ሙጬ ዛሬ መጋቢት 16/2013 ዓ.ም በግሬስ ሆስፒታል ሴት ልጇን ተገላግላለች!
እንኳን ማርያም ማረችሽ!
አራዳ ካስቲንግ ለአርቲስት አምለሰት ሙጬ እና ለባለቤቷ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ እንኳን ደስ ያላችሁ ይላል። ልጃችሁን ኃያሉ እግዚአብሔር በጥበብ ያሳድግላችሁ!
@aradacasting
እንኳን ማርያም ማረችሽ!
አራዳ ካስቲንግ ለአርቲስት አምለሰት ሙጬ እና ለባለቤቷ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ እንኳን ደስ ያላችሁ ይላል። ልጃችሁን ኃያሉ እግዚአብሔር በጥበብ ያሳድግላችሁ!
@aradacasting
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
✔ለውዴ ውዱ ነሽ✔
በጎደለ ሞልተሽ፤ በጠፋው ተክተሽ፣
ሲዝል አበርትተሽ፤ ግራውን ደግፈሽ፣
የብቸኝነት ጉዞውን፤ በጥንድ ቀይረሽ፣
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው፤ መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣ እራስሽን ደግመሽ።
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ብሩክቲ እናት?
ሁሌም አብራው ያለች፤ እየሆነች ብርታት፣
ለብላቴናው ክብሩ፤ ለልቡም ዘውድ ናት።
እንደ ግጥሜ ርዕስ፤ እንደ ስንኝ ቋጠሮ፣
እንደ ጠቢብ ቅኔ፤ እንደ ፀሐይ ኑሮ፣
ልብሽ ብሩህ ነው፤ ዘውትር የሚፈካ፣
መልክሽ በለስ ነው፤ ውዴ ባንቺ 'ረካ።
የሰጠሽው ፀጋ፤ የሰማይ ላይ መና፣
እንደ ምድር ሃመልማል፤ የፈካ ነውና፣
ልቡን ፍቅር ሞላው፤ ደስታውም አበበ፣
ለውዴ ውዱ ነሽ፤ በመልክሽ ተዋበ!
እንደ ከዋክብ ብዙ፤ እንደ ጀምበር ውብ፣
አንድ ሰው እልፍ ነው፤ ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ፤ ሁሉን የሆንሽለት፣
ጤና ይስጥሽ አምላክ፤ ዘላለም ኑሪለት!
እንደ ምድር አሸዋ፤ እንደ አባይ ጅረት፣
አንድ ሰው ብዙ ነው፤ ፍቅር ከሞላበት!
በዝተሽ አበዛሽው፤ በርተሽ አፈካሽው፣
ከፊትም ከኋላም፤ በሁሉም ከበሽው።
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
በጎደለ ሞልተሽ፤ በጠፋው ተክተሽ፣
ሲዝል አበርትተሽ፤ ግራውን ደግፈሽ፣
የብቸኝነት ጉዞውን፤ በጥንድ ቀይረሽ፣
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው፤ መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣ እራስሽን ደግመሽ።
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ብሩክቲ እናት?
ሁሌም አብራው ያለች፤ እየሆነች ብርታት፣
ለብላቴናው ክብሩ፤ ለልቡም ዘውድ ናት።
እንደ ግጥሜ ርዕስ፤ እንደ ስንኝ ቋጠሮ፣
እንደ ጠቢብ ቅኔ፤ እንደ ፀሐይ ኑሮ፣
ልብሽ ብሩህ ነው፤ ዘውትር የሚፈካ፣
መልክሽ በለስ ነው፤ ውዴ ባንቺ 'ረካ።
የሰጠሽው ፀጋ፤ የሰማይ ላይ መና፣
እንደ ምድር ሃመልማል፤ የፈካ ነውና፣
ልቡን ፍቅር ሞላው፤ ደስታውም አበበ፣
ለውዴ ውዱ ነሽ፤ በመልክሽ ተዋበ!
እንደ ከዋክብ ብዙ፤ እንደ ጀምበር ውብ፣
አንድ ሰው እልፍ ነው፤ ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ፤ ሁሉን የሆንሽለት፣
ጤና ይስጥሽ አምላክ፤ ዘላለም ኑሪለት!
እንደ ምድር አሸዋ፤ እንደ አባይ ጅረት፣
አንድ ሰው ብዙ ነው፤ ፍቅር ከሞላበት!
በዝተሽ አበዛሽው፤ በርተሽ አፈካሽው፣
ከፊትም ከኋላም፤ በሁሉም ከበሽው።
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/