Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Irreechaa2018 Baga Ayyaanaa Irreechaa Nagaan Geessan ! Ayyaana Gaari ! እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! መልካም በዓል ! @tikvahethiopia
ፎቶ፦ የ2018 ዓ/ም የኢሬቻ #ሆረ_ሀርሰዴ በዓል አከባበር #Irreechaa2018

የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔና ሆረ ሀርሰዴ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ አሳውቀዋል።

Photo Credit - ኤፍ ኤም ሲ እና ኢቲቪ

@tikvahethiopia
1.43K😡989😭88💔69🕊61👏35🤔35🥰33🙏32😢13
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አበል : አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የቀን ውሎ አበል አከፋፈልን ከላይ ተያይዟል።

ምንጭ፦ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

@tikvahethiopia
1.47K🙏209🤔105😭89💔44🕊42😡41🥰32😱24😢11
#SafaricomEthiopia

3 የስኬት ዓመታት
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ የእርስዎ እምነት ጉዟችንን አቀጣጥሎታል! 🚀

በአብሮነት ወደፊት!! 💚

#SafaricomEthiopia
#Furtheraheadtogether
#3rdAnniversary
#MissionPossible
288🤔14🥰13🕊12😡8😢3😭3🙏1💔1
" ለቢል ቦርድ ማስታወቂያ መስቀያ የተዘጋጀው ብረት ጉዳት ሳያደርስ የመፍትሔ እርምጃ ቢወሰድበት ጥሩ ነው " - ነዋሪዎች

➡️ " የጉዳዩን አንገብጋቢነት በመግለፅ በተደጋጋሚ ለባለድርሻ አካላትና አመራሮች ብናሳውቅም የመፍትሔ እርምጃ አልተወሰደም !! " - የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተባበሪያ


የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ከቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ' ሱሙዳ ' አጠገብ የሚገኘው ግዙፍ የመንግስት ቢል ቦርድ ማስታወቂያ የሚሰቀልበት ብረት ከማርጀቱ የተነሳ በዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ላይ በመደገፉ በሰውና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ፈጣን የመፍትሔ እርምጃ እንዲወሰድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት አሳስበዋል።

" የማስታወቂያ መስቀያ ብረቱ ከ20 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል " ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ " በአገልግሎት ብዛት አርጅቶ እየወደደቀ ነው። መብራት ሃይልም ሆነ የከተማ አስተዳደሩ በአደባባይ ለተከሰተ ችግር መፍትሔ ሳይሰጡ መቆየታቸው ተገቢነት የለውም " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሲዳማ ክልላዊ ማስተባበሪያ ባገኘው መረጃ ፤ ቸግሩ አሳሳቢና በሰውና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል በመግለፅ የጉዳዩን አሳሳቢነት ለክልሉና ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ቢያሳውቅም መፍትሔ አልተሰጠውም።

" የማስታወቂያ መስቀያ ብረቱ ግዙፍና ባለቤትነቱም የመንግስት በመሆኑ መብራት ሃይል ለማስነሳት ኃላፊነት አይወስድም " ያለዉ ማስተባባሪያው " ያለንን የአሰራር ሂደት ተከትለን በተደጋጋሚ ብናመለክትም መፍትሔ አልተበጀለትም " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን  መምሪያን ኃላፊን በስልክ በማናገር በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማኘት ቢሞክርም ለጊዜዉ አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
722🙏86😭30🕊17🤔15😱11🥰2😢2
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2018 ዓ/ም የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ ተደረገ። ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከመስከረም 20 - 25/2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን አሳውቋል። አመልካቾች የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት…
#MoE #NGAT

የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን መስከረም 26/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ሰርኩላር፥ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተናው ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይገልጻል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከሚኒስቴሩ አረጋግጧል።

Via @tikvahuniversity
836🙏95😡61🤔56🕊27😱22🥰12😢3💔2👏1😭1
🎁 ይቀበሉ፤ 15% ተጨማሪ ስጦታ ይውሰዱ!!

ከውጭ ሀገራት በአጋሮቻችን
Ethio remit        EZECALL
Prepaynation    ding
reloady              Omnivas
Boss

በኩል ከ200 ብር ጀምሮ የተላከልዎን የሞባይል አየርሰዓት ወይም ጥቅል ሲቀበሉ:-

💁‍♂️ ለ15 ቀናት የሚያገለግል የ15% ተጨማሪ ስጦታ እናበረክትልዎታለን፡፡

ደንብና ሁኔታዎች 👉 https://bit.ly/4j7iOcI


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
159😢3🙏2
መቼም ስለ አዲሱ የቴክኖ ካሞን 40 ስልክ የካሜራ ብቃት ሰምታችኋል፡፡

በበተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በካሞን 40 ብቻ የተነሱ አጅግ አስገራሚ ፎቶዎችን መመልከት የሚችሉበት፣ ስልኩን በቅርበት ማየት እና መሞከር የሚችሉበት፣ የቴክኖ ምርቶችን እና በርካታ ሽልማቶች የሚያሸልሙ ጨዋታዎችን የሚጫዎቱበት እና በሙዚቃ ዝግጅት ፈታ ዘና ሚሉበት ትልቅ ኤግዝቢሽን ተዘጋጅቷል።

ይሄ ሁሉ ጥቅምት 1 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ እስከ አመሻሽ ሲ ኤም ሲ የተባበሩት አደባባይ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ለናንተ በቴክኖ ኢትዮጵያ ተዘጋጅቷል፡፡

ኑ ተዝናኑ፣ ተሸለሙ ሀገራችሁን በፎቶ ይመልከቱ ቅዳሜ ጥቅምት 1 አይቀርም!

#TecnoCamon40Series #FlashSnap #TecnoAI

@tecno_et
266😭11💔7🤔6👏4🙏2
የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት አለባቸው።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ።

የመቁረጫ ነጥብ ፦

➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216

➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204

➡️ ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165

#MoE

@tikvahethiopia
2.15K🙏272😭173💔67😱53😡51🥰42🕊39🤔25👏18😢15
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ከ16 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፣ የቆሰሉትም በርካታ ናቸው” - ነዋሪዎች

➡️ “በየእለቱ ነው ጥቃት የሚደርሰው፡፡ እንደማህበር የሚደርሰን በጣም ብዙ ነው” - ማኅበሩ


ምዕራብ ጎንደር ዞን ከጎንደር መተማ መንገድ "መቃ" በተሰኘው አካባቢ በቅርብ ርቀት ላይ በታጣቂዎች ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችና የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

ነዋሪዎቹ፣ ከቀናት በፊት ተፈጸመ ባሉት በዚሁ ጥቃት ከ16 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፣ የቆሰሉትም በርካታ ናቸው" ሲሉ ገልጸዋል።

ከነዋሪዎቹ መካከል አንዳንዶቹ የቁስለኞቹን ቁጥር ከ20 አድርሰውታል፡፡ ጥቃቱ የደረሰው “የቅማንት ታጣቂዎች” ከስድስት በላይ በሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ ባደረሱት ጥቃት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

"መቃ" አካባቢ የደረሳውን ሰሞንኛው ጥቃት ማህበራችሁ ተመልክቶት ነበር? ስንል የጠየቅናቸው የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ፣ “አዎ፡፡ የጎንደር ጉዳይ ሰሞኑን ብቻ ሳይሆን በየእለቱ ነው ጥቃቱ የሚደርሰው፡፡ እንደማህበር የሚደርሰን በጣም ብዙ ነው” ብለዋል፡፡

“ከባህርዳር ወረታ ሳይደርስ መካከል ላይ ያሉ መንገዶች፤ ከአዲስ ዘመን አልፎ ሙሉ ደቡብና ሰሜን ጎንደር በየቀኑ አሽከርካሪዎች ይገደላሉ፣ ይዘረፋሉ” ነው ያሉት፡፡

“ይሄ የእየለት ተግባር ሆኗል፡፡ ማኅበሩ አማራ ክልል ላይ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ስለገባን የአሽከርካሪዎች ውሳኔ ነው የሚሆነው፡፡ እኛ ማንንም ማናገር አንችልም፣ ሾፌሮችም ተስፋ ቆርጠዋል” ብለዋል፡፡

“የከባድ መኪና አሽርካሪዎች ብቻ አይደለም፤ የአይሱዚዎችም፣ ትናንሽ መኪናዎችም ናቸው ጥቃት የሚደርስባቸው፡፡ ችግሩ የሚፈታው አካባቢው ሰላም ሲሆን ነው” ያሉት አቶ ሰለሞን፣ በሰሞንኛው ጥቃት የሞቱትን ሰዎች በውል መግለጽ ቢያስቸግርም፣ በየእለቱ ቢያንስ ሁለት ሦስት ተሽከርካሪዎች ግን ጥቃት ይፈጸማል ብለዋል፡፡

የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

ሰሞንኛውን ጥቃት የፈጸሙት “የቅማንት ታጣቂዎች ናቸው" መባሉን ተከትሎ፤ እንደ ፓርቲ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንብር አቶ አውግቸው ማለደ፣ “በቅማንት ህዝብ ውስጥ  ያሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ በጣም በርካታ የቅማንት ታጣቂዎች አሉ፤ የማንነትና የነጻን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስልን የሚሉ፡፡ እነርሱን ጀነራለይዝ አድርጎ የቅማንት ታጣቂዎች ስም ማጠልሸት ልክ አይሆንም” ብለዋል፡፡

“የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ በተሳሳተ መንገድ የሚረዱ፣ የራሳቸውን ጥቅም ማሳካት የሚፈልጉ አካላት አሉ፣ ከግራ ከቀኝ” ብለው፣ ጥቃቱን የሚያደርሱት እነርሱ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

“ዘራፊ ኃይሎች ናቸው፤ መኪናም ግለሰብም ያግታሉ፡፡ እነዚህ አካላት ግን ከአማራውም ከቅማንቱም ያሉ ናቸው፡፡ ሽርክናም አላቸው፡፡ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠሩ ሹፌሮችን መንገድ ላይ እያስወረዱ እያገቱ ወደ አማራው ቀበሌ፣ ወደ ቅማንቱ ቀበሌ ያስገባሉ” ነው ያሉት፡፡

“በአካባቢው እየተፈጠረ ያለው ጥቃት አሳሳቢ ነው፤ የሁላችንም ትግል ያስፈልጋል። መንግስት ልዩ ክትትል ማደረግ ይጠበቅበታል፤ ይህንን ድርጊት እየፈጸሙ ያሉ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰድ አለበት” ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
780😭356💔32😡29😢22🕊22🙏12🤔7😱5👏3
2025/10/25 16:19:15
Back to Top
HTML Embed Code: