የእደ ጥበብ አውደርዕይ: መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የሙያ ትርኢት እና ምረቃ ፕሮግራም
ሩትስ ኤንድ ዊንግስ ኤሊክስር መስማት የተሳናቸዉ ሴቶችን ለማበረታታት እና በሙያ የበቁ ለማድረግ በቪክቶሪ እና አልፋ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት በተለያዩ የእጅ ሙያዎች ሲያሰለጥናቸው የነበሩ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችን ያስመርቃል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ተማሪዎች የሠሯቸውን የተለያዩ የእደ ጥበብ ሥራዎች ያቀርባሉ፡፡
ቅዳሜ፡ ጥቅምት 1/ 2018 ዓ.ም
ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 8፡00
በአልፋ የመስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ግቢ ዉስጥ።
ለተሳታፊዎች ውስን ቦታ አዘጋጅተናል፡፡
መግቢያው በነጻ ሲሆን ሊንኩን በመጫን ቅጹን በመሙላት ይመዝገቡ
https://forms.gle/3qNH3nU2BtEdasmh8
ለበለጠ መረጃ የሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችንንን ይቀላቀሉ
🌐 🖥 🎸 @RWethiopia

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤352🙏8🕊7😭5👏3🤔2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA🇪🇹
በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መመረቁን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።
በተመሳሳይም በአመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር እንደተጀመረ ገልጸዋል።
" ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል " ብለዋል።
" ከሁሉም በላይ ፕሮጄክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ አይደለም። ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረታችን የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል። ለኃይል ማመንጫ እና የክሪፕቶ-ማይኒንግ ሥራዎቻችን አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ያቀርብልናል " ሲሉም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ዛሬ በሶማሌ ክልል የጀመርናቸው ከተያያዥ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ጋር በአጠቃላይ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች በተገቢ ክትትል እስከ መጠናቀቂያቸው ይደርሳሉ። የጀመርነውን ለመጨረስ ሁልጊዜም በጽናት እንደሠራነው ሁሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ይደርሳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia

4❤2.55K👏457🙏90🤔70😡57🕊33😢23🥰19😭17😱6💔3
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መመረቁን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳውቀዋል። በተመሳሳይም በአመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር እንደተጀመረ ገልጸዋል። " ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም…
" ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ የሚጠቀሙ ማንኛውም ትልልቅ መኪኖች (ትራክ) ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት የተከለከለ ነው " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃቱ ወቅት ባሰሙት ዘለግ ያለ ንግግር ፕሮጀክቱ ለሃይል ማመንጫ እና ለክሪፕቶ ማይኒንግ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ጭምር የሚያቀርብ መሆኑን ጠቁመዋል።
" ቢበዛ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ 2 ሺ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ከተማ እና ወደ ክልል የሚሄዱ ባሶች አሁን ከሚጠቀሙት ነዳጅ ወደ ጋዝ እንቀይራለን " ሲሉ የተደመጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም የትራንስፖርት ወጪ በ 50 በመቶ የሚቀንስ መሆኑን አስረድተዋል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምርቃቱ ወቅት ባሰሙት ንግግር ምን አሉ?
" በእዚህ አመት ቢበዛ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ 2 ሺህ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ከተማ እና ወደ ክልል የሚሄዱ ባሶች አሁን ከሚጠቀሙት ነዳጅ ወደ ጋዝ እንቀይራለን።
እነዚህ 2 ሺህ መኪኖች ሲቀየሩ የትራንስፖርት ዋጋ ቢበዛ ወይም ቢያንስ አሁን ካለው በ 50 በመቶ በሚቀጥለው አመት እንቀንሳለን።
በከተሞቻችን ያለው ዋናው ችግር የ ሊቪንግ ኮስት ችግር ነው የሊቪንግ ኮስት አንደኛው ምክንያት ቤት ነው።
ከ1.5 ሚሊየን በላይ ቤቶችን እንገነባለን ያልነው የዜጎቻችን የሊቪንግ ኮስት ጫና የሚያስከትለውን አንዱን ችግር እንቀርፋለን ለማለት ነው።
ሁለተኛው ትራንስፖርት ነው በከተማ ትራንስፖርት 50 በመቶ አሁን ያለውን ኮስት ቀነስን ማለት በአነስተኛ ገቢ ወጥተው የሚገቡ ሰርተው የሚውሉ ዜጎች በእጅጉ ኑሯቸውን ለማገዝ የሚጠቅም ነው።
ሦስተኛ ኢነርጂ ስናመርት ለክሪፕቶ ብቻ ሳይሆን ለብርሃንም ጭምር ስለሆነ ጋዝ ምግባችን፣ ጋዝ ትራንስፖርታችን፣ ጋዝ ለኢነርጂ ማምረቻ የሚውል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ነው።
ትላልቅ መኪና ወይም ትራክ ወደ ኢትዮጵያ ስታስገቡ የነበራቹ ዜጎች ከዛሬ ጀምሮ ልክ ለትናንሽ መኪኖች ከኤሌክትሪክ መኪና ውጪ ማስገበት ታግዶ እንደቆየው ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ የሚጠቀሙ ማንኛውም ትራክ ወደ ኢትዮጵያ መስገባት የተከለከለ ነው።
በአንጻሩ ማንኛውም የግል ባለሃብት ጋዝ የሚጠቀሙ ትራኮች የሚያስገባ ከሆነ ከቀረጥ ነጻን(Duty free) ጨምሮ አስተማማኝ ድጋፍ የሚደረግላቹ ሲሆን እንደሃገር እያወጣን ያለነውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ ፣ የሎጅስቲክስ ኮስት ለመቀነስ፣ ትራንስፖርት ለማሳለጥ የግሉ ሴክተር ከእዚህ ቀን በኋላ በጋዝ የሚጠቀሙ ትራኮች በማስገባት የሃገሩን የኢኮኖሚ እድገት እንዲያፋጥን ከአደራ ጭምር ላሳስብ እወዳለሁ " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤4.16K😡521👏335🤔130🙏95🕊61😭60🥰25😱23💔16😢15
#MesertHadush
በሴቶች ጥቃት መከላከል ዙሪያ የሚሰራው ' ሕውየት ' ተባለ የምግባረ ሰናይ ድርጅት መስራች የብሬመን ሶሊዳሪቲ አዋርድ ተሸላሚ ሆናለች።
የጀርመኗ ብሬመን ከተማ ሴኔት 19ኛውን የብሬመን ሶሊዳሪቲ ሽልማት የ ' ሕውየት ' ምግባረ ሰናይ ድርጅት መስራች ለሆነችው ኢትዮጵያዊቷ መምህርት እና አርቲስት መሰረት ሓድሽ አበርክቷል።
የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ መቐለ ማእከሉን በማድረግ የተቋቋመው ' ሕውየት ' በጦርነቱ የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ሴቶች የሚያገገሙበት ማእከል ከፍቶ በማገልገል ላይ ይገኛል።
የድርጅቱ መስራችና መሪ መምህርትና አርቲስት መሰረት ሓድሽ በጦርነቱ ወቅት ፃታዊ ጥቃት የደረሳቸው ሴቶች የሚያገግሙበትን ማእከል በመክፈቷ ለእውቅና መብቃቷን የሽልማቱ አዘጋጆች ገልፀዋል።
የብሬመን ሶሊዳሪቲ አዋርድ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሆኖ ኢ-ፍትሃዊነት ፣ ዘረኝነት ፣ የባእዳዊ አገዛዝ ቁስሎች በመታገልና በማከም ዙሪያ የሚታይ የሚጨበጥ ውጤት ላስመዘገቡት ተቋማትና ግለሰቦች የሚሰጥ እውቅና ነው።
በ1988 እ.አ.አ የደቡብ አፍሪካ የጥቁሮች መብት ተማጓች ኔልሰን ማንዴላና ባለቤታቸው ዊኒ ማንዴላን የብሬመን ሶሊዳሪቲ አዋርድ ተሸላሚ ነበሩ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

❤902👏80🙏36🕊14😭6😡5🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#MesertHadush በሴቶች ጥቃት መከላከል ዙሪያ የሚሰራው ' ሕውየት ' ተባለ የምግባረ ሰናይ ድርጅት መስራች የብሬመን ሶሊዳሪቲ አዋርድ ተሸላሚ ሆናለች። የጀርመኗ ብሬመን ከተማ ሴኔት 19ኛውን የብሬመን ሶሊዳሪቲ ሽልማት የ ' ሕውየት ' ምግባረ ሰናይ ድርጅት መስራች ለሆነችው ኢትዮጵያዊቷ መምህርት እና አርቲስት መሰረት ሓድሽ አበርክቷል። የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ መቐለ ማእከሉን በማድረግ የተቋቋመው…
#MesertHadush
በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ስለ19ኛው የብሬመን ሶልደሪቲ አዋርድ አሸናፊ መምህርትና አርቲስት መሰረት ሓዱሽ ምን አለ ?
- 19ኛው የብሬመን ሶልደሪቲ አዋርድ ለኢትዮጵያዊቷ🇪🇹 የመብት ተሟጋች እና አርቲትስ መሰረት ሓዱሽ ተበርክቷል።
- ይህ እውቅና በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውና በህይወት የተረፉ ሴቶችንና ልጃገረዶችን ለመደገፍ ላደረገችው ጥረት የተበረከተ ነው።
- መሰረት በድርጅቷ አማካኝነት መጠለያ በማዘጋጀት፣ ስነ ልቦናዊ እንክብካቤ በማድረግ ፣ ኢኮኖሚያዊ አቅም በመገንባት እንዲሁም በሴቶች ላይ የተፈፀሙ ግፎችን በመመዝገብ ለፍትህ ተሟግታለች።
- እኤአ በ2020 በሰሜን ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ጦርነት ወቅት ጾታዊ ጥቃት እንደ ስልታዊ የጦር መሳሪያ ሆኖ ነበር።
መሰረት ሓዱሽ ፥ " ይህ ሽልማት የተረፉትን (ሴቶች) ድምጽ የሚያጎላና በዓለም አቀፍ ደረጃ መሰል ወንጀሎችን ለማስወገድ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያጠናክር ነው " ብላለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ስለ19ኛው የብሬመን ሶልደሪቲ አዋርድ አሸናፊ መምህርትና አርቲስት መሰረት ሓዱሽ ምን አለ ?
- 19ኛው የብሬመን ሶልደሪቲ አዋርድ ለኢትዮጵያዊቷ
- ይህ እውቅና በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውና በህይወት የተረፉ ሴቶችንና ልጃገረዶችን ለመደገፍ ላደረገችው ጥረት የተበረከተ ነው።
- መሰረት በድርጅቷ አማካኝነት መጠለያ በማዘጋጀት፣ ስነ ልቦናዊ እንክብካቤ በማድረግ ፣ ኢኮኖሚያዊ አቅም በመገንባት እንዲሁም በሴቶች ላይ የተፈፀሙ ግፎችን በመመዝገብ ለፍትህ ተሟግታለች።
- እኤአ በ2020 በሰሜን ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ጦርነት ወቅት ጾታዊ ጥቃት እንደ ስልታዊ የጦር መሳሪያ ሆኖ ነበር።
መሰረት ሓዱሽ ፥ " ይህ ሽልማት የተረፉትን (ሴቶች) ድምጽ የሚያጎላና በዓለም አቀፍ ደረጃ መሰል ወንጀሎችን ለማስወገድ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያጠናክር ነው " ብላለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤727👏96🙏55🤔13🕊6😭3😡3😢2
#Amahra
“ መመዝገብ የነበረባቸው ተማሪዎች 7.4 ሚሊዮን ናቸው እስካሁን የተመዘገቡት ግን 3.4 ሚሊዮን ብቻ ናቸው ” - መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ ያለውን የትምህርት ስብራት በተመለከተ ዛሬ በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያም በመድረኩ ተገኝቷል፡፡
በወቅቱ ሰነድ ያቀረቡት የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፣ በአሁኑ ወቅት “ 3.6 ሚሊዮን ተማሪዎች አልተመዘገቡም፡፡ 2045 ት/ቤቶች በክልሉ ውስጥ ዝግ ሆናዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
“ ዘጠኝ ወረዳዎች ምንም አይነት የትምህርት ሥራ አልተጀመባቸውም፡፡ 1044 ትምህርት ቤቶች ከተባለለት ዓላማ ውጭ እየዋሉ ነው ” ብለዋል።
መንገሻ (ዶ/ር)፣ “አሁንም መምህራን እየታገቱ ነው፡፡ በቅርቡ ምሥራቅ ጎጃም ወደ ት/ቤት ሲሄዱ ታግተዋል፣ ሰሜን ጎጃም ታግተዋል ባለፈው ሳምንት ታግተዋል” ሲሉም ተደምጠዋል።
“መምህራን ባለፈው አመትም ተገድለዋል፤ ታግተው ገንዘብ እንዲከፍሉ ተደርገዋል፡፡ አሁንም አልቆመም፡፡ እንዲህ አይነት የሁሉንም ትግል የሚጠይቅ ስብራት ገጥሞናል” ነው ያሉት።
“በምስራቅ ጎጃም 842፣ ምዕራብ ጎጃም 514፣ ሰሜን ጎጃም 362፣ አዊ 246፣ 221 ሰሜን ጎንደር፣ ማዕከላዊ ጎንደር 141፣ ሰሜን ወሎ 115፣ ዋግኀምራ 59፣ ምዕራብ ጎንደር 50 ትምህት ቤቶች ተዘግተዋል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ዓመት፣ “4952 ትምህርት ቤቶች ዝግ ነበሩ፡፡ ከ50 በመቶ በታች ያሉ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ነው የከረሙት” ሲሉም አስታውሰዋል፡፡
“የሰሜኑን ጦርነት ጨምሮ አጠቃላይ 6154 ትምህርት ቤቶች ፈራርሰዋል፡፡ ከ6154 ት/ቤቶች ውስጥ የ1984ቱ አሁን በክልላችን ባለው ውስጣዊ ግጭት የመጣ ችግር ነው” ነው ያሉት፡፡
እንዲሁም፣ “እስከ መስከረም 20/2018 ዓ/ም ድረስ ባለን መረጃ 3.4 ሚሊዮን ህጻናት (ከታቀደው ውስጥ 46.32 በመቶ የሚሆኑት) ናቸው አሁን በትምህርት ገበታ ላይ ያሉት፡፡ መመዝገብ የነበረበት ከ7.4 ሚሊዮን ነው” ብለዋል፡፡
“ከ11,069 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 8624 ትምህርት ቤቶች ናቸው ምዝገባ የጀመሩት፡፡ 78 በመቶ ተማሪዎች መዝግበዋል፡፡ ከዚያ ውጭ ያሉት ግን አሁንም ተዘግተው ነው ያሉት፡፡ የትምህርት ማገገም በማይችልበት ሁኔታ ነው ያለው” ሲሉም ተናግረዋል።
“የትውልድ ግንባታ ስለሆነ በዚህ ላይ እጁን ያነሳ እጁ ይቆረጥ ብለን አውግዘን መታገል አለብን” በማለትም ታጣቂ ኃይሎችን ተጠያቂ አድርገዋል።
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ በመሆናቸው ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ባደረጉት ንግግር ደግሞ፣ እንደ ሀገር 74 በመቶ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ መምጣታቸውን ገልጸው፣ “አሁንም ምዝገባ እየተላሄደባቸው ያሉ ያሉ ቦታዎች አሉ” ብለዋል፡፡
በአማራ ክልል ወደ 47 በመቶ በላይ ታመሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ትምህር ገበታ የመጡት ያሉት ሚኒስትር ዴዔታዋ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የተገኙ የተለያዩ አካላትም በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

❤459😭355😢30🕊19💔18😡17👏14🤔14😱6🙏5