Telegram Web Link
#ግብር

ለተከታታይ አምስት አመታት የፕላቲኒየም ደረጃ ግብር ከፋይነታቸውን ላስቀጠሉ ግብር ከፋዮች የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው ተፈቀደ።

7ኛው ዙር የግብር ከፋዮች የእውቅና መርሃ ግብር እና የታክስ አስተዳደሩን ያዘምናሉ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን ይፋ የማድረግ መርሃ ግብር ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ ተከናውኗል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ባለፈው የ2017 ዓም በጀት ዓመት 902.7 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ በእቅድ ተይዞ ከሃገር ውስጥ ገቢ 484.49 ቢሊየን ከውጭ ሽያጭ ገቢ 415.79 ቢሊየን ብር በአጠቃላይ 902.2 ቢሊየን ብር ግብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

" በ2018 ዓም በጀት አመት ከግብር ለመሰብሰብ ከታቀደው 1.28 ትሪሊየን ብር ውስጥ በበጀት አመቱ ሁለት ወራት 271.7 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ችለናል " ብለዋል።

ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ በተካሄደው የግብር ከፋዮች የዕውቅና መርሃ ግብር ፦
- በፕላቲኒየም ደረጃ 105 ፣
- በወርቅ ደረጃ 245
- በብር ደረጃ 350 በአጠቃላይ 700 ግብር ከፋዮች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ግብር ከፋዮቹ በእውቅና መርሃ ግብር የተካተቱት ለታክስ ባላቸው ተገዢነት እና ባደረጉት አስተዋጽኦ ታይቶ መሆኑ ተገልጿል።

30 ግብር ከፋዮች ለተከታታይ አምስት አመታት የፕላቲኒየም ግብር ከፋይነት ደረጃቸውን ይዘው በማስቀጠላቸው የልዩ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ አመታዊ ግብራቸው በአጠቃላይ ከ34.3 እስከ 213.7 ሚሊየን ብር ታክስ የከፈሉ ግብር ከፋዮች በብር ደረጃ ተሸላሚ በመሆን ከገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ እጅ የእውቅና ሽልማት ተቀብለዋል።

አመታዊ ግብራቸው በአጠቃላይ ከ213.9 እስከ 652.8 ሚሊየን ድረስ የከፈሉ ግብር ከፋዮች ከኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እጅ የእውቅና ሽልማታቸውን ወስደዋል።

አመታዊ ግብራቸው በአጠቃላይ ከ655.7 ሚሊዮን እስከ 37.5 ቢሊየን ብር ድረስ ታክስ የከፈሉ ግብር ከፋዮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) እጅ የእውቅና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

ለአጠቃላይ እውቅና ካገኙ 700 ግብር ከፋዮች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት የብር ፣ 35 በመቶ የወርቅ እንዲሁም 15 በመቶ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚዎች ናቸው።

ለተከታታይ አምስት አመታት የፕላቲኒየም ግብር ከፋይነት ደረጃቸውን ይዘው ያስቀጠሉ ግብር ከፋዮች በልዩነት እውቅና አግኝተዋል።

በልዩነት እውቅና ለተሰጣቸው 30 የፕላቲኒየም ደረጃ ግብር ከፋዮች የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው መወሰኑን ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ " 30 ልዩ ተሸላሚዎች ባለቤቶቻቸው ኢትዮጵያዊያን ከሆኑ ለድርጅቱ ባለቤት ወይም CEO እንደ ድርጅቱ ምርጫ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ይሰጣቸዋል " ብለዋል።

በተጨማሪም በተከታታይ አምስት አመታት የፕላቲኒየም ደረጃ የግብር ከፋይነት ደረጃቸውን ላስቀጠሉ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ውጪ በመንግስት አጋርነት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በብር እና በወርቅ ደረጃ ተሸላሚ የሆኑ ግብር ከፋዮች በኢትዮጵያ አየር መንገድ የVIP ተርሚናል ደረጃ እንዲስተናገዱ ተወስኗል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ " ባለፈው ዓመት የምታዋጡት ግብር ለጋራ እድገት እና ለሕዝባዊ ጠቀሜታ በሚውሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል ቃል ገብተን ነበር " ያሉ ሲሆን " ዛሬ በከተማችን ኮሪደሮች የሚታየው ለውጥ ለዚያ ቃላችን ሕያው ምስክር ሆኖ ይታያል " ብለዋል።

" አስታውሱ፣ የዛሬ ጥረታችሁ የነገን ትውልድ የተሻለ መፃኢ እድል እየቀረፀ ነው። ሙስናን እና ሌብነትን ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ሥርዓቶቻችንን ማጠናከራችንን እንቀጥላለን ፤ ግብር ከፋዮችም በመሰል ጎጂ ተግባር የተሠማሩ ሰዎችን ባለመተባበር እንዲያግዙ አሳስባለሁ። በጋራ ግልጽ፣ ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገር እንገነባለን " ሲሉ ገልጻዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
31.84K😡144👏74🙏40🤔36😢19🥰18😭18🕊16💔3😱2
ይሳተፉ ፣ ተሰጥዎትን ያሳዩ ፣ 1,000,000 ብር አሸናፊ ይሁኑ !

(ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ)

የሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ተወዳጅ ምርት የሆነው ሚሪንዳ ለየት ያለ እና አስደሳች የሆነ የፈጠራ ችሎታን የሚፈትን ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል። ውድድሩ ‘ማን እንደሚሪንዳ ፡ ማን እንደእናንተ’ በሚል መርህ የተዘጋጀ አገር አቀፍ የቲክቶክ ውድድር ሲሆን ከዳንስ እስከ ኮሜዲ ፣ ከፋሽን እስከ ቪዡዋል አርት እና ኮንቴንት ክሪኤሽን ወጣቱ ትውልድ ‘ማን እንደኔ’ በሚል ልዩ ተሰጥዖውን እያሳየ የሚሸለምበት አስገራሚ ዕድል ነው።

ተወዳዳሪዎች (#ማንእንደሚሪንዳ) የሚለውን ሀሽታግ በመጠቀም እና የሚሪንዳን ምርት ቪዲዮዎቻቸው ውስጥ አካተው ቲክቶክ ላይ ፖስት በማድረግ ውድድሩን መቀላቀል ይችላሉ።
ለ 1 ወር የሚቆይ ውድድር ሲሆን ደፋር ሆነው ራሳቸውን በመግለጽ ልዩ የፈጠራ ችሎታቸውን በግልጽ ላሳዩ 3 ተወዳዳሪዎች አስደናቂ ሽልማቶችን ለመሸለም ዝግጅቱን አጠናቆ እየጠበቀ ነው።
አንደኛ ለወጣ 1,000,000 ብር ፣
ሁለተኛ ለወጣ 500,000 ብር፣
ሶስተኛ ለወጣ ደግሞ 250,000 ብር ሽልማት ይበረከትላቸዋል።

ሚሪንዳ ውድድሩን አስጀምሯል ሁሉም ሰው ይሄንን አዝናኝ የሆነ ውድድር ተቀላቅሎ የተለየ የሚያደርጋቸውን ተሰጥዖ ለመላው አገሪቷ እንዲያሳዩ እየጋበዘ ነው።

ይሳተፉ ፣ ተሰጥዎትን ያሳዩ ፣ 1,000,000 ብር አሸናፊ ይሁኑ
322👏20😢10🙏7🕊7😡5🥰3😭3😱2
#TecnoCamon40Series

የፎቶግራፍ አድናቂ ኖት?

ከሆኑ መቼም ስለ አዲሱ ቴክኖ ካሞን 40 ስልክ እና የካሜራ ብቃት ሰምታችኋል፡፡ አሁን ደግሞ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በካሞን 40 ብቻ የተነሱ አጅግ አስገራሚ ፎቶዎችን መመልከት የሚችሉበት፣ ስልኩን በቅርበት ማየት እና መሞከር የሚችሉበት፣ የቴክኖ ምርቶችን እና በርካታ ሽልማቶች የሚያሸልሙ ጨዋታዎችን የሚጫዎቱበት እና በሙዚቃ ዝግጅት ፈታ ዘና ሚሉበት ትልቅ ኤግዝቢሽን ተዘጋጅቷል።

ይሄ ሁሉ ቅዳሜ ጥቅምት 1 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ አስከ አመሻሽ ሲ ኤም ሲ የተባበሩት አደባባይ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ተዘጋጅቷል፡፡

ቅዳሜ ጥቅምት 1 በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር እንገናኝ!

#TecnoCamon40Series #FlashSnap #TecnoAI

@tecno_et
168🙏9👏6😭5🥰4💔3🕊1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ነዋሪው ' ደህንነታችንን ካላስጠበቃችሁ እኛ ታጥቀን እንደራጃለን ' የሚል መፈክር አሰምቷል " -  በ3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ቀብር ላይ የተገኘው የመተማ ከተማ ነዋሪ

በፀጥታ ችግር ምክንያት የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ይደረግበት የነበረው የጎንደር መተማ ገላባት ዋና የአስፖልት መንገድ በእጀባም ብቻ ቢኬድም  ከጥቃት የማያመልጡበት ሆኗል ይላሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የመተማ ከተማ ነዋሪዎች።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እዳንጠቅስ የጠየቁን የከተማው ነዋሪ መስከረም 23/01/2018 ዓ.ም ከጎንደር መተማ መንገድ " መቃ " ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ወጣ ብሎ 2 ኪሎ ሜትር አካባቢ  የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀይሎች በእጀባ ይጓዙ በነበሩ ብዙ ተሽከርካሪዎች ላይ በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ነግረውናል።

እኝሁ የመረጃ ምንጫችን እንደገለፁልን በጥቃቱ በመተማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሶስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የቀብር ስርዓታቸውም መስከረም 25/2018 ዓ.ም ተፈፅሟል ብለዋል።

በሟቾቹ ቀብር ስነስርዓት ላይ ብዙ ቁጥር ያለው የከተማው ነዋሪ የተገኘ ሲሆን የአካባቢው ባለስልጣናት በዞኑ የሚፈፀመውን የሰዎች ግድያና እገታ ካላስቆመ ነዋሪው ተደራጅቶ ታጥቆ እራሱን ለመከላከል እንደሚወጣ መፈክር በማሰማት ገልጿል ብለዋል።

አክለውም በመተማ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 15 ሰዎች ቆስለው የገቡ ሲሆን በትላንትናው እለት አንዲት እናት መሞታቸውን እና 14ቱ ህክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሆነ ገልጸዋል።

ግለሰቡ ቆስለው ከመጡ ታካሚዎች አገኘሁት ባሉት መረጃ በእጀባ ሲጓዙ በነበሩ ህዝብ በጫኑ 10 በሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ ታጣቂዎቹ በከፈቱት ጥቃት 18 የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል ከ20 በላይ ቆስለዋል ታግተው የተወሰዱም አሉ።

ቆስለው በመታከም ላይ ያሉ የአይን እማኞችን በቀጥታ ለማነጋገር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥረት ቢያደርግም ግለሰቦቹ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መረጃውን ማካተት አልቻልንም።

ሌላው በደህንነት ስጋት ምክንያት ስሙን እንዳንጠቅስ የጠየቀን ሹፌር እጀባ ሲጠብቁ ከነበሩት ብዛት ካላቸው መኪኖች መካከል አንዱ የጓደኛው መኪና እንደነበርና እሱም ከጓደኛው ጋር አብሮ ቆይቶ መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር ጓደኛው " አብረን ደርሰን እንመለስ " ብሎ ለምኖት እንደነበርና እርሱ ግን እምቢ ብሎ ከመኪናው መውረዱን ይናገራል።

ጓደኛውም ወደ መተማ ከሄደ ከሰዕታት በኃላ ' መቃ ' በተባለ ቦታ  ላይ በታጣቂዎች መገደሉንና በማግስቱም በ24/01/2018 ዓ.ም  ጎንደር ከተማ ላይ መቅበሩን እያለቀሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ይህው የመረጃ ምንጫችን ከሶስት ወር በፊት ማለትም ሰኔ 16/ 2017 ዓ.ም በዚሁ ' መቃ ' በተባለ ቦታ ላይ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ከ16 በላይ ሹፌሮች ሲገደሉ እርሱ በተዓምር መትረፉን በወቅቱ የአይን እማኝ በመሆን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ ሰጥቶ ነበር።

" ያኔም እንዲህ በእጀባ በሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ላይ ነበር ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የሰነዘሩት " የሚለው ይህው ሹፌር " ይህ ዓለም አቀፍ መንገድ በአሁኑ ሰዓት በፀጥታ ሀይሉ ታጅቦ የማይታለፍበት የወንበዴ መፈንጫ ሆኗል " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

በቦታው ስለ ነበረው ጥቃት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በመተማ ሆስፒታል ቆስለው እየታከሙ ካሉ የአይን እማኞች ብንሞክርም ፈቃደኛ መሆን ባለመቻላቸው የሞቱ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ፣ የቆሰሉትንና ታግተው የተወሰዱትን ሰዎች ቁጥር በዝርዝር ለማወቅ አልቻልንም።

ወቀሳ የቀረበበት የዞኑ ባለስልጣናት እስካሁን የተገደሉት ሰዎች ቁጥርንና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ያወጡት መግለጫ የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ የእጅ ስልክ ላይ በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልኩ ባለመነሳቱ ምክንያት ሀሳብ አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም።

የጎንደር መተማ ገላባት መንገድ ኢትዮጵያን እና ሱዳንን የሚያገናኝ ትልቅ የአስፓልት መንገድ ሲሆን በአካባቢው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ምክንያት በርካታ ሹፌሮችና መንገደኞች ይገደላሉ በዚህም ምክንያት ለበርካታ ወራት መንገዱ የተዘጋ ሲሆን አልፎ አልፎ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሚደረግ እጀባ ተሽከርካሪዎች ቢንቀሳቀሱም ከጥቃት እያመለጡ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia
540😭205👏14🕊13🙏9😢7😡5😱3🥰2💔2
TIKVAH-ETHIOPIA
#ግብር ለተከታታይ አምስት አመታት የፕላቲኒየም ደረጃ ግብር ከፋይነታቸውን ላስቀጠሉ ግብር ከፋዮች የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው ተፈቀደ። 7ኛው ዙር የግብር ከፋዮች የእውቅና መርሃ ግብር እና የታክስ አስተዳደሩን ያዘምናሉ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን ይፋ የማድረግ መርሃ ግብር ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ ተከናውኗል። በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስቴር…
#Ethiopia

በ7ኛው ዙር የግብር ከፋዮች የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የታክስ አስተዳደሩን ያዘምናሉ የተባሉ በርካታ ቴክኖሎጂዎች ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ይፋ ተደርገዋል።

ይፋ ከሆኑት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ምንድናቸው ?

በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል የተለያዩ የቴክኖሎጂ ስርአቶች ይፋ ተደርገዋል።

ከእነዚህም ውስጥ ፦

1. የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ካርጎ ትራፊክ ሲስተም

ይህ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ ጭነቶች ደህንነታቸው ተጠብቆ በተፈቀደላቸው ጊዜና መስመር መጓዛቸውን ለማረጋገጥ፣ ቅሸባዎችንና የእቃ ለውጦችን ለመከላከል፣ በጉምሩክ ኬላዎች ላይ ለፍተሻ የሚባክኑ ጊዜዎችን ለመቀነስ ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ህገወጥ የሆኑ ተግባሮች ሲፈጸም ደግሞ መረጃዎችን ወዲያውኑ ለማግኘት እና ለንግዱ ማህበረሰብ የትራንስፖርት ስምሪት ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ስለመሆኑ ተጠቁሟል።

2. የጉምሩክ ደንበኞች ቁጥጥር ስርአት

ይህ ስርአት ኮንትሮባንድን የመከላከል ስራን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በማስደገፍ ከማዕከል ቁጥጥር የሚደረግበትና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የራሳቸውን ሚና እንዲኖራቸው የተደረገበት ነው።

በቀን እና በምሽት በርቀት መቅረጽ የሚችል የደህንነት ካሜራዎች፣ ግራውንድ ሴንሰሮች እና ሲቲ ስካን ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የገቢና ወጭ ኮንትሮባንድን ለመከላከል ያግዛል ተብሏል።

3. የመንገደኞች ስራ አሰራር ስርአት

ይህ ስርአት በአውሮፕላን ለሚደረጉ ጉዞዎች የመንገደኞችን ቅድመ መረጃ መሰረት በማድረግ በቅድሚያ የስጋት ደረጃዎችን በመለየት ውጤታማ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።

4. ቻት ቦት

የቴክኖሎጂ ስርአት ተገልጋዮች ወደ ጉምሩክ ኮሚሽን በአካል መምጣት ሳይጠበቅባቸው በ4 ቋንቋዎች የለሙ ሲስተሞችን በመጠቀም የተቋሙ ህጎችን፣ ቅድመ መረጃዎችን ባሉበት በኦንላይን እንዲያዩ የሚያስችል ቻት ቦት (Chat bot ) ስርአት ነው።

ቴክኖሎጂዎቹን ያበለጸጓቸው የኢንፎርሜሽን መረብ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንስቲትዩት እንደሆኑ ተገልጿል። በዚህ ሂደት ውስጥ ሲያማክሩ የነበሩት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  እና በገቢዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የመረጃ ቴክኖሎጂ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት እንደሆኑ ተመላክተዋል።

በሌላ በኩል ፥ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ያዘጋጁት የቴክኖሎጂ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሲኤምሲ አደባባይ በሚገኘው አዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር እየተካሄደ ሲሆን ሄዶ መጎብኘት ይቻላል ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
416😭25🤔13🙏5👏4😡4🥰3🕊3😢2
#AddisAbaba

የጉልበት ብዝበዛ ወንጀል ሲፈፀምባቸው የነበሩ 18 ህፃናትና ታዳጊዎችን ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ' ኦ አቤም ሆቴል ' ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የሰባት ዓመት ታዳጊ በመንገድ ላይ እያለቀሰ ሳለ ለምን እንደሚያለቅስ ሲጠየቅ ለስራ የተሰጠው ሚዛን እንደጠፋበትና አሰሪዎቹም ቤት እንደማያስገቡት ይናገራል።

ፖሊስ መከታዳጊው የተቀበለውን መረጃ መነሻ በማድረግና ክትትል በማከናወን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ' ቻይና ካምፕ ' አካባቢ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ዕድሜያቸው ከ7 እስከ 13 ዓመት የሆኑ 18 ህፃናትና ታዳጊዎችን ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ሊያውል እንደቻለ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ እነዚህኑ ህፃናትና ታዳጊዎች  ክልል ድረስ በመሄድ ከቤተሰቦቻቸው ላይ " እናስተምራቸዋለን " ብለው በማምጣት ፦
- ቆሎ፣
- ሶፍት
- ሚዛን በማሰራት ከእያንዳንዳቸው በቀን ከ150 እስከ 300 ብር ገቢ እንዲያስገቡ ከማድረጋቸው በላይ የወንጀል አፈጻጸሞችን (የመኪና ስፖኪዮ አነቃቀል) ያስተምሯቸው እንደነበር አመልክቷል።

በግለሰቦቹ ላይ ተገቢው ምርመራ እየተደረገ ሲሆን በዐ/ህግም በኩል ክስ እንደተመሠረተባቸው ፖሊስ አስታውቋል፡፡

" ሕፃናትን ለእድሜያቸው በማይመጥን የጤና፣ የእድገት፣ የማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ደህንነታቸውን የሚጎዳና ለህይወታቸው አስጊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲሰሩ ማድረግ የህግ ተጠያቂነት የሚያስከትል ተግባር ነው " ብሏል።

ህብረተሰቡ መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙት በአቅራቢያው ለሚገኝ የፀጥታ ተቋም መረጃ በመስጠት በህፃናት ላይ የሚደርስ የጉልበት ብዝበዛን መከላከል ይገባል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
837😢157👏88😭48💔47🙏34😡20🤔10🕊9😱7🥰4
#Mekelle #Airport

" ከወትሮ የተለየ ምንም አዲስ ነገር የለም፤ የፈጠራ ወሬ ነው " - የኤርፖርት ኃላፊዎች

በትግራይ፣ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ወጣቶች ከመቐለ እንዳይወጡ የተለየ ክልከላ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጩት መረጃዎች ውሸት እንደሆኑ ተጓዦች እና የኤርፖርቱ ኃላፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በማህበራዊ ሚዲያው ላይ " በመቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ክልከላ እንዳለ ፤ የትግራይ የፀጥታ አካላት ውጭ እና ኤርፖርት ቁጥጥር እያደረጉ እንደሆነ፤ ሁኔታው ለጦርነት ምልመላ እንደሆነ በዚህም ወጣቱ ተስፋ እንደቆረጠ  " የሚገልጹ መረጃዎች በስፋት ተሰራጭተዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባልም የሚወራውን ለማረጋገጥ በአካል ቅኝት አድርጓል ፤ የኤርፖርት ኃላፊዎችንም አግኝቶ አነጋግሯል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ተጓዦች ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ ክልከላ የሚባለውም እንዳልገጠማቸው ገልጸዋል።

ትኬት ቢሮ ድረስ ሄደን ያነጋገራቸው ተገልጋዮችም ምንም አይነት ክልከላ እንዳልገጠማቸው በአግባቡ እየተስተናገዱ እንደሆነ ተናግረዋል።

እንዲሁም ወደ አየር መንገዱ ተጓዦች የሚያጓጓዙ የታክሲ ሹፌሮችም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ እንደሆነ ፤ ተጓዦች ላይ የተጣለ ክልከላ እንደሌለ አመልክተዋል።

መንገድ ላይ ሆነ በአውሮፕላን ማረፍያው ዙሪያ የተለየ ፍተሻና የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እንደሌለ አረጋግጠዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ተዘዋውሮ በተመለከተበት ወቅትም ምንም የተለየ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ፣ ፍተሻ ሆነ ክልከላ የለም።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሁለት የኤርፖርት ኃላፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ከወትሮው የተለይ ምንም አዲስ ነገር የለም ፤ የፈጠራ ወሬ ነው እየተሰራጨ ያለው " ብለዋል።

በኤርፓርት ዙሪያና ውስጥ ከፌደራል ፓሊስና ኢንተለጀንስ ውጪ ምንም የትግራይ ፓሊስና ታጣቂ እንደሌለ ፤ ለታጠቀ አካል ወደ ኤርፖርት መግባትም እንደማይፈቀድ ለመረዳት ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
466🙏41🕊24😢14🤔8🥰5👏5😡2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ምን ያህል ተማሪዎች በማካካሻ ትምህርት (ሬሜዲያል ፕሮግራም) ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይገባሉ ?

🎓 ከ82 ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይገባሉ !

በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ከ82 ሺሕ በላይ ተፈታኞች በማካካሻ (በሪሜዲያል) መርሐ ግብር ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ " በ2018 የትምህርት ዘመን 82,838 ተፈታኞች የማካካሻ ትምህርት ለመውሰድ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይገባሉ " ሲሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።

በግል ሆነ በመንግሥት ተቋማት ውስጥ የሪሜዲያል ፕሮግራም መከታተል የሚችሉት፣ እንደተፈተኑት የትምህርት ዓይነት ብዛት 33 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ናቸው።

ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖላቸው የሬሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ ብቻም ይሆናሉ።

የመቁረጫ ነጥብ ፦

➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216

➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204

➡️ ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165

ትምህርት ሚኒስቴር ዘንድሮም የሬሜዲያል ፕሮግራም እንደሚኖር ነገር ግን ወደፊት የማስቀጠል ሀሳብ እንደሌለና ቀስ እያለ እንደሚቆም ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
430😭24🕊15🥰14😡14👏8🙏8😱7😢2
TIKVAH-ETHIOPIA
ምን ያህል ተማሪዎች በማካካሻ ትምህርት (ሬሜዲያል ፕሮግራም) ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይገባሉ ? 🎓 ከ82 ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይገባሉ ! በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ከ82 ሺሕ በላይ ተፈታኞች በማካካሻ (በሪሜዲያል) መርሐ ግብር ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ልማት…
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ፦
➡️ በዌብሳይት፦ https://student.ethernet.edu.et
➡️ በቴሌግራም ቦት @moestudentbot ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ገልጿል።

የRemedial ፕሮግራም ምደባ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE

@tikvahethiopia
749👏76😭63😡33🕊28🙏25🥰23😢22😱9
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ (ታርጋ) ዛሬ ይፋ ሆኗል።

@tikvahethiopia
👏677260😡90😭70🤔39🙏29😱15🕊15🥰5😢5
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ (ታርጋ) ዛሬ ይፋ ሆኗል። @tikvahethiopia
ፎቶ፦ አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ (ታርጋ) ዛሬ ይፋ ሆኗል።

@tikvahethiopia
11.24K👏170🤔90😡71🙏47😭32😢29🥰28🕊20💔14😱12
2025/10/25 04:51:38
Back to Top
HTML Embed Code: