Telegram Web Link
በዘመናችን ላይ ከሰዎች ውስጥ ኸይርን ለማስቆም በወንጀል የሚንሾካሾኩ ሰዎች ሞልተዋል።ሙስሊሞቹን አላህ ያስተካክላቸው ካፊሮቹን አላህ ሂዳያ ይሳጣቸው።



አላህ እንደዚህ ነው ያለው በከበረው ቃሉ👇
أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ نُهُوا عَنِ النَّجْوَىٰ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا نُهُوا عَنْهُ وَيَتَنَاجَوْنَ بِالْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَمَعْصِيَتِ الرَّسُولِ وَإِذَا جَاءُوكَ حَيَّوْكَ بِمَا لَمْ يُحَيِّكَ بِهِ اللَّهُ وَيَقُولُونَ فِي أَنفُسِهِمْ لَوْلَا يُعَذِّبُنَا اللَّهُ بِمَا نَقُولُ ۚ حَسْبُهُمْ جَهَنَّمُ يَصْلَوْنَهَا ۖ فَبِئْسَ الْمَصِيرُ

ወደእነዚያ (በመጥፎ) ከመሾካሾክ ወደ ተከለከሉት፣ ከዚያም ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር ወደሚመለሱት፣ በኃጢአትና ድንበር በማለፍ መልክተኛውን በመቃወም ወደሚንሾካሾኩት አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) በመጡህም ጊዜ አላህ በእርሱ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል፡፡ በነፍሶቻቸውም ውስጥ (ነቢይ ከኾንክ) «በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ ገሀነም የሚገቧት ሲኾኑ በቂያቸው ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!
አላህ (ሱወ) በተከበረ ቃሉ ስለ ታጋሾች እንዲ ያበስራቸዋል

وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ

ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስራቸው
አላህ ይቀጥላል

الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡

أُولَٰئِكَ عَلَيْهِمْ صَلَوَاتٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَرَحْمَةٌ ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُهْتَدُونَ

እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የኾኑ ምሕረቶች ችሮታም አልሉ፡፡ እነርሱም (ወደ እውነት) ተመሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

አላህ ከታጋሾች ያርገን
ታላቅ የዳእዋ ፕሮግራም በሀሰን እና ሁሰይን መስጂድ👇
Forwarded from إن الحياة عقيدة و جهاد 🌿 إن الحياة عقيدة و جهاد 🌿
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ  قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم "إنَّ اللَّهَ طَيِّبٌ لَا يَقْبَلُ إلَّا طَيِّبًا، وَإِنَّ اللَّهَ أَمَرَ الْمُؤْمِنِينَ بِمَا أَمَرَ بِهِ الْمُرْسَلِينَ فَقَالَ تَعَالَى: "يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنْ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا"، وَقَالَ تَعَالَى: "يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِنْ طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ" ثُمَّ ذَكَرَ الرَّجُلَ يُطِيلُ السَّفَرَ أَشْعَثَ أَغْبَرَ يَمُدُّ يَدَيْهِ إلَى السَّمَاءِ: يَا رَبِّ! يَا رَبِّ! وَمَطْعَمُهُ حَرَامٌ، وَمَشْرَبُهُ حَرَامٌ، وَمَلْبَسُهُ حَرَامٌ، وَغُذِّيَ بِالْحَرَامِ، فَأَنَّى يُسْتَجَابُ لَهُ؟". رَوَاهُ مُسْلِمٌ [رقم:1015].አቡ ሁረይራ በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمእንዲህ አሉ። “ አላህ መልካም ነው። መልካምን እንጂ አይቀበልም። አላህ መልእክተኞችን ባዘዘው ነገር ላይ ሙእሚኖችን አዟል። አላህም እንዲህ አለ ፡ “እናንተ ያመናቹህ ሆይ ! መልካምን ተመገቡ፥ መልካምንም ስሩ።” አላህም እንዲህ አለ ፡ “እናንተ ያመናቹህ ሆይ ! ከሰጠናቹህ ሲሳይ መልካምን ተመገቡ።” ከዛ ቡሃላ ነብዩ صلى الله عليه وسلم መንገድን ያረዘመ፣ ፀጉሩ የተንጨባረረ፣ አቦራ የለበሰን ሰው አወሱ። እጁን ወደላይ ዘርግቶ ጌታዬ! ጌታዬ! ይላል፥ የሚመገበው የሓራም ነው፣ የሚጠጣው የሓራም ነው፣ የሚለብሰው የሓራም ነው፣ በሓራምም ተገንብቷል። ታድያ እንዴት ነው ከአላህ መልስ የሚያገኘው። ሓዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።
የአላህ ቃል በመስማት ላይ አትዘናጉ🌹


تَنزِيلٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

(ይህ ቁርኣን) እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ ከሆነው (አላህ) የተወረደ ነው፡፡
كِتَابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች (የተብራራ) ነው፡፡
بَشِيرًا وَنَذِيرًا فَأَعْرَضَ أَكْثَرُهُمْ فَهُمْ لَا يَسْمَعُونَ

አብሳሪና አስፈራሪ ሲኾን (ተወረደ)፡፡ አብዛኛዎቻቸውም ተዉት፡፡ እነርሱም አይሰሙም፡፡
وَقَالُوا قُلُوبُنَا فِي أَكِنَّةٍ مِّمَّا تَدْعُونَا إِلَيْهِ وَفِي آذَانِنَا وَقْرٌ وَمِن بَيْنِنَا وَبَيْنِكَ حِجَابٌ فَاعْمَلْ إِنَّنَا عَامِلُونَ

አሉም «ልቦቻችን ከእዚያ ወደእርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው፡፡ በጆሮዎቻችንም ላይ ድንቁርና አልለ፤ በእኛና ባንተም መካከል ግርዶሽ አልለ፡፡ (በሃይማኖትህ) ሥስራም፤ እኛ ሠሪዎች ነንና፡፡»

(እንዲህ) በላቸው «እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ወደእርሱም ቀጥ በሉ ምሕረትንም ለምኑት ማለት ወደእኔ ይወረድልኛል፡፡ ለአጋሪዎቹም ወዮላቸው፡፡
سورة ال فصلت
https://www.tg-me.com/theamazingquran
➴የአእራፍ ሰዎች እነማን ናቸው ?
_________

ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ ተብለው ይጠየቃሉ ፡

#ጥያቄ፡- የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ሰማሁት፡
"አእራፍ የሚባሉት በጀነትና በጀሀነም መካከል
የሚገኝ ድልድይ ላይ የሚሆኑ ሰዎች ናቸው ፡
እዚህ ቦታም ላይ ለተወሰነ ጊዜ ይቆያሉ "
ይላል ፡ ክቡር ሼኽ ይህ ትክክል ነውን ?

#መልስ፡- የትንሳኤ እለት ሰዎች ለሶስት
ይከፈላሉ ፡

#አንድኞቹ ፡ ከመጥፎ ስራቸው ይልቅ
መልካም ስራቸው ያመዘነላቸው ናቸው ፡እነዚህ
በፍፁም ቅጣትን አይቀጡም ፡ በጀነት ውስጥ
ለዘላለም ይኖራሉ ፣

ሁለተኞቹ ደግሞ፡ ከመልካም ስራቸው ይልቅ
መጥፎ ስራቸው ያመዘነባቸው ናቸው ፡ እነዚህ
ቅጣትን ተገቢዎች ናቸውና በኃጢያታቸው
ተቀጥተው ከዚያ ወደ ጀነት ይገባሉ ፣

#ሶስተኞቹ_ደግሞ ፡ መልካም ስራቸውና
መጥፎ ስራቸው እኩል የሆነባቸው ናቸው ፡
እነዚህ ናቸው የአእራፍ ሰዎች የሚባሉት ፡
የጀነት ባለቤቶችም አይደሉም ፡ የጀሀነምም
ባለቤቶች አይደሉም ፡ ይልቅ እነሱ መካከለኛ
በሆነ ከፍና ጉብ ባለ ቦታ ላይ ናቸው ፡ እዛ ላይ
ሁነው ጀነትንም ጀሀነምንም ያያሉ ፡ አሏህ እስከወሰነባቸው ጊዜ ድረስ እዛ ቦታላይ ይቆያሉ
በስተመጨረሻ ላይ ግን ወደ ጀነት ይገባሉ ፡

ይህ ሁሉ የሚያሳየው የአላህን ፍትሀዊነት
ነው ፡ እርሱ ለማንኛውም አካል ተገቢውን
ምንዳ ይሰጣል ፡፡

መልካም ስራው ያመዘነለት (የጀነት ይሆናል)፤

መጥፎ ስራው ያመዘነችበት (አሏህ
እስከወሰነበት ጊዜ ድረስ ጀሀነም ውስጥ ይቀጣል) ፣

➴መልካም ስራውና ጥሩ ስራው እኩል የሆነ
ደግሞ ፡ ከአእራፍ ሰዎች ይሆናል - ግን ይች
አእራፍ ለዘለዓለም የምትዘወትር መቆያ ቦታ
አይደለችም ፡ ከዚህ ቦታ ቆይታ ቡሀላ መጨረሻ
ላይ ወደ ጀነት ይገባሉ ፡ አላህ የጀነት ሰዎች ይበለን ፡፡

#ምንጭ፡- ሊቃዕ ባቡል መፍቱህ ( 14 )
👌" #ከመጥፎ_ጓደኞች ጋር ከመቀማመጥ ለብቻ መቀመጥ በላጭ ነው፡፡ እንዲሁም ለብቻ ከመቀመጥ ከደግ ሰው ጋር መቀማመጥ በላጭ ነው፡፡ (በሌላ በኩል) ዝም ብሎ ከመቅረት ከዕውቀት ፈላጊ ጋር መነጋገሩ በላጭ ነው፡፡ ነገር ግን ዝምታ ከከንቱ ቃላት የተሻለ ነው፡፡"
(📚 ቡኻሪ)
አላህ ከበላጮቹ ያርገን
(42) عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ رضي الله عنه، قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ ﷺ: "الْحَيَاءُ لَا يَأْتِي إِلَّا بِخَيْرٍ". (متفق عليه)

لُغَةُ الحَدِيثِ

الْحَيَاءُ: خُلُقٌ فِي النَّفْسِ يَبْعَثُ علَى تَرْكِ القَبيحِ ومَا يُذَمُّ عِلَيْهِ وَيُعابُ مِنَ الأقوالِ والأفعالِ، وفِعْلِ مَا يُحْمَدُ، ويَمْنَعُ صاحِبَهُ مِنَ التّقْصِيرِ في حقِّ ذَوِي الحُقوقِ.

فَوَائِدُ الحَدِيثِ

1- الحَيَاءُ مِنْ شُعَبِ الإِيمانِ، وَهُوَ خُلُقٌ مَحْبُوبٌ إِلَى اللهِ تَعالَى؛ لِذَلِكَ وَصَفَ اللهُ تَعَالَى نَفْسَهُ بِهِ؛ فعَنْ سَلْمَانَ الفَارِسِيِّ رضي الله عنه، عَنِ النَّبِيِّ ﷺ، قَالَ: "إِنَّ اللَّهَ حَيِيٌّ كَرِيمٌ، يَسْتَحْيِي إِذَا رَفَعَ الرَّجُلُ إِلَيْهِ يَدَيْهِ أَنْ يَرُدَّهُمَا صِفْرًا خَائِبَتَيْنِ"(1).

2- لَا يَزَالُ الحَياءُ بِصَاحِبِهِ حتَّى يَنْتَهِيَ عَنْ كُلِّ مَا يُعابُ مِنَ القَبَائِحِ والآثَامِ؛ وَمَنْ لَا حَياءَ لَهُ؛ يَتَجَرَّأُ عَلَى فِعْلِ أَيِّ شَيْءٍ؛ وَهَذا مَعْنَى قَوْلِهِ ﷺ: "إِنَّ مِمَّا أَدْرَكَ النَّاسُ مِنْ كَلاَمِ النُّبُوَّةِ الأُولَى: إِذَا لَمْ تَسْتَحْيِ؛ فَاصْنَعْ مَا شِئْتَ"(2).

3- الفَرْقُ بينَ الخَجَلِ والحَياءِ، أَنَّ الخَجَلَ أخَصُّ مِنَ الحَياءِ، فَإِنَّ الخَجَلَ لَا يَكُونُ إلَّا بَعْدَ صُدُورِ أمرٍ يُسْتَحْيا مِنْهُ، بِخِلافِ الحَياءِ، فَإِنَّهُ قَدْ يَكُونُ لِمَا لَمْ يَقَعْ فِيهِ، فَيَترُكُ الفِعْلَ لِأَجْلِهِ، وَقَدْ يَكُونُ بَعْدَ وُقُوعِ الفِعْلِ الذِي يُسْتَحْيا مِنْهُ(3).

 
አዳዲስና ወቅታዊ ዳዕዋዎች እንዲደረሷችሁ የዩቲዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ👇👇👇


የዩቲዩብ ገፃችን👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCeBtCDXtDWSHx77dGWCONzQ

የፌስቡክ ገፅ👇👇👇👇
https://www.facebook.com/104018092137005/posts/105207355351412/
@m2vbot
Convert To Voice
surretul meriym

መሳጭ ቲላዋ❤️❤️

ዋ ጥፋታቸን ለቁርአን ሰዓት ያጣን ቀን😢😢😢
#ስኬት_በኢስላም

አንድ ጥንቸል ጥዋት ተነስታ እንደሁሌው የምትበላው ለማግኘት መሽከርከር ጀመረች። ዛሬ ግን ሰፈሯ ውስጥ ያለውን ምግብ መብላት አልፈለገችም። ሌላ ፈለገች፤ ሳታውቀው ብዙ ተጓዘች፤ አሻግራ ስትመለከት በጣም የሚያምር የአትክልት ቦታ ታያለች፤ ወደ ውስጥ ለመግባት ስለፈለገች ቀረብ አለች። ቦታው በሽቦ ታጥሯል፤ ዙሪያውን አየችው ዞረችው፤ በመጨረሻም አንድ ቀዳዳ አገኘች። በደስታ ወደ ውስጥ ለመግባት ስትሞክር ለካ እሷ ወፍራም ነች፤ ቀዳዳው እያስገባትም። እሁን አንድ ነገር አሰበች።
'2 ቀን ምንም ሳልበላ ብቆይ እኮ ስልምቀንስ መግባት እችላለው' አለች።
እንዳሰብችውም 2 ቀን ምንም ሳትበላ ቆይታ ስለከሳች በዛ ቀዳዳ መግባት ቻለች። የተመፕችውን አገኘች፤ እስኪመሽ የፈለገችውን በላች፤ ጠጣች፤ አሁን ወደ ቤቷ ልትሄድ ነው። በገባችበት ቀዳዳ ለመውጣት ስትሞክር ለካ አሁን ጨምራለች (ወፍራለች) ያ ቀዳዳ ሊያሶጣት አልፈቀደም።

ያቺ መፍትሔ ማታጣው ጥንቸል አንድ ሐሳብ መጣላት። ምን ይመስላኃል?
' 2 ቀን ምንም ሳልበላ ብቆይ እኮ ስልምቀንስ መውጣት እችላለው' አለች።
እንዳሰብችውም 2 ቀን ምንም ሳትበላ ቆይታ ስለከሳች በዛ ቀዳዳ ወደ ውጪ መውጣት ቻለች። ወደ ቤቷም ሄደች።

እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ?
ይህቺ ጥንቸል ምንድ ነው ያተረፈችው? ምንም። እንዲያውም ወደ አትክልት ቦታው ከመግባቷ በፊት የነበራትን ሰውነት አጥታለች፤ 'ኪሳራ' ስትገባ በባዶ ስትወጣም በባዶ።

እኛም ወደዚህ አለም ስንመጣ ምንም ነገር ይዘን አልመጣንም። ስንሄድም ምንም ይዘን እንሄድም። ስለዚህ ሁላችንም ዛሬ ያሉን ነገሮች ብዙ ናቸው፤ 'ያለኝ ይበቃኛል' የሚል ባህሪይ እናዳብር፤ ባለን እንርካ። ያሉንን መልካም ነገሮች የማናስተውል ከሆነ የሌሉንን ነገሮች ለማግኘት ከንቱ ድካም ማሳለፋችን አይቀርም። ትርፋችን ኪሳራ እንዳይሆን!!!
Forwarded from Ab
እየኖርን ያለነው ዘመን ከፈተናው አንፃር የከበደ እንደመሆኑ መጠን ራሳችንን ከአላህ ሀቅ ላይ መፅናትን እየፈለግን እርስ በራስ ደግሞ እየተዋወስን መልካም መንገድ ላይ መጓዝ ግድ ይላል።

ለዚህም ደግሞ ሩሱሎች የያዙትን መንገድ መያዝ ወደ ጠሩት መንገድ መጣራት ለፅናት ምንጭ ይሆነናል።በዋነኝነት ጥሪያቸው የተዝኪያን መንገድ የሚያመላክት ነበር።

ከስር ባለው ቪዲዮ ተከታታይ ተዝኪያን በተመለከተ የምንማማር ይሆናል!
አላህ ለመልካሙ ይምራን!

https://youtu.be/2gyypXHoPJo
Forwarded from Subhanallah
#ምክር_ለወዳጅ❗️


🖋 በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል።

🖋 ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው! በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፤ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ።

🖋 የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ
ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል።

🖋 ዓይንህ የፊቱን ቢያይ፤ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ፤ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ።

🖋 የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው።

🖋 ክፋት አይሙቅህ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት።

🖋 ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ። ላለው አትሩጥ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው።

🖋 ለሀብታም አትሳቅ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን፣ ነገርህን በልክ፣ ቃልህን በጣዕም፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው።

🖋 እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ።

🖋 ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም።

🖋 በዓላማ ኑር፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ።

🖋 የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ነገ ከመምጣቱ በፊት ቀድመህ አስብ

🌹🌷🥀🥀🥀🥀🥀
#የአለም_ህግ

አንድ ገበሬ በጣም የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ወደ እንስሳት ሀኪም ጋር ይዞት ይሄዳል። ሀኪሙም ፈረሱ ጉረኖ ድረስ በመሄድ በሚገባ መረመረው።

ለገበሬውም - "ተላላፊ በሽታ ስላለበት ለሶስት ቀን መድሀኒት እንስጠውና ካልተሻለው ወደሌሎቹ ፈረሶች እንዳይዛመት እንገለዋለን" ብሎት ሄደ።

ይሄንን ሲያወሩ ፍየል ተደብቃ ሰምታቸው ኖሯል ለፈረሱ እያለቀሰች ያወሩትን ነገረችውና "እንደምንም ብለህ ተነስ! ያለበዛ ይገሉሀል" እያለች ተንሰቀሰቀች። የመጀመርያው ቀንሀኪሙ መጥቶ መድሀኒቱን ሰጥቶት ወጣ።
ወድያው ፍየል ለምለም ሳርና አተላ ይዛለት መጣች ና "እንደምንም ተነስ!" ብላ ተማፀነችው።
በሁለተኛውም ቀን ሀኪሙ ሲመጣ ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም መድሀኒቱን ወግቶት እስከ ቀጣዩ ቀን ጠብቆት ካልተሻለው እንደሚገለው ለገበሬው ነግሮት ሄደ።

ይሄን ግዜ ፍየል ለምለም ሳር ፈልጋ ለፈረሱ በማምጣት አፅናናችው። የመጨረሻ ቀን ሀኪሙ ሲመጣ አሁንም ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም ይሄን ጊዜ ከገበሬው ጋር ቢገሉት
እንደሚሻል በር ላይ ቆመው ሲያወሩ ፍየል ቀስ ብላ ተደብቃ ፈረሱ ጋር ገብታ እየተንሰቀሰቀች-
"በናትህ አኔንም ጓደኛ አታሳጣኝ ካልተነሳህ ይገሉሀል" ብላ አለቀሰች። ፈረሱ በፍየሏ ግፊት ቀስ ብሎ ተነሳ። ፍየል ደስ አላት።

"ጎበዝ አስኪ እሩጥ" እያለች አበረታችው። ፈረሱ በወኔ በፊት ከሚሮጥበት ፍጥነት በላይ ሮጠ። ይሄን ጊዜ ፍየል በደስታ ጮሇች። ገበሬውና ሀኪሙ የምን ጩሇት ነው ብለው ሲያዩ
ያዩትን ማመነን አቃታቸው።ፈረሱ በሓይል አየሮጠ ነው።ገበሬው በደስታ ብዛት ሀኪሙን አንቆ ሳመው። እረኛውን ጠርቶት "ዛሬ እኔ ቤት ትልቅ ድግስ አለ! ስለዚህ ቶሎ በሉ ፍየሏን እረዱልኝ! ምሳ እዚህ ነው" አለ።

سبحانالله
አንዱ የሌላው መሰላል ነው። ለአንዱ ህይወት ለሌላው ሞት ነው። ለሀብታም ህይወት የደሀው ችግር ግድ ነው። ለአንዱ ማለፍ የሌላው ውድቀት ወሳኝ ነው። ይህ የአለም ህግ ነው።አንተ የምትመራበት ህግ!

https://www.tg-me.com/theamazingquran
https://www.tg-me.com/theamazingquran
https://www.tg-me.com/theamazingquran
የመኖር ተስፋ

ማዳን ባትችል ቢያንስ ለሰዎች ለህመም መንስኤ አትሁን!!

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል።
ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው
የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ
እንዲል ይደረጋል። አልጋው የሚገኘው
በክፍሉ ብቸኛ ከሆነው መስኮት አጠገብ ነው።

ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ
በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው ስለ ኑሯቸው በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት
እንደሚያሳልፉ...ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ
እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል። በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል በሀይቁ ላይ
ዳኪዬዎች ይዋኛሉ ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ...ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል...በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ ይተርክለታል። በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።

አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ጠራች። ያ ብቻውን የቀረው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ ሊወስዱለት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀ። ወሰዱለት። በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው።

ደነገጠ ምን ሆንክ? አለቸው ነርስዋ። ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ
መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር አላት። ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር አለችው። ልብ የሚነካ ነገር...ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።

አንዳንድ ሠዎች እንዲህ ናቸው እነሡ እየሞቱ የሠውን የህይወት ብርሀን ያለመልማሉ። ሰው የመሆን ሚስጥር ደግሞ ይህ ነው ለሰወች ደስታ መኖር ሰው ማለት ለሰው መኖር ተስፋ መሆን ነው እንጂ ለሰው የችግሩ መንስኤ መሆን አየሰደለም።

አንተስ እስከመቼ የራስህ ብርሀን እያለህ የሠው ጭላንጭል ያስቀናሀል? እስከመቼ የሰወችን ደስታ ትገድላለህ? እስኪ ለአንድ ደቂቃ ዝም ብለህ አስብ መልካምነት እኮ አያስከፍልም።

የሠው ህይወት ማዳን ባትችል እንኳን ቢያንስ ለሠው ተስፋ ስጥ ይሄም የመልካምነት አንዱ ገፅ ነው።

አስታውስ ለሰወች ደስታ መስጠት ባትችል እንኳን የስቃያቼው መንስኤ አትሁን!! መልካም አድርግ መልካምነት አያስከፍልም ዋጋህን ከፈጣሪ ታገኘዋለህ!
የቡኻሪና የሙስሊም ሸይኽ ዑበይዱላሂል ቀዋሪሪይ እንዲህ ይላሉ፦አንድም ቀን የዒሻ ሰላት በጀመዓ አምልጦኝ አያውቅም ነበር።አንድ ምሸት እንግዳ ቤቴ መጣ እሱን በማስተናገድ ቢዚ ሆንኩ የዒሻ ሰላት ጀመዓ አመለጠኝ።በበስራ መስጂዶች ጀመዓ ሰላትን በመፈለግ ተዘዋወርኩ።ሰዎች ሁሉ ሰግደዋል መስጂዶችም ተዘግተዋል።ወደ ቤቴ ተመለስኩና አልኩኝ በሀዲስ እንደመጣው የጀመዓ ሰላት በተናጠል ከሚሰገድ ሰላት በ27ደረጃ ይበልጣል።የዒሻ ሰላትን 27ጊዜ ሰገድኩኝ።ከዛም በተኛሁበት ህልም አየሁኝ "ሰዎች ፈረስ ላይ ሆነው እኔም በፈረስ ሆኜ ስንሽቀዳደም ነበር እኔም ብጋልብ ብጋልብ ልደርስባቸው አልቻልኩም።አንደኛቸው ወደኔ ዞረና እንዲህ አለኝ"ፈረስህን አታድክመው አትደርስብንም።እኔም ለምን አልኩ ምክንያቱም እኛ ዒሻ ሰላትን በጀመዓ ነው የሰገድነው አንተ ግን ብቻህን ነው የሰሰገድከው አለኝ።ከእንቅልፌ ያዘንኩና የተጨነኩ ሆኜ ባነንኩኝ







አላህ ሆይ የጀመዓ ፍቅርን ልባችን ላይ አርግልን
2025/07/05 21:54:34
Back to Top
HTML Embed Code: