Telegram Web Link
" አደጋው ከባድ በመሆኑ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በአርጡማ ፋርሲ ወረዳ በጃራ ቀበሌ በተከሰተ በትራፊክ አደጋ እስካሁን ባለው 11 ሰዎዥ ህይወታቸው አልፏል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንስፔክተር ኡመር መሀመድ አደጋው የደረሰው በጨፋ ሮቢት ከተማ ልዩ ስሙ ' ጃራ ' ድልድይ አከባቢ መሆኑን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 73290 የሆነ ታታ አውቶቡስ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 41157 ተሳቢ መኪና ተጋጭተው አደጋው መድረሱን ገልጸዋል።

እስካሁን ባለው መረጃ 8 ወንድ 3 ሴት ባጠቃላይ 11 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 23 ሰዎች ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደረሰባቸው ተናግረዋል።

አደጋው ከባድ በመሆኑ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።

@tikvahethiopia
😭991463💔55😢49🙏35🕊16😱13👏5😡3🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት

ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ዉስብስብነትን ግምት ውስጥ በማስገባት በቂ እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ታምኖበት በየዓመቱ መጨረሻ ለተከታታይ ለሁለት ወራት ማለትም ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ይታወቃል።

ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የሁለት ወራት ጊዜ በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምረው ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች ቀጥለው ቆይተዋል።

በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት ፍርድ ቤቶች ከሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን መስጠት እንደሚጀምሩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳውቋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አድራሻም ቀድሞ ከነበረበት አድራሻ በመቀየር ከአብረሆት ቤተ መጸሕፍት 100 ሜትር ዝቅ ብሎ ፍርድ ቤቱ አዲስ እያስገነባ ባለው ህንጻ ውስጥ የሚጀምር መሆኑን ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
727👏61🕊34🙏31😭24😱12🥰10🤔9😡4
#ሓሸንገ_ሃይቅ

🕯ዩኒቨርሲቲ ሊገባ የመግቢያ ቀኑን እየተጠባበቀ የነበረው ተማሪ ለሽርሽር በወጣበት ሓሸንገ ሃይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።

በኦፍላ ሓሸንገ ሃይቅ ምንድነው ያጋጠመው?

ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን በትግራይ ደቡባዊ ዞን ኮረም ከተማ አሉ ከሚባሉ ብርቱ ተማሪዎች አንዱ ነው።

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትኖ 430 ነጥብ በማምጣት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ደርሶት ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱ አጠናቆ በመጠባበቅ ላይ ነበር።

ጅማ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት ቀነ ቀጠሮ መቅረቡን የተገነዘቡት ጓደኞቹ የመሸኛ ሽርሽር ዛሬ እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በሓሸንገ ሃይቅ አዘጋጁለት።

ሆኖም ዝግጅቱ ተጨናገፈ ፤ ባለራዕዩ ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን ሓሸንገ ሀይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።

የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን አስከሬን ከብዙ ፍለጋ በኃላ ዛሬ ከቀኑ 11:30 ተገኝቷል።

የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን የቀብር ስነ-ስርዓት ነገ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በኮረም ከተማ ይፈፀማል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
😭4.42K984💔539😢124🕊108🤔48🙏41😱33🥰22😡3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የክልል መንግስታት፣ የከተማ አስተዳደር ተሿሚዎች እና የህዝብ ተመራጮች የደመወዝ ስኬል ይፋ ተደርጓል።

በአስራ ሁለት ምድቦች የተከፈለው የደመወዝ ስኬሉ የክልል ፕሬዝዳንቶችን እና አፈጉባኤዎችን ጨምሮ እስከ የከተማ ቀበሌ አስተዳዳሪዎች ድረስ ያካተተ ነው።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ሙኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) የደሞዝ ስኬሉን ትክክለኛነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
397🤔226😱39😭34😡26😢16🙏16🕊10🥰7💔5
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 " ግብፅ ለጸጥታው ም/ቤት ደብዳቤ ልካለች፤ የኢትዮጵያ መንግስትም አቋሙን ልቅም አድርጎ ግብፅ ላቀረበችው ክስና ውንጀላ ምላሽ ሰጥቷል " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ➡️ " የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ይገባታል አይገባትም? ለምን ፍላጎት ኖራት? የሚለውን እኛና እኛ ብቻ ነን የምንመልሰው! " የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀ ማግስት ግብፅ ለጸጥታው ምክር ቤት ላቀረበችው…
#ETHIOPIA🇪🇹
#GERD💪

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ገና ሲጀመር አስንቶ ስትፎክር እና ስትዘት የነበረችው ግብፅ አሁንም ግድቡ ተመርቆ ፉከራዋ አልቆመም።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ ፤ " ብሔራዊ ጥቅማችንን አና የውሃ ደኅንነታችንን ለማስጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ሁሉንም እርምጃዎችን እንወስዳለን " ሲሉ ፎክረዋል።

" ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በማስተዳደር ላይ እየተከተለችው ባለው ኃላፊነት የጎደለው አካሄድ ላይ ሀገሬ እጇን አጣጥፋ አትመለከታትም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላይ መተማመናችን እንደ ድክመት መቆጠር የለበትም " ማለታቸው ተነግሯል።

ፕሬዚዳንቱ " ባልተመጣጠነ የውሃ ፍሰት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው " ሲሉ ተናግረዋል። " ኢትዮጵያ አስቀድማ ሳታሳውቀን ሳትተባበር ወጥነት የሌለው ውሃ ትለቃለች " ብለዋል።

ከሳምንታት በፊት ሱዳን ውስጥ ለደረሰ ጎርፍ ግብፅ ኢትዮጵያን ወንጅላ ነበር።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ግብፅ ላቀረበችው ውንጀላ ምላሽ ሰጥታት ነበር። ይኸው ምላሽም ግብፅ ያቀረበችችው ክስ በሀሰት የተሞላና  ተንኮል አዘል ነው " የሚል ነው።

ግብፅ የግድቡ መሰረት ሲቀመጥ ነው ፉከራና ዣቻ ማሰማት የጀመረችው ሀገሪቱ እንዲሁ እንደፎከረች እስካሁን አለች።

በተደጋጋሚ " ነይ ወደ ስምምነት ግቢ " ብትባልም ስምምነት ሳታደርግ ቀርታለች። የፉከራና እና ዛቻ መግለጫዎችን እየሰጠች ግድቡ ተመርቋል ፤ አሁንም ቢሆን ግን ከመፎከር ወደኃላ አላለችም።

ግብፅ ግድቡ እንዳይሰራ ኢትዮጵያ ድጋፍ እንዳታገኝ ዘመቻ ከማድረግ ባለፈ በሀገር ውስጥ ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት በመጠቀም እንዲሁም ለምዕራባውያን ሰዎች ጉቦ ጭምር በመስጠት ስራው እንዲደናቀፍ ጥረት ማደረጓ የአድባባይ ሚስጥር ነው። ያደረገቻቸው ሙከራዎች ሳይሳኩላት ቀርቶ ግድቡ በምርቃት ተደምድሟል።

#GERD💪
#Ethiopia🇪🇹
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.9K😡166👏102🕊65🙏48🤔25😭22😱13🥰4
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 #GERD💪 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ገና ሲጀመር አስንቶ ስትፎክር እና ስትዘት የነበረችው ግብፅ አሁንም ግድቡ ተመርቆ ፉከራዋ አልቆመም። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ ፤ " ብሔራዊ ጥቅማችንን አና የውሃ ደኅንነታችንን ለማስጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ሁሉንም እርምጃዎችን እንወስዳለን " ሲሉ ፎክረዋል። " ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በማስተዳደር ላይ እየተከተለችው…
#GERD💪

" ግድቡን እኛ ሳንሆን እነሱ ናቸው የሚጠብቁት " - የቀድሞ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ


" ግድቡን እራሳቸው ነው የሚጠብቁት " ማለት ምን ማለት ነው ?

ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ኢትዮጵያ የሁለተኛውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት ባከናወነችበት ወቅት በግብፅ ጉዳይ አንድ የማይረሳ አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ግብፆች " ግድቡን እንመታለን " እያሉ የሚዝቱት ፣ የሚያስፈራሩት ነገር እንዳለ ተናግረው የግድቡ ግዝፈት እና ጥራቱ ግን መቼውንም ቢሆን ተመቶ ይፈርሳል ተብሎ የሚታሰብ እንዳልሆነ አስረድተው ነበር።

" እንደው እንመታለን የሚለው ተሳክቶላቸው እንኳ ቢሆን የውሃ ሙሌቱ ልክ እንደ #ኒውኩሌር_ቦምብ ማለት ነው ለራሳቸው የሚሆነው ፤ ጠራርጎ ሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ነው የሚጨምራቸው " ሲሉ ነበር የገለጹት።

የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት " ግድቡን እኛ ሳንሆን እነሱ ናቸው የሚጠብቁት " ብለዋል።

ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ ብዙ የሚያስጨንቃት ነገር የለም።

ግብፆቹ ከግድቡ ግንባታ መነሻ ጀምሮ ሲፎክሩና ሲዝቱ ነው የነበሩት አሁንም ግድቡ ተጠናቆ ፉከራዋ አላቆመም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

#ETHIOPIA🇪🇹
#GERD💪

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
12.37K👏275🤔47🕊47🙏43🥰22😡18😢13💔10😭8
#Peace🕊

" በጋዛ ጦርነቱ አክትሟል " - ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ከ2 ዓመት በፊት መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ሐማስ በምዕራብ እስራኤል ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ 1,200 ሰዎችን ከገደለ እና 251 አግቶ ከወሰደ በኋላ እስራኤል በጋዛ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ አካሄዳለች።

በዚህ ወታደራዊ ዘመቻም 67,000 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከእነዚህ መካከልም 18,000 ያህሉ ሕጻናት መሆናቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

አስከፊው ጦርነት እንዲቆም ብዙ ጥረት ቢደረግም ፍሬ ሳያፈራ ቆይቷል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሆነው ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተው እስራኤል እና ሐማስ ከቀናት በፊት የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገዋል ፤ ጋዛም እፎይ ብላለች።

በመጀመሪያው ስምምነት መሰረት ሀማስ ያገታቸውን እስራኤላውያን ይለቃል እስራኤልም አጉራ ያሰረቻቸውን ፍልስጤማውያንን ትለቃለች።

ዛሬ እስራኤላውያን ታጋቾች በሀማስ ተለቀው ለቀይ መስቀል ተሰጥተዋል።

ቀጣዩ ፈተና ምን ይሁን ?

ቀጣይ የሰላም ዕቅዱ ላይ ድርድር የሚደረግባቸው ፦
➡️ ጋዛ ማን ያስተዳድር ?
➡️ የእስራኤል ወታደሮች አካባቢውን ለቅው ይውጡ፤
➡️ የሐማስ ትጥቅ መፍታት የሚሉት ከስምምነት ለመድረስ አስቸጋሪ ነጥቦች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ገብተዋል። ቴላቪቭ ሲደርሱ የእስራኤል ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ተቀብለዋቸዋል።

ትራምፕ እስራኤል ለመሄድ ወደ ኤርፎርስ ዋን አውሮፕላን እየተሳፈሩ እያለ የተኩስ አቁሙ እንደሚፀና እና በጋዛ በፍጥነት " የሰላም ቦርድ " እንደሚቋቋም ተናግረዋል።

ለአሁኑ ስምምነት ኳታርም ላደረገችው አስተዋፅኦ አመስገነዋል።

" በጋዛ ጦርነቱ አክትሟል " ሲሉም ተደምጠዋል።

ትራምፕ ጋዛን ይጎበኙ እንደሆነ ሲጠየቁ፣ ቢያደርጉት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
" ቢያንስ እግሬ ቢረግጥ ደስ ይለኛል " ብለዋል። በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ጋዛ " ተአምር " ትሆናለች ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
1.62K🕊337👏61🙏50😡36😭27💔21🤔10🥰8😢6😱3
#Tigray

በጦርነት ላይ ተሳታፊ የነበሩ የትግራይ ኃይል አባላት በዛሬው ቀንና በአሁኑ ሰዓት በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች የመብት ጥያቄ አንስተው ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

አባላቱ ከሚያሰሙት መፈክር የደመወዝ ጭማሪ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎልቶ ተደምጧል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በአሁኑ ሰዓት ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በማምራት ላይ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ጉዳዩን ተከታትሎ ተጨማሪ መረጃ ያደርሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ቪድዮ ፦ አብርሃ ገብረአረጋዊ

@tikvahethiopia
1937😭126🤔69🕊65🙏54👏33😡24🥰15😱12😢4
2025/10/21 22:15:08
Back to Top
HTML Embed Code: