Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
“ በዚህ አመት 11 አዳዲስ የስልጠና ፕሮግራሞች ይከፈታሉ ” - ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በዚህ አመት 11 የሥልጠና ፕሮግራሞችን እንደሚከፈቱ የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) “በደረጃ 8 (በ3ኛ ዲግሪ) በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት ፕሮግራሞች ስልጠና ይሰጠል” ብለዋል። አዳዲስ በሚከፈቱት ፕሮግራሞች…
“ በተያዘው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሜዲያል ተፈታኞችን እቀበላላሁ ” - ኢንስቲትዩቱ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሜዳል ተፈታኞችን እንደሚቀበልና አዲስ የተቀረጹ የስልጠና መርሃግብሮችንም ይፋ እንዳደረገ ገልጿል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ እስከ 3 ዲግሪ ባሉት ደረጃዎች እንደሚያሰለጥን ያስታወቀው ተቋሙ፣ በዚሁ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሚዳል ተፈታኞችን እንደሚቀበልም ጠቁሟል፡፡

በመደበኛው በቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በክረምት የስልጠና መርሃግብሮች ከደረጃ ስድስት እስከ 8 (ከመጀመሪያ እስከ 3ኛ ዲግሪ) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አንደሚሰጥ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞችን የሚቀበልባቸው አራት መንገዶች ምን ምን ናቸው?

- ደረጃቸውን ለማሻሻል የቴክኒክና ሙያ አመራሮችና ሰልጣኞችን፣
- የኢንዱስትሪ ቴክኒሻኖችን በማታው፣ በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራሞች፣
- የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያመጡትን፣ እንዲሁም የሪሜዳል ተፈታኞችን (ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ) እንደሚቀበል ነው የገለጸው፡፡

ተደራሽነቱ ምን ይመለስላል?

ኢንስቲትዩቱ በአዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና ካምፓሱ በተጨማሪ የሀዋሳ ካምፓስና የብየዳ ስልጠና ልህቀት ማዕከል ካምፓሶች፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚገኙ 16 የሳተላይት ተቋማት በደረጃ 6 ወይም በመጀመሪያ ዲግሪ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን አስረድቷል፡፡

አዲስ የተቀረጹት አጫጭር የስልጠና መርሃግብሮች ምንድን ናቸው?

በዘንደሮው አመት 11 አዳዲስ የስልጠና ፕርግራሞች ከመታከላቸው በተጨማሪ አዳዲስ የተቀረጹ የአጭር ጊዜ የስልጠና መርሃ ግብሮችም ይፋ ተደርገዋል፡፡ በዚህም፦
- በሲቪል ቴክኖሎጂ፣
- በኤሌክትሪክ እና አይሲቲ፣
- በመካኒካል ቴክኖሎጂ፣
- በቴክስታይል እና አፓረል፣
- በአግሪካልቸራል እና አግሮፕሮሰሲንግ፣
- በሉባን ወርኪንግ የሚሰጡ ሲሆኑ፣ በእነዚህ ስር ያሉ ዝርዝሮችና ሌሎች የስልጠና ዝርዝሮች ከላይ ተያይዘዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
828🙏45😡26😢18😭13🥰9👏7😱6🕊5
ነፃ የትምህርት ዕድል !

የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር (ወወክማ)፦

➡️ ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የራሳቸውን ስራ/ቢዝነስ ለመጀመር የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣቸዋል!
➡️ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ
➡️ በፋሽን ዲዛይን የትምህርት ዘርፍ ለመሰልጠን ፍላጎት ያለው/ያላት

ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦
ዕድሜ ፡ ከ 18 እስከ 29 ዓመት
ፎቶ ፡ አምስት (5) ጉርድ ፎቶ
የቀበሌ መታወቂያ
የድጋፍ ደብዳቤ፦ በክፍያ መማር አለመቻልን የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ከወረዳ
የትምህርት ደረጃ፡ 8ኛ ክፍል እና ከዚያ በላይ

አድራሻ፦ መስቀል ፍላወር፣ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን ፊት፣ ዶንቦስኮ ገዳም አጠገብ (ወደ ግራ 100 ሜትር ገባ ብሎ) ለበለጠ መረጃ፡ 0114160640

@tikvahethiopia
411😡39😭27🙏25🕊2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ከዓዲግራት ደቡባዊ ምስራቅ 44 ኪ/ሜ ላይ ከደቂቃዎች በፊት ተከስቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ ሲሆን ንዝረቱ በተለያዩ ከተሞችም ተሰምቷል። @tikvahethiopia
“ በርህሌ አካባቢ ሰዎች በቤት ውስጥ እያሉ ቤቶች ፈርሰው ሰዎች ላይ አደጋ ደርሷል፣ ለህክምና ወደ ሆስፒታሎች ሂደዋል ” - ፕሮፌሰር አታላይ አየለ

መቐለ ከተማና አካባቢው ከትላንት ጀምሮ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ፣ ይህም በተለያዩ የክልሉና አጎራባች ቦታዎች እንደተሰማ ተነግሯል፡፡

ለአደጋው መከሰት ምን የተለየ ምክንያት አለ? ስንል የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ተማራማሪ ፕ/ር አታላይ አየለ፣ “በቆላማው የአፋር ክፍልና በደጋማው ክፍል በግልጽ የሚታይ ዝንፈት አለ፣ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያዘወትረው ቦታ ነው” ብለዋል፡፡

“አሁን በተፈጠበት አካባቢ በተደጋጋሚ ተፈጥሮ ያውቃል፡፡ ትላንት ከእኩለ ቀን ጅምሮ ከ4.2 በሬክተር ስኬል ጀምሮ እስከ 5.6 ከፍተኛው የሆነ መሬት መንቀጥቀጥ ከሰሜን ምሥራቅ መቐሌ ጀምሮ እስከ ምሥራቅ መቐለ ድረስ ተሰምቷል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

“በርህሌ አካባቤ ጉዳት እንዳዳረሰ እየተዘገበ ነው፡፡ ሰዎች በቤት ውስጥ እያሉ ቤቶች ፈርሰው ሰዎች ላይ አደጋ ደርሷል፣ ለህክምና ወደ ሆስፒታሎች ሂደዋል”፣  ያሉት ፕሮፌሰር አታላይ፣ ይህ ክስተት በዚህ ጊዜ ይመጣል ተብሎ “የሚተነበይ" እንዳለሆነም ተናግረዋል፡፡

ጉዳት ያስተናገዱት ቤቶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ “ደረጃውን የጠበቀ ህንጻ ቢሆን ኑሮ እንደዚህ አይፈጥርም ነበር” ሲሉም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ አገር መሆኗን፣ በዚህም በሂደት ያለ የስምጥ ሸለቆ ተፈጥሮ እያስተናግደን ስለሆነ ከቀይ ባህርና ከአፋር አካባቢ ጀምሮ በድሬዳዋን፣ ናዝሬት፣ ሀዋሳ፣ አርባምንጭ እያካለለ እንደሚሄድ ገልጸዋል፡፡

አሁን በትግራይ የተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛው 5.6 ስኬል እንደሆነና የተጋነነ እንዳልሆነ አብራርተው፣ “በዚያው ይቀራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

“5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፤ እንኳ 5.6 ሦስትና ሁለት” ያሉት ተመራማሪው፣ የት ነው አደጋው የተፈጠረው? የሚለው እንደሚወስነው፣ የሬክተር ስኬሉ ሁለት የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥም ቢከሰት ቤት እንደሚያፈርስ አስረድተዋል፡፡

ምን ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ሲያስረዱ ደግሞ፣ “የግንባታ ደረጃን ማሻሻል” እንደሚገባ ገልጸው፣ በስምጥ ሸለቆ ዙሪያ የሚሰሩ ቤቶች ትንሽም ቢሆኑ ተደርምሰው አደጋ ሊያደርሱ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በፈንታሌው ጊዜ እንደተማርነው ባለመረበሽ ግንዛቤ መውሰድ እንደሚያስፈልግ መክረዋል፡፡

“መሬት መንቀጥቀጡ ብቻውን ምንም ጉዳት ሊያደርስ አይችልም” ብለው፣ ግን ከህንጻና ከመሰረተ ልማት አጠገብ፣ ከቮልቴጅ አካባቢ ከሆነ አደጋ እንደሚያደርስ አስረድተዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
974😭247🕊52😢45💔35🙏31🥰7😡7🤔6👏3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Afar

በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እድሜው 12 ዓመት የሆነ ልጅ ህይወት ሲያልፍ 6 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

የሰሜናዊ ዞን አስተዳደር  የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ ባራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች መከሰቱን አሳውቋል።

በዚህም የ12 ዓመት ልጅ ህይወቱ ሲያልፍ 6 ሰዎች ተጎድተዋል።

በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች ፈርሰዋል።

በመሬት መንቀጥቀጡ 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ያለመጠለያ ቀርተዋል።

ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዞኑ ለኤፍ ኤም ሲ ገልጿል። #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
😢505335😭125🙏29💔21🕊18🤔9🥰8
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እድሜው 12 ዓመት የሆነ ልጅ ህይወት ሲያልፍ 6 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። የሰሜናዊ ዞን አስተዳደር  የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ ባራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች መከሰቱን አሳውቋል። በዚህም የ12 ዓመት ልጅ ህይወቱ ሲያልፍ 6 ሰዎች ተጎድተዋል። በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች ፈርሰዋል።…
#Tigray
           
ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በትግራክ 6 የመኖሪያ ቤቶች አፈረሰ።

የመሬት ንዝረቱ ዛሬም ተከስቷል።

በትግራይ ክልል ከምስራቃዊ ኣፅቢ ወምበርታ ወረዳ 26 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.6  የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በቃል ኣሚን ቀበሌ ገበሬ ማህበር ቡሐለ መንደር 6 ቤቶች በከፊል እንደፈረሱ ወረዳው አሳውቋል።

እንደ ትናንትናው ከበድ ባይሆንም ዛሬ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም የመሬት ንዝረቱ በተወሰነ መልኩ መቀጠሉ የገለፀው የወረዳው አስተዳደር በሰው ፣ በእንስሳትና በንብረት ያስከተለው አደጋ እንደሌለ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
😭369315🙏53😢28💔22🕊14🤔9🥰8👏1
" አደጋው ከባድ በመሆኑ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በአርጡማ ፋርሲ ወረዳ በጃራ ቀበሌ በተከሰተ በትራፊክ አደጋ እስካሁን ባለው 11 ሰዎዥ ህይወታቸው አልፏል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንስፔክተር ኡመር መሀመድ አደጋው የደረሰው በጨፋ ሮቢት ከተማ ልዩ ስሙ ' ጃራ ' ድልድይ አከባቢ መሆኑን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 73290 የሆነ ታታ አውቶቡስ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 41157 ተሳቢ መኪና ተጋጭተው አደጋው መድረሱን ገልጸዋል።

እስካሁን ባለው መረጃ 8 ወንድ 3 ሴት ባጠቃላይ 11 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 23 ሰዎች ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደረሰባቸው ተናግረዋል።

አደጋው ከባድ በመሆኑ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።

@tikvahethiopia
😭992465💔55😢49🙏35🕊16😱13👏5😡3🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት

ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ዉስብስብነትን ግምት ውስጥ በማስገባት በቂ እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ታምኖበት በየዓመቱ መጨረሻ ለተከታታይ ለሁለት ወራት ማለትም ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ይታወቃል።

ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የሁለት ወራት ጊዜ በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምረው ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች ቀጥለው ቆይተዋል።

በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት ፍርድ ቤቶች ከሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን መስጠት እንደሚጀምሩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳውቋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አድራሻም ቀድሞ ከነበረበት አድራሻ በመቀየር ከአብረሆት ቤተ መጸሕፍት 100 ሜትር ዝቅ ብሎ ፍርድ ቤቱ አዲስ እያስገነባ ባለው ህንጻ ውስጥ የሚጀምር መሆኑን ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
728👏61🕊34🙏31😭24😱12🥰10🤔9😡4
#ሓሸንገ_ሃይቅ

🕯ዩኒቨርሲቲ ሊገባ የመግቢያ ቀኑን እየተጠባበቀ የነበረው ተማሪ ለሽርሽር በወጣበት ሓሸንገ ሃይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።

በኦፍላ ሓሸንገ ሃይቅ ምንድነው ያጋጠመው?

ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን በትግራይ ደቡባዊ ዞን ኮረም ከተማ አሉ ከሚባሉ ብርቱ ተማሪዎች አንዱ ነው።

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትኖ 430 ነጥብ በማምጣት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ደርሶት ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱ አጠናቆ በመጠባበቅ ላይ ነበር።

ጅማ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት ቀነ ቀጠሮ መቅረቡን የተገነዘቡት ጓደኞቹ የመሸኛ ሽርሽር ዛሬ እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በሓሸንገ ሃይቅ አዘጋጁለት።

ሆኖም ዝግጅቱ ተጨናገፈ ፤ ባለራዕዩ ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን ሓሸንገ ሀይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።

የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን አስከሬን ከብዙ ፍለጋ በኃላ ዛሬ ከቀኑ 11:30 ተገኝቷል።

የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን የቀብር ስነ-ስርዓት ነገ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በኮረም ከተማ ይፈፀማል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
😭4.43K984💔540😢125🕊108🤔49🙏41😱33🥰22😡3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የክልል መንግስታት፣ የከተማ አስተዳደር ተሿሚዎች እና የህዝብ ተመራጮች የደመወዝ ስኬል ይፋ ተደርጓል።

በአስራ ሁለት ምድቦች የተከፈለው የደመወዝ ስኬሉ የክልል ፕሬዝዳንቶችን እና አፈጉባኤዎችን ጨምሮ እስከ የከተማ ቀበሌ አስተዳዳሪዎች ድረስ ያካተተ ነው።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ሙኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) የደሞዝ ስኬሉን ትክክለኛነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
402🤔226😱39😭34😡26😢16🙏16🕊10🥰7💔5
2025/10/23 18:51:08
Back to Top
HTML Embed Code: