" ጥንታዊ ቤተክርስቲያን የእሳት ቃጠሎ ደርሶበት ለጊዜው አገልግሎት መስጠት እንዳይችል ሆኗል " - የወላይታ ሀገረስብከት ሥራ አስኪያጅ
በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ የሚገኘው በ1944 ዓ/ም የተመሠረተ ጥንታዊውና ታሪካዊው የሙሬ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በድንገተኛ የእሳት አደጋ ንዋዬ ቅድሳቱ ሙሉ በሙሉ መቃጠላቸዉንና ቤተክርስቲያኑም አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ሁኔታ በቃጠሎዉ መጎዳቱን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የወላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መላከሰላም ቀሲስ ቦክቻ እንጋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
" በአደጋው ምክንያት የቃል ኪዳኑ ታቦት ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ቤተልሔም እንዲገባ ተደርጓል " ሲሉ የገለፁት የሀገረስብከቱ ሥራ አስኪያጅ " ቤተክርስቲያኑ አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ሁኔታ ላይ ነው " ሲሉ አስታውቀዋል።
" አከባቢው መብራት ያልገባበት በመሆኑ የእሳቱ መነሻ በአጋጣሚ ለአገልግሎት ተለኩሶ የተረሳ ሻማ ይሆናል " ያሉት መላከሰላም ቀሲስ ቦክቻ እንጋ " በመላው ዓለም የሚገኙ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች የተቃጠለውን ቤተክርስቲያን በመሥራት የወደመውን ንዋያተ ቅድሳት በሟሟላት ያዘኑትን ምዕመናን እንዲያፅናኑ ጥሪ አቅርባለሁ " ብለዋል።
የቤተክርስቲያን አካውንት 1000720807045 እንደሆነም ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia

😭1.66K❤490💔120👏42😢29🙏29🕊26🤔21😡21🥰12
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት !
- የተመረቀው የመጀመሪያ ዙር በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችል ነው።
- የተጀመረው ሁለተኛ ዙር በአመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረው ነው።
- 1000 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው።
#PMOEthiopia

1❤1.13K👏114🙏94🤔46😡27🕊22💔14😭14🥰13😢10
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እሳቸው ቢያልፉም ብርሃናቸው ህያው ነው " - የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት
የአርቲስት ፍሬህይዎት ባህሩ የዓይን ብሌን በመለገሱ ሁለት ብርሃናቸውን ያጡ ሰዎችን ብርሃን ይመልሳል።
የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ፤ አርቲስት ፍሬህይወት ባህሩ በህይወት ሳሉ በገቡት ቃል መሰረይ የዓይን ብሌናቸውን በወንድማቸው ድንበሩ ባህሩ እና ቤተሰቦቻቸው መልካም ፍቃድ መውሰዱን ገልጿል።
" የተነሳው የአርቲስቷ የዓይን ብሌን ለሁለት ሰዎች ብርሃንን ይሰጣል " ብሏል።
" እሳቸው ቢያልፉም ብርሃናቸው ህያው ነው። አርቲስቷ በዓይናቸው ሶስት ጊዜ ለማየት በማሰብ የገቡት ቃል ተፈፃሚ ሆኗል " ሲል ገልጿል።
በአርቲስት ፍሬህይዎት ባህሩ በህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን ተመኝቷል።

❤1.57K🙏196😭74🕊64👏28🥰13😱6😡6🤔3😢2
✨🎁 ኢሬቻ የሞባይል ጥቅል!!
እስከ 51% ቅናሽ የተደረገባቸውን ልዩ ጥቅሎች በ*999#፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም አርዲ ቻትቦት ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ ያበርክቱ!
🔗 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ሲገዙ ተጨማሪ 20% ስጦታ ያገኛሉ!
🗓 እስከ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም
መልካም የኢሬቻ በዓል!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

2❤189😡125😭7💔5😢3🕊3🥰2
የትምህርት ማሻሻያ ያቀረቡ እና የሶስት እርከን ጭማሪ እንዲያገኙ የተደረጉ መምህራን የደሞዝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ተፈቀደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በትምህርት ማሻሻያ የትይዩ ሽግግር ጥያቄ ያቀረቡ መምህራን በሚመለከት መመሪያ አስተላልፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ደብዳቤ በአገር አቀፍ ደረጃ ከነባሩ የስራ ምዘና ስርዓት ወደ ነጥብ የስራ ምዘና በተደረገው የመምህራን ሽግግር መሰረት ከሐምሌ 01/2011 ጀምሮ፣ የከፍተኛ መምህር ሁለትና ሶስት ደረጃ በመታጠፉ ምክንያት የሶስት እርከን ጭማሪ እንዲያገኙ የተደረጉት መምህራን የትምህርት ማሻሻያ ሲያቀርቡ በትይዩ ወደ ሚቀጥለው ሳይክል ውስጥ ቢገቡም ምንም የደመወዝ ማስተካከያ አለመደረጉ ቅሬታ ማስነሳቱን ይገልጻል።
ቅሬታው የተነሳው የሥራ ክብደት ምዘና ሥራ ላይ ከመዋሉ ቀደም ብሎ የመምህራን ደረጃ እድገት መሰላል ዘጠኝ እንደነበር እና ከስራ ክብደት ምዘና በኋላ ግን ለመምህራን ተጠቃሚነት ሲባል ደረጃው ሰባት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የትምህርት ማሻሻያ እና ትይዩ የደረጃ እድገት ችግር በመምህራን ላይ በመፈጠሩ ነው።
ይህንንም ቅሬታ በማንሳት በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በኩል ለቀረበው የማብራሪያ ጥያቄ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነሐሴ 30/2017 ዓም ትምህርታቸውን ላሻሻሉ መምህራን የትይዩ ሽግግር አሰራርን በተመለከተ ያስተላለፈውን ሰርኩላር የክልልና የከተማ አስተዳደሮችም እንዲደርሳቸው መደረጉን ደብዳቤው ያትታል።
በተላለፈው ውሳኔ መሰረት እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህ ሰርኩላር የሚመለከታቸው መምህራን በሙሉ:-
1ኛ ይህ ሰርኩላር የሚመለከታቸው መምህራን በአገር አቀፍ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን መሰረት ከሐምሌ 1/2011 ጀምሮ በተደረገው ሽግግር ከጥር 2012 እስከ ጥር 2014/2017 ድረስ ቀጥታ ወደ ከፍተኛ መምህር ሁለትና ሶስት ደረጃ ለማደግ በሂደት ላይ እያሉ ሁለት ደረጃው የታጠፈባቸውና ወደ ጎን ሶስት እርከን ክፍያ ለተፈጸመላቸው እና ከዚህ ጥቅም በኋላ የትምህርት ማሻሻያ ላቀረቡት መምህራን ብቻ ይሆናል፡፡
2ኛ ከሐምሌ 1/2011 ጀምሮ በተደረገው ሽግግር ከጥር 2012 እስከ ጥር 2014 ድረስ የሶስት እርከን ጭማሪ ያገኙ መምህራን በ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን አሻሽለው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከተመደቡ በደረጃ 17 ከፍተኛ መሪ ላይ በመሆን ከመነሻው ወደ ጎን የሶስት እርከን ክፍያ ብር ከ15,340 ሳይበልጥ ከመስከረም 1 ቀን 2018 ጀምሮ እንዲፈጸምላቸው እንዲደረግ።
3ኛ ከሐምሌ 1/2011 ጀምሮ በተደረገው ሽግግር ከጥር 2012 እስከ ጥር 2014 ድረስ የሶስት እርከን ጭማሪ ያገኙ መምህራን ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት በማሻሻል የደረጃ ለውጥ ያመጡት የከፍተኛ መሪ መምህራን ወደ ደረጃ 16 በትይዩ ስለሚሻገሩ በመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ተመድበው ሲሰሩ ከመነሻው ወደ ጎን የሶስት እርከን ጭማሪ ሳያልፍ ከመስከረም 1 ቀን 2018 ጀምሮ ብር 13,998 እንዲፈቀድላቸው ተወስኗል።
ከላይ የተዘረዘሩትን የመምህራን የትምህርት ማሻሻያ ደመወዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የስራ መደቦች ምዘና፣ ደረጃዎች ምደባና የደመወዝ ስኬል መሰረት እንዲፈጸም የተወሰነ ስለመሆኑ ቢሮው ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ውሳኔው ለሚመለከታቸው መምህራን ብቻ በጥንቃቄ እየተረጋገጠ እንዲፈጸም ያሳሰበ ሲሆን ከተጠቀሰው ውጪ ለማይመለከታቸው ጥቅም መስጠት ተጠያቂነት እንደሚያስከትል መግለጹን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደብዳቤው ላይ ተመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤886🙏41😡16😢13😭13🕊6🤔5
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ይፋ ሆነ። የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከመስከረም 2018 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን አዲሱን የመንግሥት ሰራተኞች የደሞዝ ስኬል ይፋ አድርጓል። @tikvahethiopia
#ደመወዝ
" ማንኛውንም ጫና ተቋቁማችሁ ለሰራተኛው ከዚህ ወር ጀምሮ አዲሱን የመግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አለባቹ " - ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
የፊዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊዎች እና ለሚመለከታቸው አካላት በአዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪና የአበል ክፍያ በሚመለከት መመሪያ አስተላልፈዋል።
በሰጡት መመሪያ መሰረትም ከመስከረም ወር ጀምሮ አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።
ኮሚሽነሩ " የደሞዝና የአበል ማስተካከያ የተደረገው መንግስት የመክፈል አቅም ኖሮት ሳይሆን የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ስለሚያውቅ ትልቅ ዋጋ ተከፍሎ ነው " ብለዋል።
" ይህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ " ደሞዙ ከመስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይከፈላል ክልሎች ምንአልባት አንዳንድ አካባቢዎች በዚህ ወር ካልደረሰ ያለውን ማንኛውንም ጫና ተቋቁማችሁ ለሰራተኛው ከዚህ ወር ጀምሮ አዲሱን የመግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አለባቹ " ሲሉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

50❤2.77K🙏362👏188🤔63😡53😭51🕊39🥰30😢22💔12😱9
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደመወዝ " ማንኛውንም ጫና ተቋቁማችሁ ለሰራተኛው ከዚህ ወር ጀምሮ አዲሱን የመግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አለባቹ " - ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የፊዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊዎች እና ለሚመለከታቸው አካላት በአዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪና የአበል ክፍያ በሚመለከት መመሪያ አስተላልፈዋል።…
" ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከመስከረም ወር ደመወዙ ጋር አብሮ ባይከፈል እንኳን የመስከረም ወሯ ጭማሪ መጠን ጥቅምት ወር ውስጥ ይከፈላል ! " - መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ምን አሉ ?
" ከሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ የተደረሰው ከመስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የተስተካከለው ጭማር በመስከረም ወር መጨረሻ ከሚከፈለው የመስከረም ወር ደመወዝ ጋር እንዲከፈል መንግስት አመራር የሰጠ መሆኑን ነው።
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከመስከረም ወር ደመወዙ ጋር አብሮ ባይከፈል እንኳን የመስከረም ወሯ ጭማሪ መጠን በጥቅምት ወር ውስጥ ይከፈላል።
ማንኛውም ዓይነት ተቀናናሽ ባለመብቱ በማመልከቻ ፈርሞ ካልፈቀደ በስተቀር ከወርሃዊ ደመወዙ ላይ መቀነስ የተከለከለ መሆኑን በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በግልጽ ተደንግጓል። "

❤1.26K😡160👏106🙏60😭56🤔45🕊22😱14🥰12😢11💔11
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከመስከረም ወር ደመወዙ ጋር አብሮ ባይከፈል እንኳን የመስከረም ወሯ ጭማሪ መጠን ጥቅምት ወር ውስጥ ይከፈላል ! " - መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ምን አሉ ? " ከሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ የተደረሰው ከመስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የተስተካከለው ጭማር በመስከረም ወር መጨረሻ ከሚከፈለው…
#ደመወዝ
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የደመወዝ ማሻሻያውን በሚመለከት መንግሥት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች መሠረት በማድረግ ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል።
የመንግስት መሥሪያ ቤቶች የደመወዝ ስኬል ማሻሻያ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1110/2018 ምን ይላል ?
➡️ የደመወዝ ማሻሻያ ተጠቃሚ የሚሆኑ የመንግስት ሠራተኞች ባገኙት የደመወዝ ማሻሻያ ምክንያት የመደበኛ የደመወዝ ጭማሪ ኡደታቸው አይለወጥም፡፡
➡️ ለደረጃ እድገት የአንድ ዓመት መቆያ ጊዜ ማሟላት አይጠበቅባቸውም፡፡
➡️ ከፍ ባለ የሥራ ደረጃ ላይ በተጠባባቂነት የተመደበ ሠራተኛ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ልዩነት የሚታሰብለት በድልድሉ በተመደበበት ደረጃ ላይ ነው፡፡
➡️ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ተሻሽሎ በሥራ ላይ በዋለው ወይም አግባብ ባለው አካል በተፈቀደ የደመወዝ ስኬል ጣሪያ ላይ የደረሰና በአዲሱ የደመወዝ ስኬል ጣሪያው የሚነሳለት ሠራተኛ በተመደበበት የሥራ ደረጃ የአዲሱን የደመወዝ ስኬል ጣሪያ ሳያልፍ ማሻሻያውን እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
➡️ ኮሚሽኑ በአንድ ተቋም ከተፈጸሙ የሠራተኞች ድልድል ወይም የደረጃ እድጉት መካከል በተለያዩ ሕግን ባልተከተሉ አሠራሮች ምክንያት ያልተቀበለው ካላ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ጭማሪው የሚሰጠው በድልድል አፈጻጸም መመሪያው መሠረት ሠራተኛው በሚያሟላበት ደረጃ ከተደለደለ በኋላ ነው፡፡
➡️ ከፍ ካለ የሥራ ደረጃ ላይ በሚታሰብ ደመወዝ ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ እየተቀነሰ የሚከፈለው ሠራተኛ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ተጠቃሚ የሚሆነው በሚያሟላበት ደረጃ ላይ ተመሥርቶ ይሆናል፡፡
➡️ በሙከራ ቅጥር ላይ የሚገኝ ሠራተኛ የዚህ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
ዝርዝር የመመሪያውን አፈጻጸም ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ።

❤1.5K🙏84🕊35😡35🥰25😭20👏17💔15😢9🤔8😱6