Telegram Web Link
ፍቅር....
ኢትዮጵያችን ታሸንፍ...💚💛❤️

መሬት ሲመታ
( ቴዲ አፍሮ )

ዋልያ፣ ዋልያ፣ ዋልያ፣ ዋልያ
ዋልያው ብርቁ፣
ይታይ ሰንደቁ፣
ወኔ ታጠቁ፤ X2

ባና ባና ሳተናው ዋልያው ሆ
የኮርብታው ብርቁ
ከዳሸን ተራራ ጫፉ ላይ ያረገው
እንዲታይ ሰንደቁ X2

ታጥቄ የወኔ እሳት ግባ ከሜዳው ድፈር.....ዋልያ ዋልያ
ካናብስቶቹ ምድር ቀንሼ ልስጥህ አፈር.....ዋልያ ዋልያ
አልመህ በኳስ አፈራርሰኃል እንኳንስ ጎል ግቡን
የ30 ዓመት አሮጌ ግንቡን

ባና ባና ሳተናው ዋልያው ሆ
የኮርብታው ብርቁ
ከዳሸን ተራራ ጫፉ ላይ ያረገው
እንዲታይ ሰንደቁ X2

ዛሬም ይደነቁ...................እንዲታይ ሰንደቁ
ዘምቶ በወኔ.....................እንዲታይ ሰንደቁ
ቢወሳ አንበሳ...................እንዲታይ ሰንደቁ
ጀግና አይደለም ወይ..........እንዲታይ ሰንደቁ
ወድቆ 'ሚነሳ....................እንዲታይ ሰንደቁ X2

ወሰን አስፍቶ.....................እንዲታይ ሰንደቁ
ዘማች ሲመለስ..................እንዲታይ ሰንደቁ
እንዲህ አይደለም ወይ.........እንዲታይ ሰንደቁ
ጀግና 'ሚወደስ..................እንዲታይ ሰንደቁ
መሬት ሲመታ....................እንዲታይ ሰንደቁ
አቧራው ሲጨስ.................እንዲታይ ሰንደቁ X3

ባና ባና ሳተናው ዋልያው ሆ
የኮርብታው ብርቁ
ከዳሸን ተራራ ጫፉ ላይ ያረገው
እንዲታይ ሰንደቁ
ባና ባና ሳተናው ዋልያው ሆ
የኮርብታው ብርቁ
ከዳሸን ተራራ ጫፉ ላይ ያረገው
እንዲታይ ሰንደቁ

አርማ ማለት ሰንደቅ
ማልያ ማለት ዋልያ
ዋልያ ዋልያ
አንተን ማየት ለዓለም፤
ብርቅ ነው ከኢትዮጵያ......ዋልያ ዋልያ
አልመህ በኳስ አፈራርሰካል እንኳንስ የጎል ግቡን
የ30 ዓመት አሮጌ ግንቡን...
ይታይ ሰንደቁ!

በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ብሔራዊ ስሜታችን ሊጠናከር በሚገባበት በዚህ ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተቀዳጀው ድል የተሰማኝን ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ።

እንኳን ደስ ያላችሁ!

ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቀጣይ ዙር በማለፉ የአገራችን ዝነኛው አርቲስት ቴዲ አፍሮ የተሰማውን ደስታ ገልጿል። እንደሚታወቀው ዛሬ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከኢትዮጵያ ወደ አይቮሪኮስት በመጓዝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ለሚደግፉ ተጓዦች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና BGI ኢትዮጵያም የበኩላቸውን እንደተወጡ የደጋፊዎች ማህበር በገጹ አስታውቋል። ለአገራችን ኢትዮጵያ ዘወትር ስለምታደርገው ድጋፍ ከልብ እናመሰግንኃለን!!

የሚከተለው ጽሁፍ ከአርቲስቱ ገጽ የተወሰደ ነው።

ይታይ ሰንደቁ!

በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ብሔራዊ ስሜታችን ሊጠናከር በሚገባበት በዚህ ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተቀዳጀው ድል የተሰማኝን ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ።

እንኳን ደስ ያላችሁ!

ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
#Repost #ታታአፍሮ

መልካም ልደት ለአምለሰት ሙጬ እና ለትልቁ ልጇ ለሚካኤል ቴዎድሮስ!

ሚካኤል ቴዎድሮስ /ቾቾ/ እና አምለሰት ሙጬ መልካም ልደት ይሁንላቹ...🎂 ልጅ ሚካኤል ቴዎድሮስ የዛሬ 8 አመት መጋቢት 28/2005 ዓ.ም ተወለደ። እነሆ በታሪክ በዝህች ዕለት በኢትዮጵያ የፋሺስት ኢጣሊ ጦር አዲስ አበባን ሙሉ ለሙሉ የለቀቀበት ዕለት ሲሆን በወሩም ሚያዝያ 27 ንጉሠ ነገሥቱ የኢትዮጵያን ባንዲራ የሰቀሉባታ የአርበኞች ቀን ተብሎ የሚከበር ድርብ የደስታ ቀን ነው። ልብ በሉ የአርበኞች ቀን በደርግ ዘመን መጋቢት 28 ነበር የሚከበረው። በንጉሡ ዘመን ደግሞ እንደ አሁኑ ሚያዝያ 27 የነፃነት ቀን ተብሎ ይከበር ነበር። ይኼኛው ደግሞ ንጉሡ ገብተው በእጃቸው የኢትዮጵያን ባንዲራ የሰቀሉባት ዕለት ስለሆነች ነው። አባቱ በሚወደው ቀን አባቱ በሚሞትላት አገር ወንድ ልጅ ከደግ እናት ተወለደ። ሚካኤል ቴዎድሮስ መጋቢት 28 እናቱም በዚሁ ወር በዛሬዋ ዕለት መጋቢት 27 ወደዝህች ምድር መጡ። ለሁለቱም የንጉሡ ጉልበቶች መልካም ልደት እንመኛለን 🎂🎂

ቴሌግራማችንን ይጎብኙ..👇

https://www.tg-me.com/teddyafronet
@
የኔ ውብ ዛሬ የታላቅ ወንድምሽ 8ኛ የልደት በዓል ነው! አንቺም አስራ ሁለተኛ ቀንሽ ነው! እንኳን አየንሽ! እንኳን ተወለድሽልን....! እንወድሻለን የእናታችን የኪዳነምህረት ስጦታ!

የቴዲ አፍሮ እና የአምለሰት ሙጬ ሶስተኛ የአብራክ ክፋያቸው....
✔️ለይኩን✔️

እንዲህ ነው እንጂ ማመስገን ደጋግሞ
ሲሰጥ ሲባርክ አብልጦ ከቀድሞ!
አሁንም ይለቅጥ ተመስገን ማለቱ
ልክ እንደ ፊቱ ልክ እንደ ጥንቱ!

ምህረት እንዲሆን በቀኗ በ'ለቱ
ዘር የሰጠበት የባረከበቱ፣
አምላክ ይመስገን ለበዛ ቸርነቱ!

ፀጋን የተመላሽ ጌታን ወላጅቱ
ድንግል ስምሽ ይክብር አማላጅቱ
አምስት ለሆንበቱ!

አሜን አሜን፤ አሜን ነው መልሳችን!
ለይኩን ለይኩን፤ ለይኩን ነው ቃላችን!
ለልጅሽ ንገሪው፤ ማርያም እናታችን!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

ስዕል በአብርሃም ገነቱ
2025/07/05 02:30:50
Back to Top
HTML Embed Code: