¶በላጭ ሕዝቦች¶ via @like
አንድ ንጉስ ህዝቦቹን ሰብስቦ እንዲህ ይላቸዋል።
ሚስቱን ተገዢ በዚህ መስመር ይቁም
እንቁላል ይሸለማል
ሚስቱ የምትመራው ደግሞ በዚህ መስመር ይቁም
ፈረስ ይሸለማል
ወንዶች ሁሉ ሚስቱ የምትመራው ይቁም የተባለው መስመር ላይ ቆሙ። ንጉሱ አንድ አንድ እንቁላል ሰጣቸው።
አንድ ሰው ብቻ እኔ ሚስቴን እመራለው አለ። ንጉሱም አንተ ነህ ጀግና በል ከነዚህ ከ3 ፈረሶች የፈለግከውን ውሰድ ብሎ ሸለመው ጥቁር፣ነጭ እና ቡኒ ነበሩ።ሰውዬም ቡኒውን ፈረስ ይዞ ወደ ቤት ይሄዳል።ለሚስቱም እኔ የቤቱ አለቃ ነኝ ዛሬ ይህን ፈረስ ንጉሱ ሸልሞኝ ነው ። እንዴት ነው ፈረሱ መርጬው ነው አላት ሚስትየውም በባል ቁጥጥር ስር እንደሆነች ስለተሰማት ይህም ያምራል ግን ጥቁር ፈረስ ደግሞ የበለጠ ካንተ ጋር ይሄዳል ትለዋለች።
ባልም አሁንም የፈለግኩትን ፈረስ የመቀየር ምርጫ አለኝ ብሎ ቡኒውን ፈረስ በጥቁር እንዲለወጥለት ንጉሱ ዘንድ ድጋሜ ይሄዳል።ንገሱም ለምን ተመልሶ እንደመጣ ይጠይቀዋል። ሚስቴ ጥቁሩን ፈረስ እንድመርጥ ነግራኝ ነው ይለዋል።ንጉሱም ፈረሱን ተቀብሎ እንቁላል ሸለመው ይባላል።

ምነው አይናፍቁ ምነው አይናፍቁ
የጠፋ ግዜና ምነው አይናፍቁ
የጠፋ ግዜና ሀቅ ተናጋሪ
እባካችሁ ሲባል እውነቱን መስካሪ
ጎረቤት ሲጠፋ ውዴታ አጠንካሪ
ሌት ቀን ይናፈቃል የነብዩ ባህሪ።
ከአንጀት አልገኝ ስል ከልብ ሰላምታ
ከሰው ላይ ሲጠፋ ፍቅርና ውዴታ
ትዕግስት ችሎ ማለፍ ወይ ደግሞ ይቅርታ
የጠፋ ግዜና መልካም ፊት ፈገግታ
ትዝ ትዝ ይላሉ ነብዩ የኛ አለኝታ።
የጠፋ ግዜና ሰው የሚያከብር ሰው
ያልተገኘ ግዜ የሚኗኗሩት ሰው
የት ይገኝ ያሉ ለት የማይቀየር ሰው
የቸገረ ግዜ ሰው የሚያስታርቅ ሰው
ትዝ ትዝ ይላሉ ነብዩ መላልሰው።
የጠፋ ግዜና ለ አኺራ 'ሚዋደድ
ለቂያማ ቀን ጥላ ብሎ የሚላመድ
ሲታጣ አብሮ የሚጓዝ በእስልምና መንገድ
በሀገሩም ሲጠፋ ዘመድ አዝማድ ወዳጅ
ምነው አይናፍቁ ነብዩ ሙሀመድ።
የጠፋ ግዜና ነብሱን የሚቀጣ
ቁርአንና ሀዲስ ሰው ጥሎ ሲወጣ
እንግርግር ሲያደርግ ሰው ከ ሰው መረጣ
የነቢ መሀመድ ስብዕና እየመጣ
ሆድ ይበረብራል ዐይን እንባ እያወጣ…
ያልተገኘ ጊዜ ለታናሾቹ አዛኝ
ታላቁን አክባሪ ሲጠፋ ዕድሜ መዛኝ
ሁሉም ለኔ እኔ ሲል ሲጠፋ ተዛዛኝ
ሚዛን ሁሉ እሪ ሲል ሲጠፋ ተመዛኝ
የነብዩ ባህሪ ምነው ናፍቆ አይገዛኝ።
(ሙሀመድ አወል ሳላህ
@theamazingquran
የጠፋ ግዜና ምነው አይናፍቁ
የጠፋ ግዜና ሀቅ ተናጋሪ
እባካችሁ ሲባል እውነቱን መስካሪ
ጎረቤት ሲጠፋ ውዴታ አጠንካሪ
ሌት ቀን ይናፈቃል የነብዩ ባህሪ።
ከአንጀት አልገኝ ስል ከልብ ሰላምታ
ከሰው ላይ ሲጠፋ ፍቅርና ውዴታ
ትዕግስት ችሎ ማለፍ ወይ ደግሞ ይቅርታ
የጠፋ ግዜና መልካም ፊት ፈገግታ
ትዝ ትዝ ይላሉ ነብዩ የኛ አለኝታ።
የጠፋ ግዜና ሰው የሚያከብር ሰው
ያልተገኘ ግዜ የሚኗኗሩት ሰው
የት ይገኝ ያሉ ለት የማይቀየር ሰው
የቸገረ ግዜ ሰው የሚያስታርቅ ሰው
ትዝ ትዝ ይላሉ ነብዩ መላልሰው።
የጠፋ ግዜና ለ አኺራ 'ሚዋደድ
ለቂያማ ቀን ጥላ ብሎ የሚላመድ
ሲታጣ አብሮ የሚጓዝ በእስልምና መንገድ
በሀገሩም ሲጠፋ ዘመድ አዝማድ ወዳጅ
ምነው አይናፍቁ ነብዩ ሙሀመድ።
የጠፋ ግዜና ነብሱን የሚቀጣ
ቁርአንና ሀዲስ ሰው ጥሎ ሲወጣ
እንግርግር ሲያደርግ ሰው ከ ሰው መረጣ
የነቢ መሀመድ ስብዕና እየመጣ
ሆድ ይበረብራል ዐይን እንባ እያወጣ…
ያልተገኘ ጊዜ ለታናሾቹ አዛኝ
ታላቁን አክባሪ ሲጠፋ ዕድሜ መዛኝ
ሁሉም ለኔ እኔ ሲል ሲጠፋ ተዛዛኝ
ሚዛን ሁሉ እሪ ሲል ሲጠፋ ተመዛኝ
የነብዩ ባህሪ ምነው ናፍቆ አይገዛኝ።
(ሙሀመድ አወል ሳላህ
@theamazingquran
ስብዕና..
"ከህመሞችሁሉ ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤይድስ ሊመስለን ይችላል። እውነቱ ግን
# ከስብዕና_መዛባት የከፋ ህመም የለም። ውጫዊ መልክ የሠው የገጽ ሽፋን ነው። ስብዕና ግን የሠው እውነተኛ መልክ ነው። በየዕለቱ አብረን የምንኖረው ሰው ቢኖር፣ እውነተኛና የማያረጅ ዘላቂ ማንነታችን ሰብዕናችን ነው። በዓይናችን የማናየው እውነተኛ መልካችን በውስጥ ማንነታችን ውስጥ ተቀብሮ ያለው ሰብዕናችን ነው። የሰብዕና ስንኩልነት፣ ጠባሳዎችና መዛባቶች ቤት ያፈርሳሉ፣ አገር ይንዳሉ፣ ግንኙነትን ይመርዛሉ። ለማከም ለማዳን ብቻ ሳይሆን ለማየትና ህመሙን ለመረዳትም አዳጋች ነው።
ሰብዕና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው። የብዙ ሠው ሰብዕና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ በልጅነት ጊዜ በትክክል የሚቀርፀው ካለገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። ዕድሜው ከገፋ በኋላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶት አገር ያጠፋል። የልጅ ውበቱ በቀላሉ መሰራቱ...ያዋቂ ክፋቱ ለመለወጥ አስቸጋሪ የሆነ ክፉ እውቀቱ ነውና።"
•

ያልጠገገ ቁስል...ያልሻረ ህመም.....ያመረቀዘ አሳር
የማለዳው ንጋት
የአበባው ፍካት
የአእዋፋት ዜማ
የስኬቱን ማማ
ለማየት ያልቻለ
ብርሃን ያልታደለ
ከወንጀል አዘቀት
መውጣት ያዳገተው
ትግሉ የከበደው
መኖርን ያልኖረው
ከአድማስ ባሻገር ብርሃን የሚናፍቅ
አንድ ባሪያ አለ ጌታውን ሚያምፀው
ስሜቱን ያልገታ
ሸህዋውን ያልረታ
የአኺራን ጭንቀት በቅጡ ያልተረዳ
ነፍሱን የሚበደል እራሱን ያልረዳ
አለ አንድ ባሪያ እራሱን የጎዳ
ግን አላህዬ.....
እርጋታ አጥቶ እጅግ ቢዋትትም
ካንተ ራህመት መቼም! ፍፁም ተስፋ አይቆርጥም
ረህማን እዘንለት ሃያቱ ከብዶታል
አንተኑ ማመፅ በጣም ሰልችቶታል
ነፍሲያና ሸይጧን ተባብረውታል
አንተን ሊገዛ እንጂ ሊያምፅህ መች ይሻል
ሰትረህ እንዳኖርከው ሰትረህ አንተ አንፃው
እውነተኛ መልኩን አንተ ነህ ምታውቀው
ከልቡ ሊገዛህ ሊያመልክህ ነው ሚሻው
እባክህ ማረው ረኡፉ ራራለት
ከጀሃነም ቅጣት ከጋመው እሳት
አንተዉ ጠብቀው አንተዉ እዘንለት
ይቅር በለውና ህይወቱ ይመርለት
ከገባበት አዘቅት ስምጥ ከዋኘበት
ቁዋ ሁነውና ዳግም ያንሰራራ
በምድሩ ይራመድ እንደሰው ሳይፈራ
©አትዘን
https://www.tg-me.com/theamazingquran
የማለዳው ንጋት
የአበባው ፍካት
የአእዋፋት ዜማ
የስኬቱን ማማ
ለማየት ያልቻለ
ብርሃን ያልታደለ
ከወንጀል አዘቀት
መውጣት ያዳገተው
ትግሉ የከበደው
መኖርን ያልኖረው
ከአድማስ ባሻገር ብርሃን የሚናፍቅ
አንድ ባሪያ አለ ጌታውን ሚያምፀው
ስሜቱን ያልገታ
ሸህዋውን ያልረታ
የአኺራን ጭንቀት በቅጡ ያልተረዳ
ነፍሱን የሚበደል እራሱን ያልረዳ
አለ አንድ ባሪያ እራሱን የጎዳ
ግን አላህዬ.....
እርጋታ አጥቶ እጅግ ቢዋትትም
ካንተ ራህመት መቼም! ፍፁም ተስፋ አይቆርጥም
ረህማን እዘንለት ሃያቱ ከብዶታል
አንተኑ ማመፅ በጣም ሰልችቶታል
ነፍሲያና ሸይጧን ተባብረውታል
አንተን ሊገዛ እንጂ ሊያምፅህ መች ይሻል
ሰትረህ እንዳኖርከው ሰትረህ አንተ አንፃው
እውነተኛ መልኩን አንተ ነህ ምታውቀው
ከልቡ ሊገዛህ ሊያመልክህ ነው ሚሻው
እባክህ ማረው ረኡፉ ራራለት
ከጀሃነም ቅጣት ከጋመው እሳት
አንተዉ ጠብቀው አንተዉ እዘንለት
ይቅር በለውና ህይወቱ ይመርለት
ከገባበት አዘቅት ስምጥ ከዋኘበት
ቁዋ ሁነውና ዳግም ያንሰራራ
በምድሩ ይራመድ እንደሰው ሳይፈራ
©አትዘን
https://www.tg-me.com/theamazingquran
ትልቅ__ነጥብ
ሰዎች ዘንድ ለመወደድ ስትለፋ ጌታህ ዘንድ እንዳትጠላ ተጠንቀቅ።
ክብርን ለማግኘት ክብር ከሌለው ተግባር ተቆጠብ!
ሀቅን እንጂ ሰወችን አትከተል።
መኖርህን ስታይ መሞትህንም አትርሳ! ኖረህም የሚጠቅምህን ስትሞትም የሚከተልህን ስራ
ለምትወዳቸው ሰወች ክብር ስታበዛ የጌታህን ክብር እንዳትነካ ተጠንቀቅ።
ሰወችን በመውደድ ብቻ ስትጠመድ የጌታህን ውዴታ እንዳትነፈግ ፍራ! ጥላቸው ማለት አይደለም ውዴታህ
በልክ ይሁን!
እውነት ለመናገር ከሰወች ጥቅምን አትፈልግ! ሰወችን ለማስደሰት አትዋሽ! ለህሊናህ እረፍት አስበህ
እውነተኛ ሁን!
የራስክን ደስታ ለማሞቅ ለሌሎች ሃዘን ሰበብ አትሁን! በሌሎች ደስታ ተደሰት! ከምቀኝነት እራቅ!
ለጥፋት መሆንን እንጂ መባልን አትፍራ! ሆኖ ለመገኘት እንጂ ለመባል አትድከም።
ፍርድ ለመስጠት ከመወሰንህ በፊት ዳኛ ለመሆን አቅሙ እንዳለክ እራስክን ጠይቅ።
ለመውቀስ ከመቸኮል ለማጣራት ሞክር ! መልስ ከመስጠትህ በፊት ጥያቄውን አስተንትን!
ማንነትህን ለማሳወቅ በአፍህ ከመናገር ይልቅ ስራበት! ተግባርህ ያስረዳ!
መልካም ለመሆን አትምረጥ። ለሁሉም መልካም ሁን አትጎዳበትም።

💚 ደስታህን በአላህ እንጂ
በማንም ላይ አታንጠልጥላት‥
⇘ ወዳጅ ይደርቃል ፣ ቅርቡ ይርቃል
ነዋሪው ይሞታል ፣ ሀብትም ያልቃል
ጤናም ይወገዳል ።
⇨ከአላህ በስተቀር የሚቀር የለም
በማንም ላይ አታንጠልጥላት‥
⇘ ወዳጅ ይደርቃል ፣ ቅርቡ ይርቃል
ነዋሪው ይሞታል ፣ ሀብትም ያልቃል
ጤናም ይወገዳል ።
⇨ከአላህ በስተቀር የሚቀር የለም
#መልካም_ሥራ_ተቀባይነት_እንዲያገኝ #መሟላት_ያለባቸው_ነገሮች_ምንድ ናቸው* ?!
"መልካም ሥራ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሶስት (3) ነገሮች መሟላት አለባቸው ።
. እነሱም:-
በአላህ አንድነትና ብቸኛ አምላክነት በትክክል ማመን።!
. (ቁርአን እንዲህ ይላል😊
«إن الذين امنوا وعملوا الصالحات كانت لهم جنات الفردوس نزلآ » سورة الكهف.
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎንም የሠሩ " የፈርደውስ ገነቶች ለነሱ መስፈሪያ ናቸው።!
و قال صلى الله عليه و سلم قل امنت بالله ثم استقم « رواه مسلم. »
📰 የአላህ መልእክተኛ " ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም )
"እንዲህ ብለዋል :- በአላህ አመንኩ በልና በፍቃዱም ቀጥ በል።
. (ሙስሊም)
2} ሥራው የጠራና ከልብ የመነጨ መሆን:- ይህም ማለት ➖የሚሰራው መልካም ሥራ ለአላህ ውዴታ ተብሎ መሆን " እንዳለበት የሚያስገነዝብ ነው።
📰ሥራው" ስዎች ለማስደሰት ከሰው ፊት አክብሮትንና አድናቆትን ለማትረፍ ተብሎ የተሰራ 😞የይስሙላ ሥራ) መሆን የለበትም።!
📜 « و ما أمروا الا ليعبدوا الله مخلصين له الدين حنفاء. » سورة البينة.
አላህን ፡- ሀይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች " ቀጥተኞች ሆነው ሊገዙት፦ (98:5)
*ሰራዎች መከናወን ያለበት የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) ባስተማሩት መሰረት መሆን አለበት*።
📜 «وما اتاكم الرسول فخذوه وما نهاكم عنه فانتهوا واتقوا الله إن الله شديد العقاب» سورة الحشر.
📜መልዕክተኛው የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት። ከእርሱም የከለክላቹሁን ነገር ተከልከሉ። አላህንም ፍሩ ፦ አላህም ቅጣተ ብርቱ ነውና።(59፡7)
📜 و قال صلى الله عليه و سلم من عمل عملآ ليس عليه امرنا فهو رد » رواه مسلم.
የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም)
የእኛ ፍቃድ ያልሆነን ነገር ያከናወነ ሰው ተግባሩ ውድቅ ነው። ሲሉ ተናግረዋል። (ሙስሊም) ✍️___

ቀልብህን (ልብህን) አጥራ!
የተከበሩት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ኢብን ሷሊህ አል ዑሰይሚን አላህ ይማራቸውና እንዲህ ብለዋል፦
ወንድሜ ሆይ! አካልህን ከማፅዳትህ በፊት ልብህን ማፅዳት ላይ ጥረት አድርግ!
ስንትና ስንት ሰዎች ይሰግዳሉ ,,,
▪ይፆማሉ,,,
▪ሶደቃ ይሰጣሉ,,,
▪ሀጅ ያደርጋሉ,,
ነገር ግን ልባቸው የተበላሸ ነው።
ተመልከቱ ኸዋሪጆችን ስለ እነርሱ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተናገሩባቸውን፦
▶እነርሱ ይሰግዳሉ
▶ ይፆማሉ
▶ሶደቃ ይሰጣሉ
▶ቁርአን ይቀራሉ
▶ለይል ይቆማሉ (ይሰግዳሉ)
▶ያለቅሳሉ
▶ተሀጁድ ይሰግዳሉ
▶ሶሃባዎች ከነሱ አንጻር የራሳቸውን ሶላት ይንቃሉ!
🗯لكن قال النبي عليه الصلاة والسلام:
(( لا يجاوز إيمانهم حناجرهم )⛔️لا يدخل الإيمان قلوبهم .
ነገር ግን ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
((ኢማናቸው ከጉሮሯቸው አይወርድም))
ኢማን ቀልባቸው (ልባቸው) ውስጥ አይገባም!
ላያቸው መልካም ሆኖ ሳለ ፣ ነገር ግን አልጠቀማቸውም!
ላይህ በመስተካከሉ አትታለል
ከሁሉም ነገር በፊት ወደ ቀልብህ ተመልከት!
🌱أسأل الله أن يصلح قلبي وقلوبكم.
🌱 አላህ የኔንም የናንተንም ቀልብ እንዲያስተካክልን እጠይቀዋለሁ (እለምነዋለሁ) !
==============
📝المصدر : شرح رياض الصالحين [327/2]
=====
📝ምንጭ: ሸርህ ሪያዱ አስ–ሷሊሂን [2/327]

አንድ ሰለፍ እንዲህ አሉ ;-
"ለይል ለሰላት ስትነሳ "ይህ ሁሉ ሰው ተኝቶ እኔ ላመሰግን ተነሳሁ !" ብለህ አትመፃደቅ። ይልቅስ "እነዚህ የተኙት ስራቸው ይበቃቸው ይሆናል ። የኔ ወንጀል ግን ለይልም ቆሜ የሚታበስ አይመስልም።" ብለህ ነብስህን አሳንሳት።"
"አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድም።
🌷🌹
"ለይል ለሰላት ስትነሳ "ይህ ሁሉ ሰው ተኝቶ እኔ ላመሰግን ተነሳሁ !" ብለህ አትመፃደቅ። ይልቅስ "እነዚህ የተኙት ስራቸው ይበቃቸው ይሆናል ። የኔ ወንጀል ግን ለይልም ቆሜ የሚታበስ አይመስልም።" ብለህ ነብስህን አሳንሳት።"
"አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድም።
🌷🌹
¶በላጭ ሕዝቦች¶ via @like
አንድ እውነት አለው.....
ሀሳቡን ሰድሮ ሊገልፅ ባይቻለው
እውነቱን ተንትኖ ችሎ ባያስረዳው
ከዘመን አሻግሮ ዘመንን ያኖረው
አንድ እውነት ነበረ ልቡ ሚዘውረው
ፍቃደኛ ሆነህ ጆሮህን ብትሰጠው
ሊነግርህ ያሰበው አንድ እውነት ነበረው
ሌባ ነው አልከው ስም አወጣህለት
ለማኝ ነው አልከው ወዶ ባልገባበት
ብዙ ስም ሰጠኸው ጣትህን ቀሰርክበት
ሳትጠይቀው በፊት ፍርዱን ሰጠህበት
ልታየው አስጠላህ እጅግ አፈርክበት
እሱም ባንተ ቢያዝንም ብዙ አመት ጠበቀ
ተስፋ ሳይቆርጥብህ ድምፅህን ናፈቀ
በችግር በርሃብ እጅጉን ማቀቀ
ብትጠይቀዉ ኖሮ...
ይነግረህ ነበረ የእሱ ማንነቱን
የህይወት አሳሩን የልፋት መዓልቱን
የቀን የሌት ትግሉ መራብ መጠማቱን
ሰው የመራቡን መታረዝ ማጣቱን
ወቃሹ መብዛቱ ቀኑ ማዘቅዘቁን
ዛሬ ግን😢
የፍቅር መሻቱ
ሰውን መናፈቁ
ብቸኝነት
ማጣት
መራቡ ማጣቱ.....
ተደራርበውት
ከትግሉ ሜዳ ላይ ድንገት አፈረጡት
ቁልቁል ስበው እታች ከመሬት ለወሱት
።።።።።።።።።።።።።።።።
የግጥሙ መልክት፦ሰዎችን በቅን ልቦና ቀርበን እናድምጣቸው በመስማታችን ብቻ ምናቀልልቸው ሸክም አለ።ደሞ ከፍርድ በፊት ማድመጥ ይቀድማል አንቸኩል "ችኩልነት የሸይጧን ነው ብለዋል ሀቢቡና(ሰ.ዐ.ወ)" መልካም ቀን ይሁንላችሁ

🌿 አስገራሚው መሪ 🌿
•════•••🌺🍃•••════•
《መልዕክተኛው ወደ አማኞች መሪ ኡመር ኢብኑ አብዱል አዚዝ ዘንድ መልዕክት ይዞ መጣ። 🕯 መልዕክተኛው ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ ኡመር ሿማ እንዲመጣቸው አዘዙ፣ ሻማውን አብርተው መልዕክተኛውን ስለመጣበት ሀገር ሁኔታ ይጠይቁት ጀመሩ፦
«የሀገሩ ነዋሪዎች ስራቸው እንዴት ነው? የዋጋ ግፊት እንዴት ነው? የሙሃጂሮችና የአንሷር ልጆች እንዴት ናቸው? የመንገድ ልጆችና ድሆች በምን ላይ ይገኛሉ?» በማለት መልዕክተኛውን ጠየቁት።።።
🔦 መልዕክተኛው ለሁሉም መልካም መልስ በመስጠት ካረጋጋቸው በኋላ። መልዕክተኛው መጠየቅ ጀመረ፦
የአማኞች መሪ ሆይ እርሶ እንዴት ኖት፣ ነፍሴቶ አካሎት እንዴት ናቸው? ልጆቻቹ ቤተሰቦቻቹ እንዴት ናቸው??
የአማኞች መሪም ሻማውን አጠፉት!!
ልጆ ሆይ ጠዋፉን አምጣልኝ በማለት አቀሩበለት ልትጠፋ የቀረበችውን ጠዋፍ አበሩት። መልዕክተኛው በመገረም የአማኞች መሪን ጠየቃቸው።
የአማኞች መሪ ሆይ ፈፅሞ መረዳት ያልቻልኩት ነገር ነው የሰሩት ሚስጥሩ ምንድን ነው? ስለ ደህንነቶ ስጠይቆት ለምን ሻማውን አጠፉት?
🎙የአማኞች መሪም፦ «ስለነፍሴ በጠየከኝ ጊዜ ያጠፏኻት ሻማ ከአላህ ገንዘብና (ማሉ ሏህ) ከሙስሊሞች ሀብት የወጣች ናት፤ እኔም ስለሙስሊሞች ጉዳይ ስለአሉበት ሁኔታ እየጠየኩባት ነበር። ስለ እኔ ጉዳይና ስለቤተሰቦች ስትጠይቀኝ የሙስሊሞች ንብረት የሆነውን ሻማ አጠፋሁት።» 》
●────≪✿✺✿≫───●
[የኡመር ኢብኑ አብዱል አዚዝ ታሪክ በአብዱላህ ኢብኑ አብዱል ሀከም ከተፃፈው የተወሰደ

« ለምን ተኮነነ? »
©ሪያድ ዐብዱልጀባር
#we love muhammedﷺ
(ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር የተደገመ)
ባለማወቅ መጥቀው፤በአውቀናል ኖሩ፣
በነፃነት ሽፋን ክብሬን ተዳፈሩ፣
እናቴን፣ አባቴን፣ ሙሉ ቤተሠቤን፣
የአብራኮቼን ክፋይ፣ሀብትና ንብረቴን፣
አካል የኔነቴን፣ አንዲት ነፍሲያዬን፣
ሁሉም ላይ ዘመቱ፣ ሁሉንም ሣይጠሩ፣
ከልቤ ንጉስ ላይ ድንበር ቢሻገሩ።
ግን…ለምን…ለምን ተኮነነ?
ሠላም ባሠፈነ፣
በዘመን ማሣ ላይ ማሠብ በበተነ፣
ውሃ በሌለበት ውሃውን በሆነ፣
ድፍርሲቱን ዓለም ሠክኖ ባሠከነ፡፡
ለምን…ለምን ተኮነነ፣?
ጠብታ እምባ አንቅቶት ለእምባ በደረሠ፣
የወረዛ ጉንጭን በፍቅሩ ባበሠ፣
የምድሪቱን ረሃብ፤
የጸዳል ጥማቷን በርቶ ባስታገሠ፡፡
ለምን…ለምን ተኮነነ…?
ማስተዋልን ምጎ ጥበብ ባተነነ፣
ቀናነትን ናኝቶ እብሪትን ባደነ፣
ለምን…ለምን ተኮነነ…
እንስትን አክብሮ ክብሯን ባገነነ፣
ለዓለማት ሁላ ለፍጥረት ባዘነ፣
ለምን…ለምን ተኮነነ…
ማን በነገራቸው፤…
ማን በነገራቸው የልቤን ክጃሎት፣
ላልማዜ፣ ለክብሬ አንደምሞትለት፣
እሱኮ…እሱኮ…
ከእናቴ ልቆ ከአባቴም በላይ፣
የተዳፈነውን የልቤን ማህደር፤በብልሃት ነዳይ፣
የኔ ሁለመና የእውቀት አዳባይ፣
ግን…ለምን…ለምን ተኮነነ!
ሠላም ባሠፈነ፣
በዘመን ማሣ ላይ ማሠብ በበተነ፣
እሱኮ…እሱኮ…
ንግስናን ሣይፈልግ ንግስናን ያገኘ፣
ልዩነትን ቀርፎ ውህደትን የናኘ፣
የተናገረውን ተግብሮ ያሣየ፣
በጥሩነት ፈንጂ ክፋትን ያጋየ፣
ያገኘውን ሁሉ እየመጸወተ፣
እንደተወደደ፣
እንደተከበረ፣
እንደተናፈቀ፣ የተሰናበተ።
ታላቅ ነው የላቀ ምትክ የለሽ ፍጡር፣
ዘወትር ሚወሣ ያለማት መምህር!!!
©ሪያድ ዐብዱልጀባር
#we love muhammedﷺ
(ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር የተደገመ)
ባለማወቅ መጥቀው፤በአውቀናል ኖሩ፣
በነፃነት ሽፋን ክብሬን ተዳፈሩ፣
እናቴን፣ አባቴን፣ ሙሉ ቤተሠቤን፣
የአብራኮቼን ክፋይ፣ሀብትና ንብረቴን፣
አካል የኔነቴን፣ አንዲት ነፍሲያዬን፣
ሁሉም ላይ ዘመቱ፣ ሁሉንም ሣይጠሩ፣
ከልቤ ንጉስ ላይ ድንበር ቢሻገሩ።
ግን…ለምን…ለምን ተኮነነ?
ሠላም ባሠፈነ፣
በዘመን ማሣ ላይ ማሠብ በበተነ፣
ውሃ በሌለበት ውሃውን በሆነ፣
ድፍርሲቱን ዓለም ሠክኖ ባሠከነ፡፡
ለምን…ለምን ተኮነነ፣?
ጠብታ እምባ አንቅቶት ለእምባ በደረሠ፣
የወረዛ ጉንጭን በፍቅሩ ባበሠ፣
የምድሪቱን ረሃብ፤
የጸዳል ጥማቷን በርቶ ባስታገሠ፡፡
ለምን…ለምን ተኮነነ…?
ማስተዋልን ምጎ ጥበብ ባተነነ፣
ቀናነትን ናኝቶ እብሪትን ባደነ፣
ለምን…ለምን ተኮነነ…
እንስትን አክብሮ ክብሯን ባገነነ፣
ለዓለማት ሁላ ለፍጥረት ባዘነ፣
ለምን…ለምን ተኮነነ…
ማን በነገራቸው፤…
ማን በነገራቸው የልቤን ክጃሎት፣
ላልማዜ፣ ለክብሬ አንደምሞትለት፣
እሱኮ…እሱኮ…
ከእናቴ ልቆ ከአባቴም በላይ፣
የተዳፈነውን የልቤን ማህደር፤በብልሃት ነዳይ፣
የኔ ሁለመና የእውቀት አዳባይ፣
ግን…ለምን…ለምን ተኮነነ!
ሠላም ባሠፈነ፣
በዘመን ማሣ ላይ ማሠብ በበተነ፣
እሱኮ…እሱኮ…
ንግስናን ሣይፈልግ ንግስናን ያገኘ፣
ልዩነትን ቀርፎ ውህደትን የናኘ፣
የተናገረውን ተግብሮ ያሣየ፣
በጥሩነት ፈንጂ ክፋትን ያጋየ፣
ያገኘውን ሁሉ እየመጸወተ፣
እንደተወደደ፣
እንደተከበረ፣
እንደተናፈቀ፣ የተሰናበተ።
ታላቅ ነው የላቀ ምትክ የለሽ ፍጡር፣
ዘወትር ሚወሣ ያለማት መምህር!!!
« ለምን ተኮነነ? »
©ሪያድ ዐብዱልጀባር
#we love muhammedﷺ
(ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር የተደገመ)
ባለማወቅ መጥቀው፤በአውቀናል ኖሩ፣
በነፃነት ሽፋን ክብሬን ተዳፈሩ፣
እናቴን፣ አባቴን፣ ሙሉ ቤተሠቤን፣
የአብራኮቼን ክፋይ፣ሀብትና ንብረቴን፣
አካል የኔነቴን፣ አንዲት ነፍሲያዬን፣
ሁሉም ላይ ዘመቱ፣ ሁሉንም ሣይጠሩ፣
ከልቤ ንጉስ ላይ ድንበር ቢሻገሩ።
ግን…ለምን…ለምን ተኮነነ?
ሠላም ባሠፈነ፣
በዘመን ማሣ ላይ ማሠብ በበተነ፣
ውሃ በሌለበት ውሃውን በሆነ፣
ድፍርሲቱን ዓለም ሠክኖ ባሠከነ፡፡
ለምን…ለምን ተኮነነ፣?
ጠብታ እምባ አንቅቶት ለእምባ በደረሠ፣
የወረዛ ጉንጭን በፍቅሩ ባበሠ፣
የምድሪቱን ረሃብ፤
የጸዳል ጥማቷን በርቶ ባስታገሠ፡፡
ለምን…ለምን ተኮነነ…?
ማስተዋልን ምጎ ጥበብ ባተነነ፣
ቀናነትን ናኝቶ እብሪትን ባደነ፣
ለምን…ለምን ተኮነነ…
እንስትን አክብሮ ክብሯን ባገነነ፣
ለዓለማት ሁላ ለፍጥረት ባዘነ፣
ለምን…ለምን ተኮነነ…
ማን በነገራቸው፤…
ማን በነገራቸው የልቤን ክጃሎት፣
ላልማዜ፣ ለክብሬ አንደምሞትለት፣
እሱኮ…እሱኮ…
ከእናቴ ልቆ ከአባቴም በላይ፣
የተዳፈነውን የልቤን ማህደር፤በብልሃት ነዳይ፣
የኔ ሁለመና የእውቀት አዳባይ፣
ግን…ለምን…ለምን ተኮነነ!
ሠላም ባሠፈነ፣
በዘመን ማሣ ላይ ማሠብ በበተነ፣
እሱኮ…እሱኮ…
ንግስናን ሣይፈልግ ንግስናን ያገኘ፣
ልዩነትን ቀርፎ ውህደትን የናኘ፣
የተናገረውን ተግብሮ ያሣየ፣
በጥሩነት ፈንጂ ክፋትን ያጋየ፣
ያገኘውን ሁሉ እየመጸወተ፣
እንደተወደደ፣
እንደተከበረ፣
እንደተናፈቀ፣ የተሰናበተ።
ታላቅ ነው የላቀ ምትክ የለሽ ፍጡር፣
ዘወትር ሚወሣ ያለማት መምህር!!!
©ሪያድ ዐብዱልጀባር
#we love muhammedﷺ
(ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር የተደገመ)
ባለማወቅ መጥቀው፤በአውቀናል ኖሩ፣
በነፃነት ሽፋን ክብሬን ተዳፈሩ፣
እናቴን፣ አባቴን፣ ሙሉ ቤተሠቤን፣
የአብራኮቼን ክፋይ፣ሀብትና ንብረቴን፣
አካል የኔነቴን፣ አንዲት ነፍሲያዬን፣
ሁሉም ላይ ዘመቱ፣ ሁሉንም ሣይጠሩ፣
ከልቤ ንጉስ ላይ ድንበር ቢሻገሩ።
ግን…ለምን…ለምን ተኮነነ?
ሠላም ባሠፈነ፣
በዘመን ማሣ ላይ ማሠብ በበተነ፣
ውሃ በሌለበት ውሃውን በሆነ፣
ድፍርሲቱን ዓለም ሠክኖ ባሠከነ፡፡
ለምን…ለምን ተኮነነ፣?
ጠብታ እምባ አንቅቶት ለእምባ በደረሠ፣
የወረዛ ጉንጭን በፍቅሩ ባበሠ፣
የምድሪቱን ረሃብ፤
የጸዳል ጥማቷን በርቶ ባስታገሠ፡፡
ለምን…ለምን ተኮነነ…?
ማስተዋልን ምጎ ጥበብ ባተነነ፣
ቀናነትን ናኝቶ እብሪትን ባደነ፣
ለምን…ለምን ተኮነነ…
እንስትን አክብሮ ክብሯን ባገነነ፣
ለዓለማት ሁላ ለፍጥረት ባዘነ፣
ለምን…ለምን ተኮነነ…
ማን በነገራቸው፤…
ማን በነገራቸው የልቤን ክጃሎት፣
ላልማዜ፣ ለክብሬ አንደምሞትለት፣
እሱኮ…እሱኮ…
ከእናቴ ልቆ ከአባቴም በላይ፣
የተዳፈነውን የልቤን ማህደር፤በብልሃት ነዳይ፣
የኔ ሁለመና የእውቀት አዳባይ፣
ግን…ለምን…ለምን ተኮነነ!
ሠላም ባሠፈነ፣
በዘመን ማሣ ላይ ማሠብ በበተነ፣
እሱኮ…እሱኮ…
ንግስናን ሣይፈልግ ንግስናን ያገኘ፣
ልዩነትን ቀርፎ ውህደትን የናኘ፣
የተናገረውን ተግብሮ ያሣየ፣
በጥሩነት ፈንጂ ክፋትን ያጋየ፣
ያገኘውን ሁሉ እየመጸወተ፣
እንደተወደደ፣
እንደተከበረ፣
እንደተናፈቀ፣ የተሰናበተ።
ታላቅ ነው የላቀ ምትክ የለሽ ፍጡር፣
ዘወትር ሚወሣ ያለማት መምህር!!!
አይኑ የታመመ ብርሃን አይመቸውምና...
አላህ (ለዓለም እዝነት አድርገን እንጂ አላክንህም) እና (አንተን የሚጠላ ዘሩ የተቆረጣ፤ ከመልካም ነገር በሙሉ የተራቆተ ነው) ያለላቸው ነቢይ ላይ
ሰለዋት አብዙ።
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ بِعَدَدِ مَنْ صَلَّى عَلَيْهِ، وَصَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ بِعَدَدٍ مَنْ لَمْ يُصَلِّ عَلَيْهِ.
አይኑ የታመመ ብርሃን አይመቸውምና የዲናቸው ብርሃን አለምን ማጥለቅለቁ ሳይመቸው ቀርቶ ልቡ ተጣቦ ስማቸውን በክፉ ያነሳን በሙሉ "በቁጭትህ ሙት። የጸሐይን ብርሃን መጋረድ ከማትችለው በላይ የዲናቸውን ብርሃን መጋረድና ማስቆም አትችልም" በሉት።
ጥላቻ ያሳወረው በሙሉ ቁጭት እንዲገድለውም በሁሉም ቦታና ሁኔታ ላይ የጠላቸውን ነቢይ ሱና በመተግበር ምድርን በለፉለት ዲን ብርሃን እናሸብርቃት።
©: ዛዱል-መዓድ [ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም]

ውብ የዳዕዋ ምሽት በሀሰንና ሁሰይን መስጂድ
ሰማያትን ያለምስሶ ባቆመው ተራሮችን ችካል ባደረገው ሁን በሚለው ቃል አባታችን አደምን ባስገኘው ጌታ በአላህ ስም ከዚያም ቀጥሎ የሰው ልጆች ሁሉ ፈርጥና አርአያ በሆኑት ውዱ ነብያችን ላይ የአላህ ሰላምና እዝነት ይስፈን።
አላህ ሱ.ወ አሸናፊ በሆነው ጥበብ በሞላው ንግግሩ ሀቢቡና (ﷺ)ን በተለያየ ቦታ አወድሷቸዋል።
እዝነታቸውን ሲገልፅ
"ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡"
አዎ አዛኝ ናቸው የተጠየቁ እንደሆነ ያለስስት ይሰጣሉ።የተዋለላቸውን ውለታ ይመልሳሉ።የሙእሚኖች ችግር እጅግ ያሳስባቸዋል።መሪ ናቸው ግን መለያቸው ኩራት ሳይሆን መተናነስ ነበር።ሲርባቸው ሆዳቸው ላይ ድንጋይ ያስራሉ።ለሶስት ተከታታይ ቀን እንኳን ጠግበው በልተው አያውቁም።ከባልደረቦቻቸው የተለየ መቀመጫ ቦታ አነበራቸውም አብረዋቸው ይቀመጣሉ።ሰዎችን ይወዳሉ
እንኳን አብሯቸው ላሉት ይቅርና ያላይዋቸው ወንድሞቻቸውን እያሰቡ በናፍቆት እሩቅ ይጓዛሉ።
ረሱል (ﷺ) ወንድሞቼ ናፈቁኝ እያሉ ይተክዛሉ ያለቅሳሉ።ኡመቴን ማርልኝ በማለት እያለቀሱ የለሊቱን 1/3ኛ ቆመዋል።
ኑ ፍትሃዊ፣ታጋሽ፣ጀግና፣አንደበተ ርቱዕ፣መምህር፣ትሁት፣ተናናሽ፣እንግዳን አክባሪ፣ለስላሳ፣ገር፣ይቅር ባይ የሆኑትን ሀቢቡናﷺ በተከበረው የአላህ ቤት ውስጥ የፊታችን ሀሙስ ከመግሪብ ሰላት በኋላ በሃሰንና ሁሰይን መስጂድ እንውሳ።
በኡስታዝ ካሚል ጧሃና
በኡስታዝ አብዱል ቃድር
ቀን: ሀሙስ ታህሳስ 7 /2014
ሰዓት: ከመግሪብ ሰላት በኋላ
ቦታ: ሀሰንና ሁሰይን መስጂድ