ዛሬዉኑ የM-PESA ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ይቀላቀሉ።
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/m-pesaethiopia/
Facebook: https://www.facebook.com/61572410606905/
Instagram: www.instagram.com/mpesa.ethiopia
X (Twitter): M-PESA Ethiopia (@m_ethiopia58462) / X
TikTok: https://www.tiktok.com/@mpesa.ethiopia/
YouTube: https://youtube.com/@m-pesaethiopia?si=jldsrSE888ts2ZOe
#MPESAEthiopia

❤97🙏3😡3🥰1
ቅዳሜዎትን የሚያሳምር እጅግ አጓጊ ፕሮግራም ቴክኖ ኢትዮጵያ ጥቅምት 1 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር አዘጋጅቶላችኋል!
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በካሞን 40 ብቻ የተነሱ አጅግ አስገራሚ ፎቶዎችን መመልከት የሚችሉበት፣ ስልኩን በቅርበት ማየት እና መሞከር የሚችሉበት፣ የቴክኖ ምርቶችን እና በርካታ ሽልማቶች የሚያሸልሙ ጨዋታዎችን የሚጫዎቱበት እና በሙዚቃ ዝግጅት ፈታ ዘና ሚሉበት ትልቅ ኤግዝቢሽን ተዘጋጅቷል።
ጥቅምት 1 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ሲ ኤም ሲ የተባበሩት አደባባይ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ከኛ ጋር ይዋሉ፡፡
#TecnoCamon40Series #FlashSnap #TecnoAI
@tecno_et

❤163👏5😡5🥰3🤔1
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግዙፍ አየር መንገድ የሆነው ኢትሃድ ወደ አዲስ አበባ እለታዊ በረራ ጀምሯል።
የበረራ መስጀመሪያ ማብሰሪያ መርሃግብሩ ትላንት የኢትሃድ አቪዬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አንቶኖአልዶ ኔቬስ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በተገኙበት ተከናውኗል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አቡዳቢ መብረር የጀመረው ሐምሌ 15/2017 ዓ/ም የነበረ ሲሆን የኢትሃድ አየር መንገድ በበኩሉ ዕለታዊ በረራውን ከትላትን ጀምሮ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።
በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረው በረራ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስያ ለሚጓዙ መንገደኞች ያልተቋረጠ ግንኙነት የሚፈጥር ነው ተብሎለታል።
አዲስ አበባ የኢቲሃድ አየር መንገድ በ2025 ካስጀመራቸው አዳዲስ መዳረሻዎች አስራ አምስተኛው መዳረሻ ስትሆን አቡ ዳቢ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 145ኛ የአለም አቀፍ መዳረሻ ሆናለች።
@tikvahethiopia

❤516🤔33👏24🙏17🕊10😭8😡3🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር (ታርጋ) አይነቶች እና ምልክቶች ምን ይመስላሉ ? (ቲክቫህ ኢትዮጵያ - Tikvah Ethiopia) ➡️ የአገልግሎት አይነቱ ታክሲ ከሆነ ሠሌዳው ነጭ መደብ ከጥቁር ፊደላትና ቁጥሮች ጋር "ETH" ፣ "ኢት" የተጻፈበት እና የኢትዮጵያ ካርታ ምልክት ያለው ይሆናል። ስቲከሩ ነጭ መደብ ከቀይ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር የመለያ ቁጥር ሰሌዳው እና ታክሲ የሚል ጽሑፍ ይጻፍበታል።…
አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ለምን አልተካተተበትም ?
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ - Tikvah Ethiopia)
አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር (ታርጋ) የኢትዮጵያ አለም አቀፍ መለያ ኮድ "ETH" ፣ የኢትዮጵያ ካርታ ፣ ጦር እና ጋሻ ወይም የአድዋ ምልክት በግልጽ እና በአንጸባራቂ መብራት በመታገዝ በሚታይ መልኩ ቢኖረውም የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ግን አልተካተተበትም።
የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በአዲሱ ሰሌዳ ላይ ያልተካተተው በሃገራዊ ምክክር ሂደት ላይ የምንገኝ በመሆናችን መሆኑን የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ ምን አሉ ?
" መጀመሪያ ስናስበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን ለማስገባት አስበን ነበር ነገር ግን እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ነው ያለችው።
አንዱ የብሔራዊ ምክክሩ አጀንዳ ደግሞ የሰንደቅ አላማ ምልክት እና አርማ ላይ ነው።
ይህ ሰሌዳ ለረዥም አመታት እንዲያገለግል ተብሎ የተሰራ ነው።
በብሔራዊ ምክክር አሁን ያለው ሰንደቅ አላማ ቅርጽ እና መልክ ቢቀየር ጊዜያዊ ሰሌዳ ሊሆን ነው። ስለዚህ አንድ እና ሁለት ሚሊየን አስመርተን (ሰንደቅ አላማ ያለው) አስቀይረን በነጋታው በምምክሩ ሌላ ውጤት ቢመጣስ ብለን በማሰባችን እንዲቀር ተደርጓል" ብለዋል።
ሰሌዳው ላይ የተካተቱ ምልክቶች ታርጋዎቹ በተመሳሳይ መንገድ በፎርጅድ እንዳይሰሩ ለመከላከል እና የወል ትርክት ለመፍጠር የተቀመጡ መሆናቸው ተገልጿል።
ተመሳስለው የተሰሩ አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ አንጸባራቂዎችን ሰሌዳው ላይ በማብራት የተቀመጡትን የአድዋ ምልክቶች መመልከት ይቻላል።
በሰሌዳው ላይ የሚታዩ QR ኮድ ምልክቶች የአሽከርካሪው ሙሉ መረጃዎች የያዙ ሲሆን ለእዚህ አላማ ተብለው በሚሰሩ እና በትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና በሚመለከታቸው አካላት ስራ ላይ በሚውሉ መተግበሪያዎች አማካኝነት ስካን ማድረግ እና ማረጋገጥ እንደሚቻል ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ላይ ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤1.02K😡572🤔63😭41👏39🕊18💔13😱6😢4🥰3🙏1
#DV #USA
አሜሪካ ለዲቪ ምዝገባ 1 ዶላር ልትጠይቅ ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ሎተሪ ምዝገባ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ዶላር የአገልግሎት ክፍያ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።
ይህ የማይመለስ ክፍያ ከDV-2027 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ መሥሪያ ቤቱ ይህን ለውጥ ያመጣው የሎተሪውን የማስተዳደር ወጪ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለመከፋፈል ታስቦ እንደሆነ አስረድቷል።
ቀደም ሲል የ330 ዶላር የኢሚግሬሽን ቪዛ ክፍያ የሚከፍሉት የተመረጡት ብቻ ሲሆኑ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ያልተሳኩ አመልካቾች ምንም ሳይከፍሉ ይቆዩ ነበር።
አሁን ባለው አሰራር ግን በግምት 25 ሚሊዮን የሚሆኑ ዓመታዊ ተመዝጋቢዎች እያንዳንዳቸው 1 ዶላር በመክፈል፣ ወጪው በ55,000 አሸናፊዎች ላይ ብቻ ከመውደቅ ይልቅ በእኩል እንዲሰራጭ ያግዛል ተብሏል።
ክፍያው የሚሰበሰበው ፦
- የስርዓት ማሻሻያዎችን ለመደጎም፣
- የሳይበር ደህንነትን ለማሳደግ
- የሐሰተኛና በብዛት የሚቀርቡ የተጭበረበሩ ማመልከቻዎችን ለመቀነስ ያለመ ነው።
የምዝገባው ጊዜ እንደተለመደው በተያዘዉ በጥቅምት ወር የሚጀምር ሲሆን፣ ክፍያው የሚፈጸመው በኦፊሴላዊው ድረ-ገጽ አማካኝነት በኤሌክትሮኒክ ካርዶች ብቻ መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል። #ካፒታል

2❤1.9K😭632😡223👏90🤔88🙏60💔39😢37🕊27😱26🥰17
" በተለያዩ ማስታወቂያዎች የሚጭበረበረውን ማኅበረሰብ መጠበቅ ኃላፊነታችን ነው " - ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ
የሳይበር ደኅንነት ወር " የሳይበር ደኅንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት " በሚል መሪ ቃል ለ6ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥቅምት 1 - 30 እንደሚከበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር አስታውቋል።
የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በዚህ ዓመት በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
ምንድናቸው ?
1. በኤ አይ ዘመን የሀሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና ቁጥጥርን በተመለከተ ነው የመጀመሪያው ርዕስ። በመክፈቻው ዕለት በዚህ ዙሪያ የተጠና ጥናት ይፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ ፤ " ብዙዎችችን የምንሸወደው እውቀቱ ስለሌለን ነው " ብለዋል።
" በተለያዩ ማስታወቂያዎች የሚጭበረበረውን ማኅበረሰብ መጠበቅ በኃላፊነት የተሰጠን ማንዴት ስለሆነ ይሄንን ዘልቆ ለማሳየት ስለፈለግን ነው " ሲሉ የወሩ ርዕስ ሆኖ የተመረጠበትን ምክንያት አስረድተዋል።
2. የዲጂታላይዜሽን ደኅንነት የሚለው ሁለተኛው ርዕስ ነው።
" ከአምስት ዓመት በፊት ስናከብር የሳይበር ደኅንነት መሪ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን ሳይበር የሚለውን ብዙ የሚረዳ ዜጋም ተቋማትም በጣም ጥቂት ነበሩ አሁን ላይ እኩል ከእኛ ጋር መናገር የሚችሉ ተቋማትና ዜጎች በእኩል ደረጃ ፈጥረናል ብለን እናምናለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በ2016 ዓ.ም 8854 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም ደግሞ ቁጥሩ ከፍ ብሎ 13496 የጥቃት ሙከራዎች አስተናግዳለች። እነዚህ ጥቃቶች ውስጥ በሌሎች አካላት የሚደረጉ የመሰረተ ልማት ቅኝቶች ጭምር እንደ ጥቃት መቆጠራቸው ተገልጿል።

❤497😡25🤔13🙏12💔9😭7😱6🕊5
" የፋይናንስ ባለሙያዎችን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ
➡️ " ግለሰቦቹ ቀድሞ ተዘጋጅቶ ቮይድ በተደረገ ቼክ ተመሳሳይ አሳትመዉ ነበር ለማጭበርበር የሞከሩት " - የጎፋ ዞን አስተዳደር
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ድንገት ተከስቶ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ የተከሰተውን አጠቃላይ ጉዳት ለማካካስና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ድጋፍ ሲሰበሰብ እንደነበር ይታወሳል።
ለተጎጂዎች የተሰበሰበ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ የተወሰኑ ግለሰቦች ተመሳጥረው በተጭበረበረ መንገድ ከባንክ ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት እና ገፅታ ግንባታ ዘርፍ ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር አሸናፊ ሃይለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ገንዘቡን ከፋይናስ ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች ጋር በመመሳጠር በአንድ ግለሰብ አማካኝነት በአዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸገር ቅርንጫፍ ለማስወጣት ሲሞክሩ ባንኩ በሰጠው ጥቆማ መሰረት የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል ለክልሉ ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል " ሲሉ ገልፀዋል።
ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸዉን የፋይናስ ባለሙያዎችን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር መዋላቸዉን ገልፀው በአሁኑ ወቅት ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
የዞኑ መንግስት ምን ይላል ?
የጎፋ ዞን አስተዳደር 60 ሚሊዮን 276 ሺህ 383 (ስልሳ ሚልዮን ሁለት መቶ ሰባ ስድሰት ሺ ሶስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ) ቀደም ሲል ተሠርቶ ቮይድ በተደረገ ቼክ ቁጥር ' 42221123 ' ተመሳሳይ በማሳተም ገንዘቡን ለመዝረፍ ካመቻቹ በኋላ ከአዲስ አበባ ንግድ ባንክ ሸገር ቅርንጫፍ ለጎፋ ዞን አስተዳደር በተደረገ ጥቆማ ከአዲስ አበባ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር ገንዘቡ ሳይወጣ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።
" በተለያዩ ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ ትክክለኛና ተጨባጭ መረጃ ከመስጠት ይልቅ ሐሰተኛና የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ " ሲል አሳስቧል።
በቀጣይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የምርመራው ሂደት ሲጣራ ለሕብረተሰቡ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባደረገው ማጣራት የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ገንዘቡን ሲያጭበረብሩ የተያዙት ግለሰቦች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንደሆኑ የገለፁ ሲሆን ፖሊስ እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠዉ መረጃ የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

❤726😢56👏27😭25🙏23😱22😡17🤔8🕊6
TIKVAH-ETHIOPIA
የጤና ሚኒስቴር እስከ መስከረም 30/2018 ዓም የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያልያዙ እና ያላወጡ የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ አሳውቋል። የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድን በሚመለከት በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ ተፈርሞ በ 30/12/2017 ዓም ለሁሉም ክልሎች የተላከው ደብዳቤ " ሁሉም ክልሎች እስከ መስከረም 30/2018 ዓም ድረስ የንቅናቄ ስራ በመስራት ሁሉም ባለሙያ…
#ተራዝሟል
የጤና ሚኒስቴር እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ የአገልግሎት ጊዜዉ ባለፈበት የሙያ ፍቃድ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ጤና ባለሞያዎች ማሳደስ እንዳለባቸውና የሞያ ፍቃድ የሌላቸው ደግሞ አዲስ እንዲያወጡ ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሰርኩላር አውርዶ ነበር።
ነገር ግን በተባለው ጊዜ ለማደስ የIhris-HrI ስርዓት እያስቸገረ መሆኑን ጠቅሶ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለ1 ወር ጤና ሚኒስቴር ያራዘመ መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።
ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም በኃላ " no license, no practice " በሚል መሪ ቃል የሙያ ፍቃድ ያላወጡ እና ያላሳደሰ ባለሞያዎች በሞያዉ መስራት እንደማይችሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

❤795🙏87😡47👏44🤔34🥰21🕊20😢17😭14😱9💔2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Addis Bank
🌟 Where Trust Meets Success 🌟
At Addis Bank, we believe that success is built on a strong foundation — That foundation is trust, and your success is our mission.
Addis Bank — Where Trust Meets Success.
Follow us
Website- (http://www.addisbanksc.com/)
Telegram- (www.tg-me.com/AddisBank_sc)
Facebook- (http://facebook.com/addisinternationalbank)
Linked in- (https://www.linkedin.com/company/addis-international-bank/)

❤174🙏12😢3😭3💔2🥰1🕊1
#Tecno
የኢትዮጲያ ትልቁ የፎቶግራፊ ዝግጅት!
ሀገራችሁን በፎቶ በነፃ የምትጎበኙበት፣ የቴክኖ ምርቶችን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን ጌሞችን እየተጫወታችሁ ምትሸለሙበት፣ አዲሱን ቴክኖ ካሞን 40 በቅርበት የማየት እና የመሞከር ዕድል የሚያገኙበት እና አጅግ አጓጉ የሆነ የሙዚቃ ድግስን የሚካፈሉበት ምርጥ ዝግጅት ቅዳሜ ጥቅምት 1 ጀምሮ ሲ ኤም ሲ የተባበሩት አደባባይ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ቴክኖ ኢትዮጵያ አዘጋጅቶላችኋል፡፡
ኑ ሀገሮን እያዩ፣ እየተሸለሙ፣ አዲሱን ቴክኖ ካሞን 40 እየሞከሩ አብረን እንዋል፡፡
#TecnoCamon40Series #FlashSnap #TecnoAI
@tecno_et
የኢትዮጲያ ትልቁ የፎቶግራፊ ዝግጅት!
ሀገራችሁን በፎቶ በነፃ የምትጎበኙበት፣ የቴክኖ ምርቶችን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን ጌሞችን እየተጫወታችሁ ምትሸለሙበት፣ አዲሱን ቴክኖ ካሞን 40 በቅርበት የማየት እና የመሞከር ዕድል የሚያገኙበት እና አጅግ አጓጉ የሆነ የሙዚቃ ድግስን የሚካፈሉበት ምርጥ ዝግጅት ቅዳሜ ጥቅምት 1 ጀምሮ ሲ ኤም ሲ የተባበሩት አደባባይ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ቴክኖ ኢትዮጵያ አዘጋጅቶላችኋል፡፡
ኑ ሀገሮን እያዩ፣ እየተሸለሙ፣ አዲሱን ቴክኖ ካሞን 40 እየሞከሩ አብረን እንዋል፡፡
#TecnoCamon40Series #FlashSnap #TecnoAI
@tecno_et
❤219😡21🙏11🕊8
“ በዚህ አመት 11 አዳዲስ የስልጠና ፕሮግራሞች ይከፈታሉ ” - ብሩክ ከድር (ዶ/ር)
በዚህ አመት 11 የሥልጠና ፕሮግራሞችን እንደሚከፈቱ የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) “በደረጃ 8 (በ3ኛ ዲግሪ) በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት ፕሮግራሞች ስልጠና ይሰጠል” ብለዋል።
አዳዲስ በሚከፈቱት ፕሮግራሞች ኢንስቲትዩቱ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን በደረጃ 6 (የመጀመሪያ ድግሪ)፣ በደረጃ 7 (ሁለተኛ ዲግሪ)፣ በደረጃ 8 (ሦስተኛ ዲግሪ) በቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንደሚሰጥ አስረድተዋል።
የሚከፈቱት 11ዱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ምን ምን ናቸው ?
በደረጃ 6፦
- ባዮሜዲካል ቲክኖሎጂ፣
- የሳይበርሰኩሪቲ ቴክኖሎጂ፣
- የአርቲፊሻል ኢንተሌጀንስ ቴክኖሎጂ፣
- የኢንተሌጀንስ ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ፣
- ኒውኢነርጂይ ቪሄክል ቴክኖሎጂ፣
- ፕላስቲክ ቴክኖሎጂ እና
- ሆርቲካልቸር ናቸው።
በደረጃ 7፦
- ኢንቲሪየር ዲዛይን እና ፊኒሽንግ ቴክኖሎጂ
- ሌዘርፕሮዳክት ቴክኖሎጂ ናቸው።
በደረጃ 8፦
- ማኑፋክቸሪንግ እና ቲቪቲሊደርሽፕ የተሰኙ የስልጠና ፕሮግራሞች ናቸው ተብሏል።
ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 የመግቢያ ነጥብ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል ይፋ የሚሆን ሲሆን በደረጃ 6፣ 7 እና 8 (መጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪና 3ኛ ዲግሪ) የመቁረጫ ነጥባቸው በትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰን ሲሆን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላቸውና NGAT ተፈትነው ውጤት ያላቸው በኢንስቲትዩቱ ይስተናገዳሉ ተብሏል።
ዘርፉ ብዙም ተፈላጊ እንዳልሆነ ነው ግንዛቤው ያለው፣ ሰልጣኞች በአዳዲሶቹ ፕሮግራሞች እንዲሰለጥኑ የሚያደርግ ምን የተለዬ ነገር አለ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ብሩክ (ዶ/ር)፣ “አዳዲስ የስልጠና ዘርፎች ገበያው የሚፈልጋቸው መሆኑን አረጋግጠን ነው የከፈትናቸው” ብለዋል።
የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ከምረቃ በኋላ የሥራ እድሉ ስለመኖሩ ሲጠየቁም፣ “ስልጠናውን ሊያጠናቅቁ ሲሉ የሚቀጠሩ ሰልጣኞች ሰልጣኞች ቁጥር ከፍተኛ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

❤1.16K👏92🕊30💔26😢18🙏18🥰17🤔17😡11😱8😭5
#NobelPeacePrize
" በዓለም ላይ ግጭቶችን በማስቆም ሰላም እና መግባባት እንዲሰፍን ባደረኳቸው ጥረቶች የኖቤል ሰላም ሽልማት ለእኔ ይገባኛል " በማለት ሲናገሩ የነበሩትና የተለያዩ የሀገራት መሪዎችም " የዘንድሮው ሽልማት ለእሳቸው ይገባቸዋል " ያሉላቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም አሸናፊ ሳይሆኑ ቀሩ።
የ2025 የኖቤል የሰላም ሽልማት ለቬንዝዌላዊቷ የተቃዋሚ መሪ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ተበርክቷል። ማቻዶ በቬንዙዌላ ለዲሞክራሲ እና ለሰብዓዊ መብት መከበር አድርገውታል በተባለ ያላሰለሰ ትግል ነው ተሸላሚ የሆኑት።

2❤2.3K👏518😭138🙏78😡53💔47🥰43🤔40🕊40😢16😱15