Telegram Web Link
" ነባሩ ታርጋ በአዲስ በሚቀየርበት ወቅት የሰሌዳ ማስቀየር ስራው የሚጠይቀውን ሁሉንም ወጪ የመኪናው ባለንብረት ይሸፍናል " - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ነባሩን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር በአዲስ ለመተካት የሚያስችል አዲስ የተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሰሌዳ አይነቶችና ምልክቶች መወሰኛና የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 1050/2017 ማውጣቱ ይታወቃል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መመሪያውን አዘጋጅቶ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በ2018 ዓም ሙሉ በሙሉ ተሽከርካሪዎችን በአዲስ ታርጋ የመቀየር ስራ እንደሚሰራ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በአገልግሎት ላይ ያለውን ነባሩን የተሽከርካሪ መለያ ስሌዳ ቁጥር በአዲስ ለመተካት ካስፈለገበት ምክንያቶች ውስጥ ቀደም ሲል የነበረው የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ስሌዳ አመራረትና አሰረጫጨት የአሰራር ክፍተት እና የሃብት ብክነት ሲስተዋልበት የቆየ በመሆኑ ያንን ለመቅረፍ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ነው ተብሏል።

አሽከርካሪዎች እየተጠቀሙበት የሚገኘው በስራ ላይ ያለው ታርጋ ከ1994 ዓም በኋላ ምንም አይነት ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ ነው።

አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ፥ " ነባሩ ታርጋ በአዲስ በሚቀየርበት ወቅት የሰሌዳ ማስቀየር ስራው የሚጠይቀውን ሁሉንም ወጪ የመኪናው ባለንብረት ይሸፍናል " ብለዋል።

" ከእዚህ ቀደም የነበረው ታርጋ 9 ሚሊየን መኪኖችን ብቻ መዝግቦ የሚያበቃ ውስን ታርጋ ነበር እስካሁን ባለው መረጃም 1.6 ሚሊየን የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ተመዝግበዋል የአሁኑ ታርጋ ግን 121 ሚሊየን ታርጋዎችን መመዝገብ ያስችልናል " ሲሉም አክለዋል።

ሁለት ሚሊየን የሚሆን የተሽከርካሪ ታርጋ ለማሳተም በእቅድ ተይዞ የመጀመሪያ 50 ሺ የተታተመ ታርጋ ወደ ሃገር ስለመግባቱ የተናገሩት ሚኒስትሩ " ታርጋውን አድሎ ስራ ላይ ለማዋል የዲጂታል ስርዓት መዘርጋት ይጠበቅብናል " ብለዋል።

ስርአቱን ከሚዘረጋው አካል ጋር እየተነጋገሩ እና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ድርድር እየተካሄደ መሆኑን አክለው በ 2018 ዓም ሙሉ በሙሉ ተሽከርካሪዎችን በአዲስ ታርጋ የመቀየር ስራ ይሰራል ተብሎ መታቀዱን ገልጸዋል።

አዲሱ ታርጋ ቅየራ ስለሚከናወንበት ጊዜም " መሰራት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች መሰራት ስላለባቸው አዲሱ ታርጋ ቅየራ አልተጀመረም ከሁለት ወር ባጠረ ጊዜ አዲሱን ታርጋ መቀየር እንጀምራለን በያዝነው 2018 ዓም ሙሉ በሙሉ አዲሱን ታርጋ ቀይረን እንጨርሳለን " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.2K😡1.19K👏99😭43🤔35😢22💔21🕊20🙏17🥰13😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር (ታርጋ) አይነቶች እና ምልክቶች ምን ይመስላሉ ?

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ - Tikvah Ethiopia
)

➡️ የአገልግሎት አይነቱ ታክሲ ከሆነ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው ይሆናል።

ስቲከሩ ነጭ መደብ ከቀይ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር የመለያ ቁጥር ሰሌዳው እና ታክሲ የሚል ጽሑፍ ይጻፍበታል።

➡️ የአገልግሎት አይነቱ የቤት ከሆነ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው ይሆናል።

ስቲከር አይለጥፉም።

➡️ የአገልግሎት አይነቱ የንግድ ከሆነ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው ይሆናል።

ስቲከር ነጭ መደብ አረንጓዴ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር የመለያ ቁጥር ሰሌዳው ላይ ይለጥፋል።

➡️ የአገልግሎት አይነቱ የመንግስት ከሆነ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው ይሆናል።

ስቲከር የመንግስት ተቋሙ ስም እና አርማ ያለው ይሆናል።

➡️ የአገልግሎት አይነቱ የሃይማኖት ተቋማት እና ማህበራት ከሆነ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት እና 5 ቁጥር የተጻፈበት ይሆናል።

ስቲከሩ ነጭ መደብ ብርቱካናማ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር የማህበሩ ስም እና አርማ ይጻፍበታል።

➡️ የአገልግሎት አይነቱ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ከሆነ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት እንዲሁም የተቋሙ ስም ምሕጻረ ቃል በአማርኛ እና በላቲን ይጻፍበታል።

ስቲከሩ የተቋሙ ስም እና አርማ ያለው ይሆናል።

➡️ የአገልግሎት አይነቱ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ከሆነ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት እና 35 ቁጥር ፣"ዕድ" "AO" የሚል ይጻፍበታል።

የዲፕሎማቲክ መብት ላላቸው ደግሞ ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር የተቋሙ ስም ምሕጻረ ቃል "CD" በላቲን እናብ"ኮዲ" የሚል በአማርኛ የተጻፈበት ይሆናል።

የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እና ዲፕሎማቲክ መብት ያላቸው ተቋማት ስቲከራቸው የተቋሙ ስም እና አርማ ያለበት ይሆናል።

➡️ በኤሌክትሪክ ወይም በታዳሽ ሃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው።

ስቲከሩ መደቡ በነጭ ሆኖ ጽሑፉ አረንጓዴ ቀለም የሆነ አረንጓዴ ትራንስ ፖርት (GreenTransport) የሚል የተጻፈበት ይሆናል።

➡️ የአካል ጉዳተኞች ከሆኑ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው።

ስቲከሩ የዊልቸር ምልክት እና "አጉ" "PD" የሚል የተጻፈበት ይሆናል።

➡️ ባለሞተር ብስክሌት

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከቀይ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው።

ስቲከር አይኖራቸውም።

➡️ ልዩ ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከቀይ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው እና "ልተመ" "SME" የሚል የተጻፈበት ይሆናል።

ልዩ ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች ስቲከር አይለጥፉም

➡️ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH"፣ " ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው እንዲሁም "ተሳቢ" የሚል የተጻፈበት ይሆናል።

ስቲከሩ ነጭ መደብ አረንጓዴ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር የመለያ ቁጥር ሰሌዳው የተጻፈበት ይሆናል።

➡️ የተላላፊ ሰሌዳ

ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር ሆኖ፣ በግራ ክንፍ በኩል "ተላላፊ" የሚል ጽሑፍ ይኖረዋል ።

ስቲከር አይኖራቸውም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
32.22K👏129😡110😭41🤔35🙏35😱23😢22🕊20🥰17
#SafaricomEthiopia

አምስተኛው ዙር የበሽ ሽልማት ስነ-ስርዓት በባህርዳር እና በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወነ ሲሆን የ1,000,000 ብር አሸናፊዎች ሽልማታቸዉን ተቀብለዋል። አሸናፊዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!

ዛሬ ነገ ሳይሉ እድልዎን ይሞክሩ! ቀጣይ ዕድለኛ እርስዎ ይሆኑ ይሆናል!

📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ። https://onelink.to/ewsb22

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!

#besh
#HappyNewYear
#furtheraheadtogether
244😭9😡7🥰5🕊4
" ቅዱስነታቸው በተሟላ ጤንነት ላይ ይገኛሉ " - የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

ከሰሞኑ ቅዱስ ፓትርያርኩ " እንደራሴ እንዲሾምላቸው በደብዳቤ ጥያቄ አቀረቡ " በሚል በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ነበር።

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ተግባራትን ለመምራት ሆነ ለማከናወን የማያስችል ምንም ዓይነት የጤና እክል እንዳልገጠማቸው አሳውቋል።

ልዩ ጽሕፈት ቤቱ  ፥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማምራት የሕክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደቆዩ ፤ በቅርቡም ተመሳሳይ ጉዞ አድርገው ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓመተ ምሕረት ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ መመለሳቸውን አስታውሷል።

የመስቀል ደመራ በዓልንም በመስቀል አደባባይ ተገኝተው በማክበር ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን አባታዊ ትምህርተ ወንጌል ፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ እንዳስተላለፉም አስታውሷል።

እንዲሁም ቤተክርስቲያኗ በየዕለቱ የምታከናውናቸው መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ዓለም አቀፍ ተግባራትን በጽሕፈት ቤታቸው ሆነው በአባትነት እየመሩ በተሟላ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

" ይሁን እንጂ ድብቅ አጀንዳ ይዘው ሐሰተኛ መረጃን በማሰራጨት መደበኛውን የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ማደናቀፍ ዓላማቸው ያደረጉ አካላት በማኅበራዊ የትስስር ገጾቻቸው ባጋሩት ፍጹም ከእውነት የራቀ መረጃ ውሉደ ክህነት እና በጎ ሕሊና ያላቸው ምእመናን በእጅጉ መጨነቃቸውን ለመገንዘብ ችለናል " ብሏል።

" ስለሆነም ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ተግባራትን ለመምራትም ሆነ ለማከናወን የማያስችል ምንም ዓይነት የጤና እክል ያልገጠማቸው፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ያቀረቡት ጥያቄ የሌለ መሆኑን እንገልጻለን " ሲል ልዩ ጽሕፈት ቤቱ አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2.44K🙏403😡58🕊46🤔33🥰17😱9😢9😭7👏5
" የትግራይ ህዝብ ' ከሻዕቢያ መንግስት ጋር የሚደረግ ትብብር/ፅምዶ አልፈልግም ' ነው ያለው " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ

ትግራይ የሚገኙት የህወሓት አመራሮች ከሻዕቢያ (ከኢሳያስ መንግሥት ጋር) ሽርክና በመፍጠር ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰሩ እንደሚገኙ የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ተናገሩ።

ይህን የተናገሩት ኤን ቢ ሲ - ኢትዮጵያ ከተባለ የቴሌቪዥ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

ሌ/ጄነራል ፃድቃን ፤ የህወሓት ሰዎች ከኢሳያስ መንግስት ጋር በማበር ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰሩ ያሉት የወንጀል ስራዎቻቸውን ለመሸፈን እንደሆነ ጠቁመዋል።

" የወንጀል ስራዎች እና ወደ ጦርነት የተገባበት ውሳኔ እራሱ (የቀድሞው ጦርነት) accountable መሆን አለበት " ብለዋል።

ሌ/ጄነራሉ ፥ እጅግ በጣም ብዙ የጠፉ ፣ የተሰረቁ ፣ የተዘረፉ ንብረቶች፣ ወርቅ፣ መሬት ፣ ገንዘብ እንዳለ ጠቁመዋል። በዚህ የወንጀል ተግባር ውስጥ በግልጽ የሚታወቁ ትላልቅ አመራሮች እንዳሉበት ገልጸዋል።

እነዚህ አካላት የወንጀል ስራዎቻቸውና የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎታቸው አንድ ላይ እንደተቀላቀሉ ፤ ይህን ለመከላከል ወይም ከሰሯቸው የወንጀል ስራዎች ነጻ ለመሆን የሚያስችላቸው አንዱ መንገድ #ጦርነት መፍጠር እንደሆነ እንደሚያምኑ አመልክተዋል። ለዚህም " ከኢሳያስ መንግሥት ጋር መተባበር ነው - ፅምዶ " ብለው እየሰሩበት እንደሆነ ገልጸዋል።

" የትግራይ ህዝብ እያንዳንዱ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አውቆባቸዋል " ያሉት ሌ/ጄነራሉ ፤ የትግራይ ጄኖሳይድ ኮሚሽን ባጠናው ጥናት በትግራይ ጦርነት ወቅት 75% የግፍና የወንጀል ስራዎችን የሰራው የኤርትራ ሰራዊት እንደሆነ መመላከቱን ተናግረዋል።
- ሰው የገደለው
- ሴቶች የደፈረው
- ሴቶች ማዕፀን ላይ ያልሆነ ነገር ያስገባው የኤርትራ ሰራዊት እንደሆነ ገልጸዋል።

" የአክሱም ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ የማህበረ ደጎ ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ የማርያም ደንገላት ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ ደቡብ ትግራይ ራያ ላይ መጥቶ በመቶዎች የሚሆኑ ሰዎችን ረሽኖ የሄደው የሻዕቢያ ወታደር ነው " ብለዋል።

ህዝቡ ይሄንና የወታደራዊ እና የፖለቲካ መሪዎቹን ፍላጎት እንዲሁም የሚያደርጉትን ግንኙነት ስለሚያውቅ ከሻዕቢያ ጋር የሚደረግ ትብብር /ፅምዶ " አልፈልግም " ነው ያለው ሲሉ ተናግረዋል።

ከእነሱ ጋር በወንጀል የተሳሰረው ካልሆነ በስተቀር ህዝቡ ከኢሳያስ መንግሥት ጋር መተባበር ጥፋት እንደሚያመጣ አምኖ አልተቀበለውም ሲሉ አክለዋል።

እነዚህ ጦርነት እንዲነሳ የሚፈልጉ እና እየሰሩ ያሉ አካላት በኤርትራ ፣ በሱዳን በኩል ጥይት፣ ጠመንጃ እንደሚያስገቡ ፤ የጦር መሳሪያም እንደሚገዙ ይህንንም ሰው እንደሚያውቅ ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ተናግረዋል።

ሌ/ጄነራሉ በትግራይ ጦርነት ወቅት ጦር የመሩ፣ በኃላም የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ አመራር ሆነው የሰሩ ፣ አለመግባባት ሲፈጠር ትግራይን ለቀው የወጡ አንጋፋ የትግራይ ጄነራል ናቸው።

(የሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ንግግር ከላይ ተያይዟል - ኤን ቢ ሲ ቴሌቪዥን ኢትዮጵያ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
22.34K😡183🕊161😭86🤔69👏61🙏53😱29💔18😢16🥰9
አቢሲንያ ሼባ ካርድ
አቢሲንያ ባንክና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበጎ አላማ ተጣምረዋል። እናም ውድ ደንበኛችን በአቢሲንያ ሼባ ካርድ እየተገበያዩ የበረራ ማይልስ ይሰብስቡ። #BankofAbyssinia #Banking #VisaCard #Visa #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
112🙏11🥰2😡1
97🙏3😡3🥰1
ቅዳሜዎትን የሚያሳምር እጅግ አጓጊ ፕሮግራም ቴክኖ ኢትዮጵያ ጥቅምት 1 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር አዘጋጅቶላችኋል!

በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በካሞን 40 ብቻ የተነሱ አጅግ አስገራሚ ፎቶዎችን መመልከት የሚችሉበት፣ ስልኩን በቅርበት ማየት እና መሞከር የሚችሉበት፣ የቴክኖ ምርቶችን እና በርካታ ሽልማቶች የሚያሸልሙ ጨዋታዎችን የሚጫዎቱበት እና በሙዚቃ ዝግጅት ፈታ ዘና ሚሉበት ትልቅ ኤግዝቢሽን ተዘጋጅቷል።

ጥቅምት 1 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ሲ ኤም ሲ የተባበሩት አደባባይ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ከኛ ጋር ይዋሉ፡፡

#TecnoCamon40Series #FlashSnap #TecnoAI

@tecno_et
163👏5😡5🥰3🤔1
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዙፍ አየር መንገድ የሆነው ኢትሃድ ወደ አዲስ አበባ እለታዊ በረራ ጀምሯል።

የበረራ መስጀመሪያ ማብሰሪያ መርሃግብሩ ትላንት የኢትሃድ አቪዬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አንቶኖአልዶ ኔቬስ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በተገኙበት ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቡዳቢ መብረር የጀመረው ሐምሌ 15/2017 ዓ/ም የነበረ ሲሆን የኢትሃድ አየር መንገድ በበኩሉ ዕለታዊ በረራውን ከትላትን ጀምሮ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረው በረራ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስያ ለሚጓዙ መንገደኞች ያልተቋረጠ ግንኙነት የሚፈጥር ነው ተብሎለታል።

አዲስ አበባ የኢቲሃድ አየር መንገድ  በ2025 ካስጀመራቸው አዳዲስ መዳረሻዎች አስራ አምስተኛው መዳረሻ ስትሆን አቡ ዳቢ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 145ኛ የአለም አቀፍ መዳረሻ ሆናለች።

@tikvahethiopia
516🤔33👏24🙏17🕊10😭8😡3🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር (ታርጋ) አይነቶች እና ምልክቶች ምን ይመስላሉ ? (ቲክቫህ ኢትዮጵያ - Tikvah Ethiopia) ➡️ የአገልግሎት አይነቱ ታክሲ ከሆነ ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው ይሆናል። ስቲከሩ ነጭ መደብ ከቀይ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር የመለያ ቁጥር ሰሌዳው እና ታክሲ የሚል ጽሑፍ ይጻፍበታል።…
አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ለምን አልተካተተበትም ?

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ - Tikvah Ethiopia)

አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር (ታርጋ) የኢትዮጵያ አለም አቀፍ መለያ ኮድ "ETH" ፣ የኢትዮጵያ ካርታ ፣ ጦር እና ጋሻ ወይም የአድዋ ምልክት በግልጽ እና በአንጸባራቂ መብራት በመታገዝ በሚታይ  መልኩ ቢኖረውም የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ግን አልተካተተበትም።

የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በአዲሱ ሰሌዳ ላይ ያልተካተተው በሃገራዊ ምክክር ሂደት ላይ የምንገኝ በመሆናችን መሆኑን የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ ምን አሉ ?

" መጀመሪያ ስናስበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን ለማስገባት አስበን ነበር ነገር ግን እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ነው ያለችው።

አንዱ የብሔራዊ ምክክሩ አጀንዳ ደግሞ የሰንደቅ አላማ ምልክት እና አርማ ላይ ነው።

ይህ ሰሌዳ ለረዥም አመታት እንዲያገለግል ተብሎ የተሰራ ነው።

በብሔራዊ ምክክር አሁን ያለው ሰንደቅ አላማ ቅርጽ እና መልክ ቢቀየር ጊዜያዊ ሰሌዳ ሊሆን ነው። ስለዚህ አንድ እና ሁለት ሚሊየን አስመርተን (ሰንደቅ አላማ ያለው) አስቀይረን በነጋታው በምምክሩ ሌላ ውጤት ቢመጣስ ብለን በማሰባችን እንዲቀር ተደርጓል" ብለዋል።

ሰሌዳው ላይ የተካተቱ ምልክቶች ታርጋዎቹ በተመሳሳይ መንገድ በፎርጅድ እንዳይሰሩ ለመከላከል እና የወል ትርክት ለመፍጠር የተቀመጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ተመሳስለው የተሰሩ አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ አንጸባራቂዎችን ሰሌዳው ላይ በማብራት የተቀመጡትን የአድዋ ምልክቶች መመልከት ይቻላል።

በሰሌዳው ላይ የሚታዩ QR ኮድ ምልክቶች የአሽከርካሪው ሙሉ መረጃዎች የያዙ ሲሆን ለእዚህ አላማ ተብለው በሚሰሩ እና በትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና በሚመለከታቸው አካላት ስራ ላይ በሚውሉ መተግበሪያዎች አማካኝነት ስካን ማድረግ እና ማረጋገጥ እንደሚቻል ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ላይ ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.02K😡572🤔63😭41👏39🕊18💔13😱6😢4🥰3🙏1
#DV #USA

አሜሪካ ለዲቪ ምዝገባ 1 ዶላር ልትጠይቅ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ሎተሪ ምዝገባ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ዶላር የአገልግሎት ክፍያ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

ይህ የማይመለስ ክፍያ ከDV-2027 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ መሥሪያ ቤቱ ይህን ለውጥ ያመጣው የሎተሪውን የማስተዳደር ወጪ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለመከፋፈል ታስቦ እንደሆነ አስረድቷል።

ቀደም ሲል የ330 ዶላር የኢሚግሬሽን ቪዛ ክፍያ የሚከፍሉት የተመረጡት ብቻ ሲሆኑ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ያልተሳኩ አመልካቾች ምንም ሳይከፍሉ ይቆዩ ነበር።

አሁን ባለው አሰራር ግን በግምት 25 ሚሊዮን የሚሆኑ ዓመታዊ ተመዝጋቢዎች እያንዳንዳቸው 1 ዶላር በመክፈል፣ ወጪው በ55,000 አሸናፊዎች ላይ ብቻ ከመውደቅ ይልቅ በእኩል እንዲሰራጭ ያግዛል ተብሏል።

ክፍያው የሚሰበሰበው ፦
- የስርዓት ማሻሻያዎችን ለመደጎም፣
- የሳይበር ደህንነትን ለማሳደግ
- የሐሰተኛና በብዛት የሚቀርቡ የተጭበረበሩ ማመልከቻዎችን ለመቀነስ ያለመ ነው።

የምዝገባው ጊዜ እንደተለመደው በተያዘዉ በጥቅምት ወር የሚጀምር ሲሆን፣ ክፍያው የሚፈጸመው በኦፊሴላዊው ድረ-ገጽ አማካኝነት በኤሌክትሮኒክ ካርዶች ብቻ መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል። #ካፒታል

@tikvahethiopia
21.9K😭632😡223👏90🤔88🙏60💔39😢37🕊27😱26🥰17
" በተለያዩ ማስታወቂያዎች የሚጭበረበረውን ማኅበረሰብ መጠበቅ ኃላፊነታችን ነው " - ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ

የሳይበር ደኅንነት ወር " የሳይበር ደኅንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት " በሚል መሪ ቃል ለ6ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥቅምት 1 - 30 እንደሚከበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር አስታውቋል።

የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በዚህ ዓመት በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ምንድናቸው ?

1. በኤ አይ ዘመን የሀሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና ቁጥጥርን በተመለከተ ነው የመጀመሪያው ርዕስ። በመክፈቻው ዕለት በዚህ ዙሪያ የተጠና ጥናት ይፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ ፤ " ብዙዎችችን የምንሸወደው እውቀቱ ስለሌለን ነው " ብለዋል።

" በተለያዩ ማስታወቂያዎች የሚጭበረበረውን ማኅበረሰብ መጠበቅ በኃላፊነት የተሰጠን ማንዴት ስለሆነ ይሄንን ዘልቆ ለማሳየት ስለፈለግን ነው " ሲሉ የወሩ ርዕስ ሆኖ የተመረጠበትን ምክንያት አስረድተዋል።

2. የዲጂታላይዜሽን ደኅንነት የሚለው ሁለተኛው ርዕስ ነው።

" ከአምስት ዓመት በፊት ስናከብር የሳይበር ደኅንነት መሪ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን ሳይበር የሚለውን ብዙ የሚረዳ ዜጋም ተቋማትም በጣም ጥቂት ነበሩ አሁን ላይ እኩል ከእኛ ጋር መናገር የሚችሉ ተቋማትና ዜጎች በእኩል ደረጃ ፈጥረናል ብለን እናምናለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በ2016 ዓ.ም 8854 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም ደግሞ ቁጥሩ ከፍ ብሎ 13496 የጥቃት ሙከራዎች አስተናግዳለች። እነዚህ  ጥቃቶች ውስጥ በሌሎች አካላት የሚደረጉ የመሰረተ ልማት ቅኝቶች ጭምር እንደ ጥቃት መቆጠራቸው ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
498😡25🤔13🙏12💔9😭7😱6🕊5
2025/10/24 16:14:54
Back to Top
HTML Embed Code: