Telegram Web Link
የኢማን ጣዕም

(አላህን እና መልዕልተኛውን ከሁሉም ነገር አስበልጦ የሚወድ፣ ሰዎችን ለአላህ ብቻ ብሎ የሚወድና እሳት ላይ መወርወርን (መጥጣልን) የሚጠላውን ያክል
ከኢስላም ወጥቶ ኩፍር ውስጥ መግባትን የሚጠላ ሰው የኢማንን ጣዕም ያገኛል) ያሉት ነቢይ ላይ ሰለዋት እናብዛ።

اللهم صلِّ وسلِّم وبارك على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
💡ቁድዋ–ሣይክ
#Qudwapsyc #psychology

ወደጫፉ ኑ!

ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ ሳያስፈልገኝ ስላነበብኳቸው ብቻ ከሚያነሳሱኝ አባባሎች አንዱ፣ ታዋቂ የ20ኛ ክፍለ-ዘመን ደራሲ የነበረው ፈረንሳዊው Guillauame Apollinaire የተናገረው ይገኝበታል፡-

“ወደጫፉ ኑ አላቸው፡፡ እነሱም፣ እንፈራለንና አንመጣም አሉ፡፡ እንደገና፣ ወደጫፉ ኑ አላቸው፡፡ በቀስታ መጡለት፡፡ ከዚያም በድንገት ገፋቸው … መብረር ጀመሩ!”

ለረጅም ጊዜ በከረሙበት ስፍራ ተደላድለው መኖር የለመዱ ሰዎች ወደተሻለ ስኬታማነት ለመዝለቅ ከፈለጉ ያንን “ምቹውን ቀጠና” በመልቀቅ ወደ “አስጊው ቀጠና” እና ጫፍ መንቀሳቀስ እንዳባቸው የሚገልጽ አባባል ነው፡፡

ያለንበት ሁኔታ መለወጥ እንዳለበት እያወቅነው ለውጥን ለማምጣት መፍራት ሁሉም ሰው የሚጋራው ስሜት ነው፡፡ ስለሆነም፣ አንዳንድ ጊዜ ምንም መሻሻል ከሌለበት የተሰላቸ ሁኔታችን ለመውጣት የሚያነሳሳን ሰው ወይም ሁኔታ ያስፈልገናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ገፍቶ የሚያስገባን ሰው ወይም ሁኔታ የግድ ነው፡፡

በሰዎችም ሆነ በሁኔታዎች ምክንያት ወደማትፈልጉት ጫፍ ደርሳችሁ ራሳችሁን ካገኛችሁት፣ ሁኔታው ወደ አዲስ ከፍታ የመብረር አማራጭ የሌለው ድፍረት የምታገኙበት እድል ነውና በርቱ፡፡ ከአንድ ቦታ ሳይንቀሳቀሱ መኖሩን ያን ያህል ለምዳችሁት ከነበረ ወደ አዲስ ነገር መብረሩንም ትለምዱታላችሁ!

©Dr Eyob

ይወዳጁን
---------------
@Qudwamedia || ቁድዋ ሚድያ
@Qudwamedia || ቁድዋ ሚድያ
የቀረበን ሁሉ ወዶን አይደለም፤ የራቀን ሁሉም ጠልቶን አይምሰለን። ቀርበው ደካማ ጎናችን አጥንተው የሚጎዱን እንዳሉ ሁሉ በአብሮነታቸው እየጎዱን ስለመሰላቸው ብቻ በአካል እርቀውን ሌት ከቀን ስለእኛ መልካም እያሰቡና እየተመኙ የሚወዱንም አይጠፉም።
{እውቀት ከአደብ ጋር}
ከኢማሙ ሻፊዒይ(ረ.ዐ)ደረሳዎች መሀከል የነበረው ዩኑስ ዐብዱል አዕላ አንድ ቀን ከአስተማሪው ከኢማሙ ሻፊዒይ(ረ.ዐ)ጋር በሆነ ርእስ ላይ የአሳብ ልዩነት ተፈጠረና "ዪኑስ"በመናደድ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ቤቱ አመራ፣ከዛም ምሽት ላይ"ዩኑስ" የቤቱ በር ሲንኳኳ ሰማ፣ወደ በሩ በመጠጋትም ማን ልበል?በማለት ጠየቀ
በሩን ሲያንኳኳ የነበረው ሰውም ሙሀመድ ኢድሪስ ነኝ የሚል ምላሽ ሰጠው:ዩኑስም ከኢማሙ ሻፊዒይ ውጪ ስሙ ሙሀመድ ኢድሪስ የሚባል ሰውን ሳስብ ከሳቸው ውጪ አጣሁ!ከዛም በሩን ስከፍት ኢማሙ ሻፊዒይ መሆናቸውን ተመልክቼ በድንጋጤ ተሞላሁ!!!
ከዛም እንዲህ አሉኝ:–
–ዩኑስ ሆይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉዳዮች ላይ ተስማምተን እንዴት አንዲት ጉዳይ ትለያየናለች ...!
–ዩኑስ ሆይ በሁሉም የአሳብ ልዩነቶች ላይ ለማሸነፍ አትሞክር ...አንዳንዴ ልቦችን መግዛት አጋጣሚዎችን የግል ከማድረግ የተሻለ ነው!!
–ዩኑስ ሆይ ምናልባት የሆነ ጊዜ ለመመለሻነት ሊያስፈልግህ ስለሚችል የገነባኸውንና የተሻገርክበትን ድልድይ አታፍርሰው!
*ሁሌም ቢሆን ስህተትን ጥላ፣ነገር ግን ተሳሳቹን መቼም ቢሆን እንዳትጠላ!!
*ወንጀልን በሙሉ ልብህ ተጠየፍ፣ለወንጀለኛን ግን እዘን፣ይቅር በል!!!
–ዩኑስ ሆይ ምትተቸው ንግግሩን ይሁን፣ ተናጋሪውን ግን አክብረው ...... አላማችን በሽተኛውን ማጥፋት ሳይሆን በሽታውን ማጥፋት ነው.
-----------
ይህን አስገራሚ ታሪክ ሳነብ የእውቀት አላማውና ጥጉ:
ነፍስን ረግጦ፣ከማን አለብኝነት ወጥቶ፣ኩራትን ሳይሆን ትህትናን አውርሶ፣መኮፈስን ሳይሆን ሁሌ መፍራትንና ስብር ማለትን ማውረስ እንደሆነ ገባኝ።
እውቀት ለመከራከሪያና ጎልቶ ለመታያነት ከታለመ፣ልብን ከጥላቻና ከቂም ከቁርሾ ካላነፃ፣ነፍስ በራሷ ተገርማ ሌላውን ከምንም መቁጠር ከጀመረች ምኑን እውቀት ሆነ!!!!!!
---------------
እውቀት ነውርህን ካላፀዳህበት፣ስብእናህን ካላገራህበት፣ሰዋዊነትህን ካላፋፋህበት፣አደብን ካልሸመትክበት፣ባህሪህን ካላነፅክበት፣ወደ ጌታህ ካልቀረብክበት በራስህ ላይ መጠየቂያህንና በራስህ ላይ ማስረጃህን እያበዛህ እንደሆነ አትዘነጋ!!!!!!
ኢላሂ ጠቃሚ እውቀትን ለመንኩህ🙏
https://www.tg-me.com/theamazingquran
በጣም አጃዒብ ነው የትኛውም ልብስ ከመልበሳችን በፊት በደንብ ማየት ማንበብ ግድ የሆነበት ዘመን ላይ ነው ያለነው
እነሱ እንደሆን ሸራቸውን ቀጥለውበታል ዲዛይን ነው ብለን ችላ ማለት የለብንም ጥምጣም፣መስገጃ የተለያዩ መስገጃ ምንጣፎች አይተን መግዛት ይኖርብናል ዝም ብለን አማረን አሪፍ ነው ብለን መልበስ የለብንም
አላህ የስራቸውን ይስጣቸው ከነሱ ተንኮልና ሴራ ፊትና አላህ ይጠብቀን!‼️


ሼር
https://www.tg-me.com/theamazingquran
አልበራሒን ኦንላይን ቁርዐን

እርሶ ከቁርዓን ጋር ይተዋወቃሉ? የቂርዓቶ ደረጃንስ ማሻሻል ይፈልጋሉ?እነሆ የምስራች
በመላው አለም ለምትገኙ ለቁርዐን ትምህረት ፈላጊዎች በሙሉ አልበራሒን ኦንላይን ቁርአን
የቦታ ርቀት ሳይገድባቹ ቁርዐንን ባላቹህበት ቦታ አስተካክሎ ለመቅራት ልዩ የኦንላይን ቁርዐን ፕሮግራም አዘጋጅቷል።
በተጨማሪም ለርሶና ለልጆችዎ በመልካም ስነምግባር ይታነፁ ዘንድ ልዩ የተርቢያ ትምህርት ( አዳብ፣አዝካር እና ሀዲስ) የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው በኦንላይን የዘመኑን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ትምህረት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።


ፈጥነው ይመዝገቡ
ለበለጠ መረጃ
0912077534
0912425165

ወይም በቴሌግራም አድራሻ @NadibintAbdellah


📚ከኢብኑ መስዑድ ረድየሏሁ ዓንሁ እንደተዘገበው፣ የአሏህ መልእክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) "ከአሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ መፅሀፍ አንዲትን ፊደል ያነበበ አንድ ጥሩ ስራ ይኖረዋል። ጥሩ ስራ ደግሞ በአስር ምሳሌዋ ናት" ( الۤمۤ ) አሊፍ፣ላም፣ ሚም" አንድ ፊደል ናት አልልም! ነገር ግን አሊፍ አንድ ፊደል ናት፤ ላም አንድ ፊደል ናት፣ ሚም አንድ ፊደል ናት ነው የሚባለው አሉ። (ቲርሙዚ ዘግበውታል)


ታላቅ አጅርን ቁርዓንን በማንበቦ ብቻ ይሸምታሉ።ረመዷንን ከቁርዓን ጋር ተዋውቀን እንቀበለው! ዘመኑ ባፈራቸው መተግበሪያዎች ከውዱ ያአላህ ቃል ጋር እራሳችንን እናስተሳስር!




ማስታወሻ፦እርሶ ከፍለው ሲቀሩ ቂርዓቱን ከማስኬጅያ በዘለለ የሚገኘው ትርፍ ሙሉ በሙሉ ኢስላማዊ እንቅስቃሴዎችን በመስራት ላይ ለሚገኘው ለአርቡርሓን ኢስላማዊ ጀመዓ የሚውል ነው።
አስተማሪ ፅሁፍ❤️

አንድ ቀን አንድ ሃብታም አባት ልጁ የድሆችን አኗኗር እንዲያይ አስቦ ወደ አንድ የድሆች መንደር ይዞት ይሄዳል።ልክ ከጉዞ ሲመለሱ አባት ልጁን እንዴት ነበር ጉዞ ይለዋል።ልጁም ለአባቱ በጣም ደስ የሚል ጉዞ ነበር አባዬ ሲል መለሰለት።አባትም ድሆች እንዴት እንደሚኖሩ አየህ? ከጉዟችን ምን ተማርክ ሲል ጠየቀው። ልጅም ሲመልስ
እንዲህ አለ።

👉እኛ አንድ ውሻ አለን እነሱ አራት ውሻ አላቸው።
👉እኛ የመዋኛ ገንዳ አለን እነሱ ወንዝ አላቸው።
👉እኛ መብራት አለን እነሱ ጨረቃ አላቸው
👉እኛ ምግብ እንገዛለን እነሱ ምግባቸውን ያበቅላሉ።
👉እኛ ደህንነታችንን ለመጠበቅ አጥር አለን።እነሱ ጓደኞች አሏቸው።
👉እኛ በቴሌቭዥን ጊዜያችንን እናሳልፋለን እነሱ ጊዜያቸውን ከቤተሰቦቻቸውና ከዘመዶቻቸው ጋር ያሳልፋሉ።አባትይው ለልጁ ምን እንደሚመልስለት ጠፋው ልጅም ላባቱ አባዬ ምን ያህል ደሃ እንደሆንን ስላሰየኸየኝ አመሰግናለው አለው።



አላህ በቅዱስ ቁርዓን ላይ በሱረቱ አል ተጋቡን ምዕራፍ 64 ቁጥር 15 ላይ እንዲህ ይለናል፦

"ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው፤ አላህም እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አልለ፡፡"


ገንዘብ ዘላቂ ደስታ አይሰጥም!

ከሃብት ሁሉ በላጩ ሃብት የውስጥ እርጋታ (ጡመእኒነቱ ነፍስ) ነው።አብዛኞቹ ሰዎች ይህን ስሜት ከደስተኝነት ስሜት ጋር ይቀላቅሉታል።ግን በፍፁም አንድ አይደሉም ደስታ ማለት በቀላሉ ውስጥህ ላይ ሚፈጠር ጊዝያዊ ስሜት ነው።ደስታ ምን መሰለህ ለምሳሌ አንድ ዘፈን መስማት የሚወድ ሰው ዘፈን ሲሰማ ያሰውዬ ለጊዜው ደስታ ያገኛል ግን ልክ ዘፈኑ ካለቀ በኋላ ይሃ ደስታው ወድያው ይወገዳል።ያአኺ ሰዎች ሁሌም ደስተኛ ሁን ይሉሃል ግን እንዴት እያልክ እራስህን ደግመህ ደጋግመህ ትጠይቃለህ።ምክንያቱም ደስታ ከጊዜዎችና ከሁኔታዎች ጋር የተያያዘ ነው።መቼስ በባዶ ልደሰት ብትል አትችልም።አንድ ሰው ጠዋት ደስተኛ ሆኖ ቢነሳ ከሰዓት ላይ ደስታው በሆነ ምክንያት ሊጠፋ ይችላል።እስቲ ዘፈኖች እና ፊልሞች ትክክለኛውን ደስታ ይሰጣሉን?🤔

ይባሱኑ ዘፋኞች እና ፊልም ሰሪዎች ምን ያረጉሃል መሰለህ በህይወትህ ካለው ተጨባጭ የተለየ አጋነው ስለፍቅር ይዘፍናሉ ፊልም ይሰራሉ።አንተም ሳታስበው ይሃ በተጨባጭ ልታየው የማትችለው ህይወትን እየተመኘህ ትዋልላለህ።አደለም አንተን ሊያስደስቱ ይቅርና የራሳቸውን ህይወት መመልከት በቂ ነው።አብዛኞቹ በሱስ እራስን በማደንዘዝ ሁሉንም ነገር ለመርሳት ሲሞክሩ ይስተዋላሉ። አላህ እነዚህ የሰዎችን ልብ በመግዛት ከመንገዱ የሚያጠሙትን ሰዎች እንዲህ ሲል ገልጿቸዋል

"ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡እነርሱ በ(ንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መኾናቸውን አታይምን!እነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መኾናቸውን (አታይምን)፤"


ግን የውስጥ እርጋታ (ጡመእኒነቱ ነፍስ) ከዚህ የራቀ ነው።በቃ ባጠቃላይ እንደኔ እንደኔ አላህ ሱብሃነ ወተዓላ በመልካም ሰሪዎቹ ባሪያዎች ውስጥ ያስቀመጣት የቀልብ እርጋታ ነች።በቃ አንተ አንዴ ይቺን ስሜት አግኛት እንጂ ሁሌም

ደስተኛ ነህ! ሰዎች ይቀኑብሃል!አላህ ዱንያ ላይ ስለፈጠረህ የሚሰማህ ደስታ ወደር የለውም ጀነትን ስታስባት ደግሞ ውስጥህ እጅግ ልትገልፀው ከምትችለው በላይ በናፍቆት ይጓዛል😍!


ብዙዎች ይችን ስሜት ለማግኘት ለፍተዋል ብዙዎች ደክመዋል አንዳንዶቹ ውስጣቸው የሚላቸውን ስሜት ብቻ እየተከተሉ ፈልገውታል ።ሌሎች ብዙ ሞክረዋል ግን የሚያገኟት የትኞቹ ይሆኑ??🤔




አላህ እንደዚህ ብሏል፦




مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡




ከአላህ በላይ ቃሉን የሚሞላ የለም በአላህ ተማመን!

#ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ
BY~ @theamazingquran
∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷
“አሁን ያለህበት ቦታ ላይ ተቀምጠህ ከቆየህ የምትመኝበት ቦታ ላይ አትደርስም።”
ተራ ኑሮ መኖር ከፈለግክ መብትህ ነው። ምክንያታዊና የላቀ ህይወት ከፈለክ ግን ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁመህ ማለፍ አለብህ።
እወቅ!
ያለ ስህተት ብዙ አትማርም፣ ያለ ህመም አታድግም፣ ያለ ውድቀት ስኬት ላይ አትደርስም። ውድቀቶችን ሰብስበህ ወደ ስኬት መገልበጥ የሚቻልህ ግን ከውድቀት በኋላ መነሳት ስትጀምር ነው።

∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷∷
@theamazingquran
Audio
ኪራይ ቤት
محمد اللحيدان - فاذكروني أذكركم
[ تلاوات خاشعة ▫️ tvquran@ ]
▫️فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ▫️

• القــارئ ؛ #محمد_اللحيدان

أيسر الأعمال الذكر،
ومن رحمة الله أنه إذا فضّل زمناً فضّل ذكره فيه،
لأن ذكر الله يُطيقه كل أحد فلا يعجز عنه إلا محروم

الشيخ .. عبدالعزيز الطريفي
https://www.tg-me.com/tvquran
የቁርዓን ግብዣ❤️
Forwarded from فقير إلى الله
╔═══════════════════╗
የአድዋው ችካል
ሸህ ሆጀሌ
╚═══════════════════╝

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
Mahi Mahisho

ምንም እንኳ ለቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ ቢሆኑም በኃይለኝነታቸው እና በአደን ብቃታቸው ካሉት ታላላቅ ወንድሞቻቸው የበለጠ ምጡቅ ብቃት ነበራቸው፡፡ ኃይለኝነታቸው እና ወኔያቸው አባታቸው ዘንድ ገና በ23 ዓመታቸው የጦር መሪ ተደርገው እንዲሾሙ አድርጓቸዋል።
በወቅቱ የነበረው የደርቢሽ ሰራዊት ለነሱ እንዲገብሩ በተደጋጋሚ ጠይቀው አባታቸው ጥያቄውን ባለቀመበላቸው በደርቡሾች እና በአባታቸው ሸኽ አልሐሰን መካከል ጦርነት ተነሳ። በጦርነቱም ደርቡሾች በነበራቸው የጦር ብዛት እና ኃይል ጦርነቱን ፍፁም በሆነ የበላይነት አሸነፉ። የሸህ ሆጀሌ አባት ተማረኩ። ሱዳን ሀገር ወስደው ገደሏቸው። የአባታቸው መገደል ያንገበገባቸው ሸኽ ሆጀሌ ጦራቸውን ይዘው ወደ ጫካ ገቡ። አካባቢውን የተቆጣጠረውን የደርቦሽ ጦር መውጋት ቀጠሉ፡፡ በጠላት ላይ ትልቅ ኪሳራ በማድረስ ብዙ የጦር መሳሪያን ማረኩ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግዙፍ ሰራዊትን አቋቋሙ። ድልም አድርገው አካባቢውን ተቆጣጠሩ።

አጼ ሚኒሊክ የቤንሻንጉልን አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ ለተለያዩ ሀገረ ገዢዎችን መአረጎችን ሲሰጡ ሸይኽ ሆጀሌም “ራስሆጀሌ” የሚል ማዕረግ ተሰጣቸው። ግና የአፄውን ስያሜ ቸል ብለው "ሸይኽ" የሚለው ማዕረጋቸዉ እንዲቀጥል በመወሰናቸው በዚሁ ስያሜ ታወቁ፡፡
በአድዋ ጦርነት ለመጀመሪያ ጊዜ ከጎረቤት ሀገር ዘጠኝ ጎራሽ የወቅቱ ዘመናዊ መሳርያን በራሳቸው ገንዘብ በመግዛት ወደ ሀገር አስገብተው የኢትዮጵያን ጦር በማሰታጠቅ እንዲሁም ለጦርነቱ የሚያገለግሉ ፈረሶችን ከነጋላቢያቸው ወደ ጦርነቱ በመላክ የጣሊያን ወራሪ ኃይል እንዲቀለበስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ሲዘረጋ ከለገሀር እስከ እውቶቢስ ተራ ከጸረሙስና እስከ ካሳንችስ የውጭ ባለሞያዎችን አስመጥተው በመገንባት አዲስ አበባ ዘመናዊ ይዘቷን እንድትይዝ የጎላ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ብዛት ያለው የወርቅና የገንዘብ ድጋፍ በመላክ በሀገራችን የመጀመርያው ባንክ እንዲቋቋም ከማድረጋቸውም በላይ ከጅቡቲ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ምድርባቡር ፕሮጀክት ዝርጋታ ላይም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉ የሀገር ባለውለታ ነበሩ፡፡
በግዛታቸው ህዝብ የመሬት ባለቤትነት መብቱ እንዲረጋገጥ ከማድረጋቸውም በላይ ለገበሬዎች በሬ፣ ዘር እንዲሁም የተለያዩ ልብሶችን በነጻ በማከፋፈል በሀገሪቱ የግብርና ስራ እንዲስፋፋ ህዝቡ በምግብ እህል እራሱን እንዲችል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ወላጅ አልባ ህጻናትን በማሳደግ እንዲሁም በግዛታቸው ለአቅመ አዳም የደረሱትን ወጣቶች እንዲያገቡና ቤተሰብ እንዲመሰርቱ ለጋብቻ የሚሆን ገንዘብ፣ ቤት እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፎች አበርክተዋል፡፡

ሸኽ ሆጀሌ ከአጼ ሚኒሊክ እስከ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት በዚሁ ስልጣናቸው የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እየተገነባ ባለበት አካባቢ ከህዝብ ጋር ስብሰባ ላይ ሳሉ ሕዳር10 ቀን 1931 በአላሚ ተኳሽ የጣልያን ቅጥረኞች በጥይት ተመተው ወደ አሶሳ ለህክምና ተወሰዱ። በወቅቱ ሴራውን ያቀነባበረው የጣልያን ጦር ወደ አዲስ አበባ ሄደው መታከም አለብህ በማለት አውሮፕላን አዘጋጅቶ ወደ አዲስ አበባ ወሰዳቸው። ሆስፒታል በተኙበትም በተሰጣቸው የመርዝ መርፌ በ113 አመታቸው ሕይወታቸው አለፈ፡፡ የቀብር ስነ-ስርዓታቸው በአሶሳ ከተማ ተፈጸመ፡፡ ሸኽ ሆጀሌ በተለያየ ጊዜ ካገቧቸው ባለቤቶቻቸው 77 ልጆችን ወልደዋል፡፡
አላህ ይዘንላቸው ቀብራቸውን የጀነት ጨፌ ማረፊያቸውን ፊርደውሰል አዕላ ያድርግላቸው

╔═══════════════╗
ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት
╚═══════════════╝
ጌታዬ ሆይ! ባልሰራበት እንኳ ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ


https://www.tg-me.com/yesheh_kalidrashid_daewawoch
https://www.tg-me.com/yesheh_kalidrashid_daewawoch
ታጋሽ ሆኖ ለመገኘትም የአላህ እገዛ ያሻል። ታጋሽነት በራስ ክህሎትና በልምምድ ብቻ የሚገኝ የትግል ፍሬ አይደለም። አላህን በመማጽንም ጭምር እንጂ።

ከአላህ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው የጠንካራ ኢማን ባለቤት የሆነ ሙስሊም የታጋሽነት ደረጃውም ከፍ ያለ ይሆናል። ደካማ እምነት ያለው አማኝ ደግሞ ትእግስቱም በዚያው ልክ ደካማ ነው።
{ واصبر وما صبرك إلا بالله}
Forwarded from Abdurahim Ahmed (Abdurahim ahmed)
ወጣቱ እና ቲክ ቶክ
ቲክቶክን በተመለከቱ ወጣቱ ሙስሊም ምን ላይ ነው ያለው የሚለው ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ። ይህ ወጣት ትውልድ ሊታዘንለት፣ሊታሰብለት ይገባል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ ። ሰሞኑን አንድ ወዳጄ እስኪ እነዚህን ቪዲዮዎች እያቸው ብሎ የላከልኝ ቪዲዮ በጣም ነው ያስደነገጠኝ ። ሁላችንንም አሏህ አይባችንን ሰትሮልን ነውንጅ ብዙ ወንጀሎች አሉብን ። ነገር ግን አሏህ የሰተረልንን ነውራችንን አደባባይ ላይ ቲክ ቶክ ላይ በሙዚቃ በጭፈራ ነውራችንን አደባባይ ላይ ማስጣት እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ኪስራ ነው ።
በተለይ ሙስሊም እህቶቼ ሂጃብ ክብርሽ ነው ። ሂጃብ ውበትሽ ነው። ስላንቺ ሂጃብ ስላንቺ ክብር ሲባል ብዙ ዋጋ ተከፍሏል። ይህንን ክብርሽን ይህንን የኢስላም ባንዲራሽን ለብሰሽ አደባባይ ላይ ስትጨፍሪበት ስላንቺ ዋጋ የከፈሉ ሀቢቡና ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ምን ይሰማቸው ይሆን ?
አንተስ ሙስሊሙ ወንድሜ ሆይ ዛሬ ላይ ኢስላም ካንተ ብዙ ነገር በሚፈልግበት ጊዜ ላይ ጊዜህን በምንድን ነው እያሳለፍክ ያለኸው
በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን አጀላችንን ደርሶ ብንሞት ቀብር ላይ ምንድን ነው መልሳችን ?
ሰዎችስ በምንድን ነው የሚያስታውሱን ?
ያቺ'ኮ ቲክቶክ ላይ ሂጃብ ለብሳ የምትጨፍረው ልጅ ይቺ ናት የሞተችው ተብሎ መታወስ ዛሬ ላይ ስታስቢው ምን ስሜት ይሰጥሻል?
ዑለማዎች፣ዳዒዎችስ ይህን ሁሉ ምርጥ ትውልድ እንደዋዛ ስናጣው እስከ መቼ ነው ዝምታው
እነዚህ ወንድም እና እህቶቻችን ሊታዘንላቸው አይገባም ወይ ?
ሌላው አደራ የምለው በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ እህት እና ወንድሞችን ዱዓ ማድረግ ነውንጅ መሳደብ፣ማንወር በያዙት መንገድ በእልህ እንዲቀጥሉ ማድረግና አደብ ማጣት ነው የሚሆነው ።
ነገር ግን ዱአ ማድረግ በስርአት መምከር ተገቢ ነው ።
ሁላችንም ለብሰን ስንታይ ሰው እንመስላለንጅ ብዙ ወንጀል ያለብን ሰዎች ነን አሏህ ያስተካክለን
ከመሆኑም ጋር ግን አሏህ የሰተረልንን አይባችንን አደባባይ ላይ ማውጣት ግን በጣም ከባድ ነው ያ ጀመአ ልብ እንግዛ
አሏህ ቀናውን መንገድ ይምራን
(አብዱረሂም አህመድ )
ሞዴል ለመሆን አስባ ፍፃሜዋ በኒቃብ የተዋበች ምርጥ እንስት ታሪክ
....ሂጃብ እንዲህ ነው...

አንዲት ኢትዬጲያዊ ደም ያላት አሜሪካዊት ነች። ቤተሰቦቿም ሆኑ እሷ ሙስሊሞች ናቸው። ሆኖም ልጂቷ ሞዴል የመሆን ፍላጎት ነበራት። ቤተሠቦቿ ሂጃብ እንድትለብስ አስተምረዋት ባያውቁም ሞዴል እንድትሆን ግን ፈፅሞ አይፈልጉም እሷ ግን የቤተሠቦቿን ሳይሆን የራሷን ፍላጎት ማሳካት ነው የምትፈልገው።

እና ሞዴል የመሆን ጥረቷን ቀጠለች: በዚያው መንገድ ላይ እያለች በአጋጣሚ በኢንተርኔት ስለ ኢስላም ማንበብ ጀመረች ነገሩ እየተመቻት ሲመጣ ብዙ ነገሮችን ስለ ኢስላም መፈለግ ጀመረች። ሙስሊም መሆኗን እስክትጠራጠር ብዙ የማታውቃቸውን ኢስላመዊ ትምህርቶችን አገኘች። ያገኘችው የሚማርክ ኢስላማዊ ት/ት ሀሳቧን እስከማስቀየር ደረሰና ከቤተሠቦቿ ጋር የተጋጨችበትን የሞዴሊንግ ፍቅር በኢስላም ተካችው። ቤተሠቦቿንም አስደመመች ሒጃቧንም በመልበስ ቻው ቻው ሞዴሊንግ አለች: ማሽ አላህ አትሉም እንዴ ታዲያ..

እህታችን በአሜሪካ ምድር ሔጃቧን አድርጋ ወደ ስራ ስትሔድና ስትመለስ አንድ አሚሪካዊ ሁሌ ይከታተላታል: ሁሌም በትሬን አብሯት ይጏዛል። ይህ አሜሪካዊ በጣም እንደሚወዳት ደግሞ በጣም የሚማርከው ነገር ፀጉሯ ላይ የምታደርገው ሔጃብ እንደሆነ ይነግራታል። እህቴ እኔና አንቺ ብንሆን ይሔን አሜሪካዊ የበለጠ እንዲማርከው በማግስቱ ያሸበረቀ ሒጃብ አድርገን እንመጣ ነበር: እሷ ግን እንደዚህ አላደረገችም።
‌‌
ለካ ይሔ የማደርገው ሒጃብ ወንዶችን ይስባል ስለዚህ ትክክል አይደለሁም ብላ ከግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ የሚሸፍን ሙሉ ሒጃብ (ኒቃብ) አደረገች።

ይህ ምንም ያልተጨመረበት እውነተኛ ታሪክ ነው። ሂጃብ እንዲህ ነው ተገደን ሳይሆን ወደን: ለመማረክ ሳይሆን ለመሠተር የሚለበስ.,...

እስቲ እርሶም like ✔️share ※comment ♂
በመስጠት ስጦታውን ለሌሎች ያጋሩ
ሼር በማድረጎ እናመሰግናለን
(ሱረቱል- ጁሙዓህ))❤️


ይቀላቀሉን
εmαnι grαρhιcs♥️
https://www.tg-me.com/anigraphics
(ሱረቱ አል-ጃሢያህ - 20)

ይቀላቀሉን
εmαnι grαρhιcs♥️
https://www.tg-me.com/anigraphics
2025/07/05 17:17:07
Back to Top
HTML Embed Code: