Telegram Web Link
¶በላጭ ሕዝቦች¶
Photo
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ሚያዚያ 18 እለተ ማክሰኞ በሙስሊሞች ላይ የተከፈተው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ (ግድያ) ፣ድብደባ የመስጂዶችና የቁርአን ቃጠሎ በፆመኛ አንጀታቸው የሙስሊም እህቶቻችን ላይ የደረሰባቸው አስገድዶ መድፈር የሙስሊም ሱቆችና የንግድ ማእከሎች ተለይተው ዝርፊያና ውድመት እንደ ሃገር የመጣንበትን
እሴት የናደና በስርዓት አልበኝነትና በማን አለብኝነት የተካበ አደገኛና ውግዝ ተግባር ነው። በመሆኑም መንግስት ይህን ተረድቶ በአስቸኳይ አጥፊዎችን እንደአጥፊነታቸው እርምጃ እንዲወስድልን በተደጋጋሚ ስንጠይቅ ከርመናል።ይህ ሳይሆንም ቀርቶ ከ60ሚሊየን በላይ የሚገመተውን የኢትዮጵያ ሙስሊምን ድምፅ በማፈንና በማስቆጣት ተካሳሾች ከሳሽ ሆነው በመቅረብ የድርጊቱን ባለቤት በመቀልበስ አጥቂውም ተጠቂውም እራሱ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ነው በሚል ተራ ወሬና በሬ ወለደ በሚመስል ቅኔ ወዲህ ወዲያ በማለት ሸፍጥ ሲያሴሩ ከረመዋል።ይህን እኩይ እቅዳቸውንም በመጠቀም በውሸት በተቀናበረ ለቀናት ብቻ በማህበራዊ የትስስር ግፆች ላይ የቆየና ከዛም የጠፋ የውሸት ዶክመንተሪ ሜንስትሪም ሚዲያን ጭምር በመጠቀም ዳግም ሙስሊሙን አስቆጥተዋል።ከዚም ባሻገር የተከበረውን የረመዷን ወርን ሸኝቶ የኢድ ሰላትን ከዲያስፖራው ወንድሙ ጋር ለመስገድ በተሰበሰበው መጠነ ሰፊ ሕዝበ ሙስሊም ላይ የኢድ ሰላት ሳይጀመር በፊት ጥቃት በመክፈት አስለቃሽ ጭስን በመተኮስ በአመት ጠብቆ በሚያገኘው ልዩ በአሉ ላይ ረመጥ ጥሏል። በእለቱም የአካልና የንብረት ጉዳት ተስተናግዷል።ይህ ረበሻ መነሻውን ያደረገው በሴት እህቶቻችን በኩል መሆኑን ተከትሎ እጅግ ብዙ እናቶች ከልጆቻቸው ጋር ተጠፋፍተው የደስታቸውን ቀን በለቀሶና በሲቃ እንዲያሳልፉ ተገደዋል። ይህን ሆደ ሰፊ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በተደጋጋሚ በማስቆጣት በተለያዩ መሳጂዶች ሳይቀር ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል ሰበብ በየፖሊስ ጣቢያው እየተንከራተተና እየታጎረ ይገኛል። መንግስት ሆይ!!! ትዕግስትም ገደብ አለው በዚህ መልኩ የሚረጋገጥ ምንም አይነት በአንድ ወገን የሚሰፍን ሰላም የለም። አሁንም ሀገሪቷ እንደሀገር እንድትቆም በዚህ አስነዋሪ ድርጊት የተሳተፉ ደም መጣጥ የሽብር አባላትን እርምጃ ስትወስድ ማየት እንሻለን።አለበለዚያ ሀገር እንደሀገር የምትቀጥልበት ህልወና አጠያያቂ ይሆናል!!!!

#IslamophobiaInEthiopia
#GondarMassacre
#Share
ፅንፈኝነት በማነሳሳትና በማበረታት የሚገኙ አካላት ለሕግ ቀርበው ማየት እንሻለን
Forwarded from "ኡማ ቲቪ " Tv
ﻟﺒﻴﻚ ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻟﺒﻴﻚ ! ﻟﺒﻴﻚ ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻟﺒﻴﻚ
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
Forwarded from "ኡማ ቲቪ " Tv
ከአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ከሀጅ ሱልጣን አማን ጋር ባደረግኩት
የስልክ ምልልስ ደብዳቤው በማን ፊርማና ትዕዛዝ እንደወጣ አይታወቅም።
በዚሕ ደብዳቤ ትዕዛዝ መሰረት ለሚባክን ገንዘብ ተጠያቂው ማን እንደሆነ
አይታወቅም በሚል ምላሽ ሰጥተውኛል።
ተመልከቱ ደብዳቤው ቀንና ፊርማ እንዲሁም የትዕዛዝ ሰጪው ስም እራሱ
የለውም።
ለገንዘባችሁ ተጠንቀቁ
ደብዳቤውን አስተውሉ
እባካችሁ የሙስሊሙ ገንዘብ እንዳይበላ ሼር አድርጉ
©Abu dawud
4_5837117222509612492.mp4
5.1 MB
👉. ነፍሴ ሆይ በቃ ወንጀልሽኮ በዛ❗️

ዛሬ የፈለከውን ሰርተህ የህይወት ጎጆህ ይቀለሳል። ነገ ትሞትና ብዕሩ ይነሳል!

የሸህ ኻሊድ አል ራሺድ አማርኛ ትርጉም አድምጡት ቀልብዎ ይርሳል!!

@Anbabiwoch
https://www.tg-me.com/theamazingquran
Forwarded from INFINITY ♾️ THRIFT STORE (My Moon)
የፈጅር (የሱብሕ) ሶላት ትሩፋቶች እና ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ
~ ~ ~~~~ ~~~ ~
1. ፈጅርን ስገድና በአላህ ጥበቃ ስር ሁን፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም]
2. ፈጅርን ስገድ ሌሊቱን በሶላት እንደቆምክ ይቆጠርልሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዒሻእን በጀማዐህ የሰገደ ግማሽ ሌሊትን በሶላት እንደቆመ ነው፡፡ ሱብሕን በጀማዐህ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደቆመ ነው” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
3. ሱብሕን ስገድ እራስህን ከሙናፊቆች መገለጫ አፅዳ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሙናፊቆች ላይ እንደፈጀር እና ዒሻእ ሶላት የሚከብድ የለም” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
4. ፈጅርን ስገድ ለጭንቅ ቀን ብርሃን ይሆንሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በጨለማዎች ወደ መስጂዶች የሚጓዙትን በቂያማህ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሃን አብስራቸው” ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 570]
5. ሱብሕን ስገድ መላእክት ይመሰክሩልሃል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “በናንተ ውስጥ የሌሊት መላእክትና የቀን መላእክት ይተካካሉ፡፡ በፈጅር ሶላት እና በዐስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡ ከዚያም እነዚያ በናንተ ዘንድ ያደሩት (ወደ ሰማይ) ይወጣሉ፡፡ ይህኔም ጌታቸው በነሱ ሁኔታ አዋቂ ሆኖ ሳለ “ባሪያዎቼን በምን ሁኔታ ላይ ተዋቸኋቸው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ “እነሱ እየሰገዱ ነው የተውናቸው፡፡ እየሰገዱም ነው የመጣናቸው” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
6. ሱብሕን ስገድ ሙሉ የሐጅና የዑምራን አጅር እፈስ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የማለዳን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!” ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3403]
7. ፈጅርን ስገድ በአለም ላይ ካሉ ፀጋዎች ሁሉ በላጭ የሆነ ፀጋ የምትጎናፀፍበት እድል ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የፈጅር ሱንናህ (ከፈርዱ በፊት የምትሰገደዋ ትርፍ 2 ረከዐ ሶላት) ከዱንያ እና በውስጧ ካለ ሁሉ በላጭ ነች” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
8. ፈጅርን ስገድ ከጀሀነም መትረፊያ ጀነትን መጎናፀፊያ ብስራትን ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ፀሀይ ከመውጣቷ እና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም” ይላሉ፡፡[ሙስሊም] እነዚህ ሶላቶች ፈጅርና ዐስር ናቸው፡፡ በሌላም ሐዲሥ “ሁለት ብርዳማ ሶላቶችን የሰገደ ጀነትን ይገባል” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
9. ፈጅርን ስገድ ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ ፀጋ የሆነውን የላቀውን ጌታ መመልከትን ትታደላለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “እናንተ ይህን ጨረቃ እንደምታዩት ጌታችሁን ታያላችሁ፡፡ እሱን በማየትም አትቸጋገሩም፡፡ ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለ ሶላት አለመረታት ከቻላችሁ አድርጉት (ስገዱ)” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
10. ፈጅርን ስገድ ጥሩ ነፍስ ይዘህ አንግተህ ንቁ ሆነህ ትውላለህ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
ተጠንቀቅ!
1. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!! [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644]
3. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
4. ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡

ወንድሜ ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጋ፡፡ ወቅቱን ጠብቀህ እንድትሰግድ የሚያግዝህን ብልሃትም ተጠቀም፡፡
1. በጊዜ ተኛ፡፡ የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) በኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡
3. ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ የሞራል ልሽቀት ነው፡፡
4. ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡
5. በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ፡፡
6. በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር ካለህም እሰየው፣ ተጠቀምበት፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 21/2007)

@Damemaka
@Damemaka
ተክቢር

አሏሁ አክበር!
የክርስትና መምህራን በጥላቻ ቀን ከሌሊት ኢሥልምናን ያጠለሻሉ፥ የእነርሱ የጥላቻ ዲስኩር እጅ እጅ ያላቸው እና ከጉያቸው የነበሩት የኦርቶዶክስ ምእመናት ወደ ዲኑል ኢሥላም እየመጡ ነው። 15 ልጆች ወደ ዲኑል ኢሥላም በሸሀደተይን ገብተዋል። የእኛ መምህራን የተውሒድን ብርሃን ለሙሥሊሙ እና ሙሥሊም ላልሆነው እያስተማሩ ይገኛሉ እንጂ አሉታዊ ነገር ላይ አይጠመዱም። አሏህ ይህንን ዲን ከፈለገ በከሃዲያንም ቢሆን ያጠናክረዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 212
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነሆ ሙሥሊም የሆነች ነፍስ እንጂ ሌላው ጀነትን አይገባትም፥ አላህ ይህንን ዲን ከፈለገ በከሃዲያንም ቢሆን ያጠናክረዋል"። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗَﺎﻝ ﻋﻦ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲّ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺃﻧﻪ ﻗَﺎﻝَ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳَﺪْﺧُﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻧَﻔْﺲٌ ﻣُﺴْﻠِﻤَﺔٌ، ﻭَﺃَﻥَّ ﺍﻟﻠﻪَ ﻳُﺆَﻳِّﺪُ ﻫَﺬَﺍ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ﺑِﺎﻟﺮَّﺟُﻞِ ﺍﻟْﻔَﺎﺟِﺮِ‏

መጪው ዘመን የኢሥላም ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom
ኢባዳ – ለአላህ ውዴታ

…ከዒባዳዎች ሁሉ በላጩ በሁሉም ጊዜ ዉስጥ አላህ ዘንድ ለመወደድ መሥራት ነው። ጊዜ፣ ሁኔታና አንፃርን እያዩ፡፡ …ለምሳሌ ጂሃድ በሚያስፈልግበት ጊዜ ምርጡ ሥራ ጂሃድ ነው። እንግዳ ቢመጣ በላጩ ሥራ የሚወደዱ ዚክሮችን ጭምር በመተው ሐቁን ለመወጣት ደፋ ቀና ማለት ነው፡፡

 ከፈጅር በፊት ባለው የመጨረሻ ሌሊት ጊዜ፤ (ሱሑር) ላይ ትልቁና በላጩ ሥራ ሶላት፣ ቁርአን፣ ዱዓ፣ ዚክር እና ኢስቲግፋር ናቸው።   
  
ተማሪን በሚመክሩበትና በሚያስተምሩ ጊዜ በላጩ ነገር - ሙሉ በሙሉ ከልብ ሆኖ ማስተማር ነው፡፡

 በአዛን ጊዜ በላጩ ሥራ፡- ሙአዚኑን በመከታተል የሚለውን ማለት በዚህ ጊዜ ላይ የሚደረጉ ዚክሮችን ማድረግ ነው።

በአምስቱ ሶላቶች ወቅት በላጩ ነገር፡- ሶላቶችን ባማረና በተገቢው መልኩ ለመፈፀም የቻሉትን ያህል መጣርና መበርታት፣ ጊዜያቸው እንደገባ ወዲያዉኑ መስገድ፣ ወደ መስጂድም ሄዶ መስገድ ነው፡፡ መስጂዱ ቢርቅም የሚሻለዉና የሚመረጠው ይህ ነው።

የተቸገረን ሰው በሚረዱበት ጊዜ በላጩ ነገር፡- ሌላውን በማስተባበርም ሆነ በራስ አቅም መርዳት፣ በገንዘብ ማገዝ፣ በዚሁ በማገዙ ሥራ ራስን መወጠር፣ ከችግር እስኪወጣ ድረስ የራስ ሥራዎችና በፊት የለመዱትን የዚክርና የኸልዋ ተግባራት ጭምር በመተው ለሱ መቆም ነው።
 
በቁርአን ቂርአት ጊዜ በላጩ፡- ቀልብን  በሙሉ አሰባስቦ ትኩረትን በመጨመር ማስተንተን፣ ለመገንዘብ መጣጣር፣ አላህ ልክ እንደሚያናግር ሆኖ በትኩረት መገኘት፣ ትዕዛዙና ምልከታዉን ለመተግበር መቁረጥ ናቸው።
 
ዐረፋ ላይ በሚቆሙበት ጊዜ በላጩ ነገር፡- በመተናነስ፣ በዱዓና በዚክር መበርታት፣ የሚያዳክም ፆም አለመፆም ናቸው።
በዐሽር አልአዋኺር ረመዷን ጊዜ በላጩ፡- መስጂድ ዉስጥ መቆየት፣ በዒባዳ መገለል፣ ከሰዎች ወሬዎች መራቅ፣ ዕውቀትና ቁርአን ከማስተማርም በበለጠ በመስጂድ ዉስጥ በዒባዳ መቆየቱና መገለሉ ነው የሚመረጠው ብለዋል በርካታ ዑለሞች ።
 
ወንድም ሲታመም ወይም ሲሞት በላጩ ነገር፡- እሱን መዘየርና ማጽናናት፣ ሲሞት ጀናዛው ሽኝት ላይ መገኘትና መሸኘት ነው፡፡

መከራ ሲወርድ እና ሰዎች ችግር በደረሰባቸው ጊዜ በላጩ ነገር - ችግር ደረሰባቸው ብሎ አለመሸሽና ከነርሱ ጋር ታግሶ አብሮ መኖር ነው፡፡  በላጩ ሙስሊም ማስቸገራቸዉን የሚሸሸው ሳይሆን በማስቸገራቸው ላይ  የሚታገሰው ከነርሱ ጋር ተቀላቅሎ አብሮ የሚኖር ነው፡፡
 
በኸይር ነገር ከሙስሊሞች ጋር ተቀላቅሎ መኖር ከመገለል ይመረጣል፣ መጥፎ የሚሠሩ ከሆነ ግን ከነርሱ ጋር ከመኖር መገለሉ ይመርጣል። እነርሱን መቀላቀሉ መጥፎነታቸው የሚቀንስ ከሆነ ከነርሱ ጋ ተቀላቅሎ መኖሩ ይመረጣል።
በሁሉም ነገሮች ውስጥ በላጩ፡- የአላህን ውዴታ መምረጥና ማስበለጥ ነው፤ በዚያ ጊዜ ግዴታ የሆነዉን ነገር መወጣት፣


 የሁለገብ ዒባዳ ባለቤት ውስን የሆነ ዒባዳ ይዞና መርጦ አይንቀሳቀስም፡፡ በርካታ የአምልኮ ተግባራት ውስጥ ይገላበጣል። አንድ ወደ አላህ የሚያደርሱና ከፍ የሚያደርገው የዒባዳ መንገድ ያስተዋለ እንደሆነ ወደዚያው በመግባት ይሄድበታል፣ በዚያው ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ ይላል። ጉዞ እስኪያልቅ ድረስም ይህ መስመሩ ነው።
ፕሮግራሙ ተሰርዟል
================
(ተስፋ ያደረግነውም ቀርቷል!)
||
የፕሮግራሙ አዘጋጆች ቀድመው መጨረስ የነበረባቸውን ህጋዊ አካሄዶች ቀድመው ባለመጨረሳቸው መከልከል ለሚፈልጉ አካላት መንገዱን ስላመቻቹት፤ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ስቴዲዬም ይካሄዳል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው በሃገራችን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር ተሰርዟል። ቀጣይ አቅጣጫዎችን የፕሮግራሙ አዘጋጆችና የሚመለከታቸው አካላት የሚያሳውቁን ይሆናል።



አንዳንድ ጊዜ ትልቅ የሚባሉ ሰዎች በሁሉ ነገር እኛው በሚል ብሂል በትልቅ ህዝብ ውክልና ሽፋን የህፃን ሥራ እየሠሩ ተዋርደው ያዋርዳሉ።


የሚያሳዝኑኝ ከክፍለ ሃገር ድረስ ትምህርታቸውን፣ ሥራቸውንና የግል ጉዳያቸውን ጥለው የመጡ እህትና ወንድሞች ናቸው።

አብሽር! ለኸይር ነው። በሁሉም ነገር አላህ ይክሳችኋል። አደራ! እንዳትበሳጩ! ለበጎ ነው በሉና እለፉት!



ከዚያ ውጭ በዚህ ጉዳይ ወደ መንግስት አፍን ማንጓጠጥ አልደግፍም። በርግጥ ስህተቱ ከኛው ሰዎች ቢሆንም ለግሞ ነው እንጂ ማስተካከል ይችል ነበር። ጭራሽ ደግሞ ህግና ደንቡ በትክክል ሳይፈጸም የሚካሄዱ ፕሮግራሞች እንደሚበዙባት ሃገር ይሄን ክፍተት ማከም ይቻል ነበር። ይሄን ክፍተት ካገኘና እንደ ምክንያት ካቀረበ ግን መብቱ ነው። ማንም ሊወቅሰው አይገባም። መንግስት የሚወቀሰው የሚጠይቀውን ህጋዊ አግባብ አጠናቀህ ሰበቡን ሁሉ ካደረስክ በኋላ እምቢ ሲልህ ነው።
https://www.tg-me.com/theamazingquran
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይህን ኹጥባ ሳንለቅ ማሳደር አልቻልንም!
--------------
ፕሮፌሰር ሸይኽ ከማል አልጀዛኢሪ ዛሬ የቁርአን ውድድሩ ላይ ስለ ሀበሻ ምድር ያደረጉት ኹጥባ እጅግ ድንቅ ነበር! ሀቂቃ ለመናገር ታሪካዊ ኹጥባ ነበር!! ስለ ሀበሻ በሌሎች አንደበት እንዲህ መስማት ያስደስታል!

እነሆ እናነተም ትመለከቱትና ታጣጥሙት ዘንድ ለቀነዋል!!!

خطبة الشيخ البروفيسور كمال الجزائري في حفل المسابقة لحفظ القرأن الكريم شارك فيها الحفاظ من دول متنوعة في العالم
تم القاؤه في نادي اديس ابابا في الدولة اثيوبيا يونيو 13 عام 2022
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
𒊹︎︎︎አጫጭርና ጠቃሚ መልዕክቶች ለማግኘት ይቀላቀሉን☟︎︎︎ ☟︎︎︎
𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
☀️ሁዳ መልቲሚዲያ

ቴሌግራም 👇
www.tg-me.com/huda4eth

ፌስቡክ👇
fb.com/huda4eth

ዩትዩብ👇
http://www.youtube.com/c/HudaMultimedia
ሁሌ ውስጣችንን ቢዚ የሚያደርገን ምንድን ነው?

እውነት በውስጣችን ሌላን የዱኒያ ጉዳይ እንደምናስበው ያክል አላህን እናወሳልን?

የዱኒያ ጉዳይ አሳስቡ እንደሚያስጨንቀን ሁሉ የቀብራችን የነገ አኼራችን ጉዳይ ያስጨንቀናልን?

ኢማሙ ኢብኑልቀይም ረሒመሁሏህ እንድህ ይላሉ

«(ከጌታህ ጋር) በመለያየት የወረደብህን አደጋና (ከጌታህ) የጋረደህን የውረደት ሂጃብ(ግርዶ) ማወቅ ከፈለግክ: ቀልብህ ለማን ባሪያ፣ አካልህ ለማን አገልጋይ እንደሆነ ተመልከት ውስጥህ በምን ጉዳይ ቢዚ እንደሆነ የመተኛ ቦታህን የያዝክ (ለመተኛት በጎንህ ጋደም ባልክ) ጊዜ ቀልብህ የት እንደሚያድር ከእንቅልፍህ ስነቃ ቀልብህ ወደየት እንደሚበር ተመልከት? ያ(እንድህ ውስጥህ ቢዚ የሆነለት ነገር) ነው (በትክክል) አምላክህ።
የቂያማ እለት ሁሉም (በዱኒያ ላይ) ሲያመልክ የነበረውን ይከተል መባልን በሰማህ ጊዜ (ይህ ውስጥህን እንድህ ቢዚ ያደረገው ነገር) የሆነውም ቢሆን ከእርሱ ጋር አብረኽ ትሄዳለህ። [መዳሪጅ ሳሊኪን (3/308)]

ሐቂቃ ይህ በጣም ያስደነግጣል የሁሌ ጭንቀታችን ሀሳባችን የነገ አኼራ ወይንስ እች ርካሿ ዱኒያ? ሁላችንም ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ?
_
قال الإمام ابن القيم رحمه الله

إِذَا أَرَدْتَ أَنْ تَعْرِفَ مَا حَلَّ بِكَ مِنْ بَلَاءِ الِانْفِصَالِ، وَذُلِّ الْحِجَابِ، فَانْظُرْ لِمَنِ اسْتَعْبَدَ قَلْبَكَ، وَاسْتَخْدَمَ جَوَارِحَكَ، وَبِمَنْ شَغَلَ سِرَّكَ، وَأَيْنَ يَبِيتُ قَلْبُكَ إِذَا أَخَذْتَ مَضْجَعَكَ؟ وَإِلَى أَيْنَ يَطِيرُ إِذَا اسْتَيْقَظْتَ مِنْ مَنَامِكَ؟ فَذَلِكَ هُوَ مَعْبُودُكَ وَإِلَهُكَ، فَإِذَا سَمِعْتَ النِّدَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ: لِيَنْطَلِقَ كُلُّ وَاحِدٍ مَعَ مَنْ كَانَ يَعْبُدُهُ، انْطَلَقْتَ مَعَهُ كَائِنًا مَنْ كَانَ. [مدارج السالكين (٣/ ٣٠٨)]
Forwarded from ሰአድ ኢብኑ አቢወቃስ የኪታብ ተማሪዎች
የተክቢራ ጊዜው በሁለት ይከፈላል
1)በጊዜ ያልተገደበ ወይንም ልቅ የሆነ(unlimited)
2)በጊዜ የተገደበ ወይንም መደበኛ የሆነ

1)ልቅ የሆነው ከመጀመሪያው የዙልሂጃ ቀን ጀምሮ እስከ 13ኛው ቀን ማገባደጃ አስር ወቅት መጨረሻ ድረስ በተመቸው ሰዓት ተክቢራ ማለት ይችላል።

2)መደበኛው እና የተገደበው የተክቢራ አይነት ከዓረፋ (ሚፆምበት)ቀን ፈጅር ጀምሮ እስከ 13ው ቀን አስር ሰላት ድረስ ነው።
የተገደበ ስንል በየሰላቱ መጨረሻ ብቻ ስለሚል ነው።ይህም ከሙስሊሞች ጋር በጀምዓ ለሰገደ ብቻ የሚሆን ነው ብለው ያስቀምጣሉ።
ተክቢራ አይነቶች አሉት።
ከነሱ ውሰጥ ዑለማዎቹ የመረጡት ሃዲስ ላይ ሰነዱ ጠንካራ የሆነውን ሁለት ጊዜ ተክቢራ ያለበትን ነው።
"الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله الله أكبر الله أكبر الله ولله الحمد "

በያለንበት ቦታ እና ጊዜ ማብዛቱ በጣም የተወደደ ተግባር ነው።ሰሃባዎችኝ ያደርጉት ነበር።ልክ እንነ አቡ ሁረይራ እና ኢብን ዑመር ወደ ሱቅ በሚወጡበት ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ እያደረጉ ተክቢራቸውን ይሉ ነበር።
2025/07/04 21:29:33
Back to Top
HTML Embed Code: