Telegram Web Link
#Kenya

የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህንድ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ራይላ ኦዲንጋ ለኬንያ ፕሬዚዳንትነት 5 ጊዜ ዕጩ ሆነው ቢቀርቡም አልተሳካላቸውም።

በተጨማሪ በቅርቡ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ ቢወዳደሩም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ለረጅም አመታት በፖለቲካ ውስጥ የቆዩት ኦዲንጋ በኬንያ የበዛ ድጋፍ ያላቸው ሲሆን የኦሬንጅ ዴሞክራቲክ ሙቭመንት መሪ ነበሩ።

ለዴሞክራሲ፣ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ከህገመንግስት ሪፎርም በመታገል ይታወቃል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በራይላ ኦዲንጋ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
467😭413🕊66😢31👏27😱13🙏13🤔12💔7😡4🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ወደ መቐለ የሚያመሩ መንገዶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን በሁለት አቅጣጫ በትግራይ ኃይል ሰልፈኞች ተዘግተዋል።

የተዘጉት መንገዶች በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከመቐለ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የኣጉላዕ ከተማ ፤ በደቡባዊ ዞን ከመቐለ 100 ኪሎ ሜትር አከባቢ በምትርቀው የመኾኒ ከተማ መሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ደርሶታል።

በተጨማሪ በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስደው መንገድ ከከተማዋ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው እንዳባጉና ከተማ በሰልፈኞች ተዘግቷል።

ሰልፈኞቹ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከመቐለ ከተማ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋና መንገድ ዘግተው ውለው በዚያው ቀን ምሸት ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ተወያይተው " ጥያቄያችሁ ልክ ነው ፤ በየደረጃው ይመለሳል " ተብለው ነበር።

ጉዳዩን ተከታትለን መረጃውን የምንልክ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
500👏56🕊36😭34😡21🤔12😱6
‎" የ12 ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመው የ65 ዓመት አዛዉንት የ23 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል " - የይርጋለም ከተማ ፖሊስ

➡️ ‎" ግለሰቡ የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚና የመድሐኒት ተጠቃሚ ነበር "


‎በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የይርጋለም ከተማ አስተዳደር የ12 ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈጸመው የ65 ዓመት ግለሰብ የ23 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።

የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደግነት ደስታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ፥ የከተማው ነዋሪ የሆነ አቶ ናስር ኑር የተባለ የ65 ዓመት ግለሰብ ነሐሴ 6/12/2017 ዓ.ም በከተማው 06 ቀበሌ የ12 አመት ታዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት መፈጸሙን የሚገለፅ መረጃ ለፖሊስ ይመጣል።

ፖሊስም ጉዳዩን ከፍትህ መዋቅር ጋር በመመርመር በሰውና በህክምና ማስረጃ በማጣራት ለከተማው ዐቃቤ ህግ አስተላልፏል።

‎በምርመራና መረጃ በማሰባሰብ ሂደትም ግለሰቡ ይህን አስነዋሪ ድርጊት ከመፈፀሙ ባሻገር የኤችአይቪ /ኤድስ (HIV/AIDS) ታማሚና እንደሆነና እራሱን አውቆ የመድሐኒት ተጠቃሚ እንደነበር ማወቅ መቻሉን አዛዡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

‎ጉዳዩን የያዘዉ የይርጋለም ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ ያቀረበውን የክስ መዝገብ ሲያጣራ የቆየው የከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሳሹን " ጥፋተኛ ነህ " በማለት ተከሳሹ  እንዲከላከል ቢጠይቅም መከላከል አልቻለም።

‎እንዲሁም የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚ መሆኑን እያወቀ በታዳጊዋ ላይ በፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት ጥፋቱን በማክበድ በቀን 4/2/2018 በዋለው ወንጀል ችሎት ተከሳሹን በ23 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1😡4.65K1.05K😭668💔236😢164😱62👏57🤔52🙏49🕊30🥰9
#SafaricomEthiopia

እያንዳንዱ የሚገዙት የበሽ ጥቅል ወደ ሚሊየነርነት አንድ እርምጃ ያስጠጋዎታል! ከእለታዊ ጉርሻዎች እስከ በሕይወት ቀያሪ ሽልማቶች ይንበሽበሹ!

📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!

#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
169🥰4🙏4😢2😭2😡2😱1
TIKVAH-ETHIOPIA
በአፍሪካዊቷ ሀገር #ማዳጋስካር 🇲🇬 የሆነው ምንድነው ? (በአጭሩ) - ከ15 ቀን ገደማ በፊት የማዳጋስካር ወጣቶች የመሩት ተቃውሞ ይቀሰቀሳል። ይኸው ተቃውሞው በዋና ከተማዋ አንታናናሪቮ ካለ የኃይል መቆራረጥ እና የውሃ እጥረት ጋር የሚያያዝ ነበር። የወጣቶቹ ተቃውሞ ' Gen Z Madagascar ' የሚል ስያሜ ነበረው። - በኃላ የወጣቶቹ ተቃውሞ ቁጣ የታከለበትና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣…
#Madagascar

" እኛ ስልጠን ይዘናል " - የማዳጋስካር ጦር

" ህ ገወጥ መግለጫ ነው " - የፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት

የማዳጋስካር ጦር የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠሩን ገለጸ።

የጦሩ ዋና መሪ ኮሎኔል ሚኬል ራኔድሪኒራ በመድናዋ በሚገኘው አንታናሪቮ ፕሬዝዳንታዊ ፅህፈት ቤት በሰጡት መግለጫ " እኛ ስልጠን ይዘናል " ብለዋል።

" በቅርቡ መንግስት የሚያዋቅሩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንመርጣለን " ሲሉ ተናግረዋል።

የፕሬዝዳንት ራጆሊና ፅህፈት ቤት በበኩሉ የጦሩን እርምጃ፣ " መፈንቅለ መንግስት ተፈፅሟል፣ ህገወጥ መግለጫ ነው " ሲል ተቃውሟል።

ፅህፈት ቤቱ አክሎ፣ "ፕሬዝዳንት ራጆሊና ለደህንነታቸው ሲባል ደህንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ ተዘዋውረዋል" ብሏል።  

ፕሬዝዳንት አንድሬ ራጆሊና ሀገር ጥለው በፈረንሳይ የጦር አውሮፕላን ሸሽተዋል ቢባልም አስተባብለዋል።
#sana

Via @ThiqahEth
417👏88🤔38😭21😢6😡6🙏5🕊3🥰1😱1
VAT Strategy.pdf
6.2 MB
የገቢዎች ሚኒስቴር የተርን ኦቨር ታክስን በሚመለከት ዝርዝር የሽግግር የአሰራር ስርአት አዘጋጀ።

የገቢዎች ሚኒስቴር የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ቁጥር 308/95 ከሐምሌ 2017 ጀምሮ የተሰረዘ በመሆኑ የነባር የተርን ኦቨርታክስ ከፋዮችን በተመለከተ በታክስ አስተዳደሩ ለሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም እንዲያግዝ የሽግግር የአሰራር ስርዓት አዘጋጅቷል።

የተዘጋጀውን የአሰራር ስርዓት ተፈርሞ ከተላለፈበት መስከረም 21 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

የአሰራር ስርአቱ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በስራ ላይ የዋለው የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ከእዚህ ቀደም በስራ ላይ የነበረውን የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ የሻረ በመሆኑ ፣ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 በፊት የተርን ኦቨር ታክስ ከፋይ በነበሩ ግብር ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

የአሰራር ስርአቱ ለስድስት ተከታታይ ወራት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን የአሰራር ስርአቱ ይገልጻል።

አዲሱ የአሰራር ስርአት የታክስ ከፋይ መረጃ ማጥራት እና ማደራጀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ እና አፈጻጸም ፣ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ጨምሮ የቅሬታ አፈታት ስርአት በሚመለከት ዝርዝር ጉዳዮችን ይዟል።

(ዝርዝር የሽግግር የአሰራር ስርዓት አፈጻጸሙን ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
433😭26😱24😡15🙏12🕊3😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ ጥፋት ሲፈጸም ሰሌዳ ይፈታል የሚል ሕግ የለም ” - አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

የትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ነባሩን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር በአዲስ የመተካት ሥራ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የራሱ መለያና ስቲክር በመስጠት ሕገወጥ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ቅየራን ለማስቀረት እንደሚረዳ ገለጸ።

የተቋሙ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ ያረጁ ተሽከርካሪዎች ለጨረታ ሲወጡ ብዙዎች ተሻምተው ገዝተው ያለጉምሩክ እውቅና በሕገወጥ አዲስ ታርጋ የሚቀይሩበት ሁኔታ መስተዋሉን ገልጸዋል።

በመሆኑም በአዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ መሰረት ለተሽከርካሪዎች የሚሰጠው ታርጋ እንዳይፈታ በማድረግ፣ ምናልባት ከተፈታ እንኳ ከተሽከርካሪው በሚለጠፍ ስቲከር አማካኝነት በመፈተሽ ሕገወጥ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ቅየራን ለማስቀረት እንደሚቻል አስረድተዋል።

ጥፋት የሚፈጽሙ ታርጋቸው ተፈትቶ የሚቀጡበት አሰራር አለ፣ ታዲያ በአዲሱ አሰራር የማይፈታ መለያ ሲሰጥ ከዚህ ጋር አይጣረስም ወይ ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ “ ጥፋት ሲፈጸም ሰሌዳ ይፈታል የሚል ሕግ የለም ” ብለዋል ሚኒስትሩ።

በኢትዮጵያ በተለምዶ ስለሚፈታ እንጂ በሌሎች ባደጉት አገራት ጥፋት የፈጸመ ተሽከርካሪን ለመቅጣት ቤት ድረስም ይኬዳል እንጂ ማስቆም አያስልግም ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ ጥፋተኛን ለመቅጣት ሰሌዳ መፍታት አያስፈልግም ” ሲሉም ተደምጠዋል።

የተቋሙ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ በርሆ ሀሰንም ይህንኑ ሀሳብ ተጋርተው፣ ታርጋ እንዳይፈታ የሚያደርግ አሰራር እየተዘረጋ መሆኑን አስረድተዋል።

ሰሌዳ ለመቀየር ወጭውን የሚሸፍነው ማነው ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ “ሁሉም የራሱን ወጭ ይሸፍናል፣ የሚቀየረው የመስሪያ ቤት ተሽከርካሪ ከሆነም መስሪያ ቤቱ ይከፍላል” ነው ያሉት።
 
የተሽከርካሪ ምዝገባ ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው በ1994 በመሆኑ በግምት ወደ 1.6 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች እንዳሉ ቢታመንም ትክክለኛው ቁጥር እንደማይታወቅ ገልጸው፣ “ አዲሱ አሰራር ተሽከርካሪን በአዲስ ለመለየትና የተሽከርካሪን ቁጥር ለመለየት ይረዳል ” ብለዋል።

ወደ 2 ሚሊዮን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ለማምረት መታቀዱን፣ አዲሱን መለያ የመቀየር ስራውም ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ባለው ጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ፣ ትክክኛ ቀኑን መግለጽ ግን እንደሚያስቸግር ተገልጿል።

“ በአዲሱ አሰራር ቀደም ሲል የነበረውን የተሽከርካሪ ሰነድ በመለየት በድጋሚ የሚረጋገጥ ይሆናል ” ሲሉም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ እስከዛሬ በነበረው አሰራር ተሽከርካሪዎች የመጡበት ክልል የሚገልጽ መለያ መሰጠቱ፣ ለአድሎዓዊ አሰራር ሲዳርግ መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፣ በአዲሱ አሰራር "ETH" ወይም "ኢት" በሚል ኮድ ብቻ ስለሚሰጥ ችግሩ እንደሚቀረፍ ሚኒስትሩ አረድተዋል።

ነባሩን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር በአዲስ መልኩ መተካት ካስፈለባቸው ምክንያቶች መካከል የተሽከርካሪ ሰሌዳ አመራረትና አሰረጫጨት የአሰራር ክፍተትና የሃብት ብክነትንና ሕገወጥ የታርጋ ቅየራን ማስቀረት፣ የተሽከርካሪዎችን ብዛት ለማወቅ ማስቻል ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.14K👏99🙏25😡25🤔18🕊15😢10💔9🥰7😱6😭5
2025/10/23 17:18:03
Back to Top
HTML Embed Code: