ፎቶ፦ የ2018 ዓ/ም የኢሬቻ #ሆራ_ፊንፊኔ በዓል አከባበር #Irreechaa2018
#AyyaanaGaari ! #HappyIrreechaa !
Photo Credit - Social Media
@tikvahethiopia
#AyyaanaGaari ! #HappyIrreechaa !
Photo Credit - Social Media
@tikvahethiopia
3😡2.71K❤1.58K😭151🕊83💔71🙏64🥰50🤔48👏39😢23😱22
" እነሱ ሸሂድ ሆነዋል አላህ ጀነተል ፍርዶስ ይወፍቃቸው " - ጠቅላይ ምክር ቤቱ
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፤ " በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ መስከረም 23፣2018 ዓ.ል በመስጂድ ኑር በኢሻ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ የታጠቁ ኃይሎች በመግባት ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ ፦
1. የመስጂድ ዋና ኢማምና የወረዳው መጅሊስ ም/ሰብሳቢ
2. የመስጂድ አመራሮች
3. የመስጂድ ኻዲሞችን አሰቃቂ እና አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ መግደላቸውን የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አረጋግጦልናል " አለ።
" እነሱም ሸሂድ ሆነዋል አላህ ጀነተል ፍርዶስ ይወፍቃቸው " ሲል ገልጿል።
" ጠቅላይ ምክርቤቱ የእምነት ተቋማት የተከበሩ ቦታዎች በመሆናቸው ሊጠበቁ እንጅ እንዲህ አይነት አፀያፊ ተግባር የሚፈፀምባቸው መሆን የለባቸውምና ድርጊቱን በፅኑ እናወግዛለን " ብሏል።
" መላው የሃይማኖት ተቋማትም በእምነት ቦታዎች የሚደረጉ ትንኮሳዎች እና በእምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ መሰል የጅምላ ግድያ
ሊያወግዙና ሊያስቆሙ ይገባል " ሲል አሳስቧል።
የሃይማኖት ተቋማት እና መሪዎች ድርጊቱ አብሮ የመኖርን እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ እንዲያወግዙና እንዲቃወሙ የሚመለከታቸው አካላትም ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት " በአማራ ክልል ሙስሊሞች በእምነት ተቋሞቻቸው በመግባት የሀይማኖት አባቶችንና ምዕመናኖቻችን የመግደል አባዜ ቀጥሏል " ብሏል።
" በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳዎች፣ ጥቃቶችና ግድያዎች ለማስቆም በከፍተኛ ሆደሰፊነት ጉዳዩን ለመፍታት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ቢጥርም ነገሩ እያደረ ከመባባስና መልኩን እየቀያየረ ከመምጣት አልተወገደም " ሲል ገልጿል።
" በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ በታላቁ ኑር መስጅድ ምሽት የኢሻ ሶላት ስግደትን ለማከነወን በመስጅዱ በነበሩ የመስጅዱን ኢማም እና የመካነ ሰላም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆኑትን ሼህ ጀማል ከማል እና ሌሎች የመስጅድ እና የመጀሊስ አመራሮች በታጠቁ ሀይሎች ያለምንም ርህራሄ እና እዝነት በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል " ብሏል።
" ይህም ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች እምነት ተከታይ ወገኖች ጋር ሆን ተብሎ ለማጋጨት እና ሀገሪቱን የጦር አውድማ ለማድረግ ታስቦ የተፈጸመ ድርጊት መሆኑ አያጠራጥርም " ሲል ገልጿል።
" ይህን ፀያፍ ድርጊት ሁሉም ቤተ እምነቶች ፣ የቤተ እምነት አመራሮች እና ምእመናኖች ሊኮነነት ሊያወግዙት የሚገባ እና የኢትዮጵያውያንን ብዝሀነት የሚያራክስ ድርጊት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።
የሚመለከታቸው አካላት ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦች ወይም ቡድኖችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተጠያቂ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አቶ ኡስማን ሁሴን ዛሬ ከሰዓት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " ትላንት ማታ ላይ ታጣቂዎች መጥተው መስጅድ ውስጥ የነበሩትን የመስጂዱን ኢማም፣ የመጅሊስ አመራርና ወጣት፣ አራት ሰዎችን ገድለዋል " ብለዋል፡፡
" መስጂድ ውስጥ ነው የገደሏቸው። ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ወጥቶ ቀብሯቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" በጣም ዘግናኝ የሆነ ግድያ ነው " ያሉት አቶ ኡስማን፣ " ጣፊ የሚባለው ልጅ ወዲያው አልሞተም ነበር፣ ወደ ሀኪም ቤት እንዲሄድ አልፈለጉምና ደሙ ፈሶ ነው እዛው የሞተው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ሲገቡባቸው ማይክሮፎን ከፍተው ' ኧረ ድረሱልን እያሉ ሲጮሁ ነበር፣ እዛው እየጮሁ እያሉ ነው በጥይት የገደሏቸው " ብለዋል።
አንድ የከተማው ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ " ትላንታ ማታ ሁለት ሰዓት ከሦላት በኋላ መስጅድ ውስጥ ገብተው የወረዳው እስልምና ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንትና ኢማምና ሌሎችን ነው የገደሉት " ብለዋል፡፡
" ስርዓተ ቀብራቸውን ፈጽመናል። የቆሰሉ ሆስፒታል የገቡ ሰዎችም አሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

1😭2.09K❤1.12K😡145💔101🕊57😢52👏33🤔23🙏12🥰10
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa " የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የግምገማ ቡድኑ በሙሉ ድምፅ ወስኗል ፤ ተግባራዊነቱ የሚረጋገጠው ግን ሁለቱ ቡድኖች በሚያደርጉት የማጠቃለያ ውሳኔ ነው " - አንድ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊ ➡️ " ሌሎችም የክልልና የከተማ አስተዳደር አመራሮች በዚሁ መልክ አቅጣጫ ተቀምጦባቸዋል ! " በሲዳማ ክልል የልማትና የመልካም አስተዳደር አፈፃፀሞችን መሰረት አደርጎ እየተካሄደ…
#Hawassa
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ከስልጣናቸው ተነስተው በምትካቸው አዲስ ከንቲባ ተሹሟል።
በቅርቡ የሲዳማ ክልል ባካሄደው ክልል አቀፍ ግምገማ የከተማው ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ በተለያዩ ጉዳዮች ተገምግመው ከስልጣን እንዲነሱ ውሳኔ መተላለፉን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።
የክልሉ መንግስት ዛሬ ባወጣው መረጃ ከንቲባው ከስልጣኑ መነሳቱንና ሌሎችም የክልልና ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣናት የቦታ ሽግሽግና ምደባ መስጠቱን አስታውቋል።
በዚህም የክልል እንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተክሌ ጆንባ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።
አዲስ የተሾሙት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆንባ ከአቶ መኩሪያ መርሻዬ ስልጣኑን ተረካክበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

❤555😡47🤔37😭26👏21💔11🥰10🙏10😱4😢4🕊3
" መኪኖች መቆም እንዳይችሉ በመከልከላቸው አዛውንቶች፤ ታማሚዎች፤ ሕፃናት፤ ተማሪዎች እና ሰርቪስ ተጠቃሚዎች በጣም በጣም ተቸግረናል " - ቅሬታ አቅራቢዎች
በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ 01፣ 02፣ 03፣ ባልደራስ፣ እንግሊዝ፣ ቤልጅግ፣ ኬንያና ራሺያ ኤምባሲ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኙበት የነበረው ፌርማታ በመነሳቱ ችግር ላይ ወድቀናል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ነዋሪዎቹ ወደ መገናኛ እና አራት ኪሎ ለመሔድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኙበት ፌርማታ በኮሪደር ልማቱ በመነሳቱ ባሶችም ሆኑ ታክሲዎች ከዚህ በፊት ይቆሙበት ከነበረበት አንድ ፌርማታ አልፈው በመቆማቸው እየተቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ነዋሪዎች በዝርዝር ምን አሉ ?
" ባሶች እንዳይቆሙ ከተከለከሉ ከአንድ ወር በላይ ሆኗቸዋል፣ ከመገናኛ ስንመጣ እንግሊዝ ኤምባሲ ሳይደርስ ከባልደራስ እስከ ቀበና ጥር ድረስ መሀል ላይ ፌርማታ ነበር። በዚህ ፌርማታ የኮሪደር ልማቱ ከተሰራ በኋላ ባሶች እንዳይቆሙ ተከልክለው ነበር፣ ከዛም በኋላ በታክሲዎች ስንጠቀም ብንቆይም ከሶስት ሳምንት በፊት ጀምሮ ደግሞ ታክሲዎችም እንዳይቆሙ ተከልክለዋል " ብለዋል።
" በእንግሊዚ፣ ቤልጅግ፣ ኬንያ፣ ራሽያ እና ቀበና ጥር መካከል መቆም አይቻልም፣ በኬንያ እና በቤልጅግ ኤምባሲ መካከል በጣም የቆየ ሰፈር አለ፣ አድሱ ቤተመንግስት ከሚሰራበት ወደ ላይ ያለው አድሱ መንገድ አካባቢ በጣም በርካታ ነዋሪዎችም አለን። የባልደራስ ነዋሪዎች ወደ አራት ኪሎ ለመሔድ ቤልጅግ ኤምባሲ ጋር ነበር ትራንስፖርት የሚይዙት፣ አሁን ምንም አይነት መኪኖች እንዳይቆሙ ተከልክለዋል፣ እኛ ግን መከልከሉንም አልሰማንም፣ አሁን ታክሲ ለመያዝ አንድ ፌርማታ ለመሄድ ተገደናል " ሲሉ ተናግረዋል።
" በተለይ ቤልጅግ ኤምባሲ አካባቢ ምንም አይነት ትራንፓርት መጠቀም አልቻልንም፤ ከመገናኛ ሲመጣም ቦታው ላይ ስለሚከለክሉ አንድ ፌርማታ አልፎ ቀበና ጥር ነው የሚያውርዱን፣ በዚህም ሁሉም ሰው በጣም እየተፈተነ ነው " ብለዋል።
አክለው " መኪኖች መቆም እንዳይችሉ በመከልከላቸው አዛውንቶች፤ ታማሚዎች፤ ሕፃናት፤ ተማሪዎች እና ሰርቪስ ተጠቃሚዎች በጣም በጣም ተቸግረናል። በእለት ከእለት እንቅስቃሴያችን ላይም ጫና አሳድሮብናል " ነው ያሉት።
" በዚህ አካባቢ የሚኖረው ሰው በርካታ ነው፣ የባሶች እና የታክሲዎች ፌርማታ እንዲነሳ የተደረገውስ ምን ታስቦ ነው ? ለነዋሪዎችስ ምን መፍትሔ ተቀምጦልን ነው የተከለከለው። ስለዚህ ወደቀደመው አገልግሎት ይመለስልን " ሲሉ ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንድሰጡን የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የየካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እፀገነት አበበ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

❤1.64K😢226🙏77😡70😭51🤔38🕊30👏28💔24🥰6😱5